2022-09-28 09:09:24
#የስሜት_ብልሃትና_ተግባቦት
#Emotional_Intelligence& Communication
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ) #SHARE
ጥሩ የስሜት ብልሀት ያላቸው ሰዎች የተመሰገኑ ፣ በማንኛውም ሁኔታ የተረጋጉ ፣ የሩጫ ህይወት የማይመሩ ፣ የበለጠ ደስተኛና ራሳቸውንም ሆነ አካባቢያቸውን የሚመሩ ናቸው ፡፡
በህይወታቸው በጣም ደስተኛና ስኬታማ የሆኑ ሰዎች አንዱ መገለጫቸው ያለቸው የስሜት ብልሃት ( Emotional Intelligence ) ነው ፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት ሙያውና ችሎታው እያላቸው በባህሪ ምክንያት ይሰናበታሉ ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጥሩ ሀሳብ እያላቸው ባላቸው ባህሪና በተግባቦት እጥረት ምክኒያት ሰሚ ያጡ ፣ ተቀባይነት ያጡ ሰዎች ብዙ ናቸው ፡፡
#ለዛሬ እነዚህ የተግባቦትና የስሜት ብልሃት አለመኖር በሕይወታችን የሚያመጡትን ችግር እንመልከት ፡፡
እኔ አንዱን ድግሪዬን በማኔጅመንት ስሰራ የመመረቂያ ጽሑፌ (Competency development in business areas ) የሚል ነበር ፡፡ በዚህ ጥናት ያገኘሁት አንዱ ግኝት ሰዎች ለቢዝነሳቸው መውደቅና አለማደቅ አንዱና ዋና ምክንያት ያላቸው አነስተኛ #የተግባቦትና #የስሜት_ብልሃት ነው ፡፡
#የስሜት_ብልሃትና_ጥሩ_ተግባቦት_የሌላቸው_ሰዎች_መገለጫዎች
★የራሳቸውን ስሜት አይቆጣጠሩም ( በቀላሉ ይናደዳሉ ፣ ይበሳጫሉ ፣ ከልክ ያለፈ ቁጣ ይታይባቸዋል )
★ከሰው ጋር ተግባቢ አይደሉም ፣ ፍርሀት ጭንቀት ይታይባቸዋል ፣ ስለ ራሳቸው አሉታዊ አመለካከት የላቸውም
★በትንሽ ነገር አብዝተው ያዝናሉ
★በአካባቢያቸው ያሉ ሰዎችን ባህሪ እና ስሜት ስለማይረዱ ፣ ብዙ ጊዜ ከሰዎች ጋር በሀሳብ ፣ በወሬ የመጋጨት ሁኔታ ይታይባቸዋል
★ሰው ስለነሱ ስላለው አስተሳሰብ አብዝተው ይጨነቃሉ ፣ ይረበሻሉ ፡፡
★ሃሳባቸውን በድፍረት አይገልፁም ፣ እየተጎዱ ከጉዳቱ መውጣት እየቻሉ ዝምታን ይመርጣሉ ፣
★ለውሳኔዎች ከተገቢው በላይ ይቸኩላሉ፣ በወሰኑት ነገር ለመጸጸት ደግሞ የመጀመሪያ ናቸው
ከላይ የዘረዘርኳቸው መገለጫዎች( የስሜት ብልሃትና ጥሩ ተግባቦት ክህሎት አለመኖር) የሚያመጣቸው ጉዳቶችና የባህሪ መገለጫዎች ናቸው ።
በእርግጥ ተግባቦትም ሆነ የስሜት ብልህነት ሳይንሳዊ የሆኑ መንገዶችን በመጠቀም ማሳደግ ይቻላል ፡፡ ስለዚህ ከላይ የጠቀስኳቸውን ችግሮች በራሳችሁ ላይ የምታዩ ሰዎች ተስፋ አትቁረጡ ፡፡ በጥቂት ጊዜ ጥሩ የሆነ ተደጋጋሚ ተግባራዊ ልምምዶችን በማረግ መዉጣት ይቻላል ፡፡
___
#በዚህ ሳምንት መጨረሻ /ቅዳሜ መስከረም 21 እና እሑድ መስከረም 22 በሚጀምረው የሕይወት ክህሎት ስልጠና ላይ እነዚህን ጉዳዮች በስፋት የማነሳቸው ሲሆን በተጨማሪም በየቀኑ የሚሰሩ እነዚህን ክህሎት የሚያሳድጉ ልምምዶችን በተግባር እናያለን፡፡ ለመለወጥ የወሰናችሁ ሰዎች ካሉን ፈረቃዎች በተመቻችሁ መርጣችሁ +251912664084 በመደወል ተመዝገቡ የስልጠናው ሙሉ ማስታወቂያ ከዚህ በፊት ተለጥፏል ፡፡ የ 6 ሳምንት ስልጠናችንን ያልተመዘገባችሁ ባለን ጥቂት ቀሪ ቦታዎች ተመዝግባችሁ እንድትጀምሩ እናበረታታለን፡፡
ይህ ፅሁፍ ለሌሎችም እንዲደርስና ስልጠናው የሚያስፈልጋቸው እንዲያገኙት ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው
@PSYCHOET
294 views06:09