Get Mystery Box with random crypto!

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂

የቴሌግራም ቻናል አርማ psychoet — ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
የቴሌግራም ቻናል አርማ psychoet — ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
የሰርጥ አድራሻ: @psychoet
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.21K
የሰርጥ መግለጫ

| እውነት | ፍትህ | ፍቅር | ✔ሥነ ልቡና |
የተለወጠ ግለሰብ አለም ይለውጣል!
የተለያዩ የስነልቦናና የላቀ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የተሰሩ video ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናሌን ይከታተሉ
"የማወቅና የመለወጥ ሰአት አሁን ነው "
https://www.youtube.com/user/TheNahusenai
Facebook አድራሻዬ Fb.com/psychologyabc

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-05-13 10:52:53
ለእያንዳንዱ ጉዳይ መብከንከናችንን እናቁም

በዙሪያዬ ያሉ ጥቂት ሰዎች ኑሯቸው እንዲህ ነው፡፡ ለረባውም ላረባውም፣ ለትንሽ ትልቁ፣ ለሚለከታቸውም ለማይመለከታቸውም ነገር ትኩረት የሚሰጡ ናቸው፡፡ ለእያንዳንዷ ጥቃቅን ጉዳይ ትኩረት ከሰጠንና ከተጨነቅን ኑሯችን ጤናማ አንሆንም፡፡

እንዴት አንድ ሰው ስለሁሉም ነገር ሊጨነቅ ይችላል? ለራሳችን ጉዳይመ ተጨንቀን፣ ለሰዎች ተጨንቀን፣ ሊሆን ይችላል እያልን ተጨንቀን እንዴት እንችለዋለን? 

በጣም የሚገርመው እንዲህ አይነት ባህሪ ያላቸው ሰዎች፡
የመፍትሄ ሰዎች አለመሆናቸው ላይ ነው፡፡
አንድን ጉዳይ ለረጅም ግዜ ይተክዙበታል፡፡ 
ነገሮችን በአሉታዊ መንገድ መረዳት ይቀናቸዋል፡፡
ሲታመሙ አንኳን የሚድን አይመስላቸውም፡፡
በህይወታቸው ውስጥ ያሉትን መልካም እድሎችን  መጠቀም አይችሉበትም፡፡

ከዚህ ባህሪ ለመላቀቅ፡

መፍትሄ መስጠት የምንችለውን መፍትሄ መስጠትና መተው ያለብን ደግሞ መተው መለማመድ
ሌሎች ሰዎች እንዴት እንደሚኖሩ ማየት፣ መጠየቅና ትምህርት መውሰድ
ጓደኞችን ማፍራትና ከእነሱ ጋር ግዜ ማሳለፍ ተቃሚ መፍትሄዎቸ ናቸው፡፡

@ተመስገን አብይ Psychologist

@psychoet
2.2K viewsedited  07:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-04 16:17:21
በፍቅር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች ዋና ዋና መገለጫቸው አነዚህ ናቸው፡፡

መቀበል፡ ሰዎችን፣ ሁኔታዎችን፣ ራሳቸውን ያለ ምንም ተጨማሪ ሃሳብ አሁን ባሉበት ላይ መቀበል የሚችሉ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ከማንም ሰው ጋር በምንም ሁኔታ ውስጥ መኖር እንደሚችሉ የሚሰማቸው ሰዎች ናቸው፡፡

መረዳት፡ ሰዎችም ሃሳባቸውን እንዲገልጹ፣ አይታቸውን እንዲያካፍሉ፣ ምክንያታቸውን እንዲገልጹ እድል የሚሰጡ ናቸው፡፡ የተፈጠሩት ነገሮችም ለምን አላማ እንደሆነ ለማወቅ የበኩላቸውን ጥረት የሚያደርጉ ሰዎች ናቸው፡፡ የራሳቸወን ሃሳብ ከመወርወራቸው በፊት መረዳትን  ማስቀደም ይችሉበታል፡፡

ተፈጥሮን መውደድ፡ በፍቅር ውስጥ የሚኖሩ ሰዎች እንደ ተፈጥሮ የሚመስጣቸው ሌላ ነገር ያለ አይመስለኝም፡፡ በሰው አፈጣጠር፣ በውሃ፣ በእጽዋት፣ በእንስሳት፣ በአየር፣ በደመና፣ በዝናቡ ወዘተ እጅግ ይደመማሉ፡፡

ለሁሉም፡ ማንን ታፈቅራላችሁ ብትባሉ ማንን ትላላችሁ? በፍቅር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉንም የሚል መልስ ነው ያላቸው፡፡ ሁሉም ነገር ፍቅር አለው፤ ፍቅር ይገባዋል ይላሉ፡፡ ለቀረባቸው፣ ላገኙት፣ ለገጠማቸው ሁሉ መልሳቸው ፍቅር ነው፡፡

መፍቀድ፡ ራሳቸውን እንዲያፈቅርና ነጻ እንዲሆን ይፈቅዱለታል፡፡ በዙሪያቸው ያሉ ሰዎችን በነጻነት ይቀርባሉ፡፡ ሰዎች የፈቀዱትን እንዲያደርጉ ይተዋቸዋል፡፡ በዙሪያቸው ያለ ነገር ሁሉ የፈቀደውን እንዲሆን መፍቀድ፣ እገዛቸውንም መለገስ ይችሉበታል፡፡ በዚህም ምክንያት በሰዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ያተርፋሉ፡፡

ራስን መሆን፡ በፍቅር የሚኖር ሰው ትኩረቱ ራሱን በመሆን ላይና በማሳደግ ላይ ነው፡፡ ሌሎች ሰዎችም ራሳቸውን እንዲሆኑ ያግዟቸዋል፡፡ ትክክለኛ ፍቅር ራስን በመሆን ውስጥ እንደሆነ ያውቃሉ፡፡

ታዲያ የፍቅር ሰው ናችሁ .. ጻፍልን

ተመስገን አብይ (Psychologist)
@psychoet
326 views13:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 09:51:17 ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ pinned a photo
06:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 09:50:50
መልካም የሰራተኛ ቀን ይኹንላችሁ። ግን ደግሞ በተሰማራችሁበት ሥራ ስትለፉና ስትደክሙ ይሄንን እንዳትረሱ።
@psychoet
420 viewsedited  06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 17:09:25 #ውሸት

ለምን እንዋሻለን ??? ውሸት ተናጋሪዎችን እንዴት እናውቃለን???
ለምን እንዋሻለን ??

ሀ. ግላዊ ጥቅም ለማግኘት፡–  ለምሳሌ ለስራ ስንወዳደር ቃለ መጠየቅ ላይ የተሻለ ደመወዝ እንዲከፈለን አሁን የሚከፈለንን የደመወዝ መጠን ከፍ አድርገን እንናገራለን፡፡

ለ.ቅጣትን ለማስቀረት፡– ህፃናት በወላጆቻቸው እንዳይቀጡ ያጠፉትን ነገር አይናገሩም ወይም አልሰራንም ይላሉ፡፡

ሐ. ሌሎች ስለኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ፡- ሰዎች ስለኛ ጥሩ የሆነ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ ያልሆነውን ሆንን፣ ያላደረግነውን አደረግን ብለን እንናገራለን፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የውሸት ዓይነቶች  በእኛ ዙሪያ ያጠነጠኑ እና  እራሳችንን ለመጥቀም የታለሙ  (self oriented) ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ለሌላ ሰው  ተብለው የሚዋሹ ውሸቶችም አሉ ለምሳሌ፡-

ሀ. ሌሎች ሰዎችን ለመጥቀም፡– እናት ልጇን ከፍርድ ቤት ቅጣት ለመጠበቅ ስትል ወንጀሉ በተፈፀመበት ሰዓት ልጄ እቤት ነው ብላ ልትመሰክር ትችላለች፡፡

ለ. ሰዎች ለማህበራዊ ግንኙነት ሲባልም ይዋሻሉ፡– ጎረቤት እራት ተጋብዘን እዚህ ግባ የማይባለውን  ምግብ ጣት ያስቆረጥማል ብለን የምንወጣው ቀጣይ የሚኖረንን ግንኙነት ከግምት ውስጥ በማሰገባት ነው፡፡

ሐ. ሰዎችን ለመጉዳት እንዋሻለን :- ይህ ደግሞ በሌሎች እንዲቀጡ ባልሰሩት ነገር ላይ በሀሰት በመመስከር የሚደረግ ውሸት ነው ፡፡

ሰዎች እንደሁኔታው ዓይነት ውሸቶችን ይዋሻሉ ለምሳሌ #ሮቢንሰን ባጠናው ጥናት ላይ ስራ ለማግኘት ተብሎ ቃለ ምልልስ ላይ የሚዋሽ ውሸትን #83% የሚሆኑ የጥናት ተሳታፊዎች የነበሩት የኮሌጅ ተማሪዎች እንደ ውሸት አይቆጥሩትም፡፡
#ሮዋት ባጠናው ጥናት ደግሞ #40% የሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ወደፊት የፍቅር አጋር ይሆናል ብለው ላሰቡት ሰው በመጀመሪያ ግንኙነት ላይ እንደሚዋሹ አረጋግጠዋል፡፡
ሆኖም ግን ምን ያህል የሚሆነው የተሳካ የፍቅር ግንኙነት ኖሮት እንደቀጠለ ጥናቱ የሚለው ነገር ባይኖርም ከላይ በተቀስነው የውሸት ዓይነት ማለትም ሰዎች ስለ እኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ለማድረግ በሚዋሽ ውሸት ፍፃሜው ያማረ የፍቅር ግንኙነት ሊኖረን አይችልም፡፡

ሌላው በጥናቱ ላይ የተመለከተው ነጥብ ጾታን በተመለከተ የታየ ልዩነት የለም ይህም ማለት ሁለቱም ወንዶችም ሴቶችም በእኩል መጠን ይዋሻሉ፡፡ በእኛስ ሀገር የትኛው የበለጠ ይዋሻል?? #ወንድ ወይስ #ሴት?? መልሱን ለእናንተ ተውኩት፡፡ ተጨማሪ በሌሎች ጥናቶች ላይ እንደተመለከተው ተጫዋች (ማህበራዊ) (Extraverts) ግላዊ (Introvert) ከሆኑት በበለጠ ውሸት እንደሚያዋሹ አመልክተዋል፡፡

ውሸትን እና ውሸታሞኝችን ለመለየት ሰዎች በጥናት የተደገፉ ከቤተ ሙከራ እስከ ውሸትን የማወቂያ መሳሪያ (polygraph) ድረስ ያሉ የተለያዩ ዓይነት ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ፖሊግራፍን ውሸትን ለማወቅ የሚለካው እንደ ልብ ምትና የመሳሰሉትን አካለዊ ለውጦችን እንደመሆኑ መጠን እንደየ ግለሰቡ ባህሪ ትክክለኝነቱ ሊወሰን ይችላል፡፡ ስሜታቸውን በቀላሉ የሚቆጣጠሩ ሰዎች ውጤቱን ሊያሳስቱ ሲችሉ፤ ድንጉጥ፤ ስሜታዊና ለነገሩ አዲስ የሆኑ ግለሰቦች ደግሞ በተቃራኒው የቀጣፊነት ባህሪ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ አሁን አሁን ግን ከጎንዮሽ ጉዳቱና ከውጤቱ እርግጠኝነት ጋር በተያያዘ ፖሊግራፍ እየቀረ ያለ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

ለጊዜው ግን ለእኛ ይሆነን ዘንድ የሰዎችን ባህርይ በማየት እንዴት ውሸታሞችን መለየት እንችላለን የሚለውን እንመለከት፡፡ የተደረጉት ጥናቶች በዋናነት መሰረት ያደረጉት
#ስሜታዊነትን (emotional state)፣
#የወሬያቸውን (የመልዕክቱን) ይዘት (content complexity)  እና
#ባህርይን ለመቆጣጠር ከሚደረግ ጥረት (attempted behavioral control) በመነሳት ነው፡፡ ስሜታዊነት ላይ ሰዎች ውሸት ሲያወሩ አንደኛ ውሸት እያወሩ ስለሆነ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማቸዋል፣ ሁለተኛ በውሸቱ ምክንያት ወደፊት በሚያገኙት ጥቅም ደስተኛ ይሆናሉ ወይም ደግሞ ይታወቅብኝ ይሆን በማለት ይፈራሉ፡፡ ከወሬያቸው ይዘት ጋር በተገናኘ ውሸት ተናጋሪዎችን ለመለየት ተናጋሪውን ተደጋጋሚ ጥያቄ በመጠየቅ ተመሳሳይ መልስ እንደመለሰልን ማረጋገጥ እና ለምላስ ወለምታዎች ትኩረት መስጠት እንደ ዘዴ ተቀምጠዋል፡፡

የሰዎችን ባህርይ በማየትም ውሸት ተናጋሪዎችን መለየት እንችላለን #ዲፓውሎ_እና_ሮዘንሀል በጥናታቸው እንዳረጋገጡት ከሆነ ውሸት የሚያወሩ ሰዎች በሚያውሩበት ጊዜ እነዚህን ባህሪዎች አሳይተዋል መረጃውን  የሚያስተላልፉለትን ወይም የሚነግሩትን ሰው ዓይን ላለማየት የተለያየ ጥረት ደርጋሉ፣ አላስፈላጊ በሆነ ቦታ ላይ ሊስቁ እና ፈገግ ሊሉ ይችላሉ፣ ተደጋጋሚ የሆነ መንገድ በእጅ ለማስረዳት የእጅ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ (ውሸት የማይናገሩ ሰዎች በእጃቸው እንቅስቃሴ ለማስረዳት እንደሚሞክሩ ልብ ይሏል)፣ ፊታቸውን እና  ፀጉራቸውን ያካሉ ወይም ይነካሉ፣ በተለያዩ ፊት ለፊት በተቀመጡ ግዑዝ ነገሮች ይጫወታሉ፣ በፍጥነት ያወራሉ፣ ግንባራቸውን እና እጃቸውን ያልባቸዋል፣ ጥያቄ ሲጠየቁ እስኪመልሱ ድረስ ባንጻራዊነት ሰፊ ጊዜ ይወስዳሉ፣ በመሀል አ……ኧ….እም……ያበዛሉ፣ መንተባተብ (ቃላትን መደጋገም፣ ዐረፍተ-ነገሮችን አለመጨረስ፣ የምላስ ወለምታ)እንዲሁም  ድንገተኛ የሆነ የድምጽ መጨመርና መቀነስ ይታይባቸዋል፡፡

ሰዎች በተለያየ መንገድ ግንኙነት ፈጥረው ሲያወሩልን ወይም መልዕክት ሲያስተላልፉልን ከላይ ከጠቀስናቸው ምክንያቶች መካከል አንዳንድ ነገሮችን ካየን ውሸታም ብለን ከመፈረጃችን በፊት በእራሳችን መንገድ እና ለምን እንደዋሹን ደግሞ ማጣራት ይኖርብናል፡፡ በዚህች ባጭር ጽሁፍ መሸፈን አልችልም እንጂ ስለ Pathological liars (ህይወታቸው በሙሉ በውሸት ስለተሞላና ውሸት መናገርና ማቆም ስለማይችሉ ውሸት በሽታ ስለሆነባቸው ሰዎች) ጥቂት ባወራ ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ወደፊት ይዤላችሁ እንደምቀርብ ቃል በመግባት የዛሬውን በዚህ ልቋጨው፡፡

ሰላማችሁ ይብዛ………..

(በቁምላቸው ደርሶ)
Zepsychologist
@psychoet
1.4K views14:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 11:19:33 ስማኝ ልጄ!!!!!!! ተነቦ ሼር ይደረግ

1. ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!!!!

2. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!!!!

3. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰው ሀቅ አትለፍ ማለት እንጂ!!!!

4. አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!!!!

5. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!!

6. ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ!!!

7. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!!!!

8. ስራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ስራ ውደድ ማለት እንጂ!!!!

9. ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!!!!

10. ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ስትሰራ አትሙት ማለት እንጂ!!!!

11. ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ግዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!!!!

12. እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነትተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት ማለት እንጂ!!!!

13. አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትኑር ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!!!!

14. ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!!!

15. ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክህ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ!!!!

16. አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ!!!
ከFb የተገኘ
እንኳን ለብርሀነ ትንሳዬው በሰላምና በጤና አደረሳችሁ
በቴሌግራም @psychoet
1.2K views08:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 13:01:33 ጥንካሬን ማወቅ

በዚህ ርዕስ ላይ ስልጠና ስሰጥ እስካሁን የተረዳሁት አንድ ነገር አለ፡፡ ብዙዎቻችን ስለ ጥንካሬያችን ሳይሆን ስለ ድክመታችን ብዙ እንደምናውቅ ነው፡፡ ይኸም ደግሞ ደካማ፣ የማንችልና የበታች እንደሆንን እዲሰማን አድርጎናል፡፡

ህይወታችንን ከፍ አድርገን ለመኖርም ድክመቶቻችንን ላይ ትኩረት ማድረግ እንደ መፍትሄ እንጠቀመዋለን፡፡ ይህም ብዙ ውጤት የማያመጣ መፍትሄ ነው፡፡

ስለ ድክመቶቻችን ብቻ በማሰብና ለማሻሻል በመሞከር ብዙ ጊዜያችንን ማጥፋት ውጤት የማያመጣ ከሆነ፤ ታዲያ ውጤት የሚያመጣው ምንድን ነው?

ስለ ድክመታችን የምናውቀውን ያህል ስለጥንካሬያችን ማወቅ አለብን፡፡ ምን ተሰጥኦ አለኝ? ምን ችሎታዎች አሉኝ? ምን ማድረግ ያስደስተኛል? ምን ነገሮች ላይ ሃላፊነት እወስዳለሁ? ራሳችንን ጠይቀን ጥንካሬዎቻችንን ማወቅ የመጀመሪያው መፍትሄ ነው፡፡

ድክመቶቻችንን መቀበል አለብን፡፡ ድክመቶቻችንን ለመቀየር ከመታገል ይልቅ መቀበልና ማወቅ በቂ ነው፡፡ ለመቀየር ስንታገል አቅማችንን ወደታች እያወረደብን ይመጣል፡፡

ጥንካሬዎችንን ካወቅን በኋላ በየቀኑ መጠቀም መቻል፡፡ ጥንካሬዎቻችንን የሚያድጉት በየቀኑ ስንጠቀምባችው ነው፡፡ ዛሬ የትኛውን ጥንካሬዬን ተጠቀምኩበት? ራስን መጠየቅ

አዳዲስ ጥንካሬያችንን መፈለግ፡፡ በየጊዜ የማናውቀውን ጥንካሬ እናገኛለን፡፡ ይህም የሚሆነው አዲስ ነገሮችን ስንሞክር፣ ከአዲስ ሰዎች ጋር ስንገናኝ፣ ስንወስን ወዘተ. ነው፡፡

ጥንካሬዎቻችንን ላይ ትኩረት አደርገን መስራት ከቻልን ድክመቶቻችንን ማሸነፍ እንችላለን፡፡

ከወደዳችሁትና ከጠቀማችሁ ሼር አድርጉት!

by @temuabiy t.me/psychoet
675 viewsedited  10:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-31 22:09:37 ስኬታማ ሰዎች የሚያመሳስላቸው ነገር ሁሉም በነዚህ መንገዶች ማለፋቸው፡፡ 5ቱን ተግባራት በዚህ ቪዲዮ ያገኛሉ

986 views19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-28 19:29:32 ማህበራዊ ፍርሀት ወይም በተለምዶ አይናፋርነትን እንዴት ማስወገድ እንችላለን?
በሰው ፊት ማውራት ፣ ሀሳብ መግለፅ ይፈራሉ
ሁሌ ሰው ምንይለኛል ብለው ይጨነቃሉ
ሰው በተሰበበት መካከል አልፈው መሄድ ያስጨንቅዎታል
ትንሽ ስታወሩ ሰውነታችሁ በፍርሀት ላብ ይጠመቃል


ይህ አጭር Video ለነዚህ ሁሉ መፍትሔና መልስ አለው ፡፡
የምንለቃቸው የስነልቡና Videoዎች ቶሎ እንዲደርሳችሁ YouTube ቻናላችንን Subscribe አድርጉ ፡፡

643 views16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-25 23:24:10 ጤናማ ትዳር = ጤናማ ሕይወት!
ላገቡ፣ ላላገቡና ለማግባት በደጅ ላይ ለሚገኙ . . . በበርካታ ጥናቶች እንዲህ ይሉናል፡- አንድ ሰው ከትዳር አጋሩ ጋር ያለው ግንኙነት ጤናማ በሆነ ቁጥር የዚያ ውጤት በእድሜው ርዝመት ላይ ይንጸባረቃል፡፡
የሰመረ ትዳር ያላቸው ሰዎች ጤንነታቸው፣ ደስተኛነታቸውና ያላቸው ሙሉ የመሆን ስሜት ከሌሎቹ የተሻለ ነው፡፡ እነዚህ ሶስት ወሳኝ ሁኔታዎች ደግሞ ረጅምን እድሜ ጠግበው እንዲያሳልፉ ያግዛቸዋል፡፡
ያላገባችሁ ከሆነ የዚህን ጥናት ውጤት በመውሰድ የምታገቡት ሰው ማን ሊሆን እንደሚገባው በሚገባ አስባችሁበት ወደትዳር እንድትገቡ እንደማንቂያ ደውል ተጠቀሙበት፡፡
የወደፊት ታሪካችሁን ለጥሩ ወይም ለመጥፎ የመቀየር ጉልበት ካላቸው ምርጫዎችና ውሳኔዎች መካከል የትዳር አጋር ጉዳይ ቀዳሚው ነው፡፡
ይህንን ለመፈተሽ ከፈለጋችሁ ገና በፍቅር ግንኙነት ላይ የሚፈጠሩ ነገሮች በስሜታችሁ ላይ፣ አንዳንዴም በአካላችሁ ላይ ያላቸውን ጫና መመልከት በቂ ነው፡፡
ያገባችሁ ከሆነ ደግሞ ከትዳር አጋራችሁ ጋር ያላችሁ ግንኙነት በጤንነታችሁና አልፎም በእድሜያችሁ ላይ ይህ ነው የማይባል ስፍራ እንዳለው ለመገንዘብ ሞክሩ፡፡
ስለዚህም፣ የግንኙነታችሁን መልካም ጎን በዚያው እንድትቀጥሉበትና ያላችሁ ደካማ ጎን ላይ ደግሞ የማሻሻያ ስራን ለመስራት የምትችሉትን እንድታደርጉ ትመከራላችሁ፡፡
Dr eyob
1.2K views20:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ