Get Mystery Box with random crypto!

Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠

የቴሌግራም ቻናል አርማ melkam_enaseb — Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠 P
የቴሌግራም ቻናል አርማ melkam_enaseb — Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠
የሰርጥ አድራሻ: @melkam_enaseb
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 6.23K
የሰርጥ መግለጫ

Support channel for mental health awareness in Ethiopia. We post facts about psychology and psychological phenomenon.
''There is no health without Mental Health.''
Contact @FikrConsultSupportbot

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 20:30:02
ስለ አእምሮ ጤና እንወያይ!

ከለላ በክለብ ሃውስ ሐሙስ (ነሃሴ 26) ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ስለ አእምሮ ጤና ውይይት ላይ ተጋብዛችኋል።

@melkam_enaseb
549 views17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 10:09:31
Adjustment Disorder ምንድነው?

በህይወት ውስጥ ጫና ሲያጋጥም ጭንቀት ወይም መከፋት የተለመደ ነው። ይሄ ጭንቀት ወይም መከፋት በተለምዶ ከሚጠበቀው ጊዜ በላይ ከቆየ ወይም መጠኑ ከሚጠበቀው በላይ ከሆነ Adjustment disorder (Situational depression) ይባላል።

Adjustment disorder የሚፈጥሩት ጫናዎች አንድ ጊዜ በድንገት የሚከሰቱ አሉታዊ ነገሮች ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ፍቺ፣ የእሳት አደጋ፣ ከስራ መባረር፣ አዲስ ስራ መጀመር፣ አዲስ ቦታ መሄድ...ወዘተ። ሌላ ጊዜ ደግሞ ጫና የሚፈጥሩት ነገሮች አብረው የሚቆዩ ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ትዳር ውስጥ ያለ ጭቅጭቅ፣ ነዝናዛ አለቃ...ወዘተ። ሰዎች Adjustment disorder እንዲያጋጥማቸው የሚያደርጉት መጥፎ ነገሮች ብቻ ሳይሆኑ ጥሩ ነገሮችም ሊሆኑ ይችላሉ። ለምሳሌ ትዳር መያዝ፣ ድንገት ሀብታም መሆን፣ ሹመት...ወዘተ።

ሰዎች ጫና ሲያጋጥመን የምንሰጠው ምላሽ እንደየመልካችን ይለያያል። ለአንዳንዶች በጣም የሚያስጨንቃቸው በሌሎች አይን በጣም ቀላል ነው። ይህንን የሚወስነው አስተዳደጋችን፣ የምንጠቀማቸው ራስን የመደለያ መንገዶች (Defence Mechanisms)፣ ያለን ማህበራዊ ድጋፍ ...ወዘተ ነው።

የAdjustment disorder ህክምና በዋናነት የንግግር የስነ ልቦና ህክምና ሲሆን በጣም አልፎ አልፎ ለጥቂት ቀናት ለእንቅልፍ የሚያግዙ መድሀኒቶች ሊሰጥ ይችላል።

በዶ/ር ዮናስ ላቀው (የአእምሮ ህክምና ስፔሺያሊስት)

@melkam_enaseb
859 views07:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:02:17
#ሊታረምሚገባድርጊት

በ "Tourette Syndrome" ወይም "tics" disorder ታካሚዎች ላይ መቀለድ

ቤተልሔም አዳሙ ያሳለፍነው እሁድ በተላለፈው የእሁድን በኢቢኤስ መዝናኛ ፕሮግራም ላይ ተጋባዥ እንግዳ ሆና በመቅረብ "በገንዘብ እጦት ሚከሰት አንጃይተር ዲሶርደር ነው" በማለት መሰል ድርጊቶችን ስታሳይ ነበር።

ቤተልሔም አዳሙ በምትለቃቸው ቪዲዮዎች ከህክምና ባለሙያዎች በቪዲዮዎችዋ ምታደርጋቸው ድርጊቶች "Tourette Syndrome" ወይም "tics" disorder መገለጫ እንደሆኑ በመንገር እንድትታረም በተደጋጋሚ በፅሁፍም ሆነ ቪዲዮዎቿን በማጋራት (duet) መልእክታቸውን ሲያስተላለፉ ቆይተዋል።

በሃገራችን አሉ ከሚባሉት ታዋቂ ሚዲያዎች አንዱ የሆነው EBS/ኢቢኤስ/ ልጅቷን ትልቅ አስተማሪ የሆነ ነገር ይዛ የቀረበች በማስመሰል ከአቅራቢዎቹ ጋር በልጅቷ እሳቤ እሰይ አበጀሽ አይነት ህመሙ ባለባቸው ታካሚዎች ሪአክሽን ላይ ተመርኩዘው ሲስቁና ሲሳለቁ ይስተዋላል።

ይህ አይት ድርጊት የታካሚዎቹን ስሜት የሚጎዳና ምንም አይነት ትምህርት ለትውልድ ሊያስተምር ስለማይችል ቢታረም እያልን ጉዳዩ የቴሌቪዥን ጣቢያውን በህግ ሊያስጠይቀውም ስለሚችል ተገቢውን ይቅርታ እንዲጠይቁ እናስገነዝባለን።

Via: Hakim

@melkam_enaseb
915 views10:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 08:45:47 የአእምሮ ጤና፡ ዘግታችሁ የወጣችሁትን በር እንዳልተዘጋ የሚያሳስባችሁ የአእምሮ ሕመም - ኦሲዲ (OCD)

https://www.bbc.com/amharic/articles/c6pqpg24lvno

@melkam_enaseb
454 views05:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 08:45:22
#Dailytips

''ህልማችን እውን የሚሆነው አጥብቀን ከያዝነው እና ጠንክረን ከሠራን ነው'' - ሴሬና ዊሊያምስ

ሁሌም የአሸናፊነት መንፈስ ይዘው ሳምንትዎን ይጀምሩ! መልካም የስራ ሳምንት!

@melkam_enaseb
453 views05:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 13:27:47 የውሸት እርግዝና (pseudocyesis) or (phantom pregnancy) ምንድነው?

በዶ/ር ነጋልኝ (የማህፀንና ፅንስ ስፔሻሊስት) እና ዶ/ር ሱራፌል (የስነ አዕምሮ ስፔሻሊስት) የተፃፈ።

በአንድ ወቅት የ50 ዓመት ታካሚዬ የአስራ ሁለት ወር እርጉዝ ነኝ ልጁም አልወለድ ብሏል የምጥ መርፌ ስጠኝና ገላግለኝ አለችኝ። ይህን ገጠመኝ በመንተራስ ስለ phantom pregnancy ይህን ፅፈናል። መልካም ንባብ!

የውሸት እርግዝና እርግዝና ሳይኖር የእርግዝና ምልክቶች ሲታዩ እና ነፍሰጡር ነኝ ብሎ አይምሮን በማሳመን የሚፈጠር የአይምሮ ችግር ነው።

በሁሉም ማህበረሰብ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የመከሰት እድሉ ግን በጣም አናሳ ነው።

የታወቀ የአዕምሮ ወይም የአካል ህመም ሳይናኖርባቸው በውል በማይታወቅ ምክንያት እርግዝና አለኝ ብሎ ማመን የሚታዩ የእርግዝና ምልክቶችን ማንፀባረቅ የዚህ ችግር ተጠቂነትን ያመለክታል።

ምልክቶቹ የሚከተሉት ናቸው፦

- የሆድ መግፋት(መነፋት)
- ማቅለሽለሽና ማስመለስ
- የወር አባ መጥፋት
- ክብደት መጨመር
- የጡት መጠን መጨመር
- የምግብ ሽታ መጥላት
- የሽንት መፋጠን
- የልጅ እንቅስቃሴ መስማት

ምክነያቶቹ ምንድናቸው?

ለዚህ ችግር ምክያት ይህ ነው የሚባል ህያው መንስኤ ባይኖረውም የተለያየ አይነት ሳይንሳዊ መላምቶች ተቀምጠዋል ከእነዚህም መላምቶች የሆርሞን መዛባት፣ የአዕምሮ ጭንቀት፣ የአከባቢ ጫና በጋራ ወይም በተናጥል የሚፈጥሩት ኡደት ነው።

ተጋላጮቹ ማናቸው?

በማንኛውም እድሜና በየትኛውም ሀገር የሚኖሩ ሴቶች ሲጠቁ የሚከተሉት ችግር ይበልጥ ተጋላጭነትን ይጨምራሉ

- ከ20-39 ዓመት ያሉ
- ልጅ የጠፋባቸው
- ውርጃ ያላቸው
- የመካንነት ችግር
- የቤተሰብ እና የአካባቢ ጫና
- ትዳር ውስጥ አለመስስማማት
- የፍላጎቶች አለመሟላት
- ያለ ጊዜ ማረጥ እና የመሳሰሉ ችግሮች
እንደ አጋላጭ ባህሪያት ይታያሉ::

እስከመቼ ይቆያል?

ይህ አይነት ስሜት በአብዛኛው ከቀናት እስከ ዘጠኝ ወር ሲቆይ አስከ አንድ አመት ሊድርስ እንደሚችል ጥናቶች ያሳያሉ።

በዚህ መካከል እርግዝና የለም ሲባሉ ስለማይስማሙ ብዙ የጤና ባለሙያዎችን ይጎበኛሉ፣ ይመረመራሉ። በውጤቱም አይረኩም ሌላ ቦታ ለመታየት ይሄዳሉ ይህም ''doctor shoping'' ለአመታት ሊዘልቅ ይችላል።

የሚመሳሰሉ ችግሮች ምንድናቸው?

- Delusional pregnancy (የቅዠት እርግዝና) በአይምሮ ህሙማን ላይ የሚከሰት ሲሆን በቃ ነፍሰጡር ነኝ ብሎ ሙጭጭ የማለት ሁኔታ ነው።

- Covouid syndrome (ተላላፊ እርግዝና) ከነፍሰጡር ሴት ጋር ከመቆየት የተነሳ ነፍሰጡሯ አንዳረገዘች ያህል የሚሰማት ጊዜያዊ ሁኔታ ነው።

- Feigned pregnancy አንድ ነገር ለማግኘት (ጥቅምን ያማከለ) ሲባል እርግዝና ሳይኖር እንዳለ የማስመሰል ሁነት ነው።

መፍትሄውስ?

እስካሁን ድረስ ይህ ችግር የሚፈታ የስነ አዕምሮ መድሃኒት የሌለ ሲሆን የስነ አዕምሮ ባለሙያ እና የማህፀን ፅንስ ስፔሻሊስቶች በጥምረት በመሆን ታካሚውን መርዳት ይቻላል።

- የስነ-አዕምሮ ምክር
- ቤተሰብን ማሳተፍ
- ምርመራዎችን አድርጎ ሁኔታዎችን ግልፅ ማድረግ
- የወር አበባ ወቅቱን ጠብቆ አንዲመጣ ማገዝ
- Delusional pregnancy በስነ-አዕምሮ መድሃኒቶች ሊታከም ይችላል።

ለበለጠ መረጃ ሃኪም ያማክሩ።

@melkam_enaseb
1.0K views10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 13:27:44
930 views10:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-22 12:19:16
የጤና ወግ በክለብ ሀውስ!

የጤና ወግ የአእምሮ ጤና ስፔሺያሊስቶች በክለብ ሃውስ በ Personality Disorders ዙሪያ ያደረጉትን ውይይት በዚህ ሊንክ ማድመጥ ይችላሉ።

https://www.clubhouse.com/room/m27Kagzr?utm_medium=ch_room_terc&utm_campaign=hRlA5hD3l5eqiHBShxl5xA-334611

@melkam_enaseb
1.6K viewsedited  09:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 13:12:15
ለጤናማ አእምሮ ወሳኝ ምክሮች
Tips for good mental health

በቂ እንቅልፍ መተኛት፦

- በየቀኑ ለ7 ወይም ከዚያ በላይ ሰአታት ጥሩና ጥራት ያለው እንቅልፍ ማግኘት።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፦

- በቀን ቢያንስ ለ30 ደቂቃ በሳምንት ለ5 ቀናት እንቅስቃሴ ማድረግ።

አዎንታዊ መሆን፦

- ቀና መሆን፣ ለችግሮች መፍትሔ መፈለግ፣ ጥሩ ውጤት እና ስኬትን ማሰብ።

- ትክክለኛውን ሰዓት የጠበቀና የተመጣጠነ አመጋገብን መከተል።

- መጽሐፍ ማንበብ።

- ከቅርብ ቤተሰብና ወዳጆች ጋር በቂ ጊዜን ማሳለፍ።

መልካም ቀን!

@melkam_enaseb
1.9K views10:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 13:11:01
#Vacancy_Announcement

We are looking to hire sessional counselors to our team!

If you fulfill the criteria you can email your cv and cover letter to

bruck.tesfaye@ahaethiopia.com

Make sure you mention which position you’re applying for on the subject of your cover letter!

Only shortlisted candidates will be contacted

For additional information you can call +251116622437/ +251940200454

Use the link below to see the full detail of the posts

https://drive.google.com/file/d/1S19hcKTS_iLy_lA3hP33qWqyWRAVktoa/view?usp=sharing

(Aha Psychological Service)

@melkam_enaseb
1.5K views10:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ