Get Mystery Box with random crypto!

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂

የቴሌግራም ቻናል አርማ psychoet — ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
የቴሌግራም ቻናል አርማ psychoet — ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
የሰርጥ አድራሻ: @psychoet
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.21K
የሰርጥ መግለጫ

| እውነት | ፍትህ | ፍቅር | ✔ሥነ ልቡና |
የተለወጠ ግለሰብ አለም ይለውጣል!
የተለያዩ የስነልቦናና የላቀ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የተሰሩ video ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናሌን ይከታተሉ
"የማወቅና የመለወጥ ሰአት አሁን ነው "
https://www.youtube.com/user/TheNahusenai
Facebook አድራሻዬ Fb.com/psychologyabc

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2022-11-01 22:58:04
ሰዎች የሚሉትን ብቻ ሳይኾን ልባችሁ የሚላችሁንም ስሙ!!

@psychoet
350 viewsedited  19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-31 20:48:03 እና
#ከለታት_በአንድ_ቀን_አንድ_ዝሆንና_አንድ_ዉሻ_በተመሳሳይ_ቀን_አረገዙ፡፡
ከሶስት ወር በኀላ ዉሻዋ 6 ቡችሎችን ወለደች፡፡ ከስድስት ወር በኀላም ዉሻዋ በድጋሜ አረገዘች እናም በዘጠነኛዉ ወር ሌሎች ብዙ ቡችሎችን ወለደች ፡፡ ዉሻዋ እንዲህ እያለች ብዙ ቡችሎችን ወለደች፡፡

በ18ኛዉ ወር ግን ግራ የገባት ዉሻ ወደቀድሞ ዝሆን ጓደኛዋ ሂዳ እንዲህ ስትል ጠየቀቻት "እርግጠኛ ነሽ ግን ማርገዝሽን? " ካስታወሽ የ ዛሬ 18 ወር እኩል ነበር ያረገዝነዉ ይሁን እንጂ ባለፋት ወራት እኔ ብዙ ቡችሎችን ወልጄ አሁን ትላልቅ ሁነዋል፡፡ አንቺ ግን እስካሁን የምር እርጉዝ ነሽ? ምን እየሆነ ነዉ ስትል ጠየቀቻት፡፡

ይህን የሰማችዉ ብልህ ዝሆን በእርጋታ እንዲህ ስትል መለሰች ፡፡ ዉድ ጓደኛዬ፥ እንድታዉቂዉ የምፈልገዉ አንድ ነገር አለ፡፡ ያረገዝኩት እኮ ቡችላ ሳይሆን ዝሆን ነዉ፡፡ በሁለት አመት አንድ ዝሆን ብቻ ነዉ እኔ ልወልድ የምችለዉ፡፡ ነገር ግን ልጄን በወለድኩ ጊዜና ልጄ መሬት ሲረግጥ መሬት ራሱ ትናወጣለች ፡፡ ልጄ መንገድ ሲያቋርጥ የሰዉ ልጆች ሁሉ ቆመዉ በአድናቆት ይመለከቱታል፡፡ እኔ ያዘልኩት ፅንስ ትኩረትን የሚስብ ነዉ፡፡ የያዝኩት ትንሽ ነገር ሳይሆን ሀያል የሆነ ዝሆን ነዉ ብላ መለሰች፡፡

#ትምህርት / Lesson

ሌሎች የራሳቸዉን ግብ በፍጥነት ሲመቱ የኔ አይሳካም ብለን ተስፋ አንቁረጥ በሌሎችም አንቅና ምክንያቱም
፩ . የኛ ስኬት የሚወሰነዉ በራሳችን ትጋት(ፅንስ) እንጂ በሌሎች ላይ ስላልሆነ
፪ . ጥሩ ነገር ሁሌ ግዜ ይወስዳል ( ትልቅ ነገር ለመስራት ብቻ ሳይሆን ለማሰብም ግዜ ይወስዳል ዉጤቱ ግን ታላቅ ነዉ )
፫ . ....
ይህንን ካነቡ አይቀር በዉስጣቸዉ ትልቅ ነገር አለ ለምትሉት ጓደኛ/ዘመድ/ቤተሰብ ይህን #FORWARD #Share ያድርጉ፡፡


2015 ሀሳባችሁን የምታሳኩበት ዓመት ይኹንላችሁ !
@psychoet
1.5K views17:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 22:58:30 ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ pinned «አንድ ቀን ቀረው! መልካም ዜና! #Share ይደረግ ነፃ የስልጠና እድል ለ 100 ወጣቶች፡፡ ኖቫ ማሰልጠኛ ተቋም 100% በተግባር የተደገፈ የዲጂታል ማርኬቲንግ (Digital Marketing) ስልጠና ተመርቃችሁ ስራ እየፈለጋችሁ ላላችሁ ወጣቶች፣ ለዩኒቨርስቲና ኮሌጅ ተማሪዎች እንዲሁም ለ12ኛ ክፍል ውጤት ጠባቂዎች ሊሰጥ ነው፡፡ ስልጠናው መሰረታዊ የዲጂታል ማርኬቲንግ ዕውቀት፣ ዲጂታል አይደንቲቲ፣…»
19:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 08:33:02 አንድ ቀን ቀረው!

መልካም ዜና! #Share ይደረግ
ነፃ የስልጠና እድል ለ 100 ወጣቶች፡፡
ኖቫ ማሰልጠኛ ተቋም 100% በተግባር የተደገፈ የዲጂታል ማርኬቲንግ (Digital Marketing) ስልጠና ተመርቃችሁ ስራ እየፈለጋችሁ ላላችሁ ወጣቶች፣ ለዩኒቨርስቲና ኮሌጅ ተማሪዎች እንዲሁም ለ12ኛ ክፍል ውጤት ጠባቂዎች ሊሰጥ ነው፡፡ ስልጠናው መሰረታዊ የዲጂታል ማርኬቲንግ ዕውቀት፣ ዲጂታል አይደንቲቲ፣ ኮንተንት ክርኤሽን፣ በማህበራዊ ሚዲያ ( facebook, YouTube፣ Telegram, TikTok, Instagram …) ላይ ያተኮሩ ስራዎች፣ መሰረታዊ ቪዲዮ ኤዲቲንግ ላይ ያተኩራል፡፡
በስልክዎት ብቻ ተከፋይ ይሁኑ!

ስልጠናው ጥቅምት 16 ረቡዕ ፣17 ሀሙስ እና 18 አርብ ለ3 ቀናት ይሰጣል
በጠዋት (3-5)፣ በከሰአት(8-10) ወይም በማታ(12-2) መከታተል ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃና ለመመዝገብ 0912664084 ይደውሉ፡፡

ያለን ቦታ ውስን ስለኾነ ቀድመው ይመዝገቡ፡፡ #ለሰልጣኞች በሙሉ ሰርተፊኬት እንሰጣለን

አድራሻ ፦ 4 ኪሎ አደባባይ ቱሪስት ሆቴል ጀርባ ( አራት ኪሎ የገበያ ማዕከል ቢሮ ቁጥሮ 219 እና 221)
https://g.co/kgs/xJbSXr
ይህ እድል እንዳያመልጣቸው ለሌሎችም ያጋሩ፡፡
@ethionova
3.6K views05:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-24 07:52:44
መልካም ዜና! #Share ይደረግ
ነፃ የስልጠና እድል ለ 100 ወጣቶች፡፡
ኖቫ ማሰልጠኛ ተቋም 100% በተግባር የተደገፈ የዲጂታል ማርኬቲንግ (Digital Marketing) ስልጠና ተመርቃችሁ ስራ እየፈለጋችሁ ላላችሁ ወጣቶች፣ ለዩኒቨርስቲና ኮሌጅ ተማሪዎች እንዲሁም ለ12ኛ ክፍል ውጤት ጠባቂዎች ሊሰጥ ነው፡፡ ስልጠናው መሰረታዊ የዲጂታል ማርኬቲንግ ዕውቀት፣ ዲጂታል አይደንቲቲ፣ ኮንተንት ክርኤሽን፣ በማህበራዊ ሚዲያ ( facebook, YouTube፣ Telegram, TikTok, Instagram …) ላይ ያተኮሩ ስራዎች፣ መሰረታዊ ቪዲዮ ኤዲቲንግ ላይ ያተኩራል፡፡
በስልክዎት ብቻ ተከፋይ ይሁኑ!

ስልጠናው ጥቅምት 16 ረቡዕ ፣17 ሀሙስ እና 18 አርብ ለ3 ቀናት ይሰጣል
በጠዋት (3-5)፣ በከሰአት(8-10) ወይም በማታ(12-2) መከታተል ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃና ለመመዝገብ 0912664084 ይደውሉ፡፡

ያለን ቦታ ውስን ስለኾነ ቀድመው ይመዝገቡ፡፡ #ለሰልጣኞች በሙሉ ሰርተፊኬት እንሰጣለን

አድራሻ ፦ 4 ኪሎ አደባባይ ቱሪስት ሆቴል ጀርባ ( አራት ኪሎ የገበያ ማዕከል ቢሮ ቁጥሮ 219 እና 221)
https://g.co/kgs/xJbSXr
ይህ እድል እንዳያመልጣቸው ለሌሎችም ያጋሩ፡፡
@ethionova
3.1K views04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-23 21:50:06
ከመሞታችሁ በፊት ማድረግ ያለባችሁ 20 ነገሮች
Join Telegram t.me/psychoet

1.ትላንትናን እና ነገን እያሰባችሁ አትጨነቁ፡፡ ትናንት አልፏል ነገ አልመጣም ስለዚህ ዛሬን ቀን በሙላት ፣ በደስታ ፣በሰላም ለመኖር ጥረት አድርጉ፡፡

2.የበደሏችሁን ሰዎች ይቅርታ አድርጉላቸው ፡፡

3.ሁሉንም ሰው በእኩል ዓይን እዩ፡፡

4.ወደዚህ ምድር ያመጧችሁን እናትና አባታችሁን ውደዱ ፣ አክብሩ ፣ ታዘዙ ። *

5.የምትጠሉትን ስራ አትስሩ፡፡

6.የሕይወት ግባችሁን በመለየት በቅጡ ኑሩ፡፡

7.መስታወት ውስጥ ራሳችሁን ተመልክታችሁ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ራሳችሁን ውደዱ፡፡

8.እዚህ ምድር የመጣችሁት በፈጣሪ አላማና እጅግ በጣም ጠቃሚ ሰዎች እንደሆናችሁ አስቡ ፡፡

10.ዘወትር መሄድ እፈልጋለሁ ወደምትሉት ስፍራ ሂዱ፡፡

11.በየቀኑ ለሌሎች ቢያንስ አንድ መልካም ነገር አድርጉ፡፡*

12.ለውጥን በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ ሁኑ፡፡

13.ሁሉንም ዓይነት የሕይወት ትምህርት በፀጋ ተቀበሉ፡፡

14.የሕይወት ፈተና ውስጥ ያለውን መልካም አጋጣሚ አስተውሉ እንጂ ተስፋ አትቁረጡ፡፡

15.በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ አዎንታዊ እና በጎ አሳቢ ሆናችሁ ዝለቁ፡፡

16.በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይሆን ሰውን ሁሉ ለመውደድ ጣሩ ፡፡*

17.ከቁሳ ቁስ ጋር ያላችሁን ትስስር አላሉ፡፡

18.ልባችሁን ተከተሉ፡፡

19.ሁልጊዜም ትልቅ በመሆን ሌሎችን አነቃቁ፡፡

20.ከሰዎች ሁሉ ጋር ተጫወቱ በሰላም በመግባባት ኑሩ ፤ የተቸገሩትን ደግፉ ፡፡ ደግሞም ይህን ጽሑፍ #Share አርጉ ፡፡*

ዘጠነኛውን አንብባችሁታል ግን? .......
የዘለልኩት እስቲ እኔ ያልጠቀስኩት መደረግ ያለበት ነገር #Comment እንድታረጉልኝ ነው?
#Comment

ሰናይ ሳምንት ይሁንላችሁ
2.8K views18:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-19 20:14:28 "ከባለቤቴ ጋር ትዳር ከመሰረትን 21 ዓመት ሞላን ...ባለቤቴ አንድ እራሴን እንድፈትሽበት ያደረገኝን ጥያቄ አቀረበችልኝ ... ሃያ አንድ ዓመት ካንተ ጋር ስኖር አንድም ቀን ከእናትህ ጋር ለመዝናናት ስትወጣ አይቼክ አላውቅም ... ዛሬ ማታ እናትህን እራት ምሽት ጋብዛትና አዝናናት አለቺኝ" ውዷ ባለቤቴ ...ባቀረበችልኝ ሃሳብ ከመገረም በላይ መሰጠኝ ተስማማሁኝ እናም ወደ እናቴ ጋር ደወልኩላት ኡሚ ዛሬ ካንቺ ጋር ሽርሽር መውጣት እፈልጋለሁ አልኳት ... ደነገጠች "ምነው ሰላም አይደል ልጆችህ ምን ሆኑ ...ባለቤትህስ ሰላም አይደለች እንዴ ?" በማለት የድንጋጤ ጥያቄዎቿን አርከፈከፈችብኝ..." እማ ሁሉም ሰላም ነው ካንቺ ጋር ለመዝናናት ፈልጌ ነው" አልኳት ... በጣም ደስ አላት ተስማማች ... ወደ ማታ ተዘጋጅተሽ ጠብቂኝ አልኳት ...

... በቀጠሮዬ ሰዓት ወደ እናቴ ጋር ሄድኩኝ ... እናቴ በረንዳው ላይ ቆማ እየጠበቀቺኝ ነበር ... እናቴ ሁለመናዋ ተቀያይሯል እርጅና ተጫጭኗታል ... ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ወደ መኪናዬ አስገብቻት ጉዞ ጀመርን ... እናቴ በጣም ደስታ ይነበብባታል "ልጄ ዛሬ ካንተ ጋር ሽርሽር እንደምወጣ ለሰፈር ሰዎች ሁሉ እንዲሁም ለዘመድ አዝማዶቼ በሙሉ ተናግርያለሁኝ" በጣም ከመደሰቷ የተነሳ አንድም የምታውቀው አልቀራትም ወሬውን ለሁሉም አዳርሳዋለች ...

... ወደ ሆቴል ይዥያት ሄድኩኝ አስተናጋጁ የምግብ ዝርዝር ወረቀት የያዘ ኩፖን ሰጠን "እማ ምረጪ" አልኳት... ፈገግ አለች ከእርጅና የተነሳ ማየት እንደማትችል ተረዳሁ ... ላንብብልሽ አልኳት "ልጅ እያለህ ሆቴል ቤት ገብተን ልንመገብ ስንል የምግብ ዝርዝር አነብልህ ነበር ... አሁን እዳህን ክፈል" ብላ ፈገግ አለች እኔም ፈገግ ብዬ አነበብኩላት ... የለበሰችውን ልብስ ስመለከት ከአስራ ዘጠኝ ዓመት በፊት የሞተው አባቴ የገዛላት የመጨረሻ ልብሷ እንደነበር አስታወስኩ ... ምግቡ ቀርቦ እናቴ ከደስታ የተነሳ ምንም እየበላች አልነበርም... ደስታ በደስታ ሆናለች ... በሕይወቴ እኔም በጣም የተደሰትኩበት አጋጣሚ ነበር ከእናቴ ጋር ተዝናንተን ስናበቃ ይህ ምሽት እንዲደገም ፈልጌ "እማ መቼ ተመልሼ ልምጣና ልውሰድሽ..?" አልኳት ... በእንደዚ ቀን ና ነገር ግን እኔ ነኝ የምጋብዝህ ከተስማማህ ና" አለቺኝ ፈገግ አልኩኝ "አብሽሪ ትጋብዥኛለሽ" አልኳትና ተለያየን ... በመሃል እናቴ ታመመች ከህመሟ ድናልኝ አብርያት የማሳልፍበት ምሽት ናፈቀኝ ... ነገር ግን ከእናቴ ጋር ዳግም አልወጣንም ... እናቴ ወደ ማይቀረው የሞት ጉዞ ተጓዘች በጣም አዘንኩ አለቀስኩ ...

... ከእናቴ ጋር ቀጠሮ ይዘን በነበርንበት ቀን አመሻሹ ላይ ከአንድ ታዋቂ ሆቴል ቤት ተደወለልኝ "ዛሬ እራት ከባለቤትህ ጋር በነፃ ተጋብዛቹሃል" የሚል ነበር። ግራ ተጋባው ማነው እንዴት ... ለማንኛውም እሺ እንመጣለን ብዬ ስልኩን ዘግቼ ምሽት ላይ ከባለቤቴ ጋር ሄድኩኝ ... ግብዣው ከደብዳቤ ጋር ቀረበልን ደብዳቤውን ከፈትኩት እንዲህ ይላል:-
"ልጄ ሰላም ላንተ ይሁን የእራቱን ግብዣ ስንቀጣጠር መገኘት እንደማልችል አውቅ ነበር ... የሞት ቀጠሮዬ እየተቃረበ እንደነበር ነፍሴ ይነግረኝ ነበር ልጄ ይኸው እኔ በቃሌ መሰረት ጋብዥሃለው ... በኔ ፋንታ ውዷ ባለቤትህ አብራህ እንድትሆን ፈቅጃለሁ!" ይላል ሳይታወቀኝ እንባዬ ወረደ አለቀስኩ 21 ዓመት ሙሉ የዘነጋሁትን ውድ ዕቃ አሁን ነው ማጣቴን ያወኩት...!
--------
ስንቶቻችን ይሆን ካገባን በኋላ እናቶቻችንን የምናስታዉሳቸዉ ?
SHER.በማድረግ ለሌሎች ያካፍሉ። እረጅም እድሜ ለእናቶቻችን!!

Follow - @psychoet
4.2K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-18 19:35:29
……… በጣም ገራሚ ታሪክ

ትንሿ ቆንጅዬ ልጅ ሁለት አፕል እንደያዘች እናቷ መጣች ።
እናትም " የኔ ጣፋጭ አንዱን ለኔ ለእናትሽ ትሰጪኛለሽ ?" ስትል በትህትና ትጠይቃታለች ።
ልጅም ትኩር ብላ ከተመለከተቻት በኋላ አንዱን አፕል ግምጥ አደረገችው ። ቀጠለችና ሁለተኛውንም ደገመችው እናት በልጇ ሁኔታ ደንግጣ ፍዝዝ ብላ ቀረች ።
ስሜቷን በቁጣ ልታሳያት ብትሞክርም ድንጋጤው ከለከላት እንዴት በእኔ በእናቷ ትጨክናለች …? ብላ አሰበች ።

በዚህ መሀከል ልጅ የገመጠችውን አንዱን ለእናቷ እያቀበለቻት "እንኪ ማሚ ይበልጥ የሚጣፍጠው ይሄኛው ነው ።" አለቻት ። እናት ያልጠበቀችውን ክስተት በማየቷ ልጇን አቅፋ ተንሰቅስቃ አለቀሰች

መልካም አዳር

@psychiet
3.5K views16:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-18 05:31:09 #ሃያ አንዱ ማኅበራዊ ሕግጋት
መልዕክቱን አንብበው ሲጨርሱ #Share ያድርጉት

(Sicial Rules ተብለው የተዘረዘሩ የማኅበራዊ ሕይወት ሕግጋትን ስመለከት ለኛስ አትጠቅምም ወይ ብዬ ነው ወዲህ ማምጣቴ)
==================
1. ይሰለቹሃል
አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ!

2. 'ሼም ነው' ነው
የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ!

3. አይባልም
"... እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..." አይባልም።

4. ክፈል
አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ።

5. ነውር ነው
ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ።
============

6. አታቋርጥ
ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ። ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው።

7. አታብሽቅ
ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው። ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ።

8. አመሥግን
ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር አመሥግን።
9. ያለስስት አድንቅ
ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል አውራቸው።

10. ክፉ አስተያየትህን ቆጥብ
ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ።
===================

11. ካልሆኑ ጥያቄዎች ታቀብ
ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል። የውጤቱን ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል።

12. ስነ ስርዓት
ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው።

13. ክብር ለሁሉም
ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም።

14. ስልክህን አስቀምጥ
ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው። ከሰው ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው።

15. አድብ
ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው።
==========================

16. ተቆጠብ
ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ።

17. መነጽርህን አውልቅ
ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ። ክብርም ነው!

18. አትሳሳት
በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ።

19. ለስልክ መልዕክት ምላሽ መስጠት
በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው። ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው።

20. ዕቃ መልስ
የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ።

21. አማራጭ ሐሳቦች ሁሌም አሉ
የያዝከውን ሐሳብ ሳትፈራ አውጣው። ሌሎች እንዲወያዩበትና እንዲተቹት ክፍት አድርገው፤ አንተም ሐሳብህም ትጎለብታላችሁ። ነገርህን ደገፉትም አልደገፉት ምንጊዜም ቢሆን ላነሳኸው ሐሳብ ጥሩ ግብዓት አይጠፋም። ልክ አልሆን ወይ እያልክ ወይም ሐሳቤ ያንስ ይሆን ወይ ብለህ አትሸማቀቅ፤ ተሸማቀህ ትቀራለህ!

ሳይኮሎጂ ፔጅን #Like በማድረግ ቤተሰብ ኹኑ

@psychoet
Abraham Tsehaye
3.2K views02:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-18 05:30:27
2.1K views02:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ