Get Mystery Box with random crypto!

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂

የቴሌግራም ቻናል አርማ psychoet — ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
የቴሌግራም ቻናል አርማ psychoet — ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
የሰርጥ አድራሻ: @psychoet
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.21K
የሰርጥ መግለጫ

| እውነት | ፍትህ | ፍቅር | ✔ሥነ ልቡና |
የተለወጠ ግለሰብ አለም ይለውጣል!
የተለያዩ የስነልቦናና የላቀ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የተሰሩ video ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናሌን ይከታተሉ
"የማወቅና የመለወጥ ሰአት አሁን ነው "
https://www.youtube.com/user/TheNahusenai
Facebook አድራሻዬ Fb.com/psychologyabc

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2022-08-31 21:10:00
#ቻርሊ_ቻፕሊን
አንብባችሁ ለሌሎችም በየግሩፑ ሼር አድርጉት

ቻርሊ ቻፕሊን 88 ዓመታትን በህይወት ኖሯል ። ግን ከዚህ ሁሉ ዘመን በኋላ የተወልን አራት ዐ.ነገሮችን ብቻ ነው ።

እኛ ሁላችንም ቱሪስቶች ነን ፣ የጉዞ ወኪላችን ፈጣሪ ነው ። እሱም የመጓጓዣ ቆይታችንን ፣ የመስተንግዶ ሁኔታችንንና መዳረሻችንን ሁሉ የሚያውቀው እመነውና በህይወት ደስተኛ ሁን!! ህይወት ጉዞናት እናም ዛሬን በአግባቡ ኑራት ነገ ላትኖር ትችላለህና!! የሰማነውን በልቦናችን ያሳድርልን!!!

1 ምንም ነገር ዘላለማዊ አይደለም ፤ ሌላው ቀርቶ ችግሮቻችንም ጊዜያዊ ናቸው ።

2 በዝናብ ውስጥ መሄድ እወዳለሁ ፣ ምክንያቱም ማንም እንባዬን አያይብኝምና ።

3 በህይወታችን ታላቁ የባከነው ቀን ሳንስቅ የዋልንበት ቀን ነው ።

4 በአለም ላይ ምርጥ ስድስት ዶክተሮች:-
1. ፀሀይ
2.እረፍት
3. የሰውነት እንቅስቃሴ
4.አመጋገብ
5. የራስ-ክብር
6 ጓደኞችህን እነዚህን ጠብቃቸውና ህይወትህን አስደሳች አድርገው።

ጨረቃን ካየህ ፥ የተፈጥሮን ውበት ታያለህ፣
ፀሀይንም ካየህ፣ የፈጣሪን ኃይል ታያለህ፣
መስተዋት ካየህ ፣ የፈጣሪን ትልቅ ጥበብና ፍጡር ታያለህ ስለዚህ በፈጣሪህ እመን ።

@ከደራሲያን_አለም_ፔጅ
@psychoet
1.4K views18:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:09:38 ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ pinned a photo
10:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 13:08:52
11 ኛ ዙር የሕይወት ክህሎት ሰልጣኞቻችን እንኳን ደስ አላችሁ!

በተለይም ከወሊሶ ድረስ በመመላለስ ስትሰለጥኑ የነበራችሁትን አቶ አብዲሳ ማመስገን እንፈልጋለን፡፡ ለብዙ ወጣቶች የለውጥ አርአያ ኹነዋል፡፡

ቀጣይ የመጨረሻው የ2014 የሕይወት ክህሎት ስልጠናችን በቀጣዩ ሳምንት ነሀሴ 30 - ጳጉሜ 4 (ከሰኞ እስከ አርብ) ይካሄዳል፡፡

ያሉን ፈረቃዎች:
ጠዋት (3:00 - 6:00)
ከሰአት (8:00 - 11:00) እና
ማታ (12:00 - 2:00)

የዚህ ዙር ስልጠና ለ2015 ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም፣ የሚተገበር እቅድ አወጣጥ እና የስራ ፈጠራና የገንዘብ አጠቃቀም ላይ ያተኩራል፡፡

ባሉን ጥቂት ቦታዎች ቀድመው ይመዝገቡ
ክፍያ : 1000 ብር

አድራሻ:-4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሀን ንግድ ማዕከል ቢሮ 219 እና 221 0912664084
@psychoet
1.3K viewsedited  10:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 18:00:36 ስማኝ ልጄ!!!!!!! ተነቦ ሼር ይደረግ

1. ጠንካራ ሰው ሁን ማለት አትውደቅ ማለት አይደለም ወድቀህ መነሳትንም ልመድ ማለት እንጂ!!!!

2. ዝም በል ማለት አትናገር ማለት አይደለም ሌሎችን ለመስማት ጆሮ ስጥ ማለት እንጂ!!!!

3. ሆዳም አትሁን ማለት አትብላ ማለት አይደለም በሰው ሀቅ አትለፍ ማለት እንጂ!!!!

4. አትቆጣ ማለት ስሜት አይኑርህ ማለት አይደለም ከቁጣ ቶሎ ተመለስ ማለት እንጂ!!!!

5. ይቅርታ አድርግ ማለት አልተጎዳህም ማለት አይደለም በሆድህ ቂም መያዝ ሌላ ጉዳት ስለሆነ እንጂ!!!!

6. ጠላትህን ውደድ ማለት ጠላት ጥሩ ነው ማለት አይደለም ከጥላቻ ይልቅ ፍቅር ስለሚያሸንፍ!!!

7. ደስተኛ ሁን ማለት ሁሉ ይኑርህ ማለት አይደለም ባለህ ነገር ደስ ይበልህ ማለት እንጂ!!!!

8. ስራህን ውደድ ማለት የምትሰራው ስራ ጥሩ ነው ማለት አይደለም ነገ ጥሩ ስራ እንዲኖርህ ዛሬ የምትሰራውን ስራ ውደድ ማለት እንጂ!!!!

9. ወረኛ አትሁን ማለት አታውራ ማለት አይደለም ምንም ስለማታውቀው ነገር አታውራ ማለት እንጂ!!!!

10. ትሞታለህ ማለት አትስራ ማለት አይደለም ምንም ቁም ነገር ስትሰራ አትሙት ማለት እንጂ!!!!

11. ብቸኛ አትሁን ማለት ሮጠህ ትዳር ያዝ ማለት አይደለም ልብህን ግዜህን ያለህን ሁሉ አሳልፈ ለመስጠት ዝግጁ ሁን ማለት እንጂ!!!!

12. እውነተኛ ሁን ማለት ሰዎች ባሉበት ብቻ እውነትተናገር ማለት አይደለም ለራስህም የእውነት ኑሮ ኑር ማለት ማለት እንጂ!!!!

13. አትጣላ ማለት ከሰው ጋር አትኑር ማለት አይደለም ቂም ይዘህ አትቆይ ማለት እንጂ!!!!

14. ኩራተኛ አትሁን ማለት አትዘንጥ ማለት አይደለም ሌሎችን አትናቅ ማለት እንጂ!!!

15. ቆንጆ ነህ ማለት ከሌሎች የተሻልክህ ነህ ማለት አይደለም አምሮብሃል ማለት እንጂ!!!!

16. አዋቂ ሁን ማለት እንደገና ት/ቤት ሂድ ማለት አይደለም ብልህ ሁን ማለት እንጂ!!!
ከFb የተገኘ

በቴሌግራም @psychoet
2.0K viewsedited  15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 18:00:24
1.9K views15:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 11:52:29
ምን ያህሎቻችን የተገቢ ዝምታን ሀይል እንረዳለን?
4.0K views08:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 07:45:08
4.0K views04:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 18:22:13
ለውጥ በነፃ!

በኖቫ የስልጠና ማዕከል የሚዘጋጀውን ሳምንታዊ የስነልቡና ስልጠናና ውይይትን ይካፈሉ፡፡ በየሳምንቱ በሚመረጡት ርዕሶች አመለካከትዎንና ሕይወትዎን የሚቀይሩ ቁም ነገሮች ይገብዩ፡፡

የሳምንቱ አሰልጣኝኝና አወያይ :- ናሁሰናይ ፀዳሉ

ውስን ቦታዎች ስላሉን ቀድመው ወንበር ይያዙ፡፡
ዘወትር ሀሙስ ከ11:30 ጀምሮ

አድራሻ :- 4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል (ከቶታሉ ጀርባ)
አዲስ ብርሀን የገበያ ማዕከል ቢሮ ቁጥር 219

@psychoet
5.8K viewsedited  15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 09:50:41
የዘመኑ አሰተዋይ ሰው ማነው?
4.9K views06:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-15 19:46:28 የአካላችን ጤንነት ለአእምሮአችን ጤንነት አንዱ መሠረት ነው
☞ የጀርባ ህመም መነሻ 10 ምክንያቶች፦
.
1. በሆድ በኩል መተኛት:
በሆድ በኩል ተደፍተዉ ሲተኙ በጀርባዎና በአከርካሪ አጥንትዎ ላይ ተጨማሪ ሸክም ይጨምራል። በአከርካሪ አጥንትዎ ላይ ተጨማሪ ሸክም ጨመሩ ማለት ደግሞ የሙሉ ሰውነትዎን ቅርጽ ያዛባዋል ጭንቅላትዎን ወደ ጎን ሲያዞሩት ደግሞ ጭንቅላትዎንና አከርካሪዎት ከመደበኛ አቅጣጫዎ ውጪ አደረጉት ማለት ነው።
.
2. የሚያደርጉት ጫማ:
ጫማ ለጀርባዎ ጤንነት ከፍተኛ ሚና ይጫዎታል የማይገባ/ትክክል ያልሆነ ጫማ አቋምዎን በማዛባት ማዕከላዊ የግራቪቲ ቦታን ያዛባል ይህም በታችኛው የጀርባ ክፍልዎ ላይ ህመም ይፈጥራል።
.
3. እግርን አጣምሮ መቀመጥ:
እግርዎን አጣምረው በሚቀመጡበት ጊዜ የአከርካሪ አጥንትዎ ቀጥ ማለት ይሳነዋል። ይህም በዳሌ አካባቢ የሚገኙ ጡንቻዎች ከመጠን በላይ እንዲለጠጡ ያደርጋቸዋል። በተጨማሪም የደም ዝውውር በመስተጓጐሉ ምክንያት ቫሪኮስ ቬይን (Varicose vein) ለተባለ በሽታ ያጋልጣል።
.
4. የቢሮ ወንበር :
የቢሮ ወንበርዎ ለጀርባ ህመም ከፍተኛ አስተዋጽዎ ያደርጋል። በተለይ ሲቀመጡ ጎበጥ የሚሉ ከሆነ ጀርባዎ ላይ ጫና ያደርጉበታል፤ አከርካሪ ሊጋመንታችን ከአቅም በላይ ይለጠጥና ዲስካችን የጀርባ አጥንታችን እንዲወጠር ያደርጋል ከጊዜ ብዛት የጀርባ አጥንታችንን በመጉዳት ለጀርባ ህመም ይዳርገናል።
.
5. የሚተኙበት ፍራሽ:
የሳሳ (ስስ) ፍራሽ መጠቀም የታችኛዉን የጀርባ ክፍል እንዲሰምጥ ያደርጋል። በተጨማሪም የአከርካሪ አጥንቶችን እንዲዛቡ በማድረግ በጡንቻዎች እና የአከርካሪ መገጣጠሚያዎች ላይ ውጥረት ይፈጥራል።
.
6. የጀርባ ቦርሳ:
የሚይዙት የጀርባ ቦርሳ ትልቅ ከሆነ ብዙ እቃዎችን የመያዝ እድል ይኖርዎታል፤ ተጨማሪ ሸክም በጀርባዎ ላይ መጫን ትልቁ የጀርና ህመም ምክንያት ነው። በአንድ በኩል ያለው የሰውነት ክፍልዎ ላይ ሸክም መጨመር የአከርካሪ አጥንቶች እንዲጎብጡ በማድረግ የጀርና ህመም እንዲከሰት ያደርጋል።
.
7. ትከሻ ወይም አንገት:
ለረጂም ሰዓት አንገት አዘንብሎ (ደፍቶ) መቆየት ወይም መጓዝ በትከሻዎቻችን መሀል ያሉትን ጡንቻዎች እንዲዝሉ በማድረግ የላይኛው ጀርባ ክፍል እና የአንገት ህመም ያስከትላል።
.
8. ላኘቶኘና ስማርት ስልኮች:
በአለም ላይ ያሉ ሰዎች ሁሉ በኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎቻቸው ፍቅር ስለወደቁ በነዚህ ሰዎች ላይ የጀርባ ህመም የተለመደ ነው። በስራ በተጠመድበት ወቅት ስልክዎትን በትከሻዎና በጆሮዎ መሀል በመያዝ ለረጂም ጊዜ ማውራት የአንገት ህመም ያስከትላል።
.
9. ከመጠን ያለፈ ውፍረት:
ከሌሎች በሽታዎች በተጨማሪ ከመጠን ያለፈ ውፍረት ለጀርባ፣ መገጣጠሚያ እና ጡንቻዎች ህመም ያጋልጠናል። አብዛኛዎቹ በሚኖራቸው ውፍረት በዳሌና በታችኛው የጀርባ ክፍል ህመም ያጋጥማቸዋል።
.
10. ሲጋራ ማጨስ :
በሲጋራ ውስጥ ያለው ኒኮቲን ወደ ዲስክ (Disc) የሚሄደውን የደም ዝውውር በመቀነስ የአከርካሪና ጎን አጥንት ችግር ያስከትላል። በተጨማሪም ካልሲየም በአግባቡ ከሰውነታችን ጋር እንዳይዋሀድ በማድረግ የአጥንት እድገትን ይገታል በመሆኑም ሲጋራ የሚያጨሱ ሰዎች ከማያጨሱ ሰዎች በአንድ እጥፍ የጀርባ ህመም ችግር ያጋጥማቸዋል።
.....
@ ምንጭ: ዶክተር አለ
.ለሌሎችም ሰዎች ሼር አርጉ
.
.
Telegram channel:
@Psychoet
5.0K views16:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ