Get Mystery Box with random crypto!

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂

የቴሌግራም ቻናል አርማ psychoet — ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
የቴሌግራም ቻናል አርማ psychoet — ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
የሰርጥ አድራሻ: @psychoet
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.21K
የሰርጥ መግለጫ

| እውነት | ፍትህ | ፍቅር | ✔ሥነ ልቡና |
የተለወጠ ግለሰብ አለም ይለውጣል!
የተለያዩ የስነልቦናና የላቀ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የተሰሩ video ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናሌን ይከታተሉ
"የማወቅና የመለወጥ ሰአት አሁን ነው "
https://www.youtube.com/user/TheNahusenai
Facebook አድራሻዬ Fb.com/psychologyabc

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2022-08-02 07:38:10 የአሸናፊነት ሥነልቡና
#ክፍል_2
በናሁሰናይ ፀዳሉ

አሸናፊነት በራሱ ባህሪይ ነው ለዛውም የምንለማመደውና የምናሳድገው ፡፡ አሸናፊነት ደግሞ የሚጀምረው ከአስተሳሰብ እንጂ ከተግባር አይደለም ፡፡ በሀሳቡ ፣ በአዕምሮው የተሸነፈ ሰው በተግባር ቢያሸንፍም ውስጣዊ ደስታ እርካታ ድልን አያገኝም ፡፡ አሸናፊነት የሚለመድ የሚታይ ባህሪይ ነው ፡፡

10ሩ የአሸናፊዎች ባህሪ

ከተራ ቁጥር 1 - 5 ያሉትን ባለፈው በዝርዝር አይተናል፡፡ ዛሬ ከተራ ቁጥር 6-10 ያሉትን እናያለን ፡፡
__________
1.ልንሆነው/ልንደርስበት ስለምንፈልገው ነገር የጠራ እይታ / አመለካከት
2.ግብ ማስቀመጥ
3.አወንታዊ አመለካከት
4.ቆራጥነት
5.ራስን ማወቅ
__________

6.Self Esteem / ራስን ማክበር

አሸናፊ ሰዎች ለራሳቸው ትልቅ ክብርና አድናቆት ያለቸው ናቸው ፡፡ስለራሳቸው ጥሩ አወንታዊ አመለካከት አላቸው ይህ ማለት ግን ሌሎችን ይንቃሉ / አያከብሩም ማለት አይደለም፡፡ ራስን ማክበርና ሌሎችን ማክበር መነጣጠል የሌለባቸው ጉዳዮች ናቸው ፡፡ አንዳንድ ተሳካልን ፣ ትልቅ ደረጃ ደረስን አሸነፍን የሚሉ ሰዎች ከታች ያሉ ሰዎቾን የመናቅ ያለማክበር ሁኔታ ይታያል ይህ ግን ትልቅ ችግርና ያልተሟላ አሸናፊነት ብሎም ለወደፊነቱ ወደ ተሸናፊነት የሚወስድ መንገድ ነው ፡፡ አሸናፊ እራሱን ያከብራል ደግሞም ያስከብራል ብሎም ደግሞ ሌሎችን አክብሮ ያስከብራል ፡፡

7.Self Discipline / ስርአት መኖር

ይህ በተግባር የሚገለፅ የአሸናፊነት ባህሪ ነው ። በዚህ ዘመን ብዙ ሰው የወሬ እንጂ የስርአትና የተገባር ሰው አይደለም ከላይ አመራር ጀምሮ እስከታች ድረስ ብዙ ጊዜ ወሬ እንጂ ስርአትና / ተግባር አይታይም ፡፡ ጠንካራ ልምምዶችን እንደ ልምድ አድርጎ በተግባር አለመግለፅ አሸናፊ እንዳንሆን ያረገናል ፡፡ ለምሳሌ እግር ኳስ ተጫዋቾችን ብንመለከት ልምምዳቸውን በየጊዜው በስርአት ካልሰሩ ብዙ ሽንፈት ሊገጥማቸው ይችላል ፡፡

8.Self Talk / ከራስ ጋር ማውራት (ጊዜ መውሰድ)

አሸናፊዎች ሁልጊዜ የሚራራጡ ፣ እረፍትና እርጋታ የሌላቸው ፣ ሁሌ ሳያቋርጡ የሚሰሩ አይደሉም ፡፡፡ይልቁንስ በቂ ሰአት ስራቸው ላይ የሚያጠፉ እንዲሁም ተመጣጣኝ ጊዜ ደግሞ ለራሳቸው የሚሰጡ ፣ ነገሮችን በትኩረት ረጋ ብለው የሚያስቡ (ሳይጨነቁ ነገሮችን የሚያወጡ የሚያወርዱ) ናቸው ፡፡ ከራሳቸው ጋር በቂ ጊዜ የሚወስዱ ሰዎች ሁሌ ከውጥረት ብሎም ከጭንቀት ራሳቸውን ያስመልጣሉ ፡፡

9.Complete person / ሙሉ ሰውነት

ትክክለኛ አሸናፊ ሰው አንድ ወገን ብቻ ያደገ ፣ ሌላው ጎኑ የጎደለ ሳይሆን በሙሉ ማንነቱ የሞላ ያሸነፈ ነው ፡፡ ሕይወት ትምህርት ጥሩ ውጤት ማምጣት / ሩጦ 1ኛ መውጣት ፣ ተዋግቶ ማሸነፍ ፣ በሀብት ትልቅ ደረጃ መድረስ ብቻ አይደለችም ፡፡ አንዳንድ ሰው በገንዘብ አቅሙ ትልቅ ደረጃ ይደርስና በማህበራዊ ሕይወቱ ደግሞ 0 ይሆናል ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰው ሙሉ ሰው አንለውም ፡፡

#ሙሉ ሰውነት ላይ ወደፊት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ይዤ እቀርባለሁ ፡፡

10.Live in the present/ አሁንን መኖር

ይሄ ብዙዎች አሸናፊ እንዳይሆኑ የሚያረግ የአመለካከት ችግር ነው ፡፡ ነገራችንን በሙሉ በነገ ተስፋና በትናንት ፀፀት / ወቀሳ ዛሬ ላይ በደንቡ ሳንኖር በሀዘን እንዘልቃለን ፡፡ አሁንን በአሸናፊነት ሀሳብ/ አመለካከት ሳንኖር የነገን ያልተጨበጠ ድል በማለም በተስፋ ብቻ እንደክማለን ፡፡ ስለዚህ አሸናፊ ለመሆን የሚያስብ ሰው አሸናፊነት ስለ ነገና ስለ ወደፊት ሳይሆን ስለ አሁን ነው ፡፡


#Like #Share በማረግ ሁላችንም ባለንበት ቦታ አሸናፊ እንሁን !

አሸናፊነት የሚጀምረው ከአስተሳሰብ ነውና አስተሳሰባችሁን ቀና ፣ በጎ ፣ ጥሩ ጥሩውን ማድረግ ጀምሩ ፡፡ አሉታዊ አስተሳሰባችሁን በአወንታዊ ሀሳቦች ለውጡ ፡፡

#ነገ_ይቀጥላል ፡፡

#መልካም_ቀን!
@Psychoet
4.4K views04:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-15 20:14:53 #ውሸት
#ክፍል_1
ለምን እንዋሻለን ???

በግል የምንዋሸው እንዳለ ኾኖ አሁን አሁን በትልልቅ ሚዲያዎች ሳይቀር ቀርቦ ውሸት መናገር እየተለመደ የመጣ መጥፎ ተግባር ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ውሸትን ለብዙ ነገራቸው አየተጠቀሙት ልምድ አርገውታል፡፡ ግን
ውሸት ምንድነው?
ባለሙያዎች ውሸትንና ውሸታሞችን እንዴት ያዮቸዋል? ከታች የቀረበው ጽሑፍ ብዙ ነገሮችን ያስዳስሰናል፡፡


ውሸትን የተለያዩ ምሁራን ትርጓሜና እና ማብራሪያ ሰጥተውበታል በዚህም ነጋሪውን ለመጥቀም የታሰበ ሐሰታዊ የሆነ ግንኙነት የሚለው መጀመሪያው ሲሆን ይህም ብዙ ውዝግቦችን አስነስቶ ነበር፡፡ ምክንያቱም ነጋሪውን ብቻ ለመጥቀም  ውሸት አይነገርም የሚሉ፣ ውሸት ሆን ተብሎ የሚደረግ እውነትን የመደበቅ ስራ ነው ብለው መልስ የሰጡ ብዙ ወገኖች ነበሩ፡፡ በሁለተኛው የውሸት ማብራሪያ ወይም ፍቺ መሰረትም ሰዎች ሳያውቁት የተሳሳተ መረጃ ከተናገሩ እንደ ውሸት አይቆጠርም ማለት ነው፡፡ በርገን እና ቡለር የተባሉ ሁለት ምሁራን ደግሞ ውሸት ማለት መልዕክት ላኪው ለመልዕክት (መረጃ) ተቀባዩ ሆን ብሎ የተሳሳተ መረጃ በማቀበል መልዕክት ተቀባዩን መጉዳት ነው ይሉናል፡፡ እኛ ደግሞ የእራሳችን የሆነ የውሸት ትርጉም ወይም ፍቺ ይኖረናል፡፡

ውሸት ብዙ ጊዜ በቃላት ብቻ የሚገለጽ አይደለም በድርጊትም ጭምር እንጂ  ለምሳሌ ያልተጎዳ አትሌት እግሩን እንደተጎዳ አድርጎ እያነከሰ ከውድድር ወይም ከስልጠና ካቋረጠ ዋሽቷል ማለት ነው፡፡ መረጃን ሆን ብሎ መደበቅ ለምሳሌ የገቢን መጠን በመደበቅ ግብርን ለመቀነስ የሚደረግ ጥረትም ውሸት ነው፡፡ እኛ ሰዎች ውሸትን ለሌሎች ብቻ ሳይሆን ለእራሳችንም እንዋሻለን ለአብነትም ማሳካት የፈለግነውን ነገር በራሳችን በሆነ ምክንያት ካላሳካን ችግሩን በውጪ ኣካል በማሳበብ (Externalize) ለራሳችን ውሸት እንነግራለን፡፡ እንደ ዲፓውሎ እና ሌሎችም ምሁራን መሰረት ሶስት  የውሸት ዓይነቶች አሉ፡፡ የመጀመሪያው outright lie (falsification) ሲሆን በግርድፉ አማርኛ ፍጹም ውሸት የሚባለው ነው ይህም ውሸት ተናጋሪዎች ከእውነታው ፍጹም ተቃራኒ የሆነ መረጃን ወይም መልዕክት ይናገራሉ ወይም ያስተላልፋሉ፡፡ ሁለተኛው Exaggeration ወይም ማጋነን ሲሆን በዚህም ውሸት ተናጋሪዎች እውነታውን በማጋነን ያቀርባሉ ለምሳሌ ቀጠሮ ላይ አርፎዶ የሚመጣ ተቀጣሪ የመንገዱን መዘጋጋት ከዕውነታው በተጋነነ መልኩ ሊያቀርብ ይችላል፡፡ ሶስተኛው የውሸት ዓይነት subtle lie ሲሆን በዚህም የሚነገረው የውሸት ዓይነት ጥቂት ሆኖ ከብዙ እውነታዎች ጋር በማቅረብ ሰዎችን ለማማሳት የምንጠቀምበት ነው፡፡

ለምን እንዋሻለን ?

ሀ. ግላዊ ጥቅም ለማግኘት፡–  ለምሳሌ ለስራ ስንወዳደር ቃለ መጠየቅ ላይ የተሻለ ደመወዝ እንዲከፈለን አሁን የሚከፈለንን የደመወዝ መጠን ከፍ አድርገን እንናገራለን፡፡

ለ.ቅጣትን ለማስቀረት፡– ህፃናት በወላጆቻቸው እንዳይቀጡ ያጠፉትን ነገር አይናገሩም ወይም አልሰራንም ይላሉ፡፡

ሐ. ሌሎች ስለኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ፡- ሰዎች ስለኛ ጥሩ የሆነ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ ያልሆነውን ሆንን፣ ያላደረግነውን አደረግን ብለን እንናገራለን፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የውሸት ዓይነቶች  በእኛ ዙሪያ ያጠነጠኑ እና  እራሳችንን ለመጥቀም የታለሙ  (self oriented) ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ለሌላ ሰው  ተብለው የሚዋሹ ውሸቶችም አሉ ለምሳሌ፡-

ሀ. ሌሎች ሰዎችን ለመጥቀም፡– እናት ልጇን ከፍርድ ቤት ቅጣት ለመጠበቅ ስትል ወንጀሉ በተፈፀመበት ሰዓት ልጄ እቤት ነው ብላ ልትመሰክር ትችላለች፡፡

ለ. ሰዎች ለማህበራዊ ግንኙነት ሲባልም ይዋሻሉ፡– ጎረቤት እራት ተጋብዘን እዚህ ግባ የማይባለውን  ምግብ ጣት ያስቆረጥማል ብለን የምንወጣው ቀጣይ የሚኖረንን ግንኙነት ከግምት ውስጥ በማሰገባት ነው፡፡

ሐ. ሰዎችን ለመጉዳት እንዋሻለን :- ይህ ደግሞ በሌሎች እንዲቀጡ ባልሰሩት ነገር ላይ በሀሰት በመመስከር የሚደረግ ውሸት ነው ፡፡

ሰዎች እንደሁኔታው ዓይነት ውሸቶችን ይዋሻሉ ለምሳሌ #ሮቢንሰን ባጠናው ጥናት ላይ ስራ ለማግኘት ተብሎ ቃለ ምልልስ ላይ የሚዋሽ ውሸትን #83% የሚሆኑ የጥናት ተሳታፊዎች የነበሩት የኮሌጅ ተማሪዎች እንደ ውሸት አይቆጥሩትም፡፡
#ሮዋት ባጠናው ጥናት ደግሞ #40% የሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ወደፊት የፍቅር አጋር ይሆናል ብለው ላሰቡት ሰው በመጀመሪያ ግንኙነት ላይ እንደሚዋሹ አረጋግጠዋል፡፡
ሆኖም ግን ምን ያህል የሚሆነው የተሳካ የፍቅር ግንኙነት ኖሮት እንደቀጠለ ጥናቱ የሚለው ነገር ባይኖርም ከላይ በተቀስነው የውሸት ዓይነት ማለትም ሰዎች ስለ እኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ለማድረግ በሚዋሽ ውሸት ፍፃሜው ያማረ የፍቅር ግንኙነት ሊኖረን አይችልም፡፡

ሌላው በጥናቱ ላይ የተመለከተው ነጥብ ጾታን በተመለከተ የታየ ልዩነት የለም ይህም ማለት ሁለቱም ወንዶችም ሴቶችም በእኩል መጠን ይዋሻሉ፡፡ በእኛስ ሀገር የትኛው የበለጠ ይዋሻል?? #ወንድ ወይስ #ሴት?? መልሱን ለእናንተ ተውኩት፡፡ ተጨማሪ በሌሎች ጥናቶች ላይ እንደተመለከተው ተጫዋች (ማህበራዊ) (Extraverts) ግላዊ (Introvert) ከሆኑት በበለጠ ውሸት እንደሚያዋሹ አመልክተዋል፡፡


ቀጣዩ ክፍል ነገ ይቀጥላል ...... ያላችሁን ጥናቄና አስተያየት በ Comment አሳውቁን
በቁምላቸው ደርሶ
@Psychoet
1.5K viewsedited  17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-14 21:36:23 እንደምን አላችሁ፣ በጣም የምትጠሉትን የሰው ባህሪ Comment ላይ ጻፉልን? ብዙ ሰው የጻፈው ባህሪ ላይ ሥነልቦናዊ ማብራሪያ እናቀርባለን፡፡
2.1K viewsedited  18:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 22:38:25 እንደምን አላችሁ፣
በጣም የምትጠሉትን የሰው ባህሪ Comment ላይ ጻፉልን?

ብዙ ሰው የጻፈው ባህሪ ላይ ሥነልቦናዊ ማብራሪያ እናቀርባለን፡፡
2.5K views19:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-13 06:25:20
የትብብር ጥያቄ!

ከላይ የምትመለከቱት ኢትዮጲያዊ ሞዴል በአለምአቀፍ ደረጃ በሞዴሊንግ እየተወዳደረ የሚገኝ ሲኾን በSocial media እየገባችሁ ድምጻችሁን እንድትሰጡት በአክብሮት ይጠይቃል፡፡
2.8K views03:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-11 17:07:00
አደገኛው ስብእና/ Narcissism

ለትዳር፣ ለጓደኝነትና አብሮ ለመስራት ስንመርጣቸው አብዝተን ልንጠነቀቃቸው የሚገባ አስቸጋሪ ማንነት ያላቸው ሰዎች።

ሁል ጊዜ ጥፋተኛ እንደሆናችሁ እንድታስቡ የሚያደርጉትን። ለሚሰጧችሁ መጥፎ ምላሽ ተጠያቂው/ዋ አንተ/አንቺ ነሽ የሚሉትን።

የእነሱን ችግር እንጂ ፈፅሞ የእናንተን ማዳመጥና መረዳት የማይፈልጉትን።

ለጥፋታቸው ሀላፊነት መውሰድ የማይፈልጉ፣ ሁል ጊዜ ትክክል ነኝ ብለው የሚያስቡና ለተፈጠረው ችግር ሁሉ ምክንያቱ እናንተ እንደሆናችሁ እንዲሰማችሁ የሚያደርጉትን።

ጉራቸው ከልክ ያለፈ። ታላቅነታቸውን፣ ችሎታቸውን፣ ተፈላጊነታቸውን እና የበላይነታቸውን ሁሌ የሚናገሩትን። ከእናንተ የወሰዱትን ሀሳብ ጭምር የራሳቸው አድርገው የሚነግሯችሁን።

የሰውን ትኩረት ለመሳብ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የለም። በእያንዳንዱ ንግግራቸው እኔ....እኔ....እኔ የሚሉትን።

ለሌላ ሰው ችሎታ እውቅና የማይሰጡና የሚቀብሩትን።

ሌሎችን በጣም የሚያሳንሱ። የእነሱ ትልቅነት የሚጎላው የሌላውን ውድቀት፣ ድክመትና አለመሳካት ሲያወሩ የሚመስላቸውን።

ፈፅሞ አክብሮት የላቸውም። ተሳስቻለሁ....ይቅርታ የሚባል ነገር አይታሰብም። ለጥፋታቸው ሌላውን ተጠያቂ በማድረግ የሚያሸማቅቁትን።

እነሱ የሚፈልጉትን ሀሳብ እንድትቀበሉና በነሱ ቁጥጥር ስር እንድትሆኑ የሚያደርጉትን።

ምንም አይነት ፍቅርና ርህራሄ የሌላቸውን።

ክፋታቸውን ነቅታችሁ ስትርቋቸው ስማችሁን የሚያጠፉ። ሚስጥርና ድክመታችሁን ለሰው የሚያወሩተን። በሚችሉት ሁሉ ሊጎዷችሁ የሚሞክሩትን።

ይህንን ካነበቡ በኋላ ግንኙነቶችዎን ደግመው ይመርምሩ። ለሌሎችም እንዲጠቅም ሼር ያድርጉ

በመአዛ መንክር - ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት

@Psychoet
3.3K views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 21:17:10 የመወያያ ጥያቄ?

➊እልህ አወንታዊ ወይስ አሉታዊ ስሜት ነው? ጠቃሚ ነው ወይስ ጎጂ ስሜት(ባህሪ)?

ሀሳባችሁን አጋሩን?
3.7K views18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 07:33:33
#መልካም_የሀምሌ_ወር_ይኹንላችሁ!

ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ በኹሉም አካባቢዎች ሰላምን የምንሰማበት ፣ ፍትህን የምናይበት ይሁንልን ፡፡

ከአንድ ወር እረፍት በኀላ ተመልሰናል። ቆሞ የነበረው የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት የማሕበራዊ ሚዲያ ትምህርታችን ከዛሬ ጀምሮ በዐዲስ መልክ ይቀጥላል ፡፡

ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ።
Telegram : t.me/psychoet
Group : t.me/ethiodiscussion
Facebook : fb.com/psychologyabc

መልዕክቱን #Share #Like በማረግ ለሌሎችም እናጋራ
4.1K viewsedited  04:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 08:01:26 ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ pinned «ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች፣ በቅርቡ በተለያዩ የሕይወት ጉዳዮች ላይ የምንወያይበትና የተለያዩ አማካሪ ባለሙያዎች የሚካተቱበት የቴሌግራም ግሩፕ ስለከፈትን ማንኛውም የሕይወት ጥያቄ ያላችሁ ፣ ምክር የምትፈልጉ ይህን ግሩፕ በመቀላቀልና ጓደኞቻችሁንም በመጋበዝ ልታገኙን ትችላላችሁ፡፡ ከሥነልቡና / Psychology / አንጻር እንድንጽፍላችሁ የምትፈልጉትን ርዕስ በ comment አሳውቁን! @ethiodiscussion»
05:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 08:00:01 ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች፣

በቅርቡ በተለያዩ የሕይወት ጉዳዮች ላይ የምንወያይበትና የተለያዩ አማካሪ ባለሙያዎች የሚካተቱበት የቴሌግራም ግሩፕ ስለከፈትን ማንኛውም የሕይወት ጥያቄ ያላችሁ ፣ ምክር የምትፈልጉ ይህን ግሩፕ በመቀላቀልና ጓደኞቻችሁንም በመጋበዝ ልታገኙን ትችላላችሁ፡፡
ከሥነልቡና / Psychology / አንጻር እንድንጽፍላችሁ የምትፈልጉትን ርዕስ በ comment አሳውቁን!
@ethiodiscussion
3.3K viewsedited  05:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ