2022-11-08 15:26:59
#ይሉኝታ
እጅግ ጠቃሚ ጽሑፍ ነዉ ። በደንብ ይነበብ
#ይሉኝታ_ምንድን_ነው?
ይሉኝታ ሰዎች ምን ይሉኛል በሚል ሰበብ፤ የራስን ፍላጎት ገትቶ ሌሎችን ለማስደሰት መጣር፤ ሌሎችን ማስቀደም ማለት ነው፡፡ ይሉኝታ የሚያጠቃቸው ሰዎች ከሚጠበቅባቸው ኃላፊነት እና ግዴታ በላይ የሌሎችን ጉዳይ ለመፈጸምና ለማስፈጸም ብዙ ርቀት ይጓዛሉ፡፡ ይሉኝታ የራሳቸንን ስራና አጀንዳ ወደ ጎን አድርገን ፤ ፍላጎታችንና እና ምርጫችን ተጭነን ሌሎችን ለማስደሰት የመፈለግ ውጤት ነው፡፡
#የይሉኝታ_መንስኤዎች
✿ከመጠን በላይ የሆነ የሌሎችን ሰዎች ተቀባይነትና ትኩረት ለማግኘት መሻት
✿በራስ መተማመን ማነስ
✿ሌሎች ስለእኛ የሚያስቡት ጥሩ ብቻ እንዲሆን መጨነቅ፡-ስለራሳችን ጥሩነት የሚሰማን ሌሎች በሚሰጡን አስተያየት እና ማሞካሸት ከሆነ
✿የውስጥ መረጋጋት ከሌለን
✿አስተዳደግ፡- ያደግንበት ቤተሰብ ሰዎችን ማስደሰት እንደ ትልቅ መርህ የሚያይ ከነበረ፤ ወይም ደግሞ ቤተሰባችን ውስጥ በረባ ባልረባው የሚቆጣ ሰው ከነበረና ያንን ሰው ለማስደሰት ፍላጎታችንን እየተጫንን ያደግን ከሆነ
✿ያደግንበት ማኅበረሰብ ወግና ልማድ፡- በማኅበረሰባችን በማንኛውም መንገድ ቢሆን በመረዳዳት፤ ያለንን ለሰዎች በማከፈልና “እሺ ባይነትን” እንደ መልካም ባህሪያት መውሰድና ግለኝነትንና እምቢ ባይነትን ደግሞ እንደ እኩይ ባህሪይ የመውሰድ ልማድ
#ይሉኝታን_ለመቀነስ_የሚረዱ_መንገዶች
✿ለሰዎች መልካም በመሆንና በይሉኝታ መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት
✿ለምናደርገው ነገር ከስሜት ይልቅ ምክንያታዊነትን ማስቀደም፡፡ ለምንድን ነው ይህን ጉዳይ የምፈጽመው? ሰው ምንይለኛል ብየ ስለፈራሁ? ወይስ ስለሚያስደስተኝ? ወይስ ኃላፊነት ስለሚሰማኝ?
✿በማድረጋችን፤ ወይም በመፈጸማችን ቆይተን የምንጸጸትበትን ጉዳይ ከማድረግ መቆጠብን መልመድ
✿አስፈላጊ ሲሆን “አይሆንም” ማለትን ወይም ደግሞ “ላስብበት” ማለትን መልመድ
✿በራስ መተማመንን ሊያዳብሩ የሚችሉ የህይወት ክህሎቶችን መለማመድ
✿ከሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ጤናማ ወሰን እንዲኖረን መጣር
✿ለራሳችን ክብር መስጠት፡- ሰዎች ስለኛ ምንም ቢያስቡ፤ በማንነታችን ላይ ሊያመጣው የሚችለው ተጽእኖ ብዙ እንዳልሆነ ለራሳችን መንገር
✿ያደግንባቸውንና ከማኅበረሰብ ያገኘናቸውን ልምዶች በህይወታችን ያመጡልን በጎና መጥፎ ጎን መከለስ፤ማስተዋል
zepsychology
ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ለሌሎች ያጋሩ t.me/Psychoet
526 views12:26