Get Mystery Box with random crypto!

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂

የቴሌግራም ቻናል አርማ psychoet — ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
የቴሌግራም ቻናል አርማ psychoet — ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
የሰርጥ አድራሻ: @psychoet
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.21K
የሰርጥ መግለጫ

| እውነት | ፍትህ | ፍቅር | ✔ሥነ ልቡና |
የተለወጠ ግለሰብ አለም ይለውጣል!
የተለያዩ የስነልቦናና የላቀ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የተሰሩ video ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናሌን ይከታተሉ
"የማወቅና የመለወጥ ሰአት አሁን ነው "
https://www.youtube.com/user/TheNahusenai
Facebook አድራሻዬ Fb.com/psychologyabc

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-02-19 13:07:35
@psychoet
887 views10:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-17 19:34:02 አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2015ዓ.ም. በማታ መርሃግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አመልካቾችን ይጋብዛል
በዚህም መሰረት አመልካቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል
1. በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ$ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር ማቅረብ
2. በ12ኛ ክፍል ውጤት የምታመለክቱ አመልካቾች ከ2010-2015ዓ.ም. ድረስ ብቻ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን የምታሟሉ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ
3. ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ከ2010-2014ዓ.ም. በተለያየ ምክንያት አቋርጣችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ
4. ለዲፕሎማ ወይም ደረጃ 4 አመልካቾች በ2015ዓ.ም. ቅበላ አይኖረንም
ማሳሰቢያ፡-
1. የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲዉ ድረገጽ (https:\\portal.aau.edu.et) መሙላት
2. ከማመልከቻ ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሞባይል CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም በቅርንጫፍ አማካኝነት በ242424 አጭር ኮድ ክፍያ መፈጸም
3. ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደማመለከቻ ፎርሙ በመመለስ በፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን የወጪ መጋራት ያጠናቀቁበትን ሰነድ መላክ፤
4. ምዝገባዉ ካከናወኑ በኋላ የትምህርት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ቢሮ ቁጥር 203 ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡
5. የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
6. በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ የመረጣችሁትን ትምህርት ክፍል የምታገኙት 12ኛ ክፍል ጨርሰው ያመለከቱ ከተመደቡ በኋላ በሚተርፉ ቦታዎች ላይ ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
የምዝገባ ቀን፡ ከየካቲት 10 እስከ ከየካቲት 16 2015ዓ.ም
የምዝገባ ቦታ ፡ በሬጅስትራር ህንፃ ቢሮ ቁጥር 203
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር
265 views16:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 20:18:48 በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሂዩማኒቲስ፣ ቋንቋዎች ጥናት፣ ጋዜጠኛነትና ኮሙኒኬሽን ኮሌጅ፣ ማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ እና ሥነጥበባት ኮሌጅ ለ2015 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር
ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አመልካቾችን ይጋብዛል
• Multimedia
• Public Relations and Strategic Communication
• English Language and Literature
• Modern European Languages: Portuguese and Italian, Spanish and German
• Arabic Language and Communication
• French Language and Professional Skills
• Linguistics
• Ethiopian Sign Language and Deaf Culture
• Ethiopian Sign Language and Interpreting
• Folklore (Culture Studies)
• Oromoo Language and Communication)
• Tigrigna Language and Literature
• Archaeology and Heritage Management
• History
• Philosophy
• Social Anthropology
• Sociology
• Music
• Theater
• Fine Arts

የቅበላ መስፈርቶች፦
• አመልካቾች በ12ኛ ክፍል ውጤት በ2014ዓ.ም. ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን የሚያሟሉ እና ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ የሚችሉ
• ከላይ በተጠቀሱት መስኮች ተምረው ሃገራቸው ለማገልገል ፍላጎትና ዝንባሌ ያላቸው፣
• ማንኛውም የቅድመ-ምረቃ መርሃ ግብር ተማሪ እንዲያቀርብ የሚጠየቀውን የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
• እንደ አስፈላጊነቱ የትምህርት ክፍሎች የሚያዘጋጁትን ፈተና ለመቀበል ዝግጁ የሆኑ፣
• በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡ ፍሬሽ ማን ኮርሶችን በሚመደቡበት የትምህርት ክፍል ውስጥ ሆነው ለመማር ፈቃደኛ የሆኑ፣

ማሳሰቢያ፡-
1. የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲዉ ድረገጽ (https:\\portal.aau.edu.et) መሙላት
2. ከማመልከቻ ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 300/ሶስት መቶ ሃምሳ/ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሞባይል CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም በቅርንጫፍ አማካኝነት በ242424 አጭር ኮድ ክፍያ መፈጸም
3. ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመለከቻ ፎርሙ በመመለስ በፒዲኤፍ (PDF)ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን የወጪ መጋራትያጠናቀቁበትን ሰነድ መላክ፤
4. ምዝገባዉ ካከናወኑ በኋላ የትምህርት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ቢሮ ቁጥር 203 ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡
5. የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡


የምዝገባ ቀን፡ ከየካቲት 10 እስከ የካቲት16 2015ዓ.ም
የምዝገባ ቦታ ፡ በሬጅስትራር ህንፃ ቢሮ ቁጥር 203

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር @psychoet #Share
913 viewsedited  17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-03 11:29:07
በሕይወቴ ከገጠሙኝ መልካም ሰዎች አንዱ ነው፥ ወንድዬ ዓሊ

ነገ ቅዳሜ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ በተለያዪ የሥነ ጽሑፍ ዘርፎች ላበረከተው የላቀ አስተዋጽዖ ልዩ የምስጋናና የዕውቅና መረሐ ግብር ይካሄዳል፡፡ በተጨማሪም የበኩር ሥራው "ወፌ ቆመች" በዳግም ኅትመት ተመርቃ ለአንባቢ ትቀረርባለች። ኹላችሁም ተጋብዛችኋል፡፡
መግቢያ - በነፃ ቦታ - በአገር ፍቅር ቲአትር
ቅዳሜ ጥር 27 ከጠዋቱ 3:00 - 6:00
982 views08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-30 22:06:41
ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ በተለያዪ የሥነ ጽሑፍ ዘርፎች የላቀ አስተዋጽዖ ያበረከተውን የወንድዬ ዓሊን ልዩ የምስጋናና የዕውቅና መረሐ ግብር ኹላችሁም ተጋብዛችኋል፡፡

በዕለቱ የደራሲው የበኩር ሥራ የኾነችው "ወፌ ቆመች" በዳግም ኅትመት ተመርቃ ለአንባቢ ትቀርባለች፡፡

መግቢያ: በነፃ - ኹላችሁም ተጋብዛችኋል
ቦታ - በአገር ፍቅር ቲአትር
ቅዳሜ ጥር 27 ከጠዋቱ 3:00 - 6:00
1.5K views19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-26 17:50:31
ምን ታስባላችሁ?
3.1K viewsedited  14:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-19 10:31:03
በአሉን ለምታከብሩ ለመላ ኦርቶዶክስና ካቶሊክ ቤተሰቦች፣ እንኳን አደረሳችሁ!
@psychoet
567 views07:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-16 09:32:28 ፩. ትናንትን የምታርመውም ኾነ የምታድሰው ዛሬ ላይ ኾነህ ነው፡፡
፪. ነገ ውብ የምትኾነው ዛሬን ስትንከባከባት ነው፡፡
፫. ነገ ከተስፋነቷ በስተቀር ያንተ አይደለችም፡፡

ተስፋህ እውን ኾኖ የምታገኛት ግን ዛሬን በተጠቀምክባት ልክ ነው፡፡ ስለዚህ፣ ትዝታህ ላይ ተቀምጠህ በተስፋ ጋሪ ተሳፍረህ ዛሬን በደንብ ኑር።

ሜሎሪና
562 views06:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-16 00:33:00 #መጀመር
ማንኛውም ነገር ካልጀመርነው ይከብዳል ስንጀምረው ተግዳሮት አለዉ ደጋግመን ስናደርገዉ ቀላል ነዉ።
ሳንጀምር ይከብዳል አንበል እንደሚከብድ በምን አወቅን?
1. እንጀምረው
2. እንቀጥለው
3. እንጨርሰው ።
#ሁሌ ከሁዋላ የሚሰበረው እስክንለምድ ነው!!!
ሁንዴ

ይህን መልዕክት ለምትወዱአቸው #5 ታታሪ ጓደኞቻችሁ Forward አርጉልኝ !
#Join #Share
@psychoet
@psychoet
@psychoet
175 views21:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-11 04:49:04 በራስ መተማመንን ማጎልበት
Developing Self Confidence

በራስ መተማመን ማለት ሰው ባለው ችሎታ፣ አካላዊ ውበትና ሁለንተናዊ ማንነት አለመፍራት እና ሚዛናዊ በሆነ መልኩ ራስን መቀበል ማለት ነው፡፡ ትእቢት ፣ ትምክህት፣ ያልተገባ አውቃለሁ ባይነት እና ከመጠን ያለፈ ድፍረት በራስ መተማመን አይደለም።

በራስ መተማመንን የሚያጎለብቱ ብልሀቶች

ራስዎን ከሌሎች ጋር አለማነፃፀር።

ያለዎትን ክህሎት እና ድክመት መለየት።

የአካላዊ ገፅታ ውበትን መጠበቅ ደግሞም የሰውን ትኩረት ከልክ ባለፈ ሁኔታ የሚስቡ ጌጣጌጦችንና ሜካፖችን አለመጠቀም።

ጥሩ እና ምቹ አለባበስ መልበስ።

ነቃና ቀልጠፍ ብሎ መራመድ ።

በሰው ፊት ሀሳብዎን መግለፅ ሲኖርብዎ ቀድመው በቂ ዝግጅት ማድረግ።

መልካም በሆነ የህይወት እንቅስቃሴ የበኩልዎን አስተዋፅዖ ማድርግ።

ጥሩ የሚሰሩ ሰዎችን ማድነቅ/ ማበረታታት።

ሰዎች የተቃወሙዎት ወይም የናቁዎት ሲመስልዎ በእርጋታ ምላሽ መስጠት።

ሰዎች ስህተትዎን ሲነግሩዎ በቀና ማየት(ስለሚጠሉኝ ነው አለማለት)።

እርዳታ ሲያስፈልግዎ ያለፍርሀት መጠይቅ።

ሰአት ማክበር።

በመአዛ መንክር - ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት
YouTube: Dink Mikir

#Like #Share በማረግ ለሌሎችም እናስተምር

ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@psychoet
604 viewsedited  01:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ