Get Mystery Box with random crypto!

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂

የቴሌግራም ቻናል አርማ psychoet — ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
የቴሌግራም ቻናል አርማ psychoet — ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
የሰርጥ አድራሻ: @psychoet
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.21K
የሰርጥ መግለጫ

| እውነት | ፍትህ | ፍቅር | ✔ሥነ ልቡና |
የተለወጠ ግለሰብ አለም ይለውጣል!
የተለያዩ የስነልቦናና የላቀ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የተሰሩ video ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናሌን ይከታተሉ
"የማወቅና የመለወጥ ሰአት አሁን ነው "
https://www.youtube.com/user/TheNahusenai
Facebook አድራሻዬ Fb.com/psychologyabc

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-03-24 18:36:14 ስለ ለውጥ ካሰባችሁ ይህ ቪዲዮን እንድታዩ እመክራለሁ
1. ለምን ብዙዎቻችን መለወጥ እየፈለግን ያቅተናል
2. በአጭር ጊዜ ለመለወጥስ ማድረግ ያለብን ነገሮች ምንድናቸው?*


932 views15:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 18:34:45 ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ pinned «ተቋርጦ የነበረው የዩቲዩብ ፕሮግራማችን በእናንተ ጥያቄ ዳግም ጀምሯል

»
15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 18:24:46 ተቋርጦ የነበረው የዩቲዩብ ፕሮግራማችን በእናንተ ጥያቄ ዳግም ጀምሯል

901 viewsedited  15:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 10:24:03 መልካም ቀን ! #Share_it
#ይቅርታ_እንዴት_እንጠይቅ?
t.me/psychoet

ምን ያህሎቻችን ነን ይቅርታ ባለማረግ እና ይቅርታ ባለመጠየቅ ደስታችንን እየቀነስን ያለን ?

ይቅርታ እንዴት እንጠይቃለን በሚለው ዙሪያ ትንሽ ለማለት ዳዳው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ሌላውን ሰው አስቀይመው ወይም ጥፋት አጥፍተው ይጸጸታሉ፡፡ ነገር ግን መጸጸትና ይቅርታ መጠየቅ ይለያያሉ፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ ይቅርታቸውን ከአንገት በላይ ያደርጉና ተበዳዩን አዛኝ መስለው በከንፈር መጠጣ (lips service) ይሸነግሉታል፡፡ አልያም መልሰው እንደሚያጠፉ እርግጠኛ እየሆኑ እንኳን የይስሙላ ይቅርታ ይጠይቃሉ፡፡ ሺህ ግዜ እያጠፋ ከስህተቱ ለማይማር ሰው ይቅርታ ትርጉም የለውም፡፡ እንዲሁም ይቅርታን ለጥፋቱ መሸሸጊያ የመጨረሻ ምሽግ ያደርገዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የሌላውን ሰው ልብ ያደማል፡፡ ይቅርታው በተግባር ለውጥ ስለማይታጀብ ከአፍ አይዘልም፡፡ የዚህ ስሜት በእራሳችን ደርሶ ካላየነው በስተቀር ህመሙ አይሰማንም፡፡ ታዲያ አሳማኝ ይቅርታ እንዴት መጠየቅ ይቻላል?
አንድሪያ ብራንድ የተባለች ሳይኮሎጂስት ከዚህ የሚተሉት ስድስት ነጥቦች ይቅርታን ለመጠየቅ ጠቃሚዎች ናቸው በማለት ትመክራለች፡-

1.ከልብ የመነጨ ይቅርታ መጠየቅ፡- የተበዳይ የመንፈስ ስብራት እኛም በግለሰቡ ቦታ ብንሆን ምን ያህል እንደሚሰማን በማሰብ ከውስጥ በመነጨ ስሜት ይቅርታን መጠየቅ፡፡

2.ስለበደሉት ነገር ዕውቅና መስጠትና ዳግመኛ ላለመበደል ኃላፊነትን መውሰድ፡- ስለአጠፉት ጥፋት እቅጩን መናገር “አውቃለሁ እንዲህ ማድረግ አልነበረብኝም ፤ እኔ በእንተ ቦታ ብሆን ምን ያህል እንደሚሰማኝ እረዳለሁ፡፡ እባክህን ይቅር በለኝ!” በማለት ጥፍትን ለማረም ዝግጁ መሆንን ማሳየት፡፡

3.ዳግመኛ ላለመበደል ቁርጠኛ መሆን፡- የበደላችሁት ሰው ከጥፋታችሁ እንደተማራችሁ እንዲያውቅ ማድረግ፡፡ ይህንንም ዕለት ተዕለት በሚደረግ አግባቦትና ተግባር በግልጽ ማሳየትና ምንም ለውጥ ያላሳየን እንደሆን ወዳጆቻችን በግልጽ ቅሬታቸውን እንዲገልጹ ማድረግ፡፡

4.ይቅርታ የምትጠይቁት ሰው ለእናንተ ምን ያህል እንደሆነ መግለጽ፡- ከበደላችሁት ሰው ጋር ያላችሁ ግንኙነት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ በማድነቅ መግለጽ፡፡

5.ይቅርታ መጠየቅ፡- ይቅርታ መጠየቅ በሁለታችው መሃል ስላለው ግንኙነት አስፈላጊነት የሚያስረዳ ሲሆን፤ በምላሹ ተበዳይ ይቅርታ ለማድረግ ጊዜን ይፈልግ ይሆናል እንደ ጉዳቱ መጠን፡፡ ምክንያቱም አንዳንድ ሁኔታዎች ይቅር የሚባሉ ነገር ግን በደሉ ሊረሳ የማይችል ስለሚሆን፡፡ “Forgiven but never forgotten” እንዲል የባህር ማዶ ሰው፡፡

6.ለውጥን በተግባር ማሳየት፡- “የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ” እንደሚባለው በአገረኛው ዘይቤ፤ ያጠፉትን ጥፋት ዳግመኛ ላለመተግበር ለእራስ ቃል ታማኝ መሆን፡፡ ይህም የአእምሮ ደውል በመውስጣችን በማቃጨል “እንዲህ ላለማድረግ እኮ እንዲህ ብለህ ቃል ገብተሃል” በተግባር ቃልህን አሳይ በማለት፡፡

በደል ያቆስላል ልብንም ይሰብራል ፤ ይቅርታ ግን ቁስልን ይሽራል የተሰበረ ልብንም ይጠግናል፡፡ ይቅርታ እንታረቅ! መልካም ጊዜ!

(አንቶኒዮ ሙላቱ)
zepsychologist

t.me/psychoet
በፍትህ በፍቅርና በይቅርታ የመኖር ዘመን ይሁንልን ፡፡
235 viewsedited  07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-06 22:16:06 የአእምሮ ጤንነት ለሰው ልጅ ወሳኝ የሆነ የሕይወት ማገር ነው፡፡ ሰው እንደ ሰው ፣ ህዝብ እንደህዝብ ፣ ሀገርም እንደሀገር እንዲቀጥልና እንዲያድግ ዋናውን ሚና የሚጫወተው የአዕምሮ ጤንነት ነው ፡፡ በተለይም አሁን ያለንበት ጊዜ ደግሞ ይህ የአእምሮ ጤንነት በመንግስትም ሆነ በዘርፉ ባለሙያዎች ከፍተኛ ትኩረት ተሰቶበት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ከተለያዩ የሥነልቦና ቀውሶች ለመውጣት ወይንም የአእምሮ ጤንነታችንን ጠብቀን ለመቆየት የሚያስችሉን 5 ተግባራትን እንመለከታለን፡፡

አካላዊ ጤንነትንና ንቃትን ማዳበር

አዳዲስ ክህሎቶችን መማር

ከሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት አጥብቆ መያዝ

ከነገና ከትናንት ይልቅ በአሁን ባለው ነገር ላይ ትኩረት መስጠት

አወንታዊ ነገሮችን ማሰብ

ምንጭ : Mental wellbeing & my personal reflection
መልካም ቀን ይሁንላችሁ!

t.me/psychoet
719 viewsedited  19:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 14:17:37 ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ pinned a photo
11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-02 09:43:55
የመጨረሻ ዙር LIT (Life Improvement Training) ስልጠና (13ኛ ዙር) የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት ስልጠና በዚህ ሳምንትየካቲት 25 ይጀምራል!
ስልጠናው ላለፉት 4 አመታት ሲሰጥ የነበረና የብዙ መቶዎችን የሕይወት መንገድ ያገዘ ስልጠና የመጨረሻዉ ዙር ነው፡፡
የሕይወት አላማን መረዳትና ራስን ማግኘት
ተግባቦትና በራስ መተማመን ስኬታማ የሕይወት ዕቅድ አወጣጥና የጊዜ አጠቃቀም
የስሜት ብልህነት
ፍርሀት፣ ድብርትንና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣት
ሳይኮሎጂ/ሥነልቦና ምንድነው?
የሥነልቡና ቀውስ ምንድነው? መፍትሄዋቹስ ምንድናቸው?
ለሰልጣኞቻችን የግል የማማከር አገልግሎት እናመቻቻለን!
ስልጠናው ለ5 ሳምንት የሚቆይ ሲኾን በሳምንት አንድ ጊዜ ብቻ ይሰጣል፡፡ ያሉን ፈረቃዎች
➊ ቅዳሜ 3-6 ➋ ቅዳሜ 8-11
➌ እሑድ 3-6 ➍ እሑድ 8-11
ባሉን ውስን ቦታዎች በተመቻችሁ ፈረቃ ቀድመው ይመዝገቡ፡፡ በዚህ ሳምንት ይጀምራል ለበለጠ መረጃ በ 0912664084 ይደውሉ፡፡
ክፍያ :- ( የመመዝገቢያ፣ የሰርተፊኬት ፣ የ15 ሰአት የስልጠና ጨምሮ ) - 1000 ብር ነው
አድራሻ:- 4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሀን ንግድ ማዕከል ቢሮ 219 እና 221
ለመለወጥ መወሰን እንጂ ስበብ ማቅረብ አይጠቅምም!!!
ስልጠናውን ቢወስዱ ይጠቀማሉ ለሚሏቸው ሌሎች ወዳጅዎ #Share ያድርጉ
1.1K views06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 08:29:06
ስልጠናው ላለፉት 4 አመታት ሲሰጥ የነበረና የብዙ መቶዎችን የሕይወት መንገድ ያገዘ ስልጠና #የመጨረሻዉ ዙር ነው፡፡
818 viewsedited  05:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-22 06:30:00
የመጨረሻ ዙር LIT (Life Improvement Training) ስልጠና (13ኛ ዙር) የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት ስልጠና በዚህ ሳምንት ይጀምራል!

ስልጠናው ላለፉት 4 አመታት ሲሰጥ የነበረና የብዙ መቶዎችን የሕይወት መንገድ ያገዘ ስልጠና የመጨረሻዉ ዙር ነው፡፡

የሕይወት አላማን መረዳትና ራስን ማግኘት
ተግባቦትና በራስ መተማመን ስኬታማ የሕይወት ዕቅድ አወጣጥና የጊዜ አጠቃቀም
የስሜት ብልህነት
ፍርሀት፣ ድብርትንና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣት
ሳይኮሎጂ/ሥነልቦና ምንድነው?
የሥነልቡና ቀውስ ምንድነው? መፍትሄዋቹስ ምንድናቸው?

ለሰልጣኞቻችን የግል የማማከር አገልግሎት እናመቻቻለን!

ስልጠናው ለ5 ሳምንት የሚቆይ ሲኾን በሳምንት አንድ ጊዜ ብቻ ይሰጣል፡፡ ያሉን ፈረቃዎች
➊ ቅዳሜ 3-6 ➋ ቅዳሜ 8-11
➌ እሑድ 3-6 ➍ እሑድ 8-11

ባሉን ውስን ቦታዎች በተመቻችሁ ፈረቃ ቀድመው ይመዝገቡ፡፡ በዚህ ሳምንት ይጀምራል ለበለጠ መረጃ በ 0912664084 ይደውሉ፡፡
ክፍያ :- ( የመመዝገቢያ፣ የሻይ ቡና ሰአት፣ የሰርተፊኬት ፣ የ15 ሰአት የስልጠና ጨምሮ ) - 1000 ብር ነው
አድራሻ:- 4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሀን ንግድ ማዕከል ቢሮ 219 እና 221
ለመለወጥ መወሰን እንጂ ስበብ ማቅረብ አይጠቅምም!!!
ስልጠናውን ቢወስዱ ይጠቀማሉ ለሚሏቸው ሌሎች ወዳጅዎ #Share ያድርጉ
@psychoet
1.5K views03:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-21 20:03:53 #ሃያ አንዱ ማኅበራዊ ሕግጋት
መልዕክቱን አንብበው ሲጨርሱ #Share ያድርጉት

(Social Rules ተብለው የተዘረዘሩ የማኅበራዊ ሕይወት ሕግጋትን ስመለከት ለኛስ አትጠቅምም ወይ ብዬ ነው ወዲህ ማምጣቴ)
==================
1. ይሰለቹሃል
አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ!

2. 'ሼም ነው' ነው
የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ!

3. አይባልም
"... እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..." አይባልም።

4. ክፈል
አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ።

5. ነውር ነው
ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ።
============

6. አታቋርጥ
ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ። ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው።

7. አታብሽቅ
ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው። ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ።

8. አመሥግን
ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር አመሥግን።
9. ያለስስት አድንቅ
ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል አውራቸው።

10. ክፉ አስተያየትህን ቆጥብ
ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ።
===================

11. ካልሆኑ ጥያቄዎች ታቀብ
ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል። የውጤቱን ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል።

12. ስነ ስርዓት
ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው።

13. ክብር ለሁሉም
ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም።

14. ስልክህን አስቀምጥ
ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው። ከሰው ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው።

15. አድብ
ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው።
==========================

16. ተቆጠብ
ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ።

17. መነጽርህን አውልቅ
ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ። ክብርም ነው!

18. አትሳሳት
በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ።

19. ለስልክ መልዕክት ምላሽ መስጠት
በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው። ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው።

20. ዕቃ መልስ
የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ።

21. አማራጭ ሐሳቦች ሁሌም አሉ
የያዝከውን ሐሳብ ሳትፈራ አውጣው። ሌሎች እንዲወያዩበትና እንዲተቹት ክፍት አድርገው፤ አንተም ሐሳብህም ትጎለብታላችሁ። ነገርህን ደገፉትም አልደገፉት ምንጊዜም ቢሆን ላነሳኸው ሐሳብ ጥሩ ግብዓት አይጠፋም። ልክ አልሆን ወይ እያልክ ወይም ሐሳቤ ያንስ ይሆን ወይ ብለህ አትሸማቀቅ፤ ተሸማቀህ ትቀራለህ!

ሳይኮሎጂ ፔጅን #Like በማድረግ ቤተሰብ ኹኑ

@psychoet
587 views17:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ