Get Mystery Box with random crypto!

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂

የቴሌግራም ቻናል አርማ psychoet — ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
የቴሌግራም ቻናል አርማ psychoet — ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
የሰርጥ አድራሻ: @psychoet
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.21K
የሰርጥ መግለጫ

| እውነት | ፍትህ | ፍቅር | ✔ሥነ ልቡና |
የተለወጠ ግለሰብ አለም ይለውጣል!
የተለያዩ የስነልቦናና የላቀ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የተሰሩ video ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናሌን ይከታተሉ
"የማወቅና የመለወጥ ሰአት አሁን ነው "
https://www.youtube.com/user/TheNahusenai
Facebook አድራሻዬ Fb.com/psychologyabc

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-10-17 21:31:41 በውሳኔ መጽናት መቻል

አንድ ሰው ያለመው ቦታ እንዳይደርስ የሚያቆመው በውሳኔ መጽናት አለመቻል ነው፡፡

ለዚህ ደግሞ ብዙ ምክንያቶች አሉ ለምሳሌ ያህል፡

የወሰንንበት ጉዳይ ያልገባን ከሆነ
ነገሮች እንዳሰብናቸው ካልሆኑ
በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ውሳኔያችንን የሚሸረሽሩ ነገሮች ደጋግመው ሲነግሩን ወዘተ ናቸው፡፡

ታዲያ ምን እናድርግ? መፍትሄ፡

ሁሌም በራሳችን እርግጠኛ መሆን መቻል
ከመወሰናችን በፊት ደጋግመን ማሰብ፣ አማራጮችን መመልከት
ምን ለውጦችንና ጥቅሞችን ልናገኝ እንደምንችል ማሰብ
ልክ እንደ ወሰንን ወደ ድርጊት መግባት፣ ጊዜ አለመውሰድ

ተመስገን አብይ
@psychoet
2.4K views18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-16 13:25:26 መሸበርና መፍራት የነገን ችግር አያስወግድልንም ይልቁኑስ የዛሬን ደስታ ያሳጣናል።

ሕይወት፣ የመዘጋጃና የመኖሪያ ዕድሜ የሌላት፣ ከአፈር ለተሠራ ሰው የተሰጠች ስጦታ ነች ፡፡ የሰው ልጅም ከተፈጠረ ጀምሮ ሕይወትን በውስጡ ለማሰንበት በትግል የሚኖር፣ሲያጣትም እጅግ ጠሊቅ ሐዘን ውስጥ የሚገባ ፍጡር ነው፡፡

ሰዉ የራሱንና የሚወዳቸውን እስትንፋስ ለማቈየት፣ ከሰከንድ እስከ ሰዓታት ከዛሬው እየተበደረ ለማያውቀው ነገ ሲገብር፣ ለማያውቀው ነገ ደስታ ዛሬ ሲያለቅስ፣ ለማያውቀው ነገ ጥጋብ ዛሬ ሲራብ ሲታረዝ፣ ከማያውቀው ነገ ተበድሮ ዛሬ ሲጨነቅ የሚኖርና መኖሩን ሳያውቅ የሚሞት ፍጡር ነው…፡፡

በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡ መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቊጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል፡፡ ሁሌም እንማር፣ ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣ ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡

ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ዐዋቂ ነኝ፣ ትክክል ነኝ፣ እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡ ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡ ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡

ሜሎሪና መፅሀፍ የተወሰደ
3.2K viewsedited  10:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 15:50:48
ወዳጆቼ ኾይ፣ ከጠቀማችሁ ትንሽ ነገር ልበላችሁ

ኹላችንንም ወደዚህች ምድር የላከን ፈጣሪ ነው፡፡ አንዳችንም ወደን ፈቅደንና አስበንበት የመጣን የለንም፡፡ ታዲያ ለምን ይኾን ፈጣሪ ወደዚህች ምድር የላከን? በቃ በልተን ጠጥተን፣ ተምረን ሰርተን ፣ አግብተን ወልደን እንድንሞት ብቻ ነው? ወይስ ሌላ ምክኒያት ኖሮት ይኾን? ቆይ የሕይወት ሩጫችን የት ለመድረስ ነው? ከደረስንስ በኀላ?  የሕይወትስ ትልቁ ነገር ምንድነው?
#ራሳችንን_እንጠይቅ
@psychoet
3.7K views12:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-14 07:20:50 #ማስታወቂያ
የ11 ዙር የሕይወት ክህሎት ስልጠና ጀምሯል!

የሕይወት ክህሎት ስልጠና መሠልጠን ለሚፈልጉ መልካም አጋጣሚ ልምድ ባላቸው የሕይወት ክህሎት አሰልጣኞች እየተሰጠ ነው።

የሕይወት አላማን መረዳትና ራስን ማግኘት
የ2015 ስኬታማ ዕቅድ አወጣጥና የጊዜ አጠቃቀም
የስሜት ብልህነት
ፍርሀትና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣት
ተግባቦትና በራስ መተማመን
ሳይኮሎጂ/ሥነልቦና ምንድነው?
ለሕይወታችን ምን ይፈይደል?
የሥነልቡና ቀውስ ምንድነው? እንዴትስ ያጋጥማል? መፍትሄዋቹስ ምንድናቸው?

ለሰልጣኞቻችን የግል የማማከር አገልግሎት እናመቻቻለን!

ስልጠናው ለ6 ሳምንት የሚቆይ ሲኾን
ቅዳሜ ከሰአት 8-11
ወይም
እሑድ ጠዋት 3-6
በመረጡት ፈረቃ መውሰድ ይችላሉ፡፡

ለመመዝገብ በ 0912664084 ይደውሉ፡፡
t.m/psychoet

የስልጠና አድራሻ:-4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሀን ንግድ ማዕከል ቢሮ 219 እና 221

ለመለወጥ መወሰን እንጂ ስበብ ማቅረብ አይጠቅምም!!!
3.5K viewsedited  04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-13 05:47:35
ጠቃሚ ምክሮች

1. ከአለስፈላጊ ክርክሮች ጭቅጭቆች እና እሰጣገባዎች ራቅ።

2. ራስህን ገንቢ ሃሳብ ከሌላቸው (negative) ሰዎች አርቅ። ምክንያቱም አንተን ራሱ ሳትፈልገዉ እንደነሱ እንድታስብ ትገደድ ይሆናል፡፡

3. መቀበል የምትፈልገውን ስጥ።

4. ገንቢ ያለሆኑ ጎጂ አስታያየቶችን ከመስጠት ተቆጠብ።

5. ለሰዎች ፍቅርና አክብሮት ይኑርህ።

6. ይህ መቼም በእኔ አይደርስም አትበል፣የሕይወትን አቅጣጫ ሁሌም ቢሆን ማወቅ አንችልምና።

7. የመኪና የፊት መስታወት ትልቅ ሆኖ የኋላ መመልከቻውዠ መስታወት ግን ለምን ትንሽ የሆነ ይመስልሃል....ምክንያቱም የፊቱ ካለፈው ይልቅ አስፈላጊ ስለሆነ ነው። ስለዚህም የኀላዉን ሳትዘነጋ በትልቁ የሕይወት መስታወት ወደፊት እያየህ ተጓዝ::

#መልካም_ቀን !
#Share #Like
@Psychoet
515 views02:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 21:24:51
ውሸት አሁን አሁን በማህበረሰባችን ዘንድ ኖርማል እየሆነ የሄደ መጥፎና ጎጂ ልማድ ነው፡፡ ስለ ውሸት ምን ታስባላችሁ?
676 views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-11 05:43:38
#መልካም_የጥቅምት_ወር_ይኹንላችሁ!

ይህ ወር የአዕምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ በኹሉም አካባቢዎች ሰላምን የምንሰማበት ፣ ፍትህን የምናይበት ይሁንልን ፡፡

ከእረፍት በኀላ ተመልሰናል። ቆሞ የነበረው የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት የማሕበራዊ ሚዲያ ትምህርታችን ከዛሬ ጀምሮ በዐዲስ መልክ ይቀጥላል ፡፡

ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ።
Telegram : t.me/psychoet
Facebook : fb.com/psychologyabc

መልዕክቱን #Share #Like በማረግ ለሌሎችም እናጋራ
667 views02:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-10 07:50:51
የአለም የአእምሮ ጤና ቀን
መስከረም 30፣ 2015

የአእምሮ ጤንነትን የሚጠብቁና የሚያሳድጉ 5 ተግባራት
(በናሁሰናይ ፀዳሉ)

የአእምሮ ጤንነት ለሰው ልጅ ወሳኝ የሆነ የሕይወት ማገር ነው፡፡  ሰው እንደ ሰው ፣  ህዝብ እንደህዝብ ፣ ሀገርም እንደሀገር እንዲቀጥልና እንዲያድግ ዋናውን ሚና የሚጫወተው የአዕምሮ ጤንነት ነው ፡፡ በተለይም አሁን ያለንበት ጊዜ ደግሞ ይህ የአእምሮ ጤንነት በመንግስትም ሆነ በዘርፉ ባለሙያዎች ከፍተኛ ትኩረት ተሰቶበት ሊሰራበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ከተለያዩ የሥነልቦና ቀውሶች ለመውጣት ወይንም የአእምሮ ጤንነታችንን ጠብቀን ለመቆየት የሚያስችሉን 5 ተግባራትን እንመለከታለን፡፡

አካላዊ ጤንነትንና ንቃትን ማዳበር

አዳዲስ ክህሎቶችን መማር

ከሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት አጥብቆ መያዝ

ከነገና ከትናንት ይልቅ በአሁን ባለው ነገር ላይ ትኩረት መስጠት

አወንታዊ ነገሮችን ማሰብ

ምንጭ : Mental wellbeing & my personal reflection
መልካም ቀን ይሁንላችሁ!

ጽሑፉ ለናንተ ከጠቀማችሁ ሎችም እንዲጠቀሙበት #Share በማድረግ አካፍሉ! ማካፈል ከዚህ ይጀምራል፡፡
t.me/psychoet
768 views04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-04 07:01:49
የ11 ዙር የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት ስልጠና በዚህ ሳምንት ይጀምራል፡፡ በቀረን ቦታ ይመዝገቡ፡፡

ስለ ሳይኮሎጂ ለማወቅ ለሚፈልጉ እንዲሁም የሕይወት ክህሎት ስልጠና መሠልጠን ለሚፈልጉ መልካም አጋጣሚ ልምድ ባላቸው የሕይወት ክህሎት አሰልጣኞች።

ሳይኮሎጂ/ሥነልቦና ምንድነው?
ለሕይወታችን ምን ይፈይደል?
የሥነልቡና ቀውስ ምንድነው? እንዴትስ ያጋጥማል? መፍትሄዋቹስ ምንድናቸው?
Counseling ምንድነው?
የሕይወት አላማን መረዳትና ራስን ማግኘት
የ2015 ስኬታማ ዕቅድ አወጣጥና የጊዜ አጠቃቀም
የስሜት ብልህነት
ፍርሀትና ጭንቀትን ተቋቁሞ መውጣት
ተግባቦትና በራስ መተማመን


ለሰልጣኞቻችን የግል የማማከር አገልግሎት እናመቻቻለን!

ስልጠናው ለ6 ሳምንት የሚቆይ ሲኾን ቅዳሜ ፣እሑድ በጠዋት ፣ በከሰአትና በማታ ፈረቃ እንዲሁም እሮብ ማታ መከታተል ይችላሉ፡፡

ለበለጠ መረጃ በ 0912664084 ይደውሉ፡፡
ያለን ቦታ ውስን ስለኾነ ቀድመው ይመዝገቡ፡፡
t.me/psychoet

አድራሻ:-4ኪሎ ቱሪስት ሆቴል አጠገብ አዲስ ብርሀን ንግድ ማዕከል ቢሮ 219 እና 221

ለመለወጥ መወሰን እንጂ ስበብ ማቅረብ አይጠቅምም!!!
683 viewsedited  04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-30 20:10:55 ብዙ ሰዎች ህመማቸውን መከፋታቸውን የሚያወሩለት ወዳጅ አጥተው ሶሻል ሚዲያ ላይ ነው ሚገልፁት። እንዲህ አይነት ፖስቶችና መልእክቶች ስታዩ ረጋ ብላችሁ ምላሽ ስጡ። ቀልድ ነው ብላችሁ በምታላግጡበት ሰአት ያ ሰው ወደሞት እየቀረበ ይሆናል።

በተለይ በአፍላው እድሜ በሚገኙ ወጣቶች ዘንድ ራስን ማጥፋት በጣም እየጨመረ ነው።

እባካችሁ ራሴን ላጠፋ ነው ወይም መሮኛል ብሎ ለፖሰተ ሰው ብታቁትም ባታውቁትም አብሮነታችሁን ድጋፋችሁን አሳዩ እንጂ ቀልድ አትቀልዱ። ለቀልድና ጨዋታ ብዙ የተሻለ ቦታ አለ።

በቅርብ የምናቃቸው ሰዎች መሞታቸው ሲገለፅ የአብዛኛው ጓደኞቻቸው ምላሽ "እኔ መች ጠረጠርኩ... ደብሮኛል እያለኝ.. " ምናምንም በሚሉ ፀፀቶች የተሞላ ነው።

በዙርያችሁ ላለ ሠው ሁሉ ትኩረት ስጡ!

ራስን ማጥፋት የቀልድ ርእስ አይደለም!
Tesfa G Neda

--------------------------------------------------------------
በዓመት እስከ 800,000 ሰዎች ራሳቸውን እንደሚያጠፉ የWHO ሪፖርት ያመለክታል፡ ከዚህ ቁጥር በላይ ያሉ ሰዎች ደግሞ ራሳቸውን የማጥፋት ሙከራ ያደርጋሉ ።
እድሜያቸው ከ 15 እስከ 29 ዓመት በሆኑ ወጣቶች ሁለተኛው ከፍተኛ ሞት የሚመዘገብበት ችግር ነው ፡ እንዲሁም 79% ያህሉ በዝቅተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው ሃገራት ላይ የሚስተዋል ነው ። ሰዎች ራሳቸውን ለማጥፋት መርዝ መጠጣት መታነቅ ፣የጦር መሳሪያ መጠቀም፣ በዋናነት ይጠቀማሉ ።

አጋላጭ ሁኔታዎች
-----------------------------------------------------------------
የተለያዩ የአዕምሮ ህመሞች በተለይም ድባቴ (Depression) ከፍተኛ የአልኮል መጠጥ ችግር ፣ከባድ አካላዊ ህመም ፣ የኢኮኖሚ ቀውስ፣ ጭንቀት፣ ድንገተኛ ግጭትና ብቸኝነት ዋና ዋና በአጋላጭ ችግሮች ናቸው ። እንዲሁም ቀደም ባለ ጊዜ ያልተሳካ ራስን የማጥፋት ሙከራ ከነበረ ዋነኛ አጋላጭ ችግር ሊፈጥር ሊሆን ይችላል ።

መከላከያ መንገዶች
-----------------------------------------------------------------
ራስን የማጥፋት ችግር በሚገባ መከላከል ይቻላል
በተለይም ራስን ለማጥፋት የሚረዱ ምቹ ሁኔታዎችን መቀነስ፣ ተደጋጋሚ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርቶችን በመገናኛ ብዙሃን በመስጠት፣ ትምህርት ቤቶችን መሰረት ያደረገ ማዕከል በማደራጀት ለመምህራን ለወላጆች እንዲሁም ለትምህርት ቤት ማህበረሰብ በቂ የቅድመ ጥንቃቄ መረጃና ትምህርት መስጠት እንዲሁም ለተማሪዎች የማማከር አገልግሎት ማመቻቸት፣ የአልኮል መጠጥ አጠቃቀም ላይ ጥንቃቄ ማድረግ ፣ የአእምሮ ህመሞችን ቶሎ መለየትና በቂ ህክምና ማድረግ እንዲሁም ተገቢውን ክትትል ማድረግ፣በቂ የሱስ ማገገሚያ ማዕከላትን ማቋቋም።
================================
ማጣቀሻ ፡- WHO report
ዮሴፍ ሳህለ

ባላችሁበት የቴሌግራም ግሩፖች #share አድርጉ @psychoet
1.7K views17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ