Get Mystery Box with random crypto!

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂

የቴሌግራም ቻናል አርማ psychoet — ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
የቴሌግራም ቻናል አርማ psychoet — ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
የሰርጥ አድራሻ: @psychoet
ምድቦች: ሳይኮሎጂ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 13.21K
የሰርጥ መግለጫ

| እውነት | ፍትህ | ፍቅር | ✔ሥነ ልቡና |
የተለወጠ ግለሰብ አለም ይለውጣል!
የተለያዩ የስነልቦናና የላቀ የሰው ልጅ አስተሳሰብ ላይ የተሰሩ video ለማግኘት የዩቲዩብ ቻናሌን ይከታተሉ
"የማወቅና የመለወጥ ሰአት አሁን ነው "
https://www.youtube.com/user/TheNahusenai
Facebook አድራሻዬ Fb.com/psychologyabc

Ratings & Reviews

2.33

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-01-09 20:29:00
942 views17:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-09 07:01:58
#መልካም_የጥር_ወር_ይኹንላችሁ!

ይህ ወር የአእምሮ ደስታ ፣ ሰላም ፣ እረፍት የምታገኙበት ፤ ካሳሰባችሁና ካስጨነቃችሁ የማያልቅ የሕይወት ውጣ ውረድ እፎይ የምትሉበት ፣ ሕይወታችሁ የሚለወጥበት ፣ አስተሳሰባችሁ መልካምና ቀና የሚሆንበት ፣ ያላቀዳችሁ የምታቅዱበት ፣ ያቀዳችሁ ያቀዳችሁትን የምታሳኩበት ወር ይሁንላችሁ ፡፡

ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ በኹሉም አካባቢዎች ሰላምን የምንሰማበት ፣ ፍትህን የምናይበት ይሁንልን ፡፡

የሳይኮሎጂና የሕይወት ክህሎት የማሕበራዊ ሚዲያ ትምህርታችን በዚህ ወርም ተጠናክሮ ይቀጥላል ፡፡

ሁሌም የማያልቅ ተስፋ አለ።
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
Telegram : t.me/psychoet
Facebook : fb.com/psychologyabc

መልዕክቱን #Share #Like በማረግ ለሌሎችም እናጋራ
1.6K views04:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-08 16:56:15
ሰው መሆን በቂ ነው!

አንድ ቀን አንድ ሰው በድንገት በአንድ ጉድጓድ ውስጥ ወደቀና መውጣትም አልቻለም፡፡ ከብዙ ጥረት በኋላ ደክሞት በጉድጓዱ መካከል ቁጭ እንዳለ …

• ከንፈር መጣጭ ሰው አየውና - “ሁኔታህን ሳስበው በጣም በሃዘን እሞላለሁ” ብሎት ሄደ፡፡

• ተመራማሪ ሰው አየውና - “ይህ ጉድጓድ ከተማ መሃል ሆኖ ሰው መውደቁ አያስደንቅም” ብሎት ሄደ፡፡

• ፈራጅ ሰው አየውና- “ክፉ ሰዎች ብቻ ናቸው እንደዚህ ሊወድቁ የሚችሉት” ብሎት ሄደ፡፡

• ነጭናጫና አጉረምራሚ ሰው አየውና- “እኔ ወድቄ የነበረበትን ጉድጓድ አላየህ” ብሎት ሄደ፡፡

• አነቃቂ ንግግር አስተማሪው አየውና- “በራስህ ብታምን ከዚህ ትወጣለህ” ብሎት ሄደ፡፡

• ዘረኛ ሰው አየውና - “የምን ሃገር ሰው ነህ?” በማለት ከጠየቀው በኋላ የእርሱን ቋንቋ ስላልተናገረ ጥሎት ሄደ፡፡

•ውሸተኛ የሀይማኖት ሰው አየውና - " የኔ እምነት ተከታይ ብትሆን አወጣህ ነበር " ብሎት ሂደ፡፡

• በመጨረሻ ይህንን ሁሉ ድራማ ሲመለከት የነበረ አንድ ጨዋ ጎልማሳ ሰው ከብዙ ጥረት በኋላ እየሳበ አወጣው ፡፡

ከዚህ ታሪክ ምን እንማራለን? በእርግጥ ሰውነት ከሁሉ ይበልጣል ፡፡

ምንጭ :- ከዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ የተገኘ

በቅንነት ሼር ያድርጉ
http://t.me/psychoet
1.0K views13:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-07 18:07:58
በዓሉን ለምታከብሩ የቻናላችን ቤተሰቦች እንኳን አደረሳችሁ
912 views15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-31 19:04:41
ጭንቀትን_ድብርትንና_አሉታዊ ስሜቶችን_ለመከላከል የሚረዱ_ዘዴዎች

ባለፈ ጥፋት ወይም ውድቀት ላይ በማተኮር #ፀፀት# ውስጥ አለመግባት። ከባለፈው ስህተት በመማርና አሁን/ዛሬ ላይ ማተኮር።

ማህበራዊ ተሳትፎዎችን ማድረግ።

ከተለያዩ እፆችና አልኮል #ሱሰኝነት# መቆጠብ።

ግጭቶችን፣ ቅራኔዎችንና አለመግባባቶችን በአግባቡ መፍታት።

ውጥረትንና ጭንቀትን የሚፈጥሩብዎትን ነገሮችና ሁኔታዎችን መለየትና ከእነሱ መራቅ።

በጎ ማድረግና ምላሹን ከሰዎች አለመጠበቅ።

ጭንቀትና ድብርት ሲሰማዎ ለቅርብ ወዳጅ፣ ጓደኛ ወይም ቤተሰብ ማጋራት።

ድንገተኛ ችግር ሲያጋጥምዎ፤ ራስን ማረጋጋት።

ሌሎች ሰዎች ስለእርስዎ በሚሰጡት ትችት እና አስተያየት አለመረበሽ።

የህይወትን ጥሩ ገፅታ ማየት።

በአላማና በእቅድ መኖር ፤ ጊዜን በስራ ማሳለፍ።

የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፤ ንፅህናን መጠበቅ እና ጤናማ የአመጋገብ ስርአትን መከተል።

ለራስ ጊዜን መስጠትና እረፍት ማድረግ።

ከሁሉም በላይ በፈጣሪ መታመንና እኛ ልንፈታ የማንችላቸውን ነገሮች ለእርሱ መተው።

መልእክቱ ለብዙዎች እንዲደርስ Share & Like አይርሱ።

Psych ጤና Fb ፔጅ
በመአዛ መንክር -ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት

ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
t.me/psychoet
1.0K views16:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 22:18:59
እውነት ከሚናገር ሰው በላይ የሚጠላ የለም፡፡
@psychoet
700 views19:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-30 09:11:43
ሰው ነህ !
በሰጡህ ቦታ አትቅር ፣ ሰው እንጂ ድመት አይደለህምና።
ማንም ወደ ፈለገው አይቀይስህ፣ ሰው እንጂ የመስኖ ውኃ አይደለህምና።
በቁጣ የሠራኸውን አታፍርስ ፣ ሰው እንጂ ጎርፍ አይደለህምና።
በወደቅህበት አትቅር፣ ሰው እንጂ ዛፍ አይደለህምና።
ሰው ሁን ከሰውም ሰው ሁን::
የተባለው ከተስማማህ ሼር አድርግ

@Psychoet
1.1K viewsedited  06:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-14 18:51:16
በዛው መጠን የኛ የሆኑ ሰዎችንም እናውቅበታለን @psychoet
1.2K viewsedited  15:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 18:56:52 ወዳጆቼ ኾይ፣ ከጠቀማችሁ ትንሽ ነገር ልበላችሁ

ኹላችንንም ወደዚህች ምድር የላከን ፈጣሪ ነው፡፡ አንዳችንም ወደን ፈቅደንና አስበንበት የመጣን የለንም፡፡ ታዲያ ለምን ይኾን ፈጣሪ ወደዚህች ምድር የላከን? በቃ በልተን ጠጥተን፣ ተምረን ሰርተን ፣ አግብተን ወልደን እንድንሞት ብቻ ነው? ወይስ ሌላ ምክኒያት ኖሮት ይኾን? ቆይ የሕይወት ሩጫችን የት ለመድረስ ነው? ከደረስንስ በኀላ? የሕይወትስ ትልቁ ነገር ምንድነው?
#ራሳችንን_እንጠይቅ
@Psychoet
813 views15:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-03 06:44:32
ከወደ አርባምንጭ ሜሎሪና-ቴሎስ እየተነበበ ነው

‹‹ልጄ ያሬድ፣ የሰው ልጆችን መከራ ማሸነፊያ መሣሪያ ስለኾነው ነገር ልንገርህ፡፡ ችግሮችን ሁሉ የምናሸንፍበትና ከገባንበት አረንቋ የምንወጣበት አንድ ትልቅ መሰላል አለ፤ እሱም መልካም ተስፋ ነው፡፡ ተስፋ፣ ከምንኖርበት ቦታና ካለንበት አካባቢ አልፈንና ተሻግረን አርቀን እንድናስብ የሚረዳን ነው። ተስፋ አሳብ ነው፤ ተስፋ ምኞት ነው። ዛሬያችንን፣ ከተወረሰበት ጨለማ አራግፈን የምናወጣበት ነው፡፡ ይቺ ዓለምም ብትኾን ለተስፈኞች የተለየ ቦታ ያላት ትመስላለች፡፡ ምክንያቱም ምንም ነገር ሳይታይ፣ ሳይሰማ፣ ሳይዳሰስና ሳይጨበጥ በፊት በአሳብ ደረጃ እያለ የማይታየውን እንዲታይ፣ ያልተጨበጠውን እንዲጨበጥ የሚያደርጉት ትላልቅ ተስፈኞች
ናቸው፡፡ ተስፋ በርግጥ የወደቀውን ያነሣል፤ የተሰበረውን ይጠግናል፡፡

‹‹ስለዚህ ዛሬን በደስታ እየኖርህ ነገ የተሻለ ቦታ መድረስ እንደምትችል በፈጣሪ መልካም ተስፋ አድርግ፡፡ ኹኔታዎች ምቹ ባይመስሉም ተስፋህን ግን አታርቀው፤ ሁሌ ለችግርህና ለሐዘንህ ተስፋን አሳያቸው፡፡ ሕይወትህ መከራ፣ ችግር፣ ሐዘን ውስጥ ቢገባም በቅርቡ ወደ በለጠ ደስታ፣ ድልና ስኬት እንደምትሸጋገር እመን፡፡ በምታልፍበት የሕይወት ችግር ውስጥ የምትኖረው ለጥቂት ጊዜ ብቻ እንደኾነ ለችግርህ ንገረው፡፡ በነገ መልካም ተስፋ ዛሬን በደንብ ጠንክረህ ሥራ በደስታም ኑር፡፡››

የናንተንም ፎቶ ከወደዳችሁት ከመጽሐፉ የወጣ አባባል ጋር ላኩልን
Kibre-ab Elias ĸébå
841 views03:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ