Get Mystery Box with random crypto!

በአንድ ወቅት አንድ ሰው በመንገድ ሲያልፍ ከአንድ የሚቃጠል ቋጥኝ ውስጥ አንድ እባብ ይመለከታል:: | ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂

በአንድ ወቅት አንድ ሰው በመንገድ ሲያልፍ ከአንድ የሚቃጠል ቋጥኝ ውስጥ አንድ እባብ ይመለከታል:: ይህ ሰው ምንም እንኳን እባብ መሆኑን ቢመለከትም በእሳት ውስጥ መቃጠሉ ስላሳዘነው ከእሳት ሊያወጣው በእንጨት ሲሞክር ዘሎ እጁን ነከሰው:: ታዲያ ያ ግለሰብ ምንም እንኳን እጁን መነከሱ ቢያመውም በድጋሚ ከእሳት እንደምንም አወጣው:: ይህንን ሁኔታ በርቀት ሲመለከት የነበረ ሌላ ሰው ቀረብ ብሎ ወደሰውዬው "እንዴት እባብ መሆኑን እየተመለከትክ በእዛ ላይ እንዲህ እየነደፈህ ታድነዋለህ?" ብሎ ቢጠይቀው አንድ መልስ መለሰለት::
"እባቡ አላጠፋም ምክኒያቱም ተፈጥሮው መናደፍ ነው እሱኑ ማንነቱን ነው ያደረገው:: እኔም ተፈጥሮዬ ማገዝ: መርዳትና መልካም መሆን ነው እናም እኔም ማንነቴንና ተፈጥሮዬን ነው የሆንኩት: ስለ ድርጊቱ ብዬ እባብ አልሆንም::" አለው ይባላል::

ዛሬ በአዲስ ዓመት ዋዜማ በሰዎች ምክኒያት የጣላችሁትን ያ ውብ ማንነት የምታነሱበት አዲስ ዓመት ተመኘው::

አምባሳደር ስለሺ ሳልስ ዑመር
2014ዓ.ም የ2015ዓ.ም መባቻ