Get Mystery Box with random crypto!

Our World

የቴሌግራም ቻናል አርማ ourworl_d — Our World O
የቴሌግራም ቻናል አርማ ourworl_d — Our World
የሰርጥ አድራሻ: @ourworl_d
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 894

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-04-29 11:09:27
ለልጃቸው ሰርግ የገዟት ላም ሲሳይ ይዛ መጣች!

በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ይልማና ዴንሳ ወረዳ ደዋሮ ቀበሌ ልዩ ስሟ «አካሌ ባድማ» በተባለች መንደር ልጃቸውን ለመዳር በ18 ሺህ ብር  የገዟት ላም 40ሺህ ብር የሚጠጋ ዋጋ ያለው ማዕድን ለባለ ሰርጎቹ አበርክታለች።

በበህር ዳር ከተማ የጋፋት ወርቅ ቤት ባለቤት አለልኝ ማተቤ ማዕድኑ በተለምዶ ወርቅ ይባል እንጂ ወርቅ አይደለም፣ ዋጋው ግን ከወርቅ ማዕድን በእጅጉ ከፍ ያለ እንደሆነና በዋናነትም ጃፓነችና ቻይናዎች እንደሚገዙት ለዶይቼ ቨሌ ተናግረዋል።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ህክምናና ግብርና ኮሌጅ ፕሮፌሰር ገዛኸኝ ማሞ በበኩላቸው በአንዳንድ የቆላማ አካባቢዎች በሚገኙ እንስሳት አልፎ አልፎ የሐሞት ጠጠር ይፈጠራል፤ ሆኖም ይህ ነገር በተለምዶ ወርቅ ይባል እንጂ ወርቅ አለመሆኑን ያስረዳሉ።

ፕሮፌሰሩ፥ እንደዚህ ዓይነቱ የሀሞት ጠጠር  ወደ ቻይናና ጃፓን አገር እንደሚሸጥ እንደሚያውቁ ጠቁመው ለምን አገልግሎት እንደሚውል ግን በትክክል እንደማያውቁ ነው የተናገሩት።

የወርቅ ባለሙያው አቶ አለልኝ ማተቤ ራሳቸው ከዚህ በፊት ከእንስሳት የተገኘውን ይህን የአሞት ጠጠር እስከ 80ሺህ ብር ገዝተው እስከ 100ሺህ ብር ሸጠው እንደሚያውቁ አመልክተዋል ሲል ዘገባው ያመለክታል፡፡
31 viewsBekele Ejeta, edited  08:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 20:18:51 በአርሲ ዞን በድጋሚ ለቅርጫ ከተገዛ ሰንጋ ውስጥ 7.5 ግራም ወርቅ ተገኘ

ወርቁ 21 ሺህ 500 መቶ ብር ተሽጧል

በምስራቅ አርሲ ለትንሳኤ በዓል የገዙት በሬ ለእርድ በሚቀርበበት ሰዓት በሀሞቱ ውስጥ 7.5 ግራም የሚመዝን ወርቅ መገኘቱን የጢዮ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ግረማ ጣፋ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ግለሰቦቹ  ኩማ ተሰማ እና ንጉሴ ዲንቃ የተባሉ ሲሆን ለበዓል ቅርጫ በ38 ሺህ ብር በሬ ገዝተው  በሚያርዱበት ወቅት  በበሬው ሃሙት ውስጥ 7.5 ግራም የሚመዝን ወርቅ አግኝተዋል። ወርቁ ሃያ አንድ ሺ አምስት መቶ ብር መሸጡ ተሰምቷል።

ከቀናት በፊትም በዚሁ አካባቢ 18.5 ግራም የሚመዝን ወርቅ በበሬ ሀሞት ላይ ስለመገኘቱ እና ወርቁን 53 ሺህ ብር ስለመሸጡ ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው እንዳሁኑ ይፋ የወጣ ነገር ባይኖርም በተደጋጋሚ  በበሬዎች ሃሞት ላይ ወርቅ ስለመገኘቱም ኮማንደር ግርማ ጣፋ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
28 viewsBekele Ejeta, edited  17:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 20:07:03 በኢትዮጲያ ባለፉት ሶስት ዓመታት በኮቪድ -19 ከ7500 በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል

በኢትዮጲያ በሶስት ዓመት ውስጥ በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰው ሲያዝ ከ7500 በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው እንዳለፈ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል ።

ባለፉት ሶስት ዓመታት በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በኮቪድ -19 በሽታ 500 ሺ 774 ሰዎች ሲያዙ ከነዚህም ውስጥ 7574 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ተገልጿል ። ክትባት በሶስት ዙር የተሰጠ መሆኑንና የተፈናቀሉ እና እስረኞች የክትባት ተከታታይ ተጠቃሚነት ላይ ቁጥሩ ዝቅተኛ እንደሆነ በጤና ሚኒስቴር የክትባት ኤክስፐርት የሆኑት ዶ/ር አለማየሁ አየለ መናገራቸውን ሰምቷል ።

በዓለም ላይ በኮቪድ -19 በሽታ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች እንደሚጠቁ የተገለፀ ሲሆን ምክንያቱ እስካሁን ድረስ እንዳልታወቀ እና ጥናት እየተደረገ እንደሚገኝ ተነግሯል ። በተጨማሪ በዓለም ከ685 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሲያዙ ስድስት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ መረጃዎች ያሳያሉ ።
25 viewsBekele Ejeta, edited  17:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 21:00:16
ለቅርጫ ከታረደ በሬ ሆድ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ ተገኘ!

በአርሲ ዞን ጢዮ ወረዳ ዶሻ በምትባል ቀበሌ በጋራ ሆነው ለበዓል የቅርጫ በሬ ያረዱት ሰዎች ከበሬው ሆድ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ አግኝተዋል።በሬውን በ40 ሺሕ ብር የገዙት ተቃራጮቹ ከበሬው ሆድ ውስጥ ያገኙትን ወርቅ በ53 ሺሕ ብር በመሸጥ የበሬውን ሥጋ በነፃ በልተው 13 ሺሕ ብር ማትረፍ መቻላቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ከበሬው ሆድ ውስጥ እንዴት ወርቅ ተገኘ? ሳይንሱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላል? ለሚለው ጥያቄ መልስ የሰጡት በኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የአሰላ የእንስሳት ጤና ማዕከል የላቦራቶሪ ባለሙያ ዶ/ር አብዲሳ ለማ በበረሃማ አካባቢ የሚኖሩ ከብቶች ጥቃቅን ማዕድናት ያላቸውን ተክሎች እየተመገቡ በጊዜ ሂደት ማዕድናቱ በሐሞት ውስጥ እየተጣሩ ወደ ወርቅነት (በተለምዶ ‘የሐሞት ወርቅ’ ወደሚባለው) እንደሚቀየሩ ተናግረዋል፡፡ንጥረ ነገሩ በከብቶቹ ሆድ ውስጥ እየቆየ ሲሄድ የሐሞት ፍሳሽን ስለሚመጥጥ ከብቶቹ እንዳይደልቡ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።
104 viewsBekele Ejeta, edited  18:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 16:01:09
ከፀሐይ ክብደት 30 ቢሊየን እጥፍ የገዘፈ በርባኖስ ተገኘ

በአፅናፈ-ሰማይ ላይ ከተዘረጉ በርካታ “ጋላክሲዎች” ይልቅ የገዘፈ በርባኖስ ወይም ጥልቁ ጥቁር ጉድጓድ “ብላክ ሆል” መገኘቱን የእንግሊዝ ተመራማሪዎች አስታወቁ።

በዶክተር ጀምስ ናይቲንጌል የተመራው የእንግሊዙ ዱርሃም ዩኒቨርሲቲ የጥናት ቡድን ያገኘው በርባኖስ የፀሐይን ክብደት በ30 ቢሊየን ጊዜ እጥፍ የሚልቅ እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡

ተመራማሪወቹ ይህን ያክል መጠን ያለው በርባኖስ መገኘቱን እንግዳ እንደሆነባቸውም ነው የጥናት ቡድኑ መሪ የሚናገሩት።

በህዋ ላይ ከሚገኙ አካላት በመጠኑ ትልቁ ነው የተባለው ይህ በርባኖስ እንደ ሚልክዌይ (ፀሐይን ጨምሮ የፕላኔቶችን ስብስብ በያዘው) ጋላክሲ ባሉ ትላልቅ ጋላክሲዎች መሃል ላይ እንደሚገኝም ይታመናል።

የበርባኖሱ ግኝት ከዳር እንዲደርስ ሂደቱን በማሳለጥ ረገድ የጀርመኑ ማክስ ፕላንክ ኢንስቲትዩት ድጋፍ ማድረጉ ተነግሯል፡፡

በተጨማሪም የናሳው “ሃብል ቴሌስኮፕ” ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን ምሥሎች በማንሳት እና ትርጉም እንዲያገኙ ለዱርሃም ዩኒቨርሲቲ በመላክ በሱፐር ኮምፒዩተር በርባኖሱ መኖሩ ተረጋግጧል፡፡

ጥናቱ ትናንትና ይፋ የሆነው በሮያል የሥነ-ፈለክ ማኅበር መሆኑንም አር ቲ ዘግቧል፡፡

በርባኖስ ወይም በእንግሊዝኛው አጠራር “ብላክ ሆል” በኅዋ ላይ ያለ ጥልቅ ጉድጓድ ሲሆን ከፍተኛ የስበት ኃይል ያለውና ብርሃን እንዳይታይ አድርጎ የማስቀረት ዐቅም ያለው መሆኑን የሥነ ፈለክ ተመራማሪዎች ይገልጻሉ።
38 viewsBekele Ejeta, edited  13:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-30 15:58:06
በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከ6ኛ ፎቅ የወደቀችው ሰራተኛ በህይወት ተረፈች።

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዕድሜዋ 40 የተገመት አንዲት የሆስፒታሉ ሰራተኛ ትላንት ሌሊት 10:30 ላይ ከ6ኛ ፎቅ ላይ "ዘላ ወደ ምድር በመዉደቋ ከባድ ጉዳት ደርሶባታል" ሲል የእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ለኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጥሪ የተደረገውም፥ ከ6ኛ ፎቅ ወደ ታችኛዉ ወለል ወደ ቤዝመንት ዉስጥ የወደቀችዉን ተጎጂ ከወደቀችበት ለማንሳት ምቹ ሁኔታ ባለመኖሩ መሆኑ ተገልጿል።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም በመሰላልና በገመድ በመጠቀም ተጎጂዋን በህይወት ማውጣት ችለዋል። ተጎጂዋ ከአደጋዉ በህይወት ብትተርፍም ከባድ ጉዳት ደርሷባታል ተብሏል።

ተጎጂዋ በሆስፒታሉ ተረኛ አዋላጅ ነርስ ሆና ምሽቱን የተለመደ ስራዋን ከባልደረቦቿ ጋር ስታከናዉን እንደነበር ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በተያያዘ ዜና በትላንትናው ዕለት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታ አትላስ አካባቢ ግንባታዉ በተጠናቀቀ ህንጻ ላይ ቀለም በመቀባት ላይ ያሉ ሰራተኞች የቆሙበት ሊፍት (ዊንች) ካቦዉ ተበጥሶ በአራት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

ጉዳት የደረሰባቸዉ አራት ሰዎች በኮሚሽኑ አምቡላንስ  ዘዉዲቱ ሆስፒታል ተወስደዉ ህክምና እየተደረገላቸዉ ሲሆን ጉዳት ከደረሰባቸዉ ዉስጥ አንዱ ከባድ ጉዳት የደረሰበት ነዉ። አደጋዉ በአጋጠመበት ጊዜ አራቱም ተጎጂዎች በሊፍቱ ላይ እንደነበሩ ኮሚሽኑ አስታውቋል
27 viewsBekele Ejeta, edited  12:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 10:14:09 የሶርያ ጦርነት 12 ዓመታትን አስቆጠረ
(ረጅም ፅሁፍ)


እንዴት ተጀመረ?


መጋቢት 15 ቀን 2011 በሶርያ ዴራ፣ ደማስቆ እና አሌፖ ጎዳናዎች ላይ ከፍተኛ ብጥብጥ ተቀሰቀሰ፤ ተቃዋሚዎች ዲሞክራሲያዊ ለውጥ እንዲደረግ እና የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ጠየቁ። ለተቃውሞ መቀስቀስ ምክንያት የሆነው ከጥቂት ቀናት በፊት በዴራ ከተማ ፕሬዝዳንት አል አሳድን ለማውገዝ አደባባይ የወጡ በአሥራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን በማሰር እና በማሰቃየት ነበር።

ተቃውሞውን ተከትሎ በሶርያ መንግስት ከፍተኛ ርምጃ እና ጭቆና ተከተለ። እ.ኤ.አ. በሀምሌ 2011 ከሶርያ ጦር ኃይል የከዱ ሀይሎች መንግሥትን ለመገልበጥ ዓላማ ያለው የነፃ የሶሪያ ጦር መቋቋሙን አስታውቀው አመፁን ወደ እርስበርስ ጦርነት ለወጡት። እ.ኤ.አ. በ2012 ተቃውሞው የቀጠለ ሲሆን በዓመቱ በመላው አገሪቱ የተለያዩ አማፂ ቡድኖች ብቅ አሉ። በዚያው በ2013 አመት መጨረሻ ላይ የአይኤስ መነሳት በሰሜን እና በምስራቅ ሶሪያ እንዲሁም በርካታ የኢራቅን ግዛቶች በመውረር ፈተናው የሰፋ ሆነ።

ከአስራ ሁለት አመታት በፊት የሶርያ መንግስት ተቃዋሚዎች የሀገሪቱን ጎዳናዎች ላይ ደፍረው በመውጣት መንግስት እና ፕሬዚዳንቱን ባሽር አል አሳድን በመቃወም ነበር የእርስ በእርስ ጦርነቱ የተጀመረው። ተቃውሞዎቹ በፍጥነት አብዮታዊ ተፈጥሮን ይዘው “የአገዛዙን ውድቀት” ጠየቁ፣ ነገር ግን ከመንግስት ሃይለኛ ምላሽ በኋላ ህዝባዊ አመፁ ወደ ጦርነት ተቀየረ፣ ብዙ የውጭ ሃይሎችን እየጎተተ ሚሊዮኖችን አፈናቅሎ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ገደለ።

በጦርነቱ የተነሳ የሶሪያ ኢኮኖሚ እያሽቆለቆለ መጥቷል፣ አሁን ላይ 90 በመቶ የሚሆነው የሶርያ ህዝብ ከድህነት ወለል በታች እንደሚኖር የዓለም የምግብ ፕሮግራም መረጃ ያሳያል። የሶርያ ቀውስ ከተጀመረበት ከመጋቢት 2011 ጀምሮ በሀገሪቱ ከ306,000 በላይ ንፁሀን ዜጎች ወይም ከሶርያ ህዝብ 1.5 ከመቶ ያህሉ ተገድለዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለፈው አመት ያወጣው አሃዛዊ መረጃ ያሳያል።

መቀመጫውን በዩናይትድ ኪንግደም ያደረገው የሶሪያ የሰብአዊ መብቶች ታዛቢ ቡድን በበኩሉ በጦርነቱ በአጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ወደ 610,000 እንደሚደርስ ገምቷል። በየካቲት ወር ሰሜን ምዕራባዊ ሶሪያን ካወደመው የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት 14.6 ሚሊዮን ሶሪያውያን ሰብአዊ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጿል፣ 6.9 ሚሊዮን ሰዎች በአገር ውስጥ ተፈናቅለው የሚገኙ ሲሆን ከ5.4 ሚሊዮን በላይ የሶሪያ ስደተኞች በጎረቤት ሀገራት ተገን ጠይቀው ይኖራሉ። በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በጀርመን እና በሌሎች የአውሮጳ ህብረት ክፍሎች እንዲሁም በሌሎች አካባቢዎች ጥገኝነት ጠይቀዋል።


በሶርያ የሚገኙ ተፋላሚዎች እነሆ እነማን ናቸው?

የሶሪያ ፕሬዝዳንት ባሽር አል አሳድ እ.ኤ.አ. ከ1971 ጀምሮ በስልጣን ላይ ከነበሩት አባታቸው ሃፌዝ አል-አሳድ ስልጣኑን ተረክበው ሀገር መምራት የጀመሩት በ2000 ዓመት ነበር። ሀገሪቱን በብረት መዳፍ በመምራት ተቃዋሚዎችን በማፈን የኬሚካል ጦር መሳሪያ በመጠቀም በሺዎች በማሰር እና በማሰቃየት ምዕራባውያኑ ክስ ቢያቀርቡባቸውም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሶርያውያን ግን በደማስቆ ቤተመንግስት መቆየታቸው እንደሚያስደስታቸው ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።

ነፃ የሶሪያ ጦር (FSA) ወይም የሶሪያ ብሔራዊ ጦር የሚባለው እ.ኤ.አ በ2011 ከሶሪያ ጦር በከዱ እና በቱርክ እንዲሁን በበርካታ የአረብ ሀገራት በሚደገፉ ሲቪሎች የተቋቋመ የታጠቁ ብርጌዶች ስብስብ ነው። እ.ኤ.አ. በታህሳስ 2016 ከአሌፖ ጦርነት ጀምሮ በሰሜን ምዕራብ ሶሪያ ውስጥ የኢድሊብ ውስን ቦታዎችን ቡድኑ እንደተቆጣጠረ እስካሁን ቆይቷል።

በጦርነቱ ሌላኛው ተፋላሚ ሀያት ታህሪር አል-ሻም (ኤችቲኤስ) ሲሆን ቀደም ሲል ጀብሃ ፈታህ አል ሻም ወይም ጀብሃ አል-ኑስራ ተብሎ ይጠራ ነበር። ጀብሃ አል-ኑስራ የአል-አሳድ መንግስት ተቃዋሚ ሲሆን የአልቃይዳ አጋር ሆኖ በ 2011 ተመስርቷል።በአሁኑ ጊዜ ይህ ኤች ቲ ኤስ የተሰኘው ቡድን "ማንኛውንም ድርጅት ወይም ፓርቲ የማይከተል ገለልተኛ አካል" መሆኑን ይገልፃል።

ሌላኛው የጦርነቱ ተዋናይ ሲሆን ሂዝቦላህ ሲሆን የሺአ የታጠቀ ቡድን ነው። ሂዝቤ በሊባኖስ እና በኢራን የሚደገፍ የፖለቲካ ሃይል ሲሆን የፕሬዝዳንት አል-አሳድን መንግስትን ለመደገፍ ወደ ሶሪያ የገባ ሀይል ነው። በአሁኑ ጊዜ በሶሪያ ውስጥ ምንም አይነት ግዛት አይቆጣጠርም።

የሶሪያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች (ኤስዲኤፍ) ይህ ቡድን የኩርድ እና የአረብ ሚሊሻዎች ጥምረት ሲሆን የተመሰረተው በ2015 ዓመት ነበር።በአብዛኛው የYPG ተዋጊዎችን እና የአረብ፣ የቱርክ እና የአርመን ተዋጊዎችን ቡድኑ ያካትታል። ቱርክ ግዛት ገንጥሎ የኩርዶች ሀገር ለመመስረት የሚንቀሳቀሰው ይህው ቡድን ከ1984 ጀምሮ ከ40,000 በላይ ሰዎችን የገደለ የትጥቅ ዘመቻ ከአንካራ መንግስት ጋር አድርጓል።በኤስዲኤፍ ቁጥጥር ስር የሶርያ ዋና ዋና ከተሞች የሆኑት ራቃ፣ ኳሚሽሊ እና ሃሳኬህ የተሰኙ ከተሞች በቡድኑ እጅ ስር ይገኛሉ።

አይኤስ አይኤስ በውጭ ተዋጊዎች የተደራጀው ይህው ቡድን የመንግስት ስርዓት የፈጠረ እና በጠንካራ የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴው ይታወቅ ነበር። ይህው ቡድን እ.ኤ.አ በ2014 በግምት አንድ ሶስተኛውን የኢራቅ እና ሶሪያን ግዛቶች ተቆጣጥሮ የነበረ ቢሆን ከ2019 ወዲህ ድባቅ ተመቷል።

በሀገራት ደረጃ የሩሲያ መንግስት ዋንኛው የደማስቆ አስተዳደር ደጋፊ ሲሆን ሞስኮ በአሁኑ ወቅት በሶርያ የጦር ሰፈር ገንብታ ከባሽር አላሳድ ጎን ትገኛለች።ኢራን በተመሳሳይ ከሶርያ ጎን ተሳፋለች።

ቱርክ የባሽር አላሳድ ወዳጅ የነበረች ቢሆንም በአመፁ መነሻ ወቅት ከአቋማ ተንሸራታ የዋይፒጂን ታጣቂዎች ለመውጋት በሚል የሶርያ ታጣቂዎችን በምድሯ እስከማስታጠቅ ደርሳ ነበር።አሜሪካ የደማስቆ መንግስት ከስልጣን እንዲነሳ ታጣቂዎችን በመርዳት በጦርነቱ ሚናዋ ከፍ ያለ ነበር።

ጦርነቱ በሶርያ በዩኔስኮ ከተመዘገበችው የቤልና የባአል ሻሚ ቤተመቅደሶች መገኛ ፓልምይራ ከተማ እስከ ቱርክ ድንበር የምትጋራውን ኢድሊብን አፈራርሷል።በነዳጅ ሀብቷ ዝነኛ ከነበረችው ዴር አዝ ዞር ከተማ አንስቶ በኤፍራጥስ ወንዝ ላይ የተመሰረተችውን ራቃን 80 በመቶ መሰረተ ልማት አውድሟል።የሶርያ የኢንዱስትሪና የኢኮኖሚ ከተማ አሊፖ የወንበዴዎች መሸሸጊያ አድርጓታል።

ከ12 ዓመታት በኃላ ታዲያ ምን አዲስ?

ዛሬም የሶርያ ፕሬዝዳንት የዓይን ሀኪሙ ባሽር አላሳድ ናቸው።ለፕሬዝዳንቱ ጀርባ ሰጥተው ግንኙነት አቋርጠው የነበሩ የአረቡ ዓለም ሀገራት ዳግም ወዳጅነቱን ፈልገዋል። ኤምሬትስ በድማስቆ የዘጋችውም ኤምባሲ በድጋሚ ስትከፍት አል አሳድም አቡዳቢ ደርሰው ተመልሰዋል።ግብፅ፣ ኦማን፣ ኢራቅና ሊቢያ ወዳጅነታቸውን አጠናክረዋል።ሶርያ ወደ አረብ ሊህ እንድትመለስም ሂደቱ ተጀምሯል።ዳግም ከ12 ዓመት በፊት ሶርያ ወደነበረችበት ትመለሳለች።መቶሺዎች ሲገደሉ ሚሊዮኖች ስደተኛና የአካል ጉዳተኛ ሆኑ፣ንብረት ሲወድም፣ኢኮኖሚው ሲናጋ፣ፍርሃት ሲነግስ ከዚህ ሁሉ የእልቂት አዙሪት በኃላ ግን እየነጋ ይመስላል። እውነታው ደግሞ የተለወጠ የተገኘ አዲስ ድል ግን የለም።
40 viewsBekele Ejeta, edited  07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 22:12:53 ከ20 ሚሊዮን በላይ ሴቶች የወር አበባ ንጽሕና መጠበቂያ አያገኙም ተባለ!

በኢትዮጵያ የወር አበባ ከሚያዩ ከ35 ሚሊዮን ሴቶች ውስጥ 22 ሚሊዮን ወይም 75 በመቶ የሚሆኑ ሴቶች የወር አበባ ንጽሕና መጠበቂያ እንደማያገኙ የአደይ የሴቶች የሚታጠብ ንጽሕና መጠበቂያ መሥራች አስታወቁ።

የአደይ የሚታጠብ ንጽሕና መጠበቂያ መሥራች ወይዘሮ ሚካል ማሞ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ የአደይ የሴቶች የሚታጠብ ንጽሕና መጠበቂያ (ፓድ) ምርት በኢትዮጵያ ያለውን የሴቶች የወር አበባ የንጽሕና መጠበቂያ አቅርቦት እጥረት ለመፍታት ይረዳል። በዚህም ያለውን ከ20 ሚሊዮን በላይ ቁጥር ለመቀነስ እንዲሁም የዋጋ ንረቱን ለማረጋጋት ይረዳል።

ለዚህም አደይ ፓድ አንዱ የንጽሕና መጠበቂያ በአንድ የወር አበባ ኡደት ሁለት ጊዜ ጥቅም ላይ የሚውል ሲሆን፣ በአጠቃላይ አንድ መቶ ጊዜ መታጠብ የሚችል መሆኑን መሥራቿ ተናግረዋል። ይህ ድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውል የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ያለውን የምርት እጥረት ከመቅረፍ ባለፈ የዋጋ ንረቱንም ሊቀንስ ይችላል ብለዋል።

ይህ በድጋሚ ጥቅም ላይ የሚውል የሴቶች የንጽሕና መጠበቂያ ለሰውነት ተስማሚ ከሆነ ግብዓት የሚሠራ ምቹ የሆነ ፣ፈሳሽ የሚችል፣ምንም የጎንዮሽ ጉዳት የሌለው መሆኑን የጠቀሱት መሥራቿ፣ በአንድ ሳምንት ውስጥ ለ5ሺ ሴቶች የሚደርስ ንጽሕና መጠበቂያ እንደሚመረት ተናግረዋል።

እርሳቸው እንዳሉት፤ አንዲት ሴት በወር አበባ ምክንያት በአማካኝ ከሦስት እስከ አምስት ቀናት ከትምህርት ወይንም ከሥራዋ በንጽሕና በአቅርቦት እጥረት ምክንያት ትስተጓጎላለች። ለዚህም በትኩረት ሴት ተማሪዎች ላይ እየሠሩ ይገኛል። ይህም ምርት ከ18 እስከ 24 ወራት የሚያገለግል በመሆኑ በወር አበባ ምክንያት ከትምህርቷ ሳትስተጓጎል እንድትገኝ የሚያደርጋት ይሆናል።

የትኛዋም ሴት የንጽሕና መጠበቂያ በማጣት ምክንያት ከትምህርት ገበታዋ ይሁን ከአስፈላጊ ሥራዎቿ መቅረት የለባትም የሚሉት ወይዘሮ ሚካል እስካሁንም በሀገሪቱ ለሚገኙ ከ300 ሺ በላይ ሴት ተማሪዎች ንጹሕ የሆነ የንጽሕና መጠበቂያ በመሥራት ተደራሽ ተደርጓል ሲሉ ገልጸዋል።

ዋናው ችግራችን አብዛኛው ግብዓት ከውጭ የሚመጣ በመሆኑ የቀረጥና የግብር ጉዳይ መፍትሔ አለማግኘቱ ነው ሲሉም ተናግረው እንዲሁም የቦታ ጥበት እንዳለባቸው አስረድተዋል።

ሴቶችን ማብቃት ሲባል የመጀመሪያው ነጥብ የወር አበባ ንጽሕና መጠበቂያ ማቅረብ ነው። ለዚህም መንግሥት ይህንን የሴቶች ንጽሕና መጠበቂያ ዋጋ ንረት ለመቅረፍ እንዲሁም ተደራሽነቱን ለመጨመር ምርቶቹን እንዲሁም የምርቶቹን ጥሬ እቃ ከቀረጥ ነጻ ማድረግ እንዳለበት ጠይቀዋል።

እንደ ወይዘሮ ሚካል ገለጻ፤ ያለውን የወር አበባ ድህነት ለመቅረፍ ፣ ከቀረጥ ነፃ እንዲሆን እንዲሁም በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲቀርብ እና ተደራሽ እንዲሆን የተለያዩ ንቅናቄዎች የተደረጉ ሲሆን ከነዚያም ውስጥ ‹ቀረጥ ይወሰንልን ፣ ዋጋ ይተመንልን›፣ ‹ሰብዓዊ መብቴን አትቅረጹ›፣ ‹አበባ አየሽ ወይ ትምህርት ቤት ትሄጃለሽ ወይ?› የሚጠቀሱ ሲሆን አይ ኬር ኢትዮጵያ እና ጀግኒት ኢትዮጵያ ጋር በአጋርነት እንደሚሠሩ ወ/ሮ ሚካል ገልጸዋል።

Via EPA
24 viewsBekele Ejeta, 19:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 22:09:30 የአይጥ መርዝ በሶ ላይ በመጨመር ለልጇ ያጠጣችው እናት በቁጥጥር ስር ዋለች

በደቡብ ክልል ወላይታ ዞን ሶዶ ዙሪያ ወረዳ በአይጥ መርዝ የተመረዘ በሶ ለልጇ አጠጥታለች የተባለችዉ የ32 ዓመቷ ተጠርጣሪ በቁጥጥር  ስር  መዋሏ ፖሊስ አስታውቋል።

በዞኑ ሶዶ ዙሪያ ወረዳ ቶሚ ገረራ ቀበሌ ነዋሪ የሆነችዉ ወይዘዋ ጎረቤት ከሚገኝ አባወራ ጋር በድብቅ የፍቅር ግንኙነት መጀመሯ በሰዎች ዘንድ የሚወራዉ ወሬ ከ16 አመቱ ታዳጊ ልጇ ጆሮ ገብቶ ኖሮ የሰማዉን ነገር በአይኑ አይቶ ለማረጋገጥ በትእግስት ነገሩን ሲከታተል ቆይቷል።

ልጅ እናቱ በመንደርተኛዉ የታማችበትን የፍቅር ግንኙነት ትክክል መሆኑ በእርግጠኛነት ሲያውቅ ለወላጅ እናቱ የእናትነት ክብር ሳይነፍግ በትህትና ቀርቦ መክሮ ሊመልሳት ሲሞክር በእሺታ ተቀብላዉ ነበር።

የልጇን ምክር ተቀብላ በእሺታዋ ከመፅናት ይልቅ የእሱን ምክር ወደጎን ትታ ከሰዉየዉ ጋር የነበራትን ግንኙነት አጠናክራ ቀጠለች በዚህም የጀመረችዉ ፍቅር እናቱን ሊያሳጣዉ እንደሚችል ስጋት የገባዉ  ልጅ በድጋሚ እናቱን መክሮ ሊመልስ ጥረት ማድረጉ ይቀጥላል።

እናት ከጎረቤት የምትሰማዉ የፍቅር ቋንቋ ከልጇ ምክር ጋር ስታነፃፅረዉ የልጇ ምክር ለጆሮዋ ያልተመቸ ሆኖ ቢሰማት የጀመረችዉ የፍቅር ግንኙነት ከማቋረጥ ይልቅ ልጇን ከአጠገቧ ገለል ልታረገዉ ከዉሳኔ ትደርሳለች።

የካቲት  23 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሰዓት አካባቢ የ16 ዓመቱ ታዳጊ  ከወላጅ እናቱ የቀረበለት ቤት ያፈራዉን ማእድ ከቀማመሰ በኋላ ለተመገበዉ ምግብ ማወራረጃ ይሆን ዘንድ ያዘጋጀችለት በሶ ጠጥቶ ከቤት ወጣ ይላል።

ታዳጊዉ ከደቂቃዎች በኋላ ሆዱ ላይ በሚሰማዉ የህመም ስሜት ምክንያት  ፊቱን ላብ አጥምቆት  እራሱን ስቶ ሲወድቅ የአካባቢዉ ህብረተሰብ ታማሚዉን በፍጥነት ወደ  ሶዶ ክርስቲያን ሆስፒታል  ያደርሱታል።

ሀኪሞች ወጣቱ መመረዙ በመረዳታቸዉ ህይወቱን ለማትረፍ አስፈላጊዉ ህክምና ቢያደርጉለትም ከቆይታ በኋላ የወጣቱ ህይወት ማለፉን የደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ሀላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።

በሶዶ ዙሪያ ወረዳ የቶሚ ገረራዋ እናት ግን ለልጇ  ከምግብ በኋላ ለማወራረጃነት  በሰጠችዉ የተበጠበጠ  በሶ ዉስጥ የአይጥ መርዝ  አድርጋበት ህይወቱ እንዲያልፍ በማድረጓ በቁጥጥር ስር መዋሏን ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
20 viewsBekele Ejeta, edited  19:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 22:08:28 #ማርች 8 ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን

በሴቶች ዙሪያ የተሰሩ ጥናቶች አጫጭር መረጃዎች

በየ90 ሰከንድ ልዩነት በመላው ዓለም አንዲት ሴት ከእርግዝና እና ከወሊድ ጋር በሚፈጠር እክል ህይወቷን ታጣለች።የልብ በሽታ በሴቶች ዘንድ ቁጥር አንድ ገዳይ ነው።

ሴቶች በቀን ውስጥ 20ሺ ቃላቶችን ሲነገሩ ወንዶች 13ሺ ቃላቶችን ይናገራሉ።2 በመቶ ሴቶች ብቻ ቆንጆ ነኝ ብለው ራሳቸውን ለመግለፅ ድፍረት አላቸው።

በሩሲያ የሴቶች ቁጥር ከወንዶች በ9 ሚሊየን የሚበልጥ ሲሆን በኢምሬትስ ደግሞ በተቃራኒው 100 ሴቶች ለ219 ወንዶች ምጣኔ አለው።በቻይና 20 ሚሊዮን ወንዶች ሚስት የማግኘት ተስፋ የላቸውም።

በአሜሪካ ከሚወለዱ ህፃናት 40 በመቶ ትዳር ባልመሰረቱ ሴቶች ነው።4 በመቶ የአሜሪካ ሴቶች በዚህ ወቅት ነፍሰ ጡር ናቸው።በእርግዝና ወቅት የሚያንኮራፉ ሴቶሽ በአካለ መጠን አነስ ያሉ ልጆች ይወልዳሉ።በኒጀር የምትገኝ አንዲት እናት በአማካይ ሰባት ልጆች ትወልዳለች።

በእንግሊዝ በተካሄደ ጥናት አንዲት ሴት 75 ዓመታት በምድር ላይ ብትኖር አንድ ዓመት ያህሉን ከእድሜዋ ምን ልልበስ፣ምን ልጫማ በሚል ውሳኔ ታሳልፈዋለች።ሴቶች አራት ዓመታትን ከእድሜያቸው በወር አበባ ዑደት ያልፋል።

አንዲት ሴት በአማካይ በዓመት ከ30 እስከ 64 ጊዜ ልታለቅስ ትችላለች።የወንድ ልጅ ቢበዛ ከ6 አይበልጥም። በኒጀር በአማካይ አንዲት እናት ሰባት ልጆች ይኖራታል።

ወንዶች ከሴቶች በእጥፍ የበለጠ ይዋሻሉ።ጃማይካ እና ኮሎምቢ ከወንዶች የበለጥ የሴት የስራ ኃላፊዎች ያሉባቸው ሀገራት ናቸው።አንዲት ሴት ትምህርት ላይ በቆየች ቁጥር ገቢዋ 20 በመቶ ይጨምራል።

በእንግሊዝ በተሰራ ጥናት መሰረት ሴቶች በቀን በአማካይ ለዘጠኝ ጊዜ ያህል ስለ ሰውነታቸው አቋም አልያም ስለ ገፅታቸው ለሰከንዶችም ቢሆን ያስባሉ።ወንድ ልጅ ከሴቶች በሁለት እጥፍ የበለጠ ያልበዋል።

80 በመቶ በትክክል የጡት ማስያዣ ሴቶች እንደማያደርጉ በጥናት ተመልክቷል።በ13 ደቂቃ ልዩነት አንዲት ሴት በአሜሪካ በጡት ካንሰር ህይወቷ ያልፏል።በአሜሪካ ጡታቸውን ተፈጥሯዊ ባልሆነ መልኩ ለመጨመር የሞከሩ ሴቶች ራሳቸውን የማጥፋት እድል 3  እጥፍ ጨምሯል።

በመላው ዓለም የሚገኙ ሴቶች 18 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ የሚያገኙ ሲሆን 28 ትሪሊዮን ይቆጥባሉ።የአለማችን የመጀመሪያው የኮምፒዩተር ፕሮግራመር ሴት ናት። በአሜሪካ 30 በመቶ የንግድ እንቅስቃሴዎች በሴቶች ተይዘዋል።

Fifty Shades Of Grey የተሰኘውን መፅሃፍ ከገዙት መካከል 80 በመቶ ሴቶች ናቸው። ሴቶች ከወንዶች የበለጠ ህልም እንደሚያዩ መረጃዎች ያመላክታሉ።

ከአሜሪካ ግዙፉ ከተሞች መካከል አንዷ የሆነችው ሚያሚ በሴት የተመሰረተች ብቸኛ የዩናይትድ ስቴትስ ከተማ ናት።
19 viewsBekele Ejeta, 19:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ