Get Mystery Box with random crypto!

ለቅርጫ ከታረደ በሬ ሆድ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ ተገኘ! በአርሲ ዞን ጢዮ ወረዳ ዶሻ በምት | Our World

ለቅርጫ ከታረደ በሬ ሆድ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ ተገኘ!

በአርሲ ዞን ጢዮ ወረዳ ዶሻ በምትባል ቀበሌ በጋራ ሆነው ለበዓል የቅርጫ በሬ ያረዱት ሰዎች ከበሬው ሆድ ውስጥ 18.5 ግራም ወርቅ አግኝተዋል።በሬውን በ40 ሺሕ ብር የገዙት ተቃራጮቹ ከበሬው ሆድ ውስጥ ያገኙትን ወርቅ በ53 ሺሕ ብር በመሸጥ የበሬውን ሥጋ በነፃ በልተው 13 ሺሕ ብር ማትረፍ መቻላቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ከበሬው ሆድ ውስጥ እንዴት ወርቅ ተገኘ? ሳይንሱስ ስለዚህ ጉዳይ ምን ይላል? ለሚለው ጥያቄ መልስ የሰጡት በኦሮሚያ ክልል ግብርና ቢሮ የአሰላ የእንስሳት ጤና ማዕከል የላቦራቶሪ ባለሙያ ዶ/ር አብዲሳ ለማ በበረሃማ አካባቢ የሚኖሩ ከብቶች ጥቃቅን ማዕድናት ያላቸውን ተክሎች እየተመገቡ በጊዜ ሂደት ማዕድናቱ በሐሞት ውስጥ እየተጣሩ ወደ ወርቅነት (በተለምዶ ‘የሐሞት ወርቅ’ ወደሚባለው) እንደሚቀየሩ ተናግረዋል፡፡ንጥረ ነገሩ በከብቶቹ ሆድ ውስጥ እየቆየ ሲሄድ የሐሞት ፍሳሽን ስለሚመጥጥ ከብቶቹ እንዳይደልቡ እንደሚያደርግም ገልጸዋል።