Get Mystery Box with random crypto!

በኢትዮጲያ ባለፉት ሶስት ዓመታት በኮቪድ -19 ከ7500 በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል በኢትዮጲ | Our World

በኢትዮጲያ ባለፉት ሶስት ዓመታት በኮቪድ -19 ከ7500 በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል

በኢትዮጲያ በሶስት ዓመት ውስጥ በኮቪድ -19 ወረርሽኝ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰው ሲያዝ ከ7500 በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው እንዳለፈ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል ።

ባለፉት ሶስት ዓመታት በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች በኮቪድ -19 በሽታ 500 ሺ 774 ሰዎች ሲያዙ ከነዚህም ውስጥ 7574 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ተገልጿል ። ክትባት በሶስት ዙር የተሰጠ መሆኑንና የተፈናቀሉ እና እስረኞች የክትባት ተከታታይ ተጠቃሚነት ላይ ቁጥሩ ዝቅተኛ እንደሆነ በጤና ሚኒስቴር የክትባት ኤክስፐርት የሆኑት ዶ/ር አለማየሁ አየለ መናገራቸውን ሰምቷል ።

በዓለም ላይ በኮቪድ -19 በሽታ ከሴቶች ይልቅ ወንዶች እንደሚጠቁ የተገለፀ ሲሆን ምክንያቱ እስካሁን ድረስ እንዳልታወቀ እና ጥናት እየተደረገ እንደሚገኝ ተነግሯል ። በተጨማሪ በዓለም ከ685 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ሲያዙ ስድስት ነጥብ ስምንት ሚሊዮን ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ መረጃዎች ያሳያሉ ።