Get Mystery Box with random crypto!

በአርሲ ዞን በድጋሚ ለቅርጫ ከተገዛ ሰንጋ ውስጥ 7.5 ግራም ወርቅ ተገኘ ወርቁ 21 ሺህ 500 | Our World

በአርሲ ዞን በድጋሚ ለቅርጫ ከተገዛ ሰንጋ ውስጥ 7.5 ግራም ወርቅ ተገኘ

ወርቁ 21 ሺህ 500 መቶ ብር ተሽጧል

በምስራቅ አርሲ ለትንሳኤ በዓል የገዙት በሬ ለእርድ በሚቀርበበት ሰዓት በሀሞቱ ውስጥ 7.5 ግራም የሚመዝን ወርቅ መገኘቱን የጢዮ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ግረማ ጣፋ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡፡

ግለሰቦቹ  ኩማ ተሰማ እና ንጉሴ ዲንቃ የተባሉ ሲሆን ለበዓል ቅርጫ በ38 ሺህ ብር በሬ ገዝተው  በሚያርዱበት ወቅት  በበሬው ሃሙት ውስጥ 7.5 ግራም የሚመዝን ወርቅ አግኝተዋል። ወርቁ ሃያ አንድ ሺ አምስት መቶ ብር መሸጡ ተሰምቷል።

ከቀናት በፊትም በዚሁ አካባቢ 18.5 ግራም የሚመዝን ወርቅ በበሬ ሀሞት ላይ ስለመገኘቱ እና ወርቁን 53 ሺህ ብር ስለመሸጡ ብስራት ሬዲዮ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ በተጨማሪም በአካባቢው እንዳሁኑ ይፋ የወጣ ነገር ባይኖርም በተደጋጋሚ  በበሬዎች ሃሞት ላይ ወርቅ ስለመገኘቱም ኮማንደር ግርማ ጣፋ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።