Get Mystery Box with random crypto!

Our World

የቴሌግራም ቻናል አርማ ourworl_d — Our World O
የቴሌግራም ቻናል አርማ ourworl_d — Our World
የሰርጥ አድራሻ: @ourworl_d
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 894

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2022-07-24 12:58:02

31 viewsBekele Ejeta, 09:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 12:37:43 የተሥፋየ አለሙ "እባክህ መምህሩ" የተሰኘውን የሙዚቃ ክሊፕ በhope plus ዩቲዩብ ቻናል ያገኙታል። የመምህር ተስፋየ አለሙን ስራ subscribe በማድረግ እናበረታታው። ተስፋየ አለሙ ዘገየ አይነሥውር ወንድማችን ሲሆን በሚያዚያ 23 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የቋንቋ መምህር ነው። የተሠማችሁንም comment ስጡት. Have you watched Tesfaye Alemu's " ibakh memhur" music video??
30 viewsBekele Ejeta, edited  09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 12:34:09

26 viewsBekele Ejeta, 09:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 12:08:34 ኒኮላስ ቴስላ(electric) ለአለም ሕዝብ ያለ ቆጣሪ እንዲዳረስ ይፈልግ ነበር።

የተለዋዋጭ(alternative) መብራት ፈጣሪ የሆነው ኒኮላስ ተስላ መብራትን ያለ ገመድ በማስተላለፍ ሰዎች አንፖሎችን ብቻ በመግዛት እንዲጠቀሙ ይፈልግ ነበር።

በርግጥ መብራትን ያለሽቦ ማንቀሳቀስ የማይመስል ነገር ሊመስለን ይችላል ኒኮላስ ተስላ ግን ይሄንን ማድረግ ይቻላል ብሎ ያምናል ለዚህም እንደምሳሌ የሚያነሳው መብረቅን ነው መብረቅ መብራት ነው መብረቅ ግን ከዳመና ተነስቶ መሬት ላይ ያሉ ሰዎችን ወይም ሌሎች ነገሮችን ይመታል ሥለዚህ መብራት በአየር ላይ ያለሽቦ መንቀሳቀስ ይችላል ማለት ነው።

ኒኮላስ ቴስላም ይሄንን እንዳሳካ ይነገራል ነገር ግን ፈጠራው ሆን ተብሎ እንደተደበቀ ይታሠባል; እንደምክንያት የሚነሳው ደግሞ ይሄ ቴክኖሎጂ የመብራት ቆጣሪን ሊያጠፋ ሥለሚችል ነው ይሄ ደግሞ አገራትን እና ድርጅቶችን ኪሳራ ውስጥ የሚከት ነው ምክንያቱም መብራት በአሁኑ ሰአት ትልቅ ቢዝነስ ሥለሆነ.

!!
24 viewsBekele Ejeta, 09:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 09:35:13
32 viewsBekele Ejeta, 06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 09:35:05
32 viewsBekele Ejeta, 06:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-24 09:34:55
እንኳን ደስ አለን !

ኢትዮጵያውያን የበላይ ሆነው አጠናቀዋል !

እጅግ በጣም የሚደንቅ የቡድን ስራ በታየበት የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ውድድር በጉዳፍ ፀጋይ አማካኝነት ወርቁ ወደ ኢትዮጵያ ገቢ ተደርጓል።

ነሀስም በዳዊት ስዩም ተገኝቷል።

ከፍተኛውን የቡድን ስራ የሰራችው የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ባለድሏ ለተሰንበት ግደይ 5ኛ ደረጃ ይዛ አጠናቃለች።

ኬንያ ብር አግኝታለች።

እንኳን ደስ አለን !!
37 viewsBekele Ejeta, edited  06:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 23:50:16 በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ኬንያዊው ኪፕሩቶ ታዳጊው ኢትዮጵያዊ ሌሜቻ ግርማን በሚሊ ሜትር ቀድሞ ወርቅ ያጠለቀበት ውድድር የሚዘነጋ አይደለም።

ለሜቻ ግርማ በ3000 መሰናክል ለኢትዮጵያ ሜዳሊያ ያስገኘ የመጀመሪያው ወንድ አትሌት ነው።

አትሌት ሶፊያ አሰፋ በ2013 ሞስኮ ላይ ያገኘችው ነሐስ በርቀቱ ብቸኛው የኢትዮጵያ ሜዳሊያ ነበር።

በዘንድሮው የኦሪገን ዓለም ሻምፒዮና የታየውም ይህ ነው።

ለሜቻ ግርማ በርቀቱ ሁለተኛ ብሩን በተከታታይ አጥልቋል።

ጉዳፍ ፀጋይ ደግሞ በ1500 ሜትር ለአገሯ ብር አስገኝታለች። ኬንያዊቷ ፌይዝ ኪፕየጎን ለአገሯ ብቸኛውን ወርቅ አስገኝታለች።

የኬንያ መገናኛ ብዙኃን በዘንድሮው የኦሪገን ውጤት ደስተኛ አለመሆናቸውን እየገለጡ ነው።

ኬንያ ባለፈው የዓለም ሻምፒዮናም ሆነ በኦሊምፒክ መድረክ ከኢትዮጵያ ልቃ ብታጠናቅቅም በዓለም የቤት ውስጥ ውድድርና በአሜሪካው የዓለም ሻምፒዮና የተመዘገበው ውጤት አመርቂ ሆኖ አልተገኘም።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ሴት አትሌቶች በሻምፒዮናው መድረክ በአሜሪካዋ ኦሪገን ግዛት እየተካሄደ የሚገኘው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መጪው እሁድ ይጠናቀቃል።

በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ  በወንዶች እና ሴቶች ከ800 ሜትር እስከ ማራቶን ባሉ የውድድር ዘርፎች እየተሳተፈች ትገኛለች።

በዚህ ውድድር እስከ አሁን ሦስት የወርቅ ሜዳሊያ፣ አራት ብር እና አንድ የነሃስ ሜዳልያ በማምጣት ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ እሑድ እለት የሚካሄዱት የ800 እና 5000 ሜትር ውድድሮች በጉጉት ይጠበቃሉ።

ኢትዮጵያ እስከ አሁን በዚህ ውድድር ካገኘቻቸው ስምንት ሜዳሊያዎች አምስቱ በሴት አትሌቶች የተገኙ ናቸው።

የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በፈረንጆቹ ከ1983 ጀምሮ በየሁለት ዓመት ልዩነት መካሄድ የጀመረ ሲሆን፤ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በ5000 እና በ10000 ሜትር ውድድሮች ስመ ጥር ሆነውበታል።

ቀደም ሲል በ10 ሺህ ሜትር፣ በ5 ሺህ ሜትር እና በግማሽ ማራቶን፤ ሦስት የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነችው አትሌት ለተሰንበት ግደይ በዚህ ታላቅ መድረክ አሸናፊነቷን አስጠብቃለች።

ለተሰንበት ከውድድሩ በኋላ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጠችው አስተያየት “ህልሜ እውን ሆኗል። ይህ ድል ከዓለም ክብረወሰን በበለጠ ለእኔ ትልቅ ነው። በውጤቱ በጣም ደስተኛ ነኝ” ብላለች።

አትሌት ጎተይቶም ገብረሥላሴም በሴቶች ማራቶች የሻምፒዮናውን ክብረ ወሰን በመስበር አሸናፊ መሆኗ ይታወሳል።

በኦሪገን መድረክ ደግሞ በማራቶን ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች። ከዚህ በፊት ማሬ ዲባባ በ2015 ቤይጂንግ በተካሄደው የዓለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆና ነበር።

ኢትዮጵያ፤ በተለይ በፈረንጆቹ ከ1999 እስከ 2007 ባሉት ዓመታት በ10 ሺህ እና በ5 ሺህ ሜትር ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ውድድሩን በማሸነፍ በርካታ ሜዳሊያ አካብታለች።

ጌጤ ዋሚ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ወርቅነሽ ኪዳኔ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ብርሃኔ አደሬ፣ አልማዝ አያና እና ሌሎች በአትሌቲክሱ ዓለም አገራቸውና ያስጠሩ ሴት አትሌቶች ናቸው።

አሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ ያለውን ውድድርን ሳይጨምር ኢትዮጵያ በተሳተፈችባቸው የአትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች 85 ሜዳሊያዎችን ስታስመዘገብ፣ ከዚህ ውስጥ ደግሞ ወደ ግማሽ የሚጠጋው የተገኘው በሴቶች ነው።

በዚህም 38ቱ ሜዳሊያዎች በ1500፣ በ3000፣ 5000 እና በ10000 ሜትር እንዲሁም 2 ሜዳሊያዎች በማራቶን ውድድሮች ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች ያሰነፉት ሲሆን በአጠቃላይም 40 ሜዳሊያዎችን, አስገኝተዋል።
44 viewsBekele Ejeta, 20:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 23:50:16 በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያና ሜዳሊያ የተገናኙት ገና ከጅምሩ ፊንላንድ ሄልሲንኪ በተደረገው የመጀመሪያው ውድድር ነበር።

በዚህ የመጀመሪያው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ለኢትዮጵያ እንዲሁም ለአፍሪካ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ያስገኘው አትሌት ከበደ ባልቻ ነው።

ከበደ በማራቶን ውድድር ሁለተኛ ወጥቶ የብር ሜዳሊያ በማጥለቅ ችቦውን አቀጣጠለ።

ነገር ግን ቀጥሎ በጣሊያኗ ከተማ ሮም በተካሄደው ሁለተኛው ውድድር ኢትዮጵያ አልተሳተፈችም ነበር።

በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በርካታ ሜዳሊያ በመሰብሰብ አሜሪካንን የሚደርስባት የለም።

ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ደግሞ ጎረቤት አገር ኬንያ ናት።

ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር እስካሁን ባከማቻቸው ሜዳሊያዎች ከዓለም ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ተሾመ ቀዲዳ የ2022 የኦሬገን ሻምፒዮናን ሳይጨምር ኢትዮጵያ 85 ሜዳሊያዎች አሏት ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል።

“ኢትዮጵያ በዓለም ቻምፒዮና ታሪክ 29 ወርቅ፣ 30 ብር እንዲሁም 26 የነሐስ ሜዳሊያዎች፤ በአጠቃላይ 85 ሜዳሊያ አላት።”

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የተለየ ታሪክ አላት የሚለው ጋዜጠኛው፣ አትሌት ከበደ ባልቻም በማራቶን መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ የብር ሜዳሊያ ያስገኘ አፍሪካዊ መሆኑን ያወሳል።

በፈር ቀዳጁ ውድድር ኢትዮጵያ በከበደ ባልቻ ነሐስ ሜዳሊያ ከዓለም 15ኛ ሆና አጠናቃለች።

ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት የቻለች ብቸኛዋ አፍሪካዊት አገር ናት።

በወቅቱ ምሥራቅ ጀመርን [ጀርመን አንድ ከመሆኗ በፊት] 19 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ አንደኛ ሆና ስታጠናቅቅ፣ የውድድሩ ኃያል አገር አሜሪካ ደግሞ ሁለተኛ ሆና ነበር።

በጣልያኗ ሮም በተካሄደው ሁለተኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና “የአትሌቲክስ ቡድን እየመራ የሚጓዝ አሠልጣኝ ባለመገኘቱ ነው ኢትዮጵያ ያልተሳተፈችው” ይላል ጋዜጠኛ ተሾመ።

ኢትዮጵያ በዚህ ታላቅ የአትሌቲክስ መድረክ የመጀመሪያውን ወርቅ ያገኘችው በአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ አማካይነት ነው።

ኃይሌ የጀርመኗ ስቱትጋርት ባዘጋጀችው አራተኛው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር ወርቅ ማምጣት ችሏል።

አትሌቱ በዚህ ሳይገታ በ5 ሺህ ውድድር ደግሞ የነሐስ ሜዳሊያ ለአገሩ አስገኝቷል።

አትሌት ፊጣ ባይሳ ደግሞ ሌላ ነሐስ አክሎ ኢትዮጵያ በሦስት ሜዳሊያ አሸብርቃ ተመለሰች።

ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መድረክ በስዊድኗ ጉተምበርግ ከተማ እስከተሰናዳው ውድድር ድረስ ከአፍሪካ አንደኛ ሆና ስታጠናቅቅ ቆየች።

ነገር ግን በጉተምበርግ በተካሄደው ውድድር ኬንያ ወደ ኃይልነት መጣች።

በዚህ ውድድር ኬንያ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ጨምሮ ስድስት ሜዳሊያ በመሰብሰብ ስሟን ከፍ አደረገች።

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያና ኬንያ ከጉተምበርጉ ፍልሚያ በኋላ ፉክክራቸው እየበረታ መጣ።

በፈረንጆቹ 2003 በተካሄደው የፓሪሱ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 3 ወርቅ፣ 2 ብርና 2 ነሐስ በማምጣት ከዓለም አራተኛ ሆና ያጠናቀቀችበት መድረክ የሚረሳ አይደለም ይላል ጋዜጠኛ ተሾመ።

በሄልሲንኪ የተካሄደው 10ኛው ሻምፒዮና ግን ልዩ ነበር ሲል ያክላል።

ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር ከአሜሪካና ከሩሲያ በመቀጠል በ3 ወርቅ፣ በ4 ብርና በ2 ነሐስ ከዓለም ሦስተኛ ሆና አጠናቀቀች።

ይህ የሄልሲንኪው ውድድር “አረንጓዴው ጎርፍ” ተብሎ ይጠራል።

አረንጓዴው ጎርፍ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሦስት ተከታትለው በመግባት ዓለምን አጀብ ያሰኙበት ዘመን ነው።

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ 2 ወርቅ ባጠለቅችበት በዚህ ውድድር የአረንጓዴው ጎርፍ አርማዎቹ መሠረት ደፋር፣ ብርሃኔ አደሬ እና እጅጋየሁ ዲባባ የነበራቸው ተሳትፎ የሚዘነጋ አይደለም።

በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ደግሞ ቀነኒሳ በቀለና ስለሺ ስህን ተከታትለው በመግባት ሄልሲንኪን የማይረሳ አድረጓት።

ከሁለት ዓመታት በኋላ ግን ጃፓን ኦሳካ ባሰናዳችው ውድድር ድል ወደ ኬንያ ዞረ።

ኬንያ በዚህ ሻምፒዮና 5 ወርቅን ጨምሮ 15 ሜዳሊያዎች አሸነፈች።

ከዚያ በኋላ በነበሩት የበርሊን፣ ዴጎ፣ ሞስኮ፣ ቤይጂንግ፣ ለንዶን፣ ዶሃ ላይ ኬንያ በሜዳሊያ ብዛት ኢትዮጵያን እየመራች ቆይታለች።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ በደራርቱ አመራር ደራርቱ ቱሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ሻምፒዮና የተሳተፈችው በፈረንጆቹ 1991 ቶኪዮ በተዘጋጀው ውድድር ነበር።

ምንም እንኳ ደራርቱ በተሳተፈተችበት የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ሜዳሊያ ባታመጣም በቀጣዩ ዓመት ባርሴሎና በተዘጋጀው ኦሊምፒክ ላይ ወርቅ ማጥለቅ ችላለች።

የአገሯን ስም በተለያዩ መድረኮች ያስጠራችው ደራርቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆና ከተመረጠች በኋላ ለውጥ ማምጣት ችላለች ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ነገር ግን ለደራርቱ ሁኔታዎች ሁሉ የተመቻቹ ነበሩ ማለት ከባድ ነው።

ደራርቱ ፌዴሬሽኑን መምራት ከጀመረች ወዲህ ሁለት ጊዜ በዓለም ሻምፒዮና፤ አንድ ጊዜ በኦሊምፒክ መድረክ፤ አንድ ጊዜ ደግሞ በዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ተሳትፋለች።

በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ በተሰናደው የ2019 የዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለት ወርቅ፣ አምስት ብርና አንድ ነሐስ ይዛ ተመልሳለች።

በዚህ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች በሚታወቁበት የመካከለኛና ረዥም ርቀት ውድድር የተለመደውን ወርቅ ማስመዝገብ ባይችሉም ተስፋ ያላቸው አትሌቶች ታይተዋል።

ኢትዮጵያ በመድረኩ በስምንት ሜዳሊያ አምስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቀቀች።

ከዚህ በኋላ በደራርቱ የተመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ታላቅ ወደ ሚባለው የኦሊምፒክ መድረክ ነው ያቀናው።

በ2022 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ ያገኘችው ሜዳሊያ ብዛት አራት ነው።

ይህ ውጤት ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ መድረክ ካመጣቻቸው ዝቅተኛ ከተባሉት የሚመደብ ነው።

ቀጥሎ ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት ዓለም አቀፍ መድረክ ባለፈው መጋቢት የተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ፍልሚያ ነው።

ይህ መድረክ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደምቀው የታዩበት ነበር።

ኢትዮጵያ፤ በአራት ወርቅ፣ በሦስት ብርና በሁለት የነሐስ አሜሪካን አስከትላ ከዓለም ቁንጮ ሆና አጠናቃለች።

በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት እየተካሄደ ባለው የዘንድሮው የዓለም ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ውጤት ከጅምሩ አመርቂ መሆን ችሏል።

በተለይ በመድረኩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የምንጊዜም ተቀናቃኝ የሆነችው ኬንያ በምትታወቅባቸው ሩጫዎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ብቅ ብቅ ማለታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

ኢትዮጵያና ኬንያ በዓለም ሻምፒዮና ኬንያና ኢትዮጵያ ድንበር ብቻ አይደለም የሚጋሩት። ሜዳሊያ የሚታደልበት የአትሌቲክስ መድረክንም ጭምር እንጂ።

በተለይ በረዥም ርቀት የሩጫ ውድድር ሁለቱ አገራት በየመድረኩ አንገት ለአንገት ሲተናነቁ ማየት አዲስ አይደለም።

ኃይሌና ፖልቴርጋን በሚሊ ሜትር ተቀዳድመው ሲገቡ የነበረውን ትዕይንት ማን ይዘነጋል።

ቀነኒሳና ኪፕቾጌ በሁለት ሰከንድ ልዩነት የጨበጡት የማራቶን ክብረ ወሰንም እንዲሁም ተመዝገቦ የሚኖር ነው።

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በመካከለኛ ርቀት ማለትም በ5 ሺህና በ10 ሺህ ሜትር፤ ኬንያ ደግሞ በአጭርና በመካከለኛ የ800፣ የ1500 እና, የ3000 ሜትር ርቀቶች ሲነግሱ ማየት የተለመደ ነው።

ነገር ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኬንያዊያን በመካከለኛ ርቀት ኢትዮጵያን ሲፋለሙ ተመልክተናል።

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደግሞ በ1500 እና 3000 ሜትር መሰናክል ውድድሮች ኬንያዊያንን መፈተን ይዘዋል።

ለምሳሌ በ2019 የዶሃ ዓለም ሻምፒዮና
46 viewsBekele Ejeta, 20:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 09:53:24

63 viewsBekele Ejeta, edited  06:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ