2022-06-29 20:47:10
የሬቢስ በሽታ ምንድን ነው?
- በተለምዶ የእብድ ውሻ በሽታ (Rabies) የምንለው ሬቢስ በሚባል ቫይረስ አማካኝነት የሚመጣ ከእንስሳት ወደ የሰዉ ልጅ የሚተላለፍ በሽታ ነው።
- የእብድ ውሻ በሽታ የተባለበት ምክንያት በአበዛኛው የቫይረሱ ተሸካሚዎች በአካባቢያችን የሚገኙ ውሾች በመሆናቸው ነው። ከዚህ በተጨማሪ የለሊት ወፍ ፣ ፈረስ ፣ ላም ፣ የቫይረሱ ተሸካሚ ሊሆኑ ይችላሉ።
- ከዉሻ ጋር ተያይዞ የሚመጣ የሬቢስ በሽታ በአብዛኛው ታዳጊ ሀገራትን የሚያጠቃ ሲሆን በተለይ ህጻናት ለጆችን ስለበሽታው እና ከትባቱ በቂ ግንዛቤ በሌላቸው የሀገራችን ክፍሎች ላይ በብዛት ይስተዋላል።
መተላለፊያ መንገዶች ምንድን ናቸው?
- በቫይረሱ ከተጠቁ እንስሳት በተለይ ከውሾች ወደ የሰው ልጅ በንክሻ ወይም በመቧጨር ከአፉቸው በሚወጣ ፈሳሽ (saliva) በቀጥታ ቆዳን ዘልቆ የሚገባ ከሆነ ወይም በሰወነታችን ትኩስ ቁስል (fresh skin wounds) ካለ ሊተላለፍ ይችላል።
- በተለይ የተነከስነው ወይም የተቧጨርነው አንገት እነ ከአንገት በላይ ከሆነ ቫየረሱ በፍጥነት ወደ ማእከላዊ የነርቭ ስርአት (central nervous system) ቅርብ ስለሆነ በፍጥነት ወደ አንጎል (brain) በመድረስ ለሞት ሊዳርገን ይችላል።
- የሬቢስ በሽታ theroetically ከቫይረሱ ተሸካሚ ሰው ወደ ሰው በንክሻ ይተላለፋል ተብሎ ይታሰባል።
ምልክቶቹስ ምንድን ናቸው?
-አንድ ሰው በቫይረሱ ከተጋለጠ በዃላ ምልክት እስከሚያሳይ (incubation period) ከ3ሳምንት እስከ 3 ወር ሊቆይ ይችላል።
- ምልክት የሚያሳዩ ሰዎች የተነከሰበት ቦታ ለይ መጠዝጠዝ አና መደንዘዝ ፣ ትኩሳት ፣ እራስ ምታት ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ ፣ ጡንቻ አካባቢ የህመም ስሜት ፣ ፍራቻ ፣ ከመጠን በላይ ምራቅ መኖር ፣ ለመዋጥ መቸገር ፣ ቅዠት ፣ ግራ መጋባት ፣ ዉሃን መፍራት (hydrophobia) ፣ እንቅልፍ ማጣት ፣ የከፉ ደረጃ ሲደርስም ለኮማ ከዛም ለሞት ሊዳረግ ይችላል።
- ምልክቶቹን ማሳየት የጀመረ ሰው የመዳን አድሉ እጅግ በጣም ጠባብ ነው።
እንዴት መከላከል አነችላለን?
- የቤትም ሆነ የዱር እንስሳ ካለን ማስከተብ
-ሌላው መርሳት የሌለብን ነገር ክትባቱን ባልተከተቡ እንስሳት ከተነክሰን ወይም ጥርጣሬ እንኳን ቢኖርብን ግዜ ሳንሰጥ ወዲያውኑ የህክምና ባለሙያ በማማከር የተጋላጭነት ክትባቱን (post exposure prohpylaxis) መዉሰድ አለብን።
ህክምናውስ?
- የሬቢስ በሽታ ይሄ ነው ሚባል ህክምና የለውም። ምክነያቱም የሬቢስ ቫይረስ ሰውታችን ውስጥ ከገባ እራሱን ስለሚደብቅ በጸረ ቫይረስ (Anti viral) አንኳን መዳን አይችልም።
- ስለዚህ ማንኛውም አይነት ቁስል በሰውነታችን ለይ ካለ በአግባቡ መታከም እና ተጋላጭ ከሆንን ጊዜ ሳነሰጥ የህክምና ቦታ በመሄድ ከትባቱን መከተብ ብቸኛ አማራጮች ናቸው።
- በአጠቃላይ የሬቢስ በሽታ ችላ የማይባል ለህልፈት የሚዳርግ በሽታ ነው።
ጤና ይብዛሎ
Dr. Ermias Mamo
via: HakimEthio
82 viewsBekele Ejeta, 17:47