Get Mystery Box with random crypto!

Our World

የቴሌግራም ቻናል አርማ ourworl_d — Our World O
የቴሌግራም ቻናል አርማ ourworl_d — Our World
የሰርጥ አድራሻ: @ourworl_d
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 894

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-11-15 10:00:05
ኢንተርኔት ላይ እጃችሁ እስኪደክም ብታስሱ ከዚህ የተሻለ የእውቀት ክምችት አታገኙም―ላይብረሪ ጀነሲስ 4 ሚሊየን መፅሀፍት እና 80 ሚሊየን ሳይንሳዊ መጣጥፎች አሉት። ታዲያ ሁሉንም በነፃ ነው የሚያቀርቡላችሁ― ድምቡሎ አትከፍሉም።

ታዲያ ይህ ተግባራቸው ብዙ ተቃውሞ እና የክስ ጋጋታ አስከትሎባቸዋል። ከነዚህ ከሳሾች አንዱ ኤልሰቪር ይባላል። ኤልሰቪር ታዋቂ የሳይንስ ምርምር እና ጥናት ውጤቶችን በመጣጥፍ እና በመፅሀፍ የሚያሳትም ድርጅት ነው።

ታድያ የላይብረሪ ጀነሲስ ሰዎች ይህን የሚመክት ጥሩ መከራከሪያ አቀረቡ፦

"እንደ ኤልሰቪር ያሉ የምርምርና የጥናት ወረቀት አሳታሚዎች በመንግስት የሚደጎሙ ናቸው። መንግስት ደግሞ ገንዘቡን ከየትም አያመጣውም― ከታክስ ከፋዮች ነው። ስለዚህ በተዘዋዋሪ ህዝቡ ለዚህ እውቀት ከፍሏል። ወረቀቶቹን በነፃ ማቅረባችን ሙሉ ለሙሉ ህጋዊ ነው" ብለው በፍርድ ቤት በዳኛ ፊት የኤልሰቪር ሰዎችን አፍ አዘግተዋል።

ለማንኛውም ሳትሳቀቁ ዳውንሎድ አድርጉ አንብቡ። ወንጀል የሚሆነው ባወቃችሁት ነገር ምንም ሳትሰሩ ስትቀሩ ነው!

Library Genesis
https://libgen.li/
https://libgen.li/
https://libgen.li/
35 viewsBekele Ejeta, 07:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-15 09:43:46 በአንዲት ትንሽየ ከተማ ውስጥ ለብዙ ዘመናት ማራኪ ስዕሎችን በመሳል ለከተማዋ ነዋሪዎች እና ከሩቅ አካባቢ ለሚመጡ እንግዶች በጥሩ ዋጋ እየሸጠ ደስታ የተሞላበት ሕይወት የሚኖር አዛውንት ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን በከተማዋ ውስጥ ከሚገኙ ድሃዎች
መካከል አንዱ መጣና ሰዓሊውን «በሥራህ ብዙ ገቢ እያገኘህ ለምንድን ነው በከተማዋ ያሉ የኔ ቢጤ ደሃዎችን ለመርዳት ንፉግ ያደረገህ ??...

የዚያ ልኳንዳ ቤት ባለቤት እዚህ ግባ የሚባል ገንዘብ ሳይኖረው ለድሃዎች በየቀኑ ስጋ ያድላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ የዚያ ዳቦቤት ባለቤት ዘወትር በየቀኑ በነፍስ ወከፍ ለድሃዎች ዳቦ ይሰጣል» በማለት ጠየቀው። ሰዓሊው ምንም መልስ ሳይሰጠው በሰከነ መንፈስ ታጅቦ በስሱ ፈገግ አለ።

ድሃው በሰዓሊው ዝምታ ተበሳጭቶ ከቤቱ ውስጥ ተስፈንጥሮ ወጣ። ወደ መሃል ከተማ በመገስገስ አላፊ አግዳሚውን እያስቆመ «ሰዓሊው ብዙ ኃብት ቢያከማችም ድሃወችን
ለመርዳት ፍላጎት የሌለውና ስስታም ነው» በማለት ወሬ መንዛት ጀመረ። የአካባቢው ነዋሪዎች በሰዓሊው ላይ ጥርስ ነከሱበት። ማህበራዊ መገለል ደረሰበት። የሚያናግረው አንድ ሰው እንኳ አጣ።

ከተወሰኑ ቀናት በኋላ አዛውንቱ ሰዓሊ ክፉኛ ታመመ። ከአካቢቢው ነዋሪዎች መካከል አንድም ሰው ትኩረት የሰጠው አልነበረም። ከጎኑ ማንም ሳይኖር ብቻውን ሞተ።

ቀናት በንፋስ ፍጥነት ነጎዱ። የከተማዋ ነዋሪዎች የልኳንዳ ቤቱ ባለቤት ለድሃዎች በነጻ የሚያድለውን ስጋ እንዳቆመ አስተዋሉ። የዳቦ ቤቱ ባለቤትም ለሚስኪኖች በነጻ
የሚያከፋፍለውን ዳቦ እንዳቋረጠ ተገነዘቡ። ድሃዎቹ በልኳንዳ ቤቱ በር ፊት ለፊት ቆመው የለመዱትን ስጋ ለማግኘት ቢማጸኑም ሰሚ አጡ። በዳቦ ቤቱ መስኮት ዙሪያ ቢያንዣብቡም
ለስም እንኳ የሚያዳምጣቸው አንድ ሰው አጡ።

የከተማዋ ነዋሪዎች ተሰብስበው የልኳንዳ እና ዳቦ ቤቶቹን ባለቤቶች «ዘወትር በየቀኑ ለድሃዎች ትሰጡ የነበረውን ስጋ እና ዳቦ ለምን
አቆማችሁ» ብለው ሲጠይቋቸው «በየቀኑ ለከተማዋ ድሃዎች በነጻ የምንሰጠውን የስጋና ዳቦ ዋጋ በየወሩ የሚከፍለን አዛውንቱ ሰዓሊ ነበር። ከሱ ህልፈት በኋላ ክፍያ የሚፈጽምልን
ሰው ባለመኖሩ በነጻ ማደሉን አቋርጠነዋል» በማለት ወሽመጥ ቆራጭ ምላሽ ሰጧቸው።

የተወሰኑ ሰዎች ባንተ ላይ ክፉ ጥርጣሬ ሊያሳድሩ ይችላሉ። አንዳዶች ደግም እንደ ሐጫ በረዶ የጠራህ አድርገው ሊስሉህ ይችላሉ። ሁለቱም አይጠቅሙህም። አይጎዱህምም።
ቁም ነገሩ ያለው ፈጣሪ ስላንተ የሚያውቀው ትክክለኛ ማንነትህ ላይ ነው። ለክፉ አሳቢዎች ክፋ ምላሽ ላለመስጠት ጥረት አድርግ።

ደግነትህ ለብዙዎች የዕድሜ ማራዘሚያ ሰበብ ስለሆነ እንዳይከስም ጠብቀው። ለጋስ በመሆንህ በምላሹ ከሌሎች ምንም ነገር አትጠብቅ። የጊዜ ጉዳይ ቢሆን እንጂ መልካም ነገር ሁሌም ከፈጣሪህ በጎ ምላሽ አለው።
ህሊናህ ይረካ ዘንድ ከመቀበል ይልቅ ሰጪ ሁን። በምግባርህ ፈጣሪህን ለማስደሰት ሁሌም ጥረት አድርግ። እርሱ ከወደደህ ደስታ በእጅህ ትገባለች።በመልካም ስነ ምግባር ሽቶ የተርከፈከፈ ስብዕና ከመሬት በታች አፈር ለብሶ እንኳ መዓዛው ያውዳል።
               
36 viewsBekele Ejeta, edited  06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 02:15:16
This Picture Teaches Us One Important Lesson.

Today you are flying up the sky, tomorrow you will need someone on the ground to carry you. So be humble, love people and invest in people.

LESSONS: Remember no matter how big flying object you are, some thing can carry you that can never fly. Never underestimate people below you, carry them above if you can but never push them down.
49 viewsBekele Ejeta, 23:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-09 02:06:12 በአንድ ወቅት አንድ ጋቭሮብ ይቸገርና ብር ለመበደር ወደ ሌላኛው ጋቭሮብ ጓደኛው ቤት በምሽት ያመራል። እሳት ዳር ቁጭ ብለው እያወጉም የገጠመውን ችግር ለጓደኛው ያወያየውና ለስራ መጀመሪያ የሚሆነውን የተወሰነ ብር እንዲያበድረው ይጠይቀዋል። ጓደኛውም በሀዘኔታ የተባለውን ብር ቆጥሮ ይሰጠውና የጓደኝነት የእሳት ዳር ወጋቸውን ቀጠሉ። በመሐል ግን ፡ ብር የተበደረው ጋቭሮብ ከአንደኛው ኪሱ ውስጥ ሲጃራ ያወጣል ፣ ከሌላኛው ኪሱ ውስጥም ክብሪት ያወጣና ሲጃራውን ለኩሶ ማጨስ ይጀምራል። በዚህን ጊዜም ፡ አበዳሪው ጋቭሮብ "እስኪ ቅድም የሰጠሁክን ብር አንዴ ስጠኝ። በትክክል የቆጠርኩት አልመሰልኝምና ደግሜ ልቁጠረው!" በማለት ጓደኛውን ጠየቀው። ተበዳሪው ጋቭሮብም ምንም ሳያመነታ ብሩን አውጥቶ ድጋሚ ይቆጥረው ዘንድ ለአበዳሪው ጓደኛው ሰጠው። አበዳሪው ጋቭሮብም ብሩን በእጁ ካስገባ በኋላ ፡ ተበዳሪ ጓደኛውን "ጓደኛዬ ሆይ! ፊት ለፊትህ ይህን የመሠለ ቦግ ብሎ የነደደ እሳት እያለልህ ፡ ሲጃራህን ለመለኮስ አንዲት ክብሪትን በመጫር ያባከንክ ሰው ፡ ነገ ነግደህ ያበደርኩህን ብር ትመልሳለህ ብዬ ስለማላስብ ማበደሬን ትቼዋለሁኝ!" አለውና እሳቱ አጠገብ ቁጭ ያለውን ተበዳሪ ጓደኛውን ጥሎት ወደ ቤቱ ገባ!

ትንሽ ቀልድ መሳይ ታሪክ ናት። በውስጧ ግን ትልቅ አስተምህሮን አዝላለች።
ሰዎች ከአፋችን በሚወጡ ትናንሽ ቃላቶች ጭምር ማንነታችንን ይዳኛሉ። በምንተገብራት ትንሽ ተግባርም ብትሆን ሰለ ማንነታችን ይገምታሉ። ልክ በትልቅ ድስት የተሰራን ወጥ ፡ ጠብታውን ብቻ በመቅመስ "ወጡ ጨው አለው ወይም አንሶታል ፣ ወጡ ይጣፍጣል ወይም አይጣፍጥም... ወዘተ" እያልን የትልቁን ድስት ወጥን እንደምንዳኘው ሁሉ ማለት ነው። ሰዎችም ከውስጣችን በወጣች ትንሽ ቃልን በመስማትና ፡ ከልባችን የተገበርነው ትንሽ ተግባርን በመመልከት ማንነታችንን ይዳኛሉ!

በእለት ተእለት የምንተገብራቸው ትናንሽ ተግባሮችና የምናወራቸው ትናንሽ ቃላቶች የማንነታችን መገለጫ ናቸውና እራሳችንን ለመፈተሽ ይጠቅሙናል!

   
183 viewsBekele Ejeta, 23:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-03 01:38:28 ​መንግሥት እና ህወሃት በምን ጉዳዮች ተስማሙ?!

የፌዴራል መንግስት እና ህወሓት በዛሬው ዕለት በደቡብ አፍሪካ የሰላም ስምምነት ተፈራርመዋል። ከመንግሥት ምንጮች እንደተገኘው መረጃ ከሆነ ስምምነቱ ከነገ ጀመሮ ተግባራዊ ይሆናሉ የተባሉ ጉዳዮችን አካቷል።

ለስምንት ቀናት በከፍተኛ ውጥረትና ክርክር የተካሄደው ውይይት መቋጫ “ሁለቱም ወገኖች ጦርነቱን ከማቆም ውጭ አማራጭ እንደሌላቸው እንደተገነዘቡ የታየበት መደምደሚያ” ነው ተብሏል።

ተፈረመ የተባለው ስምምነት ሙሉ ቅጅ ገና ለሕዝብ ይፋ አልሆነም። ዋዜማ የደረሳት መረጃ ስምንት ጉዳዮችን ይዳስሳል። ይህንን ዝርዝር ከህወሓት ወይንም ከአድራዳሪዎቹ ወገን በቅርቡ የሚረጋገጥ ሆኖ እንደመከተለው አቅርበናቸዋል።

ቁልፍ የስምምነት አጀንዳዎች፦

1.ህወሓት ሙሉ በሙሉ ትጥቅ ለመፍታት መስማማቱን፦ በስምምነቱ መሰረት ከዛሬ ጀምሮ በሰላሳ ቀናት ውስጥ ቡድኑ ሙሉ በሙሉ ትጥቅ እንደሚፈታ፤ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ ለማድረግ የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች በ24 ሰዓት ውስጥ አመቺ ቦታ መርጠው ንግግር ያደርጋሉ፤

2.ስምምነቱ በተፈረመ አምስት ቀናት ውስጥ የሁለቱ ወገን ወታደራዊ አመራሮች የትጥቅ ማስፈታት ሂደቱ የሚመራበትን ዝርዝር አፈጻጻም በጋራ በማውጣት ተግባራዊ ሥራዎችን መሥራት ይጀምራሉ።

3. የሁለቱ ወገን ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች በተገናኙ አስር ቀናት ውስጥ ህወሓት ያሉትን ሁሉንም የቡድን እና ከባድ መሣሪያዎች ለመከላከያ ሠራዊት ያስረክባል።

4. ስምምነቱ በተፈረመ ሰባት ቀናት ውስጥ የፌደራል መንግሥት መቀሌን ተረክቦ በከተማው ውስጥ እና ዙሪያ ሁሉንም አይነት የጦር መሣሪያ ያስፈታል፤

5. በአጭር ቀናት ውስጥ አሁን ያለው የህወሓት መዋቅር ፈርሶ የፌደራል መንግሥት የሚመራው የጊዜያዊ አስተዳደር ይቋቋማል። በሚዋቀረው ጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥም የትግራይን ሕዝብ የሚወክል አካል ይሳተፋል።

6. የሀገር መከላከያ ሠራዊት ከጎረቤት ሀገራት የሚያዋስኑ የድንበር አካባቢዎችን ደኅንነትና ሰላም የሚያረጋግጥ ስምሪት የሚያደርግ ይሆናል። መከላከያ ሠራዊቱ በማንኛውም የትግራይ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ ሕግ የማስከበር ስልጣኑን ከህወሓት ሙሉ በሙሉ ይቀበላል። ህወሓት ለተግበራዊነቱ ምንም አይነት እንቅፋት እንደማይፈጥር ተስማምቷል።

7.የሚመሰረተው ጊዜያዊ አስተዳደር በሁሉም የትግራይ አካባቢዎች የማኅበራዊ አገልግሎቶች በፍጥነት እንዲጀመሩ ሁኔታዎች ያመቻቻል፤ ተግባራዊነታቸውን ያረጋግ8.ህወሓት ያለ ፌደራል መንግሥት እውቅና ከማንኛውም የውጭ አካል ጋር ግንኙነት ማድረግ ያቆማል። እንዲህ አይነት ተግባር የሚፈጹ ግለሰቦች ካሉ በሀገሪቱ ሕግ የሚጠየቁ ይሆናል።(
13 viewsBekele Ejeta, edited  22:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-11-01 03:46:24

14 viewsBekele Ejeta, 00:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-30 13:17:09


አንዳንድ ነገሮች



“ሊነጋ ነው…”

በረጅሙ የጨለማ ዘመን ውስጥ ሊነጋ ነው ብለው የሰበኩን የተስፋ ነጋዴዎች ብዙ ናቸው። ይነጋ ይሆን ብለው የጓጉ ገበያተኞች በአይነትም በጠገራ ብርም ተስፋ ሲገዙ፣ በተስፋ ብርቱ ሰልፍ ተሰልፈው ከድቅድቅ ሲፋለሙ ባጅተው አልፈዋል።

ተስፋ ግን አሁንም ተፈላጊ ሸቀጥ ሆኖ ቀጥሏል። “ሊነጋ ነው” ይልሃል ጀምበሩ ደመቀ። “ሊነጋ ሲል ይጨልማል” ይልሃል ዘማሪው የአሁን ጨለማ አይርታህ ሲል። “በል በርታ ታጠቅ!” ይልሃል ሃይለ ቃል የሚያትት አፈ ቀላጢ ወቀሳጢ።

ድቅድቁ ግን አልተረታም። ነጋ ተብለን ነቅተን ነበር ። ነጋልን እነሆ ደማቅ ጮራ ፈነጠቀ ብለን አረንጓዴ መስክና የሱፍ አበባ ልናይ ጓጉተን ተስፋ ሰነቅን። አይኖቻችንን በነጠላ ጫፍ አብሰን ብናይ ግን አይን ይወጋል ጨለማው። ከአይኖቻችን ቡኒ እዥ ፈሰሰ። ስንጨናበስ ከረምን። ተስፋ የጠበቁ አይኖች ዳፍንት ዳበረባቸው።

ተስፋ የሸጠልን ግን ከበረ።

ግድግዳዎቻችን ላይ “ሆፒንግ ኢዝ ሆፕለስ!”



አንዲት ታካሚ ለማነጋገር የተኛችበት ሄጄ ነበር። ሳይታወቀኝ ከሚገባው በላይ ተነጫነጭኩባት። እየወጣሁ ሳስበው የነበረው “ምን አድርጋኝ ነው እንዲህ የተቆናጠርኩባት?” ነበረ።

ሁሉም ሰው ይነጫነጫል ያለው። እኔም፣ ኮንሰልታንቱም፣ ሌሎች ሀኪሞችም ይቆናጠራሉ። ሆስፒታል ብቻ ሳይሆን ሁሉም ቦታ ነው። ሁሉም ሰው ነው። ምን ሆነን ነው?

ቀላል መልስ የለውም።

ወደቤቴ እያዘገምኩ እያሰብኩት ነበር።

ቀና መልስ የሚመልስ ሰው የለም። እንካ ስትለው ዓረፍተ ነገር፣ ሀይለ ቃል ይመልስልሃል ዘጠና ዘጠኝ።

መቼ ለት አንዱ ጀብራሬ መንገድ ላይ ያለምክንያት የአይን ቀለምህ አላማረኝም ብሎ ጥንብ እርኩሴን አወጣኝ። ደነቆርኩ ከስድቡ የተነሳ። ምን ሆነን ነው ይሄ ሁሉ tenderness አልኩ?

ቤቴ ስገባ አገኘሁት መልሱን።

አስቤዛ ስለመግዛት ማሰብ አለብኝ።



“Is your brain a vestigial organ?“

*insert Alfred Hitchcock's voice*

አንዱ በጥይት ጭንቅላቱን ተመትቶ መጥቶ የተጎዳውን አንጎሉን በቀዶ ህክምና ተወገደለትና ወደቤቱ ተመለሰ። debridement።

ከሳምንታት በኋላ በቀጠሮ ሲመጣ አስታማሚው “አሁንማ ተሽሎት ከበፊቱ የተሻለ ሰው ሆኗል” ብሎ ቀለደ።

አባባሉ አየር ላይ እየተንገዋለለች ቀረች።

“የተሻለ ሰው ሆኗል”፤ “አንጎሉ ጎድቶት ነበረንስ?” ፤“የማይጠቅም አንጎል ይዞ ይዞር ነበረን?”፤ “are we heading back to a fast track evolution where we don't need our frontal cortexes anymore?"

ባዮሎጂው ባያስኬድም አነዋወራችን ግን ይናገራል። የማንጠቀምበት የአንጎል ሸክም ግንባራችን ስር አለ።

አንቱ፥ ማጣፊያ አጥሮዎ ተቸግረዋል? እንኪያስ አንጎልዎን ያስቀንሱት። ህይወትዎን በተሻለ ያጣጥሙ።



“በሰማይ ላም አለኝ። በሬም ጭምር። ቤትና መኪናም። ድራፍት በማድጋ እጠጣለሁ፣ የተገኘውን ሁላ ፋክ አደርጋለሁ።”

— ወድቆ የተገኘ ዋሌት ውስጥ የነበረ ህልም።
36 viewsBekele Ejeta, 10:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 08:19:31
ትውልደ ህንዳዊው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ

የ42 ዓመቱ ትውልደ ህንዳዊው ሪሺ ሱናክ አዲሱ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስተር ሆነው ተሾሙ። ሪሽ ሱናክ በዛሬው እለት የእንግሊዝ ገዢ ፓርቲ የሆነው የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ ሊቀ መንበር ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ ቀጣይ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆኑ ተረጋግጧል።

ትውልደ ህንዳዊው ሪሺ ሱናክ ከዚህ ቀደም የእንግሊዝ የፋይናንስ ሚኒስትር ሆነው በቀድሞ ጠቅላይ ቦሪስ ጆነሰን ተሹመው ነበር። በጠቅላይ ሚኒስትርነት ፉክክሩም ቦሪስ ጆንሰን ራሳቸውን ማግለላቸውን ተከትሎ በአብላጫ ድምፅ ሀገሪቱን እንዲያስተዳድሩ ተመርጠዋል። ለ45 ቀናት በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገልግለው በቃኝ ያሉትን ሊዝ ትረስን በመተካት ሪሺ ሱናክ ከቀደሞው አለቃቸው ቦሪስ ጆነሰን ጋር ቢወዳዳሩም ቦሪስ ጆንሰን በትላንትናው ዕለት እራሳቸውን ከእጩነት አግልለዋል።

ህንድ የእንግሊዝ የረጅም ጊዜ ቅኝ ተገዢ ሀገር የነበረች ቢሆንም ሪሽ ሱናክ በአመራር ልምዳቸው አብዛኛው የፓርቲያቸው አባላት ድጋፋቸውን ሰጥተዋቸዋል። ሪሽ ሱናክ በፈረንጆች 2016 በእንግሊዝ በተደረገው የአውሮፓ ህብረት አባልነት ምርጫ ላይ ሀገራቸው ከአውሮፓ ህብረት እንድትወጣ መርጠው ነበር
72 viewsBekele Ejeta, 05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 08:11:04
ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ዛሬ በአውሮፓ እና ኤሲያ ይታያል !

ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ዛሬ ጥቅምት 15 ቀን 2015ዓም (ኦክቶበር 25 ቀን 2022) በተለያዩ የአውሮፓ እና የኤሲያ ክፍሎች ይታያል።

የ2022 የፀሐይ ግርዶሽ በጥቅምት 15 ቀን 2015 በ 08፡58 ጂኤምቲ በኢትዮጵያ (5ሰዓት ከ58 አካባቢ) ይጀምራል፣ ከዛ በ13፡02 GMT (በኢትዮጵያ 7ሰዓት አካባቢ) ያበቃል።

የሚታዩባቸው አንዳንድ ከተሞች እና የፀሐይ ሽፋን በፐርሰንት

ስቶክሆልም፣ ስዊድን (46.20%)
ሄልሲንኪ፣ ፊንላንድ (54.03%)
ኦስሎ፣ ኖርዌይ (39.28%)
ታሊን፣ ኢስቶኒያ (53.22%)
ኪየቭ፣ ዩክሬን (51.30%)
ቼልያቢንስክ፣ ሩሲያ (78.70%)
ቴህራን፣ ኢራን (55.36%)
ኒው ዴሊ፣ ህንድ (43.96%)

የፀሐይ ብርሀን መጠን (86.2%) ሆኖ በሩሲያ በምእራብ ሳይቤሪያ ይታያል። ይህ መጠን በቻይና ሰሜናዊ ምዕራብ አካባቢ ወደ 70% እና በኖርዌይ እና ፊንላንድ ሰሜናዊ ምስራቅ ክፍሎች ወደ 63-62% ቀንሶ ይታያል። ግርዶሹን በቀጥታ በዓይን መመልከት በእይታ ላይ ከፍተኛ አደጋ ይፈጥራል እና መመልከቻ መጠቀም የግድ ነው።
49 viewsBekele Ejeta, 05:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-25 07:58:47 በፊሊፒንስ ተማሪዎች ፈተና እንዳይሰርቁ ፊታቸውን እንዲሸፍኑ ተደረገ

በማህበራዊ ትስስር ገጾች መነጋገሪያ የሆነው ''የፀረ-ኩረጃ ኮፍያ''

ተማሪዎች ፈተና እንዳይሰርቁ በተለያዩ ዓለማት የተለያዩ ተግባራትን ይጠቀማሉ፡፡ ይህ ተግባር የተለመደ ቢሆንም ከሰሞኑ ፊሊፒንስ ተማሪዎች ፈተና እንዳይሰርቁ ወሰደችው እርምጃ ግን መነጋገርያ ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያ ዘንድሮ የወሰደችውን እርምጃን ጨምሮ በርካታ የዓለማችን ሀገራት በራሳቸው ጥረት የሚሰጣቸውን ፈተና እንዲያልፉ የተለያዩ እርምጃዎች ይወሰዳሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ ትላልቅ የመፈተኛ አከባቢዎችን ማዘጋጀት አንዱ ሲሆን ይህም ዋና ዓላማው ጥራት ያለውን ትምህርት ለሀገር ግንባታ ያለውን እስተዋፅኦ ለመጠበቅ ነው፡፡

ይሁን እንጅ ከሰሞኑ የፊሊፒንስ መንግስት የወሰደው እርምጃ የዓለምን ትኩር ስቦ ታይቷል፡፡ፊሊፒንስ የኮሌጅ ፈተና ለመፈተን እየተሰናዳች ባለችበት ግዜ የተማሪዎች ፈተና ኩረጃ እጅጉንም እንዳሳሰባት ትገልፃለች፡፡ ይህን ተከትሎ መንግስት እንድ ውሳኔ እንዲወሰን እና በውሳኔው መሰረት ዘመቻ እንዲደረግ ትእዛዝ እንዲተላለፍ ተደርጓል፡፡ ይህም ትእዛዝ ''የፀረ-ኩረጃ ኮፍያ'' የሚል ነው፡፡

ኮሌጅ ፈተና ተፈታኝ የነበሩት የሌጋዝቢ ከተማ ተማሪዎች ፊታቸውን የሚሸፍን የፀረ ኩረጃ ኮፍያ እንዲያደርጉ ሲጠየቁ ሁሉም ተማሪ ካገኘው ነገር ሁሉ ኮፍያ ይሆንልኛል ብሎ ያሰበዉን ሰርቶ በመምጣት ፈተና ላይ ተቀምጠዋል። የተማሪዎቹ ውሳኔ ተመችቶኛል ያለው የፊሊፒንስ መንግስት በዚህ ሂደት ውስጥ ሲኮርጅ የታየ ተማሪ የለም በማለት ፈተና ላይ እንዲቀመጡ የተደረጉ ተማሪዎች በሙሉ ፈተናቸዉን በአግባቡ መፈተናቸውን አስታውቋል፡፡

ተማሪዎቹ በየቤታቸው ወዳድቀው ከሚገኙ ቁሳቁሶች የመሸፈኛ ባርኔጣቸዉን የሰሩ ሲሆን የእንቁላል ማሰቀመጫ፣ ካርቶን እና የወዳደቁ ፒላቲኮች ኮፍያዎቹ ከተሰሩባቸው ግብዓቶች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው። ሃሳቡን እንዳመጡ ሚነገርላቸው በቢኮል ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ኮሌጅ መምህርት ሜሪ ጆይ ማንዳኔ (ፕ/ር) ወደዚህ ሃሳብ እንዲመጡ የፈለጉት ተማሪዎች እየተዝናኑ ታማኝነትን እንዲለማመዱ በማሰብ ብለዋል፡፡

ታድያ ሃሳባቸው ውጤታማ እንደሆነ ነው የተነገረላቸው፡፡ በዚህ አጋጣሚ የተስተዋለው ነገር ተማሪዎቹ ታማኝንነትን ተለማመዱበት ብቻ ሳይሆን ውስብስብ ናቸው የተባሉ የተለየ የፈጠራ ስራም የታየበት መሆኑ የበርካቶችን ትኩረት ስቧል፡፡ መምህርቷ ተማሪዎቿን ፎቶ በማህበራዊ ገፅዋ ላይ ለጥፋት በጥቂት ደቂቃ ውስጥ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ተጋርተውታል፡፡ በተጨማሪ ሌሎች ኮሌጆች ይህን ፈለግ እንዲከተሉ አነሳስቷል የተባለ ሲሆን በፈተናው ላይ የተሳተፉ ተማሪዎችም የተሸለ ውጤት እንዲያመጡ እንደረዳቸው ተነግሯል።
54 viewsBekele Ejeta, 04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ