Get Mystery Box with random crypto!

በፊሊፒንስ ተማሪዎች ፈተና እንዳይሰርቁ ፊታቸውን እንዲሸፍኑ ተደረገ በማህበራዊ ትስስር ገጾች መነ | Our World

በፊሊፒንስ ተማሪዎች ፈተና እንዳይሰርቁ ፊታቸውን እንዲሸፍኑ ተደረገ

በማህበራዊ ትስስር ገጾች መነጋገሪያ የሆነው ''የፀረ-ኩረጃ ኮፍያ''

ተማሪዎች ፈተና እንዳይሰርቁ በተለያዩ ዓለማት የተለያዩ ተግባራትን ይጠቀማሉ፡፡ ይህ ተግባር የተለመደ ቢሆንም ከሰሞኑ ፊሊፒንስ ተማሪዎች ፈተና እንዳይሰርቁ ወሰደችው እርምጃ ግን መነጋገርያ ሆኗል፡፡ ኢትዮጵያ ዘንድሮ የወሰደችውን እርምጃን ጨምሮ በርካታ የዓለማችን ሀገራት በራሳቸው ጥረት የሚሰጣቸውን ፈተና እንዲያልፉ የተለያዩ እርምጃዎች ይወሰዳሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ ትላልቅ የመፈተኛ አከባቢዎችን ማዘጋጀት አንዱ ሲሆን ይህም ዋና ዓላማው ጥራት ያለውን ትምህርት ለሀገር ግንባታ ያለውን እስተዋፅኦ ለመጠበቅ ነው፡፡

ይሁን እንጅ ከሰሞኑ የፊሊፒንስ መንግስት የወሰደው እርምጃ የዓለምን ትኩር ስቦ ታይቷል፡፡ፊሊፒንስ የኮሌጅ ፈተና ለመፈተን እየተሰናዳች ባለችበት ግዜ የተማሪዎች ፈተና ኩረጃ እጅጉንም እንዳሳሰባት ትገልፃለች፡፡ ይህን ተከትሎ መንግስት እንድ ውሳኔ እንዲወሰን እና በውሳኔው መሰረት ዘመቻ እንዲደረግ ትእዛዝ እንዲተላለፍ ተደርጓል፡፡ ይህም ትእዛዝ ''የፀረ-ኩረጃ ኮፍያ'' የሚል ነው፡፡

ኮሌጅ ፈተና ተፈታኝ የነበሩት የሌጋዝቢ ከተማ ተማሪዎች ፊታቸውን የሚሸፍን የፀረ ኩረጃ ኮፍያ እንዲያደርጉ ሲጠየቁ ሁሉም ተማሪ ካገኘው ነገር ሁሉ ኮፍያ ይሆንልኛል ብሎ ያሰበዉን ሰርቶ በመምጣት ፈተና ላይ ተቀምጠዋል። የተማሪዎቹ ውሳኔ ተመችቶኛል ያለው የፊሊፒንስ መንግስት በዚህ ሂደት ውስጥ ሲኮርጅ የታየ ተማሪ የለም በማለት ፈተና ላይ እንዲቀመጡ የተደረጉ ተማሪዎች በሙሉ ፈተናቸዉን በአግባቡ መፈተናቸውን አስታውቋል፡፡

ተማሪዎቹ በየቤታቸው ወዳድቀው ከሚገኙ ቁሳቁሶች የመሸፈኛ ባርኔጣቸዉን የሰሩ ሲሆን የእንቁላል ማሰቀመጫ፣ ካርቶን እና የወዳደቁ ፒላቲኮች ኮፍያዎቹ ከተሰሩባቸው ግብዓቶች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው። ሃሳቡን እንዳመጡ ሚነገርላቸው በቢኮል ዩኒቨርሲቲ የምህንድስና ኮሌጅ መምህርት ሜሪ ጆይ ማንዳኔ (ፕ/ር) ወደዚህ ሃሳብ እንዲመጡ የፈለጉት ተማሪዎች እየተዝናኑ ታማኝነትን እንዲለማመዱ በማሰብ ብለዋል፡፡

ታድያ ሃሳባቸው ውጤታማ እንደሆነ ነው የተነገረላቸው፡፡ በዚህ አጋጣሚ የተስተዋለው ነገር ተማሪዎቹ ታማኝንነትን ተለማመዱበት ብቻ ሳይሆን ውስብስብ ናቸው የተባሉ የተለየ የፈጠራ ስራም የታየበት መሆኑ የበርካቶችን ትኩረት ስቧል፡፡ መምህርቷ ተማሪዎቿን ፎቶ በማህበራዊ ገፅዋ ላይ ለጥፋት በጥቂት ደቂቃ ውስጥ በብዙ ሺሕ የሚቆጠሩ ሰዎች ተጋርተውታል፡፡ በተጨማሪ ሌሎች ኮሌጆች ይህን ፈለግ እንዲከተሉ አነሳስቷል የተባለ ሲሆን በፈተናው ላይ የተሳተፉ ተማሪዎችም የተሸለ ውጤት እንዲያመጡ እንደረዳቸው ተነግሯል።