ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ዛሬ በአውሮፓ እና ኤሲያ ይታያል !ከፊል የፀሐይ ግርዶሽ ዛሬ ጥቅምት 15 ቀን 2015ዓም (ኦክቶበር 25 ቀን 2022) በተለያዩ የአውሮፓ እና የኤሲያ ክፍሎች ይታያል።
የ2022 የፀሐይ ግርዶሽ በጥቅምት 15 ቀን 2015 በ 08፡58 ጂኤምቲ በኢትዮጵያ (5ሰዓት ከ58 አካባቢ) ይጀምራል፣ ከዛ በ13፡02 GMT (በኢትዮጵያ 7ሰዓት አካባቢ) ያበቃል።
የሚታዩባቸው አንዳንድ ከተሞች እና የፀሐይ ሽፋን በፐርሰንት
ስቶክሆልም፣ ስዊድን (46.20%)
ሄልሲንኪ፣ ፊንላንድ (54.03%)
ኦስሎ፣ ኖርዌይ (39.28%)
ታሊን፣ ኢስቶኒያ (53.22%)
ኪየቭ፣ ዩክሬን (51.30%)
ቼልያቢንስክ፣ ሩሲያ (78.70%)
ቴህራን፣ ኢራን (55.36%)
ኒው ዴሊ፣ ህንድ (43.96%)
የፀሐይ ብርሀን መጠን (86.2%) ሆኖ በሩሲያ በምእራብ ሳይቤሪያ ይታያል። ይህ መጠን በቻይና ሰሜናዊ ምዕራብ አካባቢ ወደ 70% እና በኖርዌይ እና ፊንላንድ ሰሜናዊ ምስራቅ ክፍሎች ወደ 63-62% ቀንሶ ይታያል። ግርዶሹን በቀጥታ በዓይን መመልከት በእይታ ላይ ከፍተኛ አደጋ ይፈጥራል እና መመልከቻ መጠቀም የግድ ነው።