Get Mystery Box with random crypto!

ትውልደ ህንዳዊው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ የ42 ዓመቱ ትውልደ ህንዳዊው ሪሺ ሱናክ አዲሱ | Our World

ትውልደ ህንዳዊው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆኑ

የ42 ዓመቱ ትውልደ ህንዳዊው ሪሺ ሱናክ አዲሱ የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስተር ሆነው ተሾሙ። ሪሽ ሱናክ በዛሬው እለት የእንግሊዝ ገዢ ፓርቲ የሆነው የኮንሰርቫቲቭ ፓርቲ ሊቀ መንበር ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ የሀገሪቱ ቀጣይ ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆኑ ተረጋግጧል።

ትውልደ ህንዳዊው ሪሺ ሱናክ ከዚህ ቀደም የእንግሊዝ የፋይናንስ ሚኒስትር ሆነው በቀድሞ ጠቅላይ ቦሪስ ጆነሰን ተሹመው ነበር። በጠቅላይ ሚኒስትርነት ፉክክሩም ቦሪስ ጆንሰን ራሳቸውን ማግለላቸውን ተከትሎ በአብላጫ ድምፅ ሀገሪቱን እንዲያስተዳድሩ ተመርጠዋል። ለ45 ቀናት በጠቅላይ ሚኒስትርነት አገልግለው በቃኝ ያሉትን ሊዝ ትረስን በመተካት ሪሺ ሱናክ ከቀደሞው አለቃቸው ቦሪስ ጆነሰን ጋር ቢወዳዳሩም ቦሪስ ጆንሰን በትላንትናው ዕለት እራሳቸውን ከእጩነት አግልለዋል።

ህንድ የእንግሊዝ የረጅም ጊዜ ቅኝ ተገዢ ሀገር የነበረች ቢሆንም ሪሽ ሱናክ በአመራር ልምዳቸው አብዛኛው የፓርቲያቸው አባላት ድጋፋቸውን ሰጥተዋቸዋል። ሪሽ ሱናክ በፈረንጆች 2016 በእንግሊዝ በተደረገው የአውሮፓ ህብረት አባልነት ምርጫ ላይ ሀገራቸው ከአውሮፓ ህብረት እንድትወጣ መርጠው ነበር