Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንድ ነገሮች ① “ሊነጋ ነው…” በረጅሙ የጨለማ ዘመን ውስጥ ሊነጋ ነው ብለው የሰበኩ | Our World




አንዳንድ ነገሮች



“ሊነጋ ነው…”

በረጅሙ የጨለማ ዘመን ውስጥ ሊነጋ ነው ብለው የሰበኩን የተስፋ ነጋዴዎች ብዙ ናቸው። ይነጋ ይሆን ብለው የጓጉ ገበያተኞች በአይነትም በጠገራ ብርም ተስፋ ሲገዙ፣ በተስፋ ብርቱ ሰልፍ ተሰልፈው ከድቅድቅ ሲፋለሙ ባጅተው አልፈዋል።

ተስፋ ግን አሁንም ተፈላጊ ሸቀጥ ሆኖ ቀጥሏል። “ሊነጋ ነው” ይልሃል ጀምበሩ ደመቀ። “ሊነጋ ሲል ይጨልማል” ይልሃል ዘማሪው የአሁን ጨለማ አይርታህ ሲል። “በል በርታ ታጠቅ!” ይልሃል ሃይለ ቃል የሚያትት አፈ ቀላጢ ወቀሳጢ።

ድቅድቁ ግን አልተረታም። ነጋ ተብለን ነቅተን ነበር ። ነጋልን እነሆ ደማቅ ጮራ ፈነጠቀ ብለን አረንጓዴ መስክና የሱፍ አበባ ልናይ ጓጉተን ተስፋ ሰነቅን። አይኖቻችንን በነጠላ ጫፍ አብሰን ብናይ ግን አይን ይወጋል ጨለማው። ከአይኖቻችን ቡኒ እዥ ፈሰሰ። ስንጨናበስ ከረምን። ተስፋ የጠበቁ አይኖች ዳፍንት ዳበረባቸው።

ተስፋ የሸጠልን ግን ከበረ።

ግድግዳዎቻችን ላይ “ሆፒንግ ኢዝ ሆፕለስ!”



አንዲት ታካሚ ለማነጋገር የተኛችበት ሄጄ ነበር። ሳይታወቀኝ ከሚገባው በላይ ተነጫነጭኩባት። እየወጣሁ ሳስበው የነበረው “ምን አድርጋኝ ነው እንዲህ የተቆናጠርኩባት?” ነበረ።

ሁሉም ሰው ይነጫነጫል ያለው። እኔም፣ ኮንሰልታንቱም፣ ሌሎች ሀኪሞችም ይቆናጠራሉ። ሆስፒታል ብቻ ሳይሆን ሁሉም ቦታ ነው። ሁሉም ሰው ነው። ምን ሆነን ነው?

ቀላል መልስ የለውም።

ወደቤቴ እያዘገምኩ እያሰብኩት ነበር።

ቀና መልስ የሚመልስ ሰው የለም። እንካ ስትለው ዓረፍተ ነገር፣ ሀይለ ቃል ይመልስልሃል ዘጠና ዘጠኝ።

መቼ ለት አንዱ ጀብራሬ መንገድ ላይ ያለምክንያት የአይን ቀለምህ አላማረኝም ብሎ ጥንብ እርኩሴን አወጣኝ። ደነቆርኩ ከስድቡ የተነሳ። ምን ሆነን ነው ይሄ ሁሉ tenderness አልኩ?

ቤቴ ስገባ አገኘሁት መልሱን።

አስቤዛ ስለመግዛት ማሰብ አለብኝ።



“Is your brain a vestigial organ?“

*insert Alfred Hitchcock's voice*

አንዱ በጥይት ጭንቅላቱን ተመትቶ መጥቶ የተጎዳውን አንጎሉን በቀዶ ህክምና ተወገደለትና ወደቤቱ ተመለሰ። debridement።

ከሳምንታት በኋላ በቀጠሮ ሲመጣ አስታማሚው “አሁንማ ተሽሎት ከበፊቱ የተሻለ ሰው ሆኗል” ብሎ ቀለደ።

አባባሉ አየር ላይ እየተንገዋለለች ቀረች።

“የተሻለ ሰው ሆኗል”፤ “አንጎሉ ጎድቶት ነበረንስ?” ፤“የማይጠቅም አንጎል ይዞ ይዞር ነበረን?”፤ “are we heading back to a fast track evolution where we don't need our frontal cortexes anymore?"

ባዮሎጂው ባያስኬድም አነዋወራችን ግን ይናገራል። የማንጠቀምበት የአንጎል ሸክም ግንባራችን ስር አለ።

አንቱ፥ ማጣፊያ አጥሮዎ ተቸግረዋል? እንኪያስ አንጎልዎን ያስቀንሱት። ህይወትዎን በተሻለ ያጣጥሙ።



“በሰማይ ላም አለኝ። በሬም ጭምር። ቤትና መኪናም። ድራፍት በማድጋ እጠጣለሁ፣ የተገኘውን ሁላ ፋክ አደርጋለሁ።”

— ወድቆ የተገኘ ዋሌት ውስጥ የነበረ ህልም።