Get Mystery Box with random crypto!

ሊባኖሳዊቷ ሳሊ ሃፊዝ ገንዘቧን ወደምትቆጥብበት ቤይሩት ውስጥ ወደሚገኘው ብሎም ባንክ ሄዳ ማናጀሩን | Our World

ሊባኖሳዊቷ ሳሊ ሃፊዝ ገንዘቧን ወደምትቆጥብበት ቤይሩት ውስጥ ወደሚገኘው ብሎም ባንክ ሄዳ ማናጀሩን ማናገር እንደምትፈልግ ነግራ ወደማናጀሩ ቢሮ በማምራት የመጣችበትን ጉዳይ ከእንባዋ ጋር እየታገለች አስረዳችው ።
..................
እኔ የዚህ ባንክ የአመታት ደንበኛ ነኝ ። በተደጋጋሚ እየመጣሁ ለባንክ ሰራተኞቹ ጉዳዬን ባስረዳም ምንም መፍትሄ ሊሰጡኝ አልቻሉም ። እህቴ በከፍተኛ ሁኔታ በካንሰር ተይዛ ህመም ላይ ነች ። ከህመሟ እንድታገግም ብር ያስፈልጋታል ። እናም እዚህ ባንክ የቆጠብኩትን 12 ሺህ ዶላር በሙሉ አውጥቼ እህቴን ከስቃይ ማዳን እፈልጋለሁ ። እርዳኝ ስትል ተማፀነችው ።
......................
የባንኩ ማናጀር ጉዳዩ አሳዛኝ ቢሆንም ፡ ለባንኮች በወጣው ህግ መሰረት ፡ በወር ከ200 ዶላር በላይ ሊሰጣት እንደማይችል ነገራት ። ሳሊ ሃፊዝ ይህን መልስ ወደባንኩ በተመላለሰች ቁጥር ሰምታዋለች ። ዛሬ ማናጀሩን ቀርባ ያናገረችው ፡ የችግሯን አሳሳቢነት ተረድቶ መፍትሄ እንደሚሰጣት ገምታ ነበር ። ሆኖም ፡ የተለየ ነገር አልጠበቃትም ። ሳሊ የባንኩን ማናጀር መለመን ያዘች ። አዝናለሁ በርግጥ የራስሽ ብር ቢሆንም በገጠመን የኤኮኖሚ ግሽበት ምክንያት የወጣውን  ህግ ተላልፈን ልንረዳሽ አንችልም ፡ ሲል ቁርጥ ያለ ምላሽ ሰጣት ።
................
ሳሊ ሃፊዝ የማናጀሩን ምላሽ እንደሰማች ወደ ቤቷ በማምራት ፡ በሶሻል ሚዲያ ከምታውቃቸው ሰወች ጋር በጉዳዩ ላይ አውርታ ፡ ነገ ልታደርግ ያሰበችውን ነገር ነገረቻቸው ። የሳሊ ጓደኞች እቅዷን እንደሰሙ አብረዋት እንደሚቆሙ ቃል ገብተውላት ፡ በማግስቱ የሚገናኙበትን ቦታ ተቀጣጥረው ተለያዩ ።
................
በማግስቱ ጠዋት ሳሊ ሃፊዝና ጓደኞቿ ገንዘቧን ወዳስቀመጠችበት ብሎም ባንክ አመሩ ።
.................
ወደባንኩ እንደገቡም ፡ ሳሊ ሃፊዝ የባንኩ ባንኮኒ ላይ ወጥታ  ከወገቧ ስር ያስቀመጠችውን ሽጉጥ በማውጣት ፡ እየጮኸች መናገር ጀመረች ። በባንኩ ውስጥ ይስተናገዱ የነበሩት ደንበኞች በድንጋጤ መርበትበት  ጀመሩ ።
..................

አንድም ሰው እንዳይንቀሳቀስ ፡ እኔ ማንንም ሰው ለመግደል አልመጣሁም ፡ ሳሊ ሃፊዝ እባላለሁ ፡ የዚህ ባንክ ደንበኛ ነኝ ፡ በዚህ ወቅት እህቴ በካንሰር ታማ ሆስፒታል ትገኛለች ፡ በዚህ ባንክ የቆጠብኩትን ገንዘብ አውጥቼ እህቴን ለማሳከም የባንኩን ሰራተኞችና ማናጀሩን ጠይቄ ምላሽ ስላጣሁ በዚህ መልኩ ገንዘቤን ለመውሰድ መጥቻለሁ ።
..........
ይህን እንደሰሙ የባንኩ ሰራተኞችና ማናጀሩ በድንጋጤ መተያየት ጀመሩ ፡ ሳሊ ሃፊዝ ወደነሱ እያየች በፍጥነት የራሷን ብር እንደምትፈልግና ይህን ካላደረጉ የባንኩ ሰራተኞችና ባንኩ ላይ እርምጃ እንደምትወስድ ተናግራ ፡  ፡ ከሷ ጋር ለመጡት ጓደኞቿ ምልክት አሳየቻቸው ። በዚህ ጊዜ የሳሊ ጓደኞች በትንሽ ጀሪካን የያዙትን ጋዝ  ባንክ ቤቱ ወለል ላይ ማርከፍከፍ ጀመሩ ።

................
የባንክ ሰራተኞቹ ገንዘቧን ካልሰጧት ጉዳቱ የከፋ እንደሆነ ስላወቁ ፡ በባንኩ ውስጥ የቆጠበችውን 12 ሺህ ዶላር ቆጥረው ሰጧት ። ሳሊ በፍጥነት ከቆመችበት የባንኩ ባንኮኒ ላይ ወርዳ ለመውጣት ወደበሩ ሲያመሩ ፡ ባንኩ በፖሊስ እንደተከበበ አወቁ በዚህ ጊዜ በሌኛው የባንኩ ጎን ያለውን ትልቅ መስታወት በመስበር ገንዘባቸውን ይዘው አመለጡ ።
........................
ይህ ጉዳይ ከተሰማ በኋላ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ሳይቀሩ ፡ ከሳሊ ሃፊዝ ጋር በመቆም ፡ ወጣቷ ማንንም እንዳልጎዳች ፡ ከቆጠበችው ገንዘብ ውጭም አንዳች የባንኩን ብር እንዳልወሰደች በመግለፅ ፡ እህቷን ከስቃይ ለማዳን ያደረገችው የሰብአዊነት ተግባር እንጂ ፡ አንዳች ወንጀል አልፈፀመችም ፡ በመሆኑም ተጠያቂ መሆን የለባትም በማለት ከጎኗ እየቆሙ ነው  ።
....................
ሳሊ ሃፊዝ የወሰደችውን ገንዘብ ለእህቷ መታከሚያ እንዲውል መክፈሏ ታውቋል ። ከሷ ጋር ሆነው ባንኩን ካስገደዱት ወጣቶች መሃከል የተወሰኑትን መያዙን ፖሊስ ቢያስታውቅም ፡ ሳሊ፡ሃፊዝን በተመለከተ ግን የሚወጡት  መረጃዎች የተለያዩ ናቸው ፡ አንዳንዶቹ ከሃገር መውጣቷን ሲገልፁ ሌሎቹ ግን እዛው ሊባኖስ ውስጥ እንዳለች ተናግረዋል ።
..................
  ስለጉዳዩ በቅርበት የሚያውቁ ሰወች እንደገለፁት ግን   ከወንድሟ ልጅ በወሰደችው ፡ አርቲፊሻል የልጆች ሽጉጥ ባንክን አስገድዳ ገንዘቧን የወሰደችው ሳሊ ሃፊዝ እስካሁን በፖሊስ አልተያዘችም