Get Mystery Box with random crypto!

Our World

የቴሌግራም ቻናል አርማ ourworl_d — Our World O
የቴሌግራም ቻናል አርማ ourworl_d — Our World
የሰርጥ አድራሻ: @ourworl_d
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 894

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-03-02 09:59:03 ባል የሚገዛበት የህንዱ የሙሽራ ገበያ
በህንድ ቢሃር ግዛት የሚገኘው ገበያው 700 ዓመታትን ያስቆጠረ ነው


ባል የሚፈልጉ ሴቶች ከቤተሰቦቻቸው ጋር በመሆን ወደ ገበያው ሄደው መግዛት ይችላሉ
ከ700 ለሚበልጡ ዓመታት የህንድ የቢሃር ግዛት ሴቶች እና ቤተሰቦቻቸው ባል የሚገዙበትን ልዩ የሙሽራ ገበያ እያስተናገደች ነው።
በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ወንዶች በህንድ ቢሃር ግዛት ማዱባኒ በተባለ በአከባቢ ወደሚገኘው የገበያ ቦታ በመሄድ ፒፓል ዛፎች ስር የሚሰበሰቡ ሲሆን፤ እዛ በመሆንም ሚስት የምትሆናቸው ሴት እስክትመርጣቸው ድረስ ይጠባበቃሉ።
የሙሽራ ገበያው “ሳውራት ሜላ” ወይም “ሳባጋቺሂ” እየተባለ የሚጠራ ሲሆን፤ በዓመት አንድ ጊዜ የሚቆምና ለ9 ቀናት የሚቆይ መሆኑን ከኦዲቲ ሴንትራል ድረ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በራጃ ሃሪ ሲንግ የካርናት ስርወ መንግስት ከ700 መቶ ዓመታት በፊት እንደተጀመረ የሚነገርለት ይህ የባል ገበያ ሴቶች ይሆነኛል ብለው ያመኑበትን ባል እንዲመርጡ ለማስቻል እንደተጀመረ ተግሯል።
በገበያው ባል ለመሆን ለሚቀርቡ ለእያንዳንዱ ሙሽራ የትምህርት ደረጃቸውን እና የቤተሰቡን የኑሮ ሁኔታ መሰረት ባድረገ መልኩ ዋጋ የሚቆረጥለት መሆኑም ተነግሯል።
የቢሃር ባህላዊ የሙሽራ ገበያ ኢንጂነሮች፣ ዶክተሮች እና የመንግስት ሰራተኞች በጣም እንደሚፈለጉ የሚነገር ሲሆን፤ ወጣቶች በጣም ተወዳጅ እንደሆኑ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በባል መረጣ እና ግዢው ላይ ከሙሽሪት ይልቅ ለቤተሰቦቿ ምርጫ ቅድሚያ የሚሰጥ ሲሆን፤ በዚህም ጥሩ ልምድ ያለውን ባል በተመጣጣኝ ዋጋ በማመዛዘን የሚወሰን ይሆናል።
ምንም እንኳን ጥሎሽ በህንድ ውስጥ በይፋ ህገ-ወጥ ቢሆንም፣ አሁንም ወጣት እና ብቁ የሆኑ ዋት ያላገቡ ወንዶች ከሙሽሪት ቤተሰብ ከፍተኛ ጥሎሽ እንደሚጠይቁ ይነገራል፤ የሙሽራ ገበያው ዋነኛ ዓላምም ጥሎሽለን ለማስቀረት ያለመ ነው ተብሏል።
የሚያስገርመው በህንድ የባል ገበያ እንዳለ ሁሉ የሚስት ገበያም መኖሩ ሲሆን፤ በህንድ ሃውዳቲ ውስጥ በሚገኘው የሙሽሪት ገበያ እንደየብቃታቸው እና የቤት ስራ ችሎታቸው ለተለያዩ ዋጋዎች ተቆርጦላቸው ያገባሉ!
27 viewsBekele Ejeta, edited  06:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 01:51:24
የናይጄሪያ እግር ኳስ ክለብ መሪ ሜዳ ውስጥ ውሃ ሽንት ሲሸኑ በመገኘታቸው ተቀጡ

የናይጄሪያ እግር ኳስ ባለስልጣናት በኢባዳ የሚገኘውን የአንደኛ ዲቪዚዮን ክለብ ወደ 1,000 ዶላር የገንዘብ ቅጣት በክለቡ አንድ ባለስልጣን ላይ የጣለ ሲሆን በመጫወቻ ሜዳ ላይ ውሃ ሽንህ ሲሸኑ መታየታቸውን ተከትሎ ነው።

ድርጊቱ የተፈፀመው እሁድ እለት ባለሜዳው ሹቲንግ ስታርስ በሜዳቸው ከአክዋ ዩናይትድ ጋር ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት የተነሳ ፎቶ መሆኑ ተመላክቷል። ድርጊቱን ፈፅመዋል የተባሉት አውዋል መሀመድ ከናይጄሪያ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ሊግ (NPFL) ጋር በተገናኘ ከማንኛውም እንቅስቃሴ ለአንድ አመት ታግደዋል። የናይጄሪያን ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ሊግ የሚያስተዳድረው አካል ጊዚያዊ አስተዳደር ኮሚቴ ለሹቲንግ ስታርስ በጻፈው ደብዳቤ ጨዋታውን ያዋረደ “አጸያፊ ተግባር” ሲል ገልጿል።

"የባለስልጣኖቻችሁን ስነምግባር መቆጣጠር እንደተሳናችሁ ማሳያው አውዋል መሀመድ በጨዋታ ሜዳ ላይ ውሃ ሽንታቸውን በተመልካች ህዝብ ፊት እንዲህ ማድረጋቸው ነው" ሲል መግለጫው አክሏል።
5 viewsBekele Ejeta, 22:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 01:51:24
በቻይና አንድ ሙሽራ በሰርጉ እለት የእኛም ፍቅረኛ ነበረ ያሉ ከ10 በላይ ሴቶች በጋብቻ ቀኑ ሰላማዊ ሰልፍ ወጡ

በቻይና ዩ አን ግዛት ሄንግዲ መንደር ከ10 በላይ ሴቶች ቼን ሶንግ የእኛም ፍቅረኛ ነበረ በማለት "እኛ የቼን ሶንግ የቀድሞ የሴት ጓደኛሞች ነን ዛሬ ይህ ጋብቻ መበላሸት አለበት" የሚል ትልቅ ቀይ ባነር ይዘው ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል። መጀመሪያ ላይ በርካቶች ያልተለመደው ትዕይንት ቀልድ መስሏቸው የነበረ ቢሆንም ሴቶቹ በእርግጥ የቼን የቀድሞ ፍቅረኞች መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።

ሴቶቹ ከቼን የሰርግ ቦታ በፀጥታ መንገድ ላይ ቆመው ቀይ ባነር ይዘው ታይተዋል።በሰርጉ እለት እንዲህ ዓይነት ክስተት የገጠመው ቼን ሶንግ በጣም አሳፍሮኛል ባለቤቴና ቤተሰቧ ተበሳጭተውብኛል ሲሉ ተናግሯል። ሙሽራው ከዚህ ቀደም በአንዳንድ የቀድሞ ፍቅረኛዎቹ ላይ መጥፎ ባህሪ እንደነበረው አልሸሸገም፣ ነገር ግን እድሜዬ እየጨመራ ሲመጣ አካሄዴን ለውጫለሁ ሲል ገልጿል። ያም ሆኖ  ግብ ሚስቱ እና አማቶቹ ስለ አስገራሚው የሰርግ ትዕይንት አጥጋቢ ማብራሪያ እስኪያገኙ ድረስ እንደማያናግሩት ተናግረዋል።


"በወጣትነቴ ያልበሰሉ ነበርኩ፣ እና ብዙ ልጃገረዶችን እጎዳ ነበር" ሲል ቼን ተናግሯል፣ ከዚህ በፊት ባደረገው ድርጊት ማዘኑን በማንሳት "ሌሎች ወንዶች ሴቶችን በአክብሮት እንዲይዙ መክሯል። "ለሴት ጓደኛህ እሷን ከማታለል ይልቅ ታማኝ መሆን አለብህ ሲል ቼን ከልምዱ ተናግሯል።
5 viewsBekele Ejeta, 22:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-23 01:49:58 እኛ ሻማዎች ነን

<<...ባንድ ምሽት ሰውዬው በባሕር ዳርቻ ባለው የወደብ ከፍታ ቦታ ትንሽ ሻማ ይዞ መውጣት ይጀምራል። በዚህ ጊዜ 'ወዴት ነው እየሄድን ያለንው?' ሲል ሻማው ጥያቄ አቀረበለት።
"እየሄድን ያለነው ከቤቱ ባሻገር ከፍ ብሎ ወደሚታየው ቦታ ነው። በዚህም ለመርከቡ የወደቡን አቅጣጫ ማሳየት እንችላለን" አለው።
"እንደምታየው የእኔ ብርሃን በጣም ውስን ናት። እንዴትስ ከርቀት ያለ መርከብ በእኔ ብርሃን ተመርቶ ወደቡ ጋር መድረስ ይችላል?" አለ ሻማው።

"ምንም እንኳ ያንተ ብርሃን ትንሽ ብትሆንም የምትችለውን ያህል ማብራትህን አታቋርጥ፣ የቀረውን ነገር ለእኔ ተውው" አለው ሰውየው። በዚህ ንግግራቸው መሀል እያሉ ከከፍታ ቦታው ደረሱና ሰውዬው ትልቁን የፋኖስ ብርጭቆ እያሳየው ሻማውን በማስጠጋት ፋኖሱን ለኮሰው። ወዲያውኑም የተለኮሰው ፋኖስ የባሕሩን አካባቢ በብርሃን ጸዳል ሞላው።

እኛ ሻማዎች ነን። ከእኛ የሚጠበቀውም የሻማነታችንን ያህል ማብራት ነው። ቀሪው የሥራችን ስኬት ላይ ፈጣሪ ይታከልበታል። የአንዲት ትንሽ ሻማ መብራት ወይም ክብሪት ጫካ ሙሉ እሳት እንደምትፈጥር ሁሉ በእያንዳችን ያለች የብርሃን ምሳሌ ስናውቅም ሳናውቅም ለሌሎች ሕይወት መለወጥ ምክንያት ትሆናለችና ብርሃናችንን ሳንሳሳላት እንድትበራ እድል እንስጣት።

ዕድገትም ቅብብሎሽ ነው። እኛ ማድረግ የምንችለውን ሰርተን ለተገቢውና ለሚጠበቅብን ስናስረክበው እሱም በፈንታው ዳር ያደርሰዋል። ሻማዋ ለፋኖሱ እንዳቀበለችው ማለት ነው። ይህ ነው፣ ለዕድገት የድርሻን መወጣት ማለት፤ ሻማነታችንን ማበርከት የሚጠበቅብንን መወጣት። >>

እርካብና መንበር [ ]
4 viewsBekele Ejeta, 22:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-13 04:38:04

22 viewsBekele Ejeta, 01:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-09 21:47:08
በአሁኑ ሰዓት TELEGRAM እየሰራ አይደለም።።

ከታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቴሌግራም ሳይቆራረጥ መጠቀም ትችላላችሁ።

https://t.me/proxy?server=russia-dd.proxy.digitalresistance.dog&port=443&secret=ddd41d8cd98f00b204e9800998ecf8427e
8 viewsBekele Ejeta, edited  18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 01:12:18 https://t.me/atc_news/18762
37 viewsBekele Ejeta, 22:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 22:20:30 ኒው ዮርክ የሰው ልጅን አስክሬን ወደ ብስባሽ አፈር መቀየር የሚፈቅድ ሕግ አጸደቀች።

ይህን ተከትሎ ሰዎች ሲሞቱ አስክሬናቸው ወደ ብስባሸ አፈርነት እንዲቀየር መናዘዝ ይችላሉ።

አስክሬንን በሳጥን አኑሮ ግብዓተ መሬቱን መፈጸም ወይም ሬሳን ማቃጠል ለአካባቢ ጥበቃ መልካም አይደለም ይላሉ ተመራማሪዎች።

ይህን ችግር ለመቅረፍ አዲስና ዘመናዊ የሬሳ ማስወገጃ ሥራ ተግባር ላይ ማዋል አስፈልጓል።

በእንግሊዝኛው ናቹራል ኦርጋኒክ ሪዳክሽን ("natural organic reduction") የሚባለውና አስክሬንን ወደ ብስባሽ አፈር የሚቀይረው ይህ ዘመናዊ ሂደት ሬሳዎችን አሽጎ በማቆየት የሚፈጸም አካባቢን የማይበክል ሂደት ነው ይላሉ ተመራማሪዎች።

ከአራት ዓመት በፊት ዋሽንግተን ተመሳሳይ ደንብን ሕግ አድርጋ አጽድቃ እንደነበር ይታወሳል።

ኮሎራዶ፣ ኦሪገን፣ ቬርሞንት እና ካሊፎርኒያ ዋሽንግተንን ተከትለው ይህንን ሕግ አጽደቀዋል።

ኒው ዮርክ አስክሬንን ወደ ብስባሽ አፈርነት መቀየር የሚፈቅድ ሕግ ስታጸድቅ ስድስተኛዋ የአሜሪካ ግዛት ናት።

ይህን ረቂቅ የኒው ዮርክ ገዥ የሆኑት ዲሞክራቷ ካቲ ሆኩል ሕግ እንዲሆን ፈርመውበታል።

ይህ ሬሳን ወደ ብስባሸ የሚቀይረው ሳይንስ ከመሬት ከፍ ብሎ በሚቀመጥ የሳጥን በርሜል የሚፈጸም ነው።

አስክሬኖች ዝግ በሆነ በርሜል መሰል ማስቀመጫ ከተጋደሙ በኋላ የእንጨት ፍቅፋቂ፣ ሳር፣ አፈርና እና ሌሎች ንጥረ ነገሮች ይርከፈከፉባቸዋል። ከዚያ አስክሬን አብሮ ይቀየጣል።

ማንኛውም ተላላፊ በሽታ እንዳይኖር ከፍ ያለ ሙቀት ይደረግበታል።

ከአንድ ወር በኋላ ብስባሽ አፈር ሆኖ ለቤተሰብ ይሰጣል። ቤተሰብ ይህን አፈር ተቀብሎ ለጓሮ አትክልት ሊያውለው ይችላል።

የፎቶው ባለመብት, RECOMPOSE/MOLT STUDIOS

ሪኮምፖስ የሚባል አንድ የአሜሪካ ኩባንያ እንደሚለው ይህ ሂደት የካርበን ልቀትን በብዙ ደረጃ ቀንሶ የአካባቢ ብክለትን የሚከላከል ሁነኛ ዘዴ ሲል አሞካሽቶታል።

የካርቦንዳይኦክሳይድ ልቀት ለዓለም አየር ንብረት መለወጥ አንድ ሁነኛ ምክንያት ነው።

ይህም የመሬትን ከባቢ በማፈን ሙቀትን ስለሚፈጥር ነው።

ባሕላዊው ሬሳን የመቅበሪያ ዘዴ በርካታ ሳጥን መፈለጉና ለዚህም ሲባል በርካታ የደን ምንጣሮ ስለሚያስፈልግ ነው።

ከምንጣሮ ሌላ መካነ መቃብርም በርካታ ቦታ ይይዛል። በከተሞች አካባቢ ይህ ትልቅ ፈተና ሆኗል።

የዚህ ሬሳን ወደ ብስባሽ አፈርነት የመቀየር ሂደት ደጋፊ የሆኑ ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህ ዘዴ በተለይ መሬት ውድ ለሆነባቸው የዓለም ከተሞች ሁነኛ መፍትሄ ነው።

በተቃራኒው ሌሎች የሞራል ጥያቄን ያነሳሉ።

የኒው ዮርክ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቄስ “የሰው ልጅ ክቡር ነው፤ አስክሬኑ እንደቆሻሻ ብስባሽ አይደረግም፤ ነውር ነው’ ሲሉ ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።

ይህን ሬሳን ብስባሽ የማድረግ ሂደት ከተለመደው ቀብር የማስፈጸሚያ በዋጋ አነስተኛ ቢሆንም እስከ 7ሺህ ዶላር ወጪ ያስወጣል።

የሰውን አስክሬን ወደ ብስባሽ አፈር የመቀየር ሂደት በስዊድን ሕጋዊ ነው።

በዩኬ ደግሞ አስክሬንን ያለ ሬሳ ሳጥን መቅበር ይፈቀዳል።
56 viewsBekele Ejeta, 19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-04 22:13:45
በታይላንድ ሚስቱን ለዉሃ ሽንት ከመኪና አስወርዶ ረስቶ ከ100 ኪ.ሜ በላይ የተጓዘው ባል መነጋገሪያ ሆኗል

በታይላንድ የ55 ዓመቱ ቦንቶም ቻይሙን እና ባለቤቱ የሆነችዉ የ49 ዓመቷ አምኑዋይ ቻይሙን አዲስ አመትን በትውልድ ከተማቸው ማሃ ሳራክሃም ግዛት ለማሳለፍ እሁድ ከጠዋቱ 3 ሰአት ጉዞ ይጀምራሉ፡፡ሁለቱም ዉሃ ሽንት ይይዛቸዉና በቅርብ ካለዉ ነዳጅ ማደያ ይልቅ ወደ ጫካ ዉስጥ በተለያያ መስመር ይገባሉ፡፡

ለአስቸኳይ ሽንት የወረዱት ጥንዶች ባል ጉዳዩን ፈጽሞ መኪናዉን ማሽከርከር ይጀምራል፡፡ሆኖም ግን ሚስቱን ለዉሃ ሽንት ካወረደ በኃላ ረስቷት መሄዱን ያስተዋለዉ ከቆይታ በኃላ ነበር፡፡ሚስት ከዉሃ ሽንጽ ስትመለስ ባሏ ያለ እርሷ መኪና አስነስቶ መሄዱን ታረጋግጣለች፡፡

የበዓል ቀን እንደመሆኑ መንገዱ ጭር ያለባት እና የፍርሃት ስሜት ዉስጥ ያለችዉ አምኑዋይ ወደ ካቢን ቡሪ አውራጃ 20 ኪሜ ያህል ርቀት በእግሯ ለመሄድ ትወስናለች። ማለቂያ የሌለው የሚመስለውን የእግር ጉዞ ካደረገች በኋላ ከቀኑ 5 ሰአት ላይ በአካባቢው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ደርሳ ሪፖርት አድርጋለች።የባሏን ስልክ ቁጥር በቃሏ እንደማታዉቀዉና መኪናው ውስጥ የራሷን ስልክ ከነቦርሳዋ እንደነበር ተናግራለች፡፡

በስተመጨረሻ ጥንዶቹ የተገናኙ ሲሆን እሷ መቅረቷን ሳታውቅ እንዴት መንዳት እንደቻለ ሲጠየቅ፣ ከኋላ ወንበር ላይ ሆና ተኝታለች ብዬ አስቤ ነበር ሲል ባለቤቱን ሚስቱን ይቅርታ ጠይቋል
49 viewsBekele Ejeta, edited  19:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-12-15 01:48:29
በአለም ዋንጫ ፍፃሜ ጨዋታ የደቡብ አሜሪካ ሀገራት እና የአውሮፓ ሀገሮች ተገናኝተው ብዙ ዋንጫ ያሸነፉት ላቲኖች ናቸው 7 አውሮፓ 3።

2014 | አርጀንቲና ከ ጀርመን ጀርመን ሻምፒዮን
2002 | ብራዚል ከ ጀርመን ብራዚል ሻምፒዮን
1998 | ብራዚል ከ ፈረንሳይ ፈረንሳይ ሻምፒዮን
1994 | ብራዚል ከ ጣሊያን ብራዚል ሻምፒዮን
1990 | አርጀንቲና ከ ጀርመን ጀርመን ሻምፒዮን
1986 | አርጀንቲና ከ ከጀርመን አርጀንቲና ሻምፒዮን
1978 | አርጀንቲና ከ ኔዘርላንድ አርጀንቲና ሻምፒዮን
1970 | ብራዚል ከ ጣሊያን ብራዚል ሻምፒዮን
1962 | ብራዚል ከ ቼኮስሎቫኒያ ብራዚል ሻምፒዮን
1958 | ብራዚል ከ ስዊድን ብራዚል ሻምፒዮን

2022 | አርጀንቲና ከ ፈረንሳይ ?
26 viewsBekele Ejeta, edited  22:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ