Get Mystery Box with random crypto!

በታይላንድ ሚስቱን ለዉሃ ሽንት ከመኪና አስወርዶ ረስቶ ከ100 ኪ.ሜ በላይ የተጓዘው ባል መነጋገሪ | Our World

በታይላንድ ሚስቱን ለዉሃ ሽንት ከመኪና አስወርዶ ረስቶ ከ100 ኪ.ሜ በላይ የተጓዘው ባል መነጋገሪያ ሆኗል

በታይላንድ የ55 ዓመቱ ቦንቶም ቻይሙን እና ባለቤቱ የሆነችዉ የ49 ዓመቷ አምኑዋይ ቻይሙን አዲስ አመትን በትውልድ ከተማቸው ማሃ ሳራክሃም ግዛት ለማሳለፍ እሁድ ከጠዋቱ 3 ሰአት ጉዞ ይጀምራሉ፡፡ሁለቱም ዉሃ ሽንት ይይዛቸዉና በቅርብ ካለዉ ነዳጅ ማደያ ይልቅ ወደ ጫካ ዉስጥ በተለያያ መስመር ይገባሉ፡፡

ለአስቸኳይ ሽንት የወረዱት ጥንዶች ባል ጉዳዩን ፈጽሞ መኪናዉን ማሽከርከር ይጀምራል፡፡ሆኖም ግን ሚስቱን ለዉሃ ሽንት ካወረደ በኃላ ረስቷት መሄዱን ያስተዋለዉ ከቆይታ በኃላ ነበር፡፡ሚስት ከዉሃ ሽንጽ ስትመለስ ባሏ ያለ እርሷ መኪና አስነስቶ መሄዱን ታረጋግጣለች፡፡

የበዓል ቀን እንደመሆኑ መንገዱ ጭር ያለባት እና የፍርሃት ስሜት ዉስጥ ያለችዉ አምኑዋይ ወደ ካቢን ቡሪ አውራጃ 20 ኪሜ ያህል ርቀት በእግሯ ለመሄድ ትወስናለች። ማለቂያ የሌለው የሚመስለውን የእግር ጉዞ ካደረገች በኋላ ከቀኑ 5 ሰአት ላይ በአካባቢው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ደርሳ ሪፖርት አድርጋለች።የባሏን ስልክ ቁጥር በቃሏ እንደማታዉቀዉና መኪናው ውስጥ የራሷን ስልክ ከነቦርሳዋ እንደነበር ተናግራለች፡፡

በስተመጨረሻ ጥንዶቹ የተገናኙ ሲሆን እሷ መቅረቷን ሳታውቅ እንዴት መንዳት እንደቻለ ሲጠየቅ፣ ከኋላ ወንበር ላይ ሆና ተኝታለች ብዬ አስቤ ነበር ሲል ባለቤቱን ሚስቱን ይቅርታ ጠይቋል