Get Mystery Box with random crypto!

በቻይና አንድ ሙሽራ በሰርጉ እለት የእኛም ፍቅረኛ ነበረ ያሉ ከ10 በላይ ሴቶች በጋብቻ ቀኑ ሰላማ | Our World

በቻይና አንድ ሙሽራ በሰርጉ እለት የእኛም ፍቅረኛ ነበረ ያሉ ከ10 በላይ ሴቶች በጋብቻ ቀኑ ሰላማዊ ሰልፍ ወጡ

በቻይና ዩ አን ግዛት ሄንግዲ መንደር ከ10 በላይ ሴቶች ቼን ሶንግ የእኛም ፍቅረኛ ነበረ በማለት "እኛ የቼን ሶንግ የቀድሞ የሴት ጓደኛሞች ነን ዛሬ ይህ ጋብቻ መበላሸት አለበት" የሚል ትልቅ ቀይ ባነር ይዘው ሰላማዊ ሰልፍ ወጥተዋል። መጀመሪያ ላይ በርካቶች ያልተለመደው ትዕይንት ቀልድ መስሏቸው የነበረ ቢሆንም ሴቶቹ በእርግጥ የቼን የቀድሞ ፍቅረኞች መሆናቸውን ማረጋገጥ ተችሏል።

ሴቶቹ ከቼን የሰርግ ቦታ በፀጥታ መንገድ ላይ ቆመው ቀይ ባነር ይዘው ታይተዋል።በሰርጉ እለት እንዲህ ዓይነት ክስተት የገጠመው ቼን ሶንግ በጣም አሳፍሮኛል ባለቤቴና ቤተሰቧ ተበሳጭተውብኛል ሲሉ ተናግሯል። ሙሽራው ከዚህ ቀደም በአንዳንድ የቀድሞ ፍቅረኛዎቹ ላይ መጥፎ ባህሪ እንደነበረው አልሸሸገም፣ ነገር ግን እድሜዬ እየጨመራ ሲመጣ አካሄዴን ለውጫለሁ ሲል ገልጿል። ያም ሆኖ  ግብ ሚስቱ እና አማቶቹ ስለ አስገራሚው የሰርግ ትዕይንት አጥጋቢ ማብራሪያ እስኪያገኙ ድረስ እንደማያናግሩት ተናግረዋል።


"በወጣትነቴ ያልበሰሉ ነበርኩ፣ እና ብዙ ልጃገረዶችን እጎዳ ነበር" ሲል ቼን ተናግሯል፣ ከዚህ በፊት ባደረገው ድርጊት ማዘኑን በማንሳት "ሌሎች ወንዶች ሴቶችን በአክብሮት እንዲይዙ መክሯል። "ለሴት ጓደኛህ እሷን ከማታለል ይልቅ ታማኝ መሆን አለብህ ሲል ቼን ከልምዱ ተናግሯል።