Get Mystery Box with random crypto!

የናይጄሪያ እግር ኳስ ክለብ መሪ ሜዳ ውስጥ ውሃ ሽንት ሲሸኑ በመገኘታቸው ተቀጡ የናይጄሪያ እግ | Our World

የናይጄሪያ እግር ኳስ ክለብ መሪ ሜዳ ውስጥ ውሃ ሽንት ሲሸኑ በመገኘታቸው ተቀጡ

የናይጄሪያ እግር ኳስ ባለስልጣናት በኢባዳ የሚገኘውን የአንደኛ ዲቪዚዮን ክለብ ወደ 1,000 ዶላር የገንዘብ ቅጣት በክለቡ አንድ ባለስልጣን ላይ የጣለ ሲሆን በመጫወቻ ሜዳ ላይ ውሃ ሽንህ ሲሸኑ መታየታቸውን ተከትሎ ነው።

ድርጊቱ የተፈፀመው እሁድ እለት ባለሜዳው ሹቲንግ ስታርስ በሜዳቸው ከአክዋ ዩናይትድ ጋር ጨዋታ ከመጀመሩ በፊት የተነሳ ፎቶ መሆኑ ተመላክቷል። ድርጊቱን ፈፅመዋል የተባሉት አውዋል መሀመድ ከናይጄሪያ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ሊግ (NPFL) ጋር በተገናኘ ከማንኛውም እንቅስቃሴ ለአንድ አመት ታግደዋል። የናይጄሪያን ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ሊግ የሚያስተዳድረው አካል ጊዚያዊ አስተዳደር ኮሚቴ ለሹቲንግ ስታርስ በጻፈው ደብዳቤ ጨዋታውን ያዋረደ “አጸያፊ ተግባር” ሲል ገልጿል።

"የባለስልጣኖቻችሁን ስነምግባር መቆጣጠር እንደተሳናችሁ ማሳያው አውዋል መሀመድ በጨዋታ ሜዳ ላይ ውሃ ሽንታቸውን በተመልካች ህዝብ ፊት እንዲህ ማድረጋቸው ነው" ሲል መግለጫው አክሏል።