Get Mystery Box with random crypto!

Our World

የቴሌግራም ቻናል አርማ ourworl_d — Our World O
የቴሌግራም ቻናል አርማ ourworl_d — Our World
የሰርጥ አድራሻ: @ourworl_d
ምድቦች: ቴክኖሎጂዎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 894

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2022-08-12 09:17:57
በ2014 (2021/22) በጀት ዓመት ማለቂያ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ሴክተር እውነታዎች፦

የባንኮች ብዛት = 30

የባንክ ቅርንጫፎች ብዛት = 8944

ጠቅላላ የባንኮች ካፒታል = 199.1 ቢሊዮን ብር

ጠቅላላ የባንኮች ሀብት = 2.4 ትሪሊዮን ብር

ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ = 1.7 ትሪሊዮን ብር

የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ብዛት = 16.3 ሚሊዮን

የዴቢት ካርድ ተጠቃሚዎች ብዛት = 30.7 ሚሊዮን

የሞባይል ገንዘብ ተጠቃሚዎች ብዛት = 43.3 ሚሊዮን

የኤቲኤሞች ብዛት = 6902

የፖስ ብዛት = 11,760

የኢንሹራንስ ተቋማት ብዛት = 18

የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ብዛት = 40

ምንጭ፦ CBE
58 viewsBekele Ejeta, edited  06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 22:27:16 ለአሥር ዓመት ሥልጠናውን ያልወሰዱ መምህራን ከመምህርነት ሙያ ይወጣሉ

የማስተማር ሙያ ሥልጠና ባልወሰዱ መምህራን ላይ አስገዳጅ ውሳኔ ተላለፈ

--የግል ትምህርት ቤቶች በራሳቸው ወጪ መምህራኖቻቸው እንዲያሠለጥኑ ይደርጋሉ

በግልም ሆነ በመንግሥት ትምህርት ቤቶች እያስተማሩ የሚገኙና የማስተማር ሙያ ሥልጠና (Post Graduate Diploma in Teaching – PGDT) ያልወሰዱ የአፕላይድ ሳይንስ ምሩቅ መምህራንን በሚመለከት ትምህርት ሚኒስቴር ውሳኔ አስተላለፈ፡፡

ከውሳኔዎቹ መካከልም ከአሥር ዓመታት በላይ ሥልጠና ሳይወስዱ እያስተማሩ የሚገኙ መምህራንን ከሙያ የሚያስወጣ፣ የግል ትምህርት ቤቶችም በራሳቸው ወጪ መምህራኖቻቸውን እንዲያሠለጥኑ የሚሉት ይገኙበታል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ከተለያዩ የክልልና የከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች ጋር በተደጋጋሚ በመምከር ስምምነት ላይ የተደረሰበት ውሳኔ፣ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) ፊርማ ወጪ ከተደረገ ደብዳቤ ጋር አባሪ ተድርጎ ለአሥር ክልሎችና ለሁለት ከተማ አስተዳደሮች (ትግራይን ሳይጨምር) የትምህርት ቢሮዎች በተላከው መሠረት፣ የውሳኔው ተግባራዊነት ከነሐሴ 1 ቀን 2014 ዓ.ም. ጀምሮ ይሆናል፡፡

የትምህርት ቢሮዎቹና ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የመምህራን ደረጃ፣ ዕድገትና የትምህርት ደረጃ መሻሻልን እንደ ዋነኛ ምክንያት በማድረግ፣ የተወያዩበትና ውሳኔዎቹን ያሳለፉባቸው አራት ዋና ዋና ጉዳዮች ናቸው፡፡

ከእነዚህ መሀል አንደኛው በቅጥር ውል ፈርመው በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እያስተማሩ የሚገኙ የአፕላይድ ሳይንስ ምሩቃንን በሚመለከት ሲሆን፣ ከሦስት ዓመታት በታች አገልግሎት የሰጡ ጀማሪ መምህራን የመምህርነት ሙያ ቢያሟሉም ከተፈቀደው እርከን አንድ ደረጃ ዝቅ ያለ መነሻ ደመወዝ ያገኛሉ፡፡

በተያያዘም ከሦስት እስከ አምስት ዓመታት በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ያስተማሩ የአፕላይድ ሳይንስ ምሩቅ መምህራን፣ የማስተማር ሙያ ሥልጠናን ሳይመቻችላቸው የቀሩ ሆነው የመምህራን ሙያ ሥልጠና ያልወሰዱት፣ ለጀማሪ መምህር መደብ የተዘጋጀውን መነሻ ደመወዝ ያገኛሉ፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ሆነው ነገር ግን ከስድስት እስከ ስምንት ዓመታት ያገለገሉ የአፕላይድ ሳይንስ ምሩቅ መምህራን፣ ለመለስተኛ መምህር የተመደበ ደመወዝ ያገኛሉ፡፡

አገልግሎታቸው ከአምስት ዓመታት በላይ ሆኖ፣ ነገር ግን መንግሥት ያመቻቸላቸውን ሥልጠና በግላቸው ምክንያት ሳይወስዱ የቀሩ መምህራን፣ አገልግሎታቸው ስምንት ዓመት እስኪሞላ ድረስ በግላቸው ወይም መንግሥት በሚያመቻቸው ሥልጠና አጠናቀው እስኪገኙ ድረስ ለጀማሪ መምህር የተፈቀደውን መነሻ ደመወዝ ብቻ ያገኛሉ፡፡

በግል ትምህርት ተቋማት ለሚያስተምሩ የአፕላይድ ሳይንስ ተመራቂዎች፣ ነገር ግን የማስተማር ሙያ ሥልጠና ሳይወስዱ ለቀሩ መምህራን የትምህርት ተቋማቱ ባለቤቶች ሙሉ ወጪያቸውን ችለው እንዲያሠለጥኗቸው፣ ይህም በትምህርት ሚኒስቴር መዋቅር ቁጥጥር እንዲደረግበትም ተወስኗል፡፡

መምህራኖቹም የሚያስተምሩት የትምህርት ዓይነት ከተመረቁበት ጋር ቀጥተኛ ዝምድና እንዲኖረው ሲል ውሳኔው ይገልጻል፡፡

የማስተማር ሙያ ሥልጠና (PGDT) የሚሰጠው በተመረጡ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ሆኖ፣ ሥልጠናውን የሚወስደውም ከትምህርት ሚኒስቴር የተፈቀደለት መምህር ይሆናል፡፡

ከአሥር ዓመታት በላይ ሥልጠናውን ሳይወስዱ የሚያስተምሩ የአፕላይድ ሳይንስ ምሩቃንም፣ ከመምህርነት ሙያ ወጥተው ድጋፍ ሰጪ ብቻ እንዲሆኑ እንደሚደረግ ተወስኗል፡፡

የትምህርት ቢሮዎች በሥራቸው በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የአፕላይድ ሳይንስ ምሩቃንን መቅጠር ከፈለጉ፣ ከፍተኛ ውጤት ያመጡትን መልምለው የአንድ ዓመት (10 ወራት) የማስተማር ሙያ (PGDT) በአሠልጣኝ ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሠለጥኑ በማድረግ መቅጠር ይችላሉ፡፡ ነገር ግን የመምህራን አጥረት ቢገጥማቸው ምሩቃኑን ከጀማሪ መምህራን አንድ ዕርከን ዝቅ አድርገው መቅጠር ይችላሉ፡፡

ሪፖርተር ለኢትዮጵያ መምህራን ማኅበር ፕሬዚዳንት ለዮሐንስ በንቲ (ዶ/ር)፣ በምን ደረጀ ላይ ሆነው ምን ምን ያሟሉ መምህር መሆን እንደሚችሉ ላቀረበላቸው ጥያቄ፣ ‹‹ማንኛውንም የትምህርት መሥፈርት የሚያሟሉ፣ ብቃት ያላቸውና አስፈላጊውን ሥልጠና ወስደው በመምህርነት እየሠሩ የሚገኙ አባል መሆን ይችላሉ፤›› ብለዋል፡፡

አስተማሪ የሆኑና የማስተማር ሙያ ሥልጠና (PGDT) ባይሠለጥኑም እንደ አሠሪና ሠራተኛ በመደራጀት ማኅበር አባል የሆኑ አሉ ብለው፣ ማንኛውም መምህርን ይህንን ሥልጠና መውሰድ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

‹‹የአስተማሪ እጥረት ሲከሰት የግል ብቻ ሳይሆን፣ የመንግሥት ትምህርት ቤቶችም ያልሠለጠኑ ምሩቃንን ሲቀጥሩ ነበር፤›› ሲሉ ዮሐንስ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

እንደ እሳቸው ገለጻ፣ ከበፊትም ጀምሮ የነበረ ሕግ መሆኑንና ከሰሞኑ በተደረጉ ማኅበሩም በተሳተፈባቸው ተደጋጋሚ ስብሰባዎች ይህ ውሳኔ ሊተላለፍ ችሏል፡፡

ለመመህራን የሙያ ሥልጠና መስጠት ያለባቸው የተወሰኑ የመንግሥት አሠልጣኝ ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውን በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) የተፈረመው የውሳኔ ደብዳቤ ያመለክታል፡፡
22 viewsBekele Ejeta, 19:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-11 07:57:01 አንድ ቤተሰብ ውስጥ አባት ከሞተ በኋላ የሚመገቡት እስኪያሳስባቸው ድረስ ይቸገራሉ።

አንድ ጌጣጌጥ መሸጫ ሱቅ ያለው ዘመድ አላቸው እና እናትየው ለልጇ ያላትን ለረጅም ጊዜ የተቀመጠ የአንገት እና የጣት ዳይመንድ ጌጥ ሰጥታው እዛ ሱቅ ሄዶ እንዲሸጠው ትሰጠዋለች፡፡

ልጁ የተባለው የዘመድ ጌጣ ጌጥ ሱቅ ሄዶ እናቱ እንደላከችው አስረድቶ እንዲገዛው ይጠይቃል፡፡ሰውየውም ከመረመረው በኋላ

"አሁን ገበያው ወድቋል ትንሽ ግዜ ጠብቀን በጥሩ ዋጋ እንሸጠዋለን፡፡"

ብሎ ይመልስለትና የተወሰነ ገንዘብ ከሰጠው በኋላ ለልጁም እስከዛው በየጊዜው እየመጣ እዛው ሱቅ ስራ እንዲሰራ ያደርጋል።

ልጁ በየግዜው እየሄደ የጌጣጌጥአሰራር ጥበብ ተካነ፡፡ የገበያም እውቀት አካበተ በስራውም ታዋቂም ለመሆን ቻለ፡፡

ይሄኔ ባለሱቁ

"የሆነ ግዜ ልትሸጠው አምጠተኸው የነበረውን ጌጥ አሁን አምጣው አሁን ገበያው ጣራ ነክቷል እና ታተርፋላችሁ ፡፡"

ብሎ ይልከዋል፡፡ልጁ እንደተባለው እቤት ሄዶ ጌጣጌጡን በአይኑ በማየት ብቻ አርቴፊሻል ሆኖ ያገኘዋል፡፡

ወደ ሱቅ ይመለሳል፡፡ባለቤቱ ይጠይቃል

"ዳይመንዱስ ?" ልጁም "አርቴፊሻል ነው ግን እያወክ ያን ጊዜ ለምን አልገርከኝም? አሁንስ ለምን ላከኝ?ሲል ጠየቀው፡፡ዘመዱም "ያን ጊዜ ለረጅም ዘመን ዳይመንድ ነው ብላችሁ ያመናችሁትን ነበር ይዘህ የመጣኸው፡፡ያለምንም እውቀት፤ ባዶህን እና በሙሉ እምነት ብቻ ! በሰዓቱ ባለህበት ሁኔታ ልክ ያልሆነ ነገር ለማስረዳት ይከብዳል፡፡ ምናልባት ላታምኑኝ ትችሉ ነበር ፡፡ምናልባትም ባለመግባባት የሚፈጠሩ የቃላት ልውውጥ አሁን ላይ መጥፎ ስሜት ሊያሳድርብን በቻለ ነበር ።" ብሎ በትህትና መለሰለት፡፡

እንዲህ ያለ የላቀ ስብዕና ባለቤትና ነገሮችን በብዙ አቅጣጫ የምናይበት ህሊና ይስጠን፡፡
107 viewsBekele Ejeta, 04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 14:25:07

42 viewsBekele Ejeta, 11:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 09:46:32
በኮሎምቢያ ካሊ ሲካሄድ በነበረው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ አስራ ሁለት (12) ሜዳሊያዎችን አገኘች።

ላለፉት ስድስት ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ትናንት (ሐምሌ 30/2014 ዓ.ም) ሌሊት ላይ ፍፃሜውን ባገኘው የኮሎምቢያ ካሊ የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ስድስት የወርቅ፣ አምስት የብር እና አንድ የነሃስ በድምሩ አስራ ሁለት (12) ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

በዚህም በደረጃ ሰንጠረዡ ከአሜሪካ እና ጃማይካ ቀጥላ ከአለም ሶስተኛ ከአፍሪካ በቀዳሚነት ማጠናቀቅ ችላለች።የተገኘው ውጤት እስከ ዛሬ ከተካሄዱት የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳትፎ ታሪክ ለገራችን ኢትዮጵያ ከፍተኛው ነው።
]
32 viewsBekele Ejeta, edited  06:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 02:56:22 በት/ት ፍኖተ ካርታ ከቅድመ መደበኛ እስከ በመጀመሪያ መካከለኛ ት/ቤቶች በየክፍል ደረጃ የሚሠጡ የት/ት አይነቶች:-

= ቅድመ መደበኛ (KG) ለሁለት አመት የሚሠጥ:-
1ኛ= የአፍ መፍቻ ቋንቋ
2ኛ= አካባቢ ሳይንስ
3ኛ= ሙያ
4ኛ= ሂሳብ
5ኛ= የሠውነት ማጎልመሻ ናቸው፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ከ1ኛ-6ኛ ክፍል የሚሠጡ የት/ት አይነቶች:-
1ኛ= የአፍ መፍቻ ቋንቋ
2ኛ= አገር አቀፍ ቋንቋ
3ኛ= እንግሊዘኛ
4ኛ= ሂሳብ
5ኛ= አካባቢ ሳይንስ
6ኛ= የግብረገብ ት/ት
7ኛ= ሙያ
8ኛ= የሠውነት ማጎልመሻ ናቸው፡፡

በመጀመሪያ መካከለኛ ደረጃ ከ7ኛ-8ኛ ክፍል የሚሠጡ የት/ት አይነቶች:-
1ኛ= የአፍ መፍቻ ቋንቋ
2ኛ= የአገር አቀፍ ቋንቋ
3ኛ=እንግሊዘኛ
4ኛ= ሂሳብ
5= ሳይንስ
6ኛ= ህብረተሰብ
7ኛ= ስነ -ዜጋ
8ኛ= ሙያ
9ኛ= አይቲ (IT)
10ኛ= የሠውነት ማጎልመሻ ናቸው::

ሀምሌ 22/2014
114 viewsBekele Ejeta, 23:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 02:56:22 ቀን 29 /11/2014 ዓ.ም

የ2015 ትምህርት ዘመን የትምህርት ካላንደር

* በክፍል ውስጥ የመደበኛ ትምህርት መስከረም 9/ 2015 ይጀምራል።

* የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ማጠቃለያ ፈተና (ሚንስትሪ) ከሰኔ 5 - 9/ 2015 ዓ.ም ይሰጣል።

* የ2015 ዓ.ም 12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ ፈተና ከግንቦት 21 - 25/ 2015 ዓ.ም ይሰጣል።

* ሰኔ 30/ 2015 ዓ.ም የዓመቱ ትምህርት ማጠናቀቂያ ይሆናል።

መልካም የትምህርት ዘመን !!


የአዲስ አበባ ከተማ ት/ቢሮ
106 viewsBekele Ejeta, 23:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-04 05:12:49 ሁለት ሰዎችን በመግደል በውሃ መፍሰሻ ቱቦ ውስጥ የጨመሩት የጥበቃ ሠራተኞች በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተቀጡ!

በአምስት ቀናት ልዩነት ውስጥ ሁለት ግለሰቦችን ነፍስ በማጥፋት አስክሬናቸውን በውሃ መፍሰሻ የመንገድ ቱቦ ውስጥ የከተቱት ግለሰቦች በእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተቀጡ፡፡በፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ልዩ ልዩ ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያሳየው 1ኛ ተከሳሽ ዘካሪያስ ኮዶ 2ኛ ተከሳሽ ዮሃንስ ማጠሉ 3ኛ ተከሳሽ አስራት አበበ የተባሉት ተከሳሾች በተለያየ ጊዜ በመገናኘት ባጃጅ ከግለሰቦች ላይ በሃይል ለመንጠቅ ሲመካከሩ እና ሲዘጋጁ ቆይተዋል፡፡

በዝግጅታቸው መሰረትም ጥር 27 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 02፡30 ሲሆን÷ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 ክልል ልዩ ቦታው ቦሌ ቡልቡላ ሙሉ ወንጌል አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ የባጃጅ ባለቤት የሆነው ሟች ማናየ እንየውን በ30 ብር ኮንትራት በማናገር ወደ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን እንዲወስዳቸው ይስማማሉ፡፡

ሟች አድርሷቸው ከባጃጁ ሊያወርዳቸው ሲቆም 3ኛ ተከሳሽ ሟችን በክርኑ አንቆ ሲይዘው፣ 2ኛ እና 3ኛ ተከሳሾች የሟችን እግር በጋራ ይዘው በማውረድ መሞቱን ሲያረጋግጡ ከቤተ ክርስቲያኑ ፊት ለፊት ካለ የመንገድ ቱቦ በመክተት የሟችን 500 ብር የሚገመት ስልክ እና 185 ሺህ ብር የሚገመት ባጃጅ ወስደዋል፡፡

በተጨማሪም የካቲት 2 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 03፡30 ሰዓት ሲሆን 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች የመጀመሪያውን ወንጀል ከፈጸሙ ከአምስት ቀናት በኋላ ምትኩ መለሰ የተባለን ግለሰብ 1ኛ ተከሳሽ የጀኔሬተር ባትሪ ሊሸጥለት በተስማሙት መሰረት ደውሎ እንዲመጣ በማድረግ ተከሻሶች በጥበቃ ሰራተኝነት ተቀጥረው ከሚሰሩበት ሙሉ ወንጌል ቤተ ክርስቲያን ጊቢ ውስጥ እንዲገባ እና እንዲደበቅ አድርገዋል፡፡

ከደበቁ በኋላም 2ኛ ተከሳሽ “ሌባ ሌባ” በማለት ሟችን በያዘው የጥበቃ ዱላ ጭንቅላቱን ሲመታው 1ኛ ተከሳሽም ሟች በወደቀበት የመታው በመሆኑ ህይወቱ አልፏል፡፡በዚህ ጊዜም የሟችን 450 ብር የሚገመት ስልኩን እና ይዞት የነበረውን 3 ሺህ ብር በመውሰድ ከአሁን በፊት የማናየ እንየውን አስክሬን በከተቱበት ቱቦ ውስጥ መደበቃቸው ተገልጿል፡፡ተከሳሾች በፖሊስ ክትትል እና በህብረተሰቡ ድጋፍ ተይዘው በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ በመተላለፍ በፈጸሙት የሰው መግደል እና ከባድ የውንብድና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸውዋል፡፡

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሰው መግደል ወንጀል ችሎት የቀረቡት ተከሳሾች ድርጊቱን አልፈፀምንም በሚል የእምነት ክህደት ቃላቸውን የሰጡ በመሆኑ ዓቃቤ ህግ ያሰባሰባቸውን የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች በማቅረብ ተከራክሯል፡፡ተከሳሾችም መከላከያ ማስረጃ በማቅረብ ያሰሙ ቢሆንም በዓቃቤ ህግ የቀረበውን ሰው እና የሰነድ ማስረጃ ማስተባበል ባለመቻላቸው ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹን በተከሰሱበት አንቀፅ ስር ጥፋተኛ ናቸው ማለቱን ከፍትሕ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡ፍርድ ቤቱ ሀምሌ 25 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት 1ኛ እና 2ኛ ተከሳሾች የፈፀሙት ተደራራቢ ወንጀል በመሆኑ በሁለቱም ክሶች አንድ የቅጣት ማክበጃ በመያዝ እያንዳንዳቸው በእድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጡ 3ኛ ተከሳሽ 4 የቅጣት ማቅለያ ተይዞለት በ15 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል፡፡
44 viewsBekele Ejeta, edited  02:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 02:25:57
#breaking_news

የአልቃይዳው መሪ አይማን አል ዘዋሪ በአሜሪካ አየር ጥቃት ተገደሉ

የቀድሞውን መሪ ኦሳማ ቢላደንን በመተካት የሽብር ቡድኑ ሲመሩ የነበሩት ትውልደ ግብፃዊው የሽብር ቡድኑን ቁልፍ መሪዎችን ኢላማ በማድረግ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት ነው አፍጋኒስታን ውስጥ መገደላቸውን እነ ሲኤንኤን ስፑትኒክን ጨምሮ አለማቀፍ ሚድያዎች መዘገባቸውን ዘናይል ፅፏል
68 viewsBekele Ejeta, edited  23:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-01 12:29:00

75 viewsBekele Ejeta, edited  09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ