Get Mystery Box with random crypto!

በኮሎምቢያ ካሊ ሲካሄድ በነበረው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ አስራ ሁ | Our World

በኮሎምቢያ ካሊ ሲካሄድ በነበረው የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ አስራ ሁለት (12) ሜዳሊያዎችን አገኘች።

ላለፉት ስድስት ቀናት ሲካሄድ ቆይቶ ትናንት (ሐምሌ 30/2014 ዓ.ም) ሌሊት ላይ ፍፃሜውን ባገኘው የኮሎምቢያ ካሊ የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ስድስት የወርቅ፣ አምስት የብር እና አንድ የነሃስ በድምሩ አስራ ሁለት (12) ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።

በዚህም በደረጃ ሰንጠረዡ ከአሜሪካ እና ጃማይካ ቀጥላ ከአለም ሶስተኛ ከአፍሪካ በቀዳሚነት ማጠናቀቅ ችላለች።የተገኘው ውጤት እስከ ዛሬ ከተካሄዱት የዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳትፎ ታሪክ ለገራችን ኢትዮጵያ ከፍተኛው ነው።
]