Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያ የፎሬንሲክ ዲ ኤን ኤ ምርመራን በሀገር ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች። የፎሬንሲክ ዲ | Our World

ኢትዮጵያ የፎሬንሲክ ዲ ኤን ኤ ምርመራን በሀገር ውስጥ ተግባራዊ ማድረግ ጀመረች።

የፎሬንሲክ ዲ ኤን ኤ ምርመራ ላብራቶሪ በኢትዮጵያ ፖሊስ ሆስፒታል ሥራውን ዛሬ የጀመረ ሲሆን ላብራቶሪው እጅግ ዘመናዊና ዓለም የደረሰበትን ቴክኖሎጂ የሚጠቀም መሆኑ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረ ሚካኤል በዚሁ ወቅት እንዳሉት የዲ ኤን ኤ ፎሬንሲክ የምርመራ ላብራቶሪው በሀገር ውስጥ ሥራ መጀመሩ የፍትህ ሥርዓቱ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት ሚናው የላቀ ነው።

የፖሊስ የምርመራ አቅምን በይበልጥ ለማሳደግ እንደሚያስችል የገለጹት ኮሚሽነሩ ከዚህ ቀደም በውጭ ሀገር ለዲ ኤን ኤ ምርመራ የሚወጣውን ከፍተኛ ወጪ የሚያስቀር እንደሆነም መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@