Get Mystery Box with random crypto!

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያና ሜዳሊያ የተገናኙት ገና ከጅምሩ ፊንላንድ ሄልሲንኪ በተደረገ | Our World

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያና ሜዳሊያ የተገናኙት ገና ከጅምሩ ፊንላንድ ሄልሲንኪ በተደረገው የመጀመሪያው ውድድር ነበር።

በዚህ የመጀመሪያው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና ለኢትዮጵያ እንዲሁም ለአፍሪካ የመጀመሪያውን ሜዳሊያ ያስገኘው አትሌት ከበደ ባልቻ ነው።

ከበደ በማራቶን ውድድር ሁለተኛ ወጥቶ የብር ሜዳሊያ በማጥለቅ ችቦውን አቀጣጠለ።

ነገር ግን ቀጥሎ በጣሊያኗ ከተማ ሮም በተካሄደው ሁለተኛው ውድድር ኢትዮጵያ አልተሳተፈችም ነበር።

በየሁለት ዓመቱ የሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በርካታ ሜዳሊያ በመሰብሰብ አሜሪካንን የሚደርስባት የለም።

ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ደግሞ ጎረቤት አገር ኬንያ ናት።

ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር እስካሁን ባከማቻቸው ሜዳሊያዎች ከዓለም ሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

አንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ ተሾመ ቀዲዳ የ2022 የኦሬገን ሻምፒዮናን ሳይጨምር ኢትዮጵያ 85 ሜዳሊያዎች አሏት ሲል ለቢቢሲ ተናግሯል።

“ኢትዮጵያ በዓለም ቻምፒዮና ታሪክ 29 ወርቅ፣ 30 ብር እንዲሁም 26 የነሐስ ሜዳሊያዎች፤ በአጠቃላይ 85 ሜዳሊያ አላት።”

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ የተለየ ታሪክ አላት የሚለው ጋዜጠኛው፣ አትሌት ከበደ ባልቻም በማራቶን መድረክ ለመጀመሪያ ጊዜ የብር ሜዳሊያ ያስገኘ አፍሪካዊ መሆኑን ያወሳል።

በፈር ቀዳጁ ውድድር ኢትዮጵያ በከበደ ባልቻ ነሐስ ሜዳሊያ ከዓለም 15ኛ ሆና አጠናቃለች።

ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር የሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መግባት የቻለች ብቸኛዋ አፍሪካዊት አገር ናት።

በወቅቱ ምሥራቅ ጀመርን [ጀርመን አንድ ከመሆኗ በፊት] 19 ሜዳሊያዎችን በመሰብሰብ አንደኛ ሆና ስታጠናቅቅ፣ የውድድሩ ኃያል አገር አሜሪካ ደግሞ ሁለተኛ ሆና ነበር።

በጣልያኗ ሮም በተካሄደው ሁለተኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና “የአትሌቲክስ ቡድን እየመራ የሚጓዝ አሠልጣኝ ባለመገኘቱ ነው ኢትዮጵያ ያልተሳተፈችው” ይላል ጋዜጠኛ ተሾመ።

ኢትዮጵያ በዚህ ታላቅ የአትሌቲክስ መድረክ የመጀመሪያውን ወርቅ ያገኘችው በአትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ አማካይነት ነው።

ኃይሌ የጀርመኗ ስቱትጋርት ባዘጋጀችው አራተኛው የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በ10 ሺህ ሜትር ወርቅ ማምጣት ችሏል።

አትሌቱ በዚህ ሳይገታ በ5 ሺህ ውድድር ደግሞ የነሐስ ሜዳሊያ ለአገሩ አስገኝቷል።

አትሌት ፊጣ ባይሳ ደግሞ ሌላ ነሐስ አክሎ ኢትዮጵያ በሦስት ሜዳሊያ አሸብርቃ ተመለሰች።

ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መድረክ በስዊድኗ ጉተምበርግ ከተማ እስከተሰናዳው ውድድር ድረስ ከአፍሪካ አንደኛ ሆና ስታጠናቅቅ ቆየች።

ነገር ግን በጉተምበርግ በተካሄደው ውድድር ኬንያ ወደ ኃይልነት መጣች።

በዚህ ውድድር ኬንያ ሁለት የወርቅ ሜዳሊያዎችን ጨምሮ ስድስት ሜዳሊያ በመሰብሰብ ስሟን ከፍ አደረገች።

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያና ኬንያ ከጉተምበርጉ ፍልሚያ በኋላ ፉክክራቸው እየበረታ መጣ።

በፈረንጆቹ 2003 በተካሄደው የፓሪሱ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ 3 ወርቅ፣ 2 ብርና 2 ነሐስ በማምጣት ከዓለም አራተኛ ሆና ያጠናቀቀችበት መድረክ የሚረሳ አይደለም ይላል ጋዜጠኛ ተሾመ።

በሄልሲንኪ የተካሄደው 10ኛው ሻምፒዮና ግን ልዩ ነበር ሲል ያክላል።

ኢትዮጵያ በዚህ ውድድር ከአሜሪካና ከሩሲያ በመቀጠል በ3 ወርቅ፣ በ4 ብርና በ2 ነሐስ ከዓለም ሦስተኛ ሆና አጠናቀቀች።

ይህ የሄልሲንኪው ውድድር “አረንጓዴው ጎርፍ” ተብሎ ይጠራል።

አረንጓዴው ጎርፍ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከአንድ እስከ ሦስት ተከታትለው በመግባት ዓለምን አጀብ ያሰኙበት ዘመን ነው።

አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ 2 ወርቅ ባጠለቅችበት በዚህ ውድድር የአረንጓዴው ጎርፍ አርማዎቹ መሠረት ደፋር፣ ብርሃኔ አደሬ እና እጅጋየሁ ዲባባ የነበራቸው ተሳትፎ የሚዘነጋ አይደለም።

በ10 ሺህ ሜትር ወንዶች ደግሞ ቀነኒሳ በቀለና ስለሺ ስህን ተከታትለው በመግባት ሄልሲንኪን የማይረሳ አድረጓት።

ከሁለት ዓመታት በኋላ ግን ጃፓን ኦሳካ ባሰናዳችው ውድድር ድል ወደ ኬንያ ዞረ።

ኬንያ በዚህ ሻምፒዮና 5 ወርቅን ጨምሮ 15 ሜዳሊያዎች አሸነፈች።

ከዚያ በኋላ በነበሩት የበርሊን፣ ዴጎ፣ ሞስኮ፣ ቤይጂንግ፣ ለንዶን፣ ዶሃ ላይ ኬንያ በሜዳሊያ ብዛት ኢትዮጵያን እየመራች ቆይታለች።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ በደራርቱ አመራር ደራርቱ ቱሉ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም ሻምፒዮና የተሳተፈችው በፈረንጆቹ 1991 ቶኪዮ በተዘጋጀው ውድድር ነበር።

ምንም እንኳ ደራርቱ በተሳተፈተችበት የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ሜዳሊያ ባታመጣም በቀጣዩ ዓመት ባርሴሎና በተዘጋጀው ኦሊምፒክ ላይ ወርቅ ማጥለቅ ችላለች።

የአገሯን ስም በተለያዩ መድረኮች ያስጠራችው ደራርቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ሆና ከተመረጠች በኋላ ለውጥ ማምጣት ችላለች ቢባል ማጋነን አይሆንም።

ነገር ግን ለደራርቱ ሁኔታዎች ሁሉ የተመቻቹ ነበሩ ማለት ከባድ ነው።

ደራርቱ ፌዴሬሽኑን መምራት ከጀመረች ወዲህ ሁለት ጊዜ በዓለም ሻምፒዮና፤ አንድ ጊዜ በኦሊምፒክ መድረክ፤ አንድ ጊዜ ደግሞ በዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ተሳትፋለች።

በኳታር ዋና ከተማ ዶሃ በተሰናደው የ2019 የዓለም ሻምፒዮና ኢትዮጵያ ሁለት ወርቅ፣ አምስት ብርና አንድ ነሐስ ይዛ ተመልሳለች።

በዚህ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች በሚታወቁበት የመካከለኛና ረዥም ርቀት ውድድር የተለመደውን ወርቅ ማስመዝገብ ባይችሉም ተስፋ ያላቸው አትሌቶች ታይተዋል።

ኢትዮጵያ በመድረኩ በስምንት ሜዳሊያ አምስተኛ ደረጃ ይዛ አጠናቀቀች።

ከዚህ በኋላ በደራርቱ የተመራው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን ታላቅ ወደ ሚባለው የኦሊምፒክ መድረክ ነው ያቀናው።

በ2022 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ኢትዮጵያ ያገኘችው ሜዳሊያ ብዛት አራት ነው።

ይህ ውጤት ኢትዮጵያ በኦሊምፒክ መድረክ ካመጣቻቸው ዝቅተኛ ከተባሉት የሚመደብ ነው።

ቀጥሎ ኢትዮጵያ የተሳተፈችበት ዓለም አቀፍ መድረክ ባለፈው መጋቢት የተካሄደው የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ፍልሚያ ነው።

ይህ መድረክ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደምቀው የታዩበት ነበር።

ኢትዮጵያ፤ በአራት ወርቅ፣ በሦስት ብርና በሁለት የነሐስ አሜሪካን አስከትላ ከዓለም ቁንጮ ሆና አጠናቃለች።

በአሜሪካ ኦሪገን ግዛት እየተካሄደ ባለው የዘንድሮው የዓለም ሻምፒዮና የኢትዮጵያ ውጤት ከጅምሩ አመርቂ መሆን ችሏል።

በተለይ በመድረኩ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የምንጊዜም ተቀናቃኝ የሆነችው ኬንያ በምትታወቅባቸው ሩጫዎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ብቅ ብቅ ማለታቸው አነጋጋሪ ሆኗል።

ኢትዮጵያና ኬንያ በዓለም ሻምፒዮና ኬንያና ኢትዮጵያ ድንበር ብቻ አይደለም የሚጋሩት። ሜዳሊያ የሚታደልበት የአትሌቲክስ መድረክንም ጭምር እንጂ።

በተለይ በረዥም ርቀት የሩጫ ውድድር ሁለቱ አገራት በየመድረኩ አንገት ለአንገት ሲተናነቁ ማየት አዲስ አይደለም።

ኃይሌና ፖልቴርጋን በሚሊ ሜትር ተቀዳድመው ሲገቡ የነበረውን ትዕይንት ማን ይዘነጋል።

ቀነኒሳና ኪፕቾጌ በሁለት ሰከንድ ልዩነት የጨበጡት የማራቶን ክብረ ወሰንም እንዲሁም ተመዝገቦ የሚኖር ነው።

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በመካከለኛ ርቀት ማለትም በ5 ሺህና በ10 ሺህ ሜትር፤ ኬንያ ደግሞ በአጭርና በመካከለኛ የ800፣ የ1500 እና, የ3000 ሜትር ርቀቶች ሲነግሱ ማየት የተለመደ ነው።

ነገር ግን ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ኬንያዊያን በመካከለኛ ርቀት ኢትዮጵያን ሲፋለሙ ተመልክተናል።

ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደግሞ በ1500 እና 3000 ሜትር መሰናክል ውድድሮች ኬንያዊያንን መፈተን ይዘዋል።

ለምሳሌ በ2019 የዶሃ ዓለም ሻምፒዮና