Get Mystery Box with random crypto!

በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ኬንያዊው ኪፕሩቶ ታዳጊው ኢትዮጵያዊ ሌሜቻ ግርማን በሚሊ ሜትር ቀድሞ ወር | Our World

በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል ኬንያዊው ኪፕሩቶ ታዳጊው ኢትዮጵያዊ ሌሜቻ ግርማን በሚሊ ሜትር ቀድሞ ወርቅ ያጠለቀበት ውድድር የሚዘነጋ አይደለም።

ለሜቻ ግርማ በ3000 መሰናክል ለኢትዮጵያ ሜዳሊያ ያስገኘ የመጀመሪያው ወንድ አትሌት ነው።

አትሌት ሶፊያ አሰፋ በ2013 ሞስኮ ላይ ያገኘችው ነሐስ በርቀቱ ብቸኛው የኢትዮጵያ ሜዳሊያ ነበር።

በዘንድሮው የኦሪገን ዓለም ሻምፒዮና የታየውም ይህ ነው።

ለሜቻ ግርማ በርቀቱ ሁለተኛ ብሩን በተከታታይ አጥልቋል።

ጉዳፍ ፀጋይ ደግሞ በ1500 ሜትር ለአገሯ ብር አስገኝታለች። ኬንያዊቷ ፌይዝ ኪፕየጎን ለአገሯ ብቸኛውን ወርቅ አስገኝታለች።

የኬንያ መገናኛ ብዙኃን በዘንድሮው የኦሪገን ውጤት ደስተኛ አለመሆናቸውን እየገለጡ ነው።

ኬንያ ባለፈው የዓለም ሻምፒዮናም ሆነ በኦሊምፒክ መድረክ ከኢትዮጵያ ልቃ ብታጠናቅቅም በዓለም የቤት ውስጥ ውድድርና በአሜሪካው የዓለም ሻምፒዮና የተመዘገበው ውጤት አመርቂ ሆኖ አልተገኘም።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ሴት አትሌቶች በሻምፒዮናው መድረክ በአሜሪካዋ ኦሪገን ግዛት እየተካሄደ የሚገኘው 18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና መጪው እሁድ ይጠናቀቃል።

በዚህ ውድድር ኢትዮጵያ  በወንዶች እና ሴቶች ከ800 ሜትር እስከ ማራቶን ባሉ የውድድር ዘርፎች እየተሳተፈች ትገኛለች።

በዚህ ውድድር እስከ አሁን ሦስት የወርቅ ሜዳሊያ፣ አራት ብር እና አንድ የነሃስ ሜዳልያ በማምጣት ሁለተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን፤ እሑድ እለት የሚካሄዱት የ800 እና 5000 ሜትር ውድድሮች በጉጉት ይጠበቃሉ።

ኢትዮጵያ እስከ አሁን በዚህ ውድድር ካገኘቻቸው ስምንት ሜዳሊያዎች አምስቱ በሴት አትሌቶች የተገኙ ናቸው።

የዓለም አትሌቲክስ ቻምፒዮና በፈረንጆቹ ከ1983 ጀምሮ በየሁለት ዓመት ልዩነት መካሄድ የጀመረ ሲሆን፤ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በ5000 እና በ10000 ሜትር ውድድሮች ስመ ጥር ሆነውበታል።

ቀደም ሲል በ10 ሺህ ሜትር፣ በ5 ሺህ ሜትር እና በግማሽ ማራቶን፤ ሦስት የዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት የሆነችው አትሌት ለተሰንበት ግደይ በዚህ ታላቅ መድረክ አሸናፊነቷን አስጠብቃለች።

ለተሰንበት ከውድድሩ በኋላ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጠችው አስተያየት “ህልሜ እውን ሆኗል። ይህ ድል ከዓለም ክብረወሰን በበለጠ ለእኔ ትልቅ ነው። በውጤቱ በጣም ደስተኛ ነኝ” ብላለች።

አትሌት ጎተይቶም ገብረሥላሴም በሴቶች ማራቶች የሻምፒዮናውን ክብረ ወሰን በመስበር አሸናፊ መሆኗ ይታወሳል።

በኦሪገን መድረክ ደግሞ በማራቶን ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች። ከዚህ በፊት ማሬ ዲባባ በ2015 ቤይጂንግ በተካሄደው የዓለም ሻምፒዮና የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ሆና ነበር።

ኢትዮጵያ፤ በተለይ በፈረንጆቹ ከ1999 እስከ 2007 ባሉት ዓመታት በ10 ሺህ እና በ5 ሺህ ሜትር ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ውድድሩን በማሸነፍ በርካታ ሜዳሊያ አካብታለች።

ጌጤ ዋሚ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ወርቅነሽ ኪዳኔ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ ብርሃኔ አደሬ፣ አልማዝ አያና እና ሌሎች በአትሌቲክሱ ዓለም አገራቸውና ያስጠሩ ሴት አትሌቶች ናቸው።

አሜሪካ ኦሪገን እየተካሄደ ያለውን ውድድርን ሳይጨምር ኢትዮጵያ በተሳተፈችባቸው የአትሌቲክስ ሻምፒዮናዎች 85 ሜዳሊያዎችን ስታስመዘገብ፣ ከዚህ ውስጥ ደግሞ ወደ ግማሽ የሚጠጋው የተገኘው በሴቶች ነው።

በዚህም 38ቱ ሜዳሊያዎች በ1500፣ በ3000፣ 5000 እና በ10000 ሜትር እንዲሁም 2 ሜዳሊያዎች በማራቶን ውድድሮች ላይ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን ሴት አትሌቶች ያሰነፉት ሲሆን በአጠቃላይም 40 ሜዳሊያዎችን, አስገኝተዋል።