Get Mystery Box with random crypto!

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከ6ኛ ፎቅ የወደቀችው ሰራተኛ በህይወት ተረፈች። በጥቁር አንበሳ ሆስፒታ | Our World

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ከ6ኛ ፎቅ የወደቀችው ሰራተኛ በህይወት ተረፈች።

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዕድሜዋ 40 የተገመት አንዲት የሆስፒታሉ ሰራተኛ ትላንት ሌሊት 10:30 ላይ ከ6ኛ ፎቅ ላይ "ዘላ ወደ ምድር በመዉደቋ ከባድ ጉዳት ደርሶባታል" ሲል የእሳትና አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

ለኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጥሪ የተደረገውም፥ ከ6ኛ ፎቅ ወደ ታችኛዉ ወለል ወደ ቤዝመንት ዉስጥ የወደቀችዉን ተጎጂ ከወደቀችበት ለማንሳት ምቹ ሁኔታ ባለመኖሩ መሆኑ ተገልጿል።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችም በመሰላልና በገመድ በመጠቀም ተጎጂዋን በህይወት ማውጣት ችለዋል። ተጎጂዋ ከአደጋዉ በህይወት ብትተርፍም ከባድ ጉዳት ደርሷባታል ተብሏል።

ተጎጂዋ በሆስፒታሉ ተረኛ አዋላጅ ነርስ ሆና ምሽቱን የተለመደ ስራዋን ከባልደረቦቿ ጋር ስታከናዉን እንደነበር ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በተያያዘ ዜና በትላንትናው ዕለት በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታ አትላስ አካባቢ ግንባታዉ በተጠናቀቀ ህንጻ ላይ ቀለም በመቀባት ላይ ያሉ ሰራተኞች የቆሙበት ሊፍት (ዊንች) ካቦዉ ተበጥሶ በአራት ሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

ጉዳት የደረሰባቸዉ አራት ሰዎች በኮሚሽኑ አምቡላንስ  ዘዉዲቱ ሆስፒታል ተወስደዉ ህክምና እየተደረገላቸዉ ሲሆን ጉዳት ከደረሰባቸዉ ዉስጥ አንዱ ከባድ ጉዳት የደረሰበት ነዉ። አደጋዉ በአጋጠመበት ጊዜ አራቱም ተጎጂዎች በሊፍቱ ላይ እንደነበሩ ኮሚሽኑ አስታውቋል