Get Mystery Box with random crypto!

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxtewahdoc — "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxtewahdoc — "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
የሰርጥ አድራሻ: @orthodoxtewahdoc
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 21.12K
የሰርጥ መግለጫ

🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን
/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ።
📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼
❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-21 20:30:05 በጨነቃችሁ ጊዜ ሁሉ ቅዱስ ቂርቆስ አባቴ አለው ይበላችሁ።

2.7K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 17:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 20:20:21 ነገ ሐምሌ 15 ቅዱስ ቂርቆስ እና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ ናቸው።

ወቶ ከመቅረት ካልታሰበ አደጋ ሁሉ ይሰውረን
2.7K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 17:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 14:05:13 ፨ወር በገባ በ15 ቅድስት እንባ መሪና ወራኀዊ በዐሏ ነው፨

"ቤተክርስቲያን እንቁዎቼ ብላ ከምትጠራቸው የሴት ጻድቃኖች አንዳ ቅድስት እንባ መሪና ናት።ጣዕመ ዜናዋ ሙሉ ሕይወቷ አስገራሚም አስተማሪም ነው። ቅድስቲቷ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በምድረ ግብፅ ተወልዳ ያደገቾ ሰማዕት ናት ። ወላጆቿ ከእሷ ሌላ ልጅ የሌላቸው ሲሆን በአኗኗራቸው ደግ እና ቅን ነበሩ።

ቅድስት እንባ መሪና ትክክለኛ ስሟ መሪና ነው።ምክንያቱም እንባ መሪና የወንድ ስም ነውና።ነገር ግን በወንድ የተጠራችበት የራሱ የሆነ ምክንያት አለው።የዛሬ ሴት ሳይጠይቋት ሰላሳውን ትቀባጥራለች ይህች እናት ግን ሴትነቷን ደብቃ ወንድ ነኝ ብላ የአባቷ ደቀ መዝሙር በመሆን ለብዙ አመታት የተጋደለች ናት በታላቁ ፈተናዋ ውስጥ ከፍተኛ ፈተና አጋጠማት ይህም አንዲት ሴት መነኩሴ ይህ ወንድ መነኩሴ አስረግዞኛል በማለት ክስ ለገዳሙ አባቶች አቀረበች ይህች እናትም እሺ አዎን አድርጌዋለሁ በማለት ልጁን ተቀበለች ከገዳሙ እረኞች ለልጁ ወተት እያመጡለት በዚያ እንዲህ እያለች እየተጋደላችሁ ቆየች ልጁንም ኤፍሬም አለችው። መነኮሳቱና አበምኔቱ አናግረው ወደ ገዳሙ መለሷት ከዚያም ባረፈችበት ቀን መነኮሳቱ ሲያዩ ሴት ሆና አገኟት አዘኑ አበምኔቱም በጣም አዘኑ አለቀሱ በጣም ተስቃይታ ስለነበር ማለት ነው።

በመጨረሻም አላስቀብርም ቢሉ ከሙታን ተነስታ እግዚአብሔር ሁላችንም ይቅር ይበለን ብላ ተመልሳ አርፋለች።እረድኤት በረከቷን ከሁላችን ጋር ይኑር አሜን።

----------------------------///////////////------------------------
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
2.1K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 11:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 14:04:14 ወር በገባ በ15 ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ነው።
ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊ

❖ ይህም ቅዱስ ከዋክብትን ከሚያመልኩ ሰዎች ሀገር ነው አባቱም ክብር ይግባውና የክርስቶስን አምልኮት የሚጠላ የጣዖት ካህን ነበር፤ በዚያን ጊዜም የእግዚአብሔር ቸርነት ቀሰቀሰችውና አነሳሥታ የንጽቢን ጳጳስ ወደሆነው ወደ አባ ያዕቆብ ወሰደችው እርሱም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተምሮ የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው በእርሱም ዘንድ በጾምና በጸሎት ያለማቋረጥ እየተጋደለ ለብዙ ዘመናት ኖረ።
❖ የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ አደረበት አሕዛብን ተከራክሮ ይረታቸው ነበር፤ ኒቅያ በሚባል ከተማ የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት አባቶች ኤጲስቆጶሳት ጉባኤ በተደረገ ጊዜ ይህ ቅዱስ ኤፍሬም ከመምህሩ ከአባ ያዕቆብ ጋራ ወደ ቅዱሳን ጉባኤው ሔደ።
❖ ከሀዲው አርዮስንም አውግዘው ከለዩት በኋላ ይህ ቅዱስ ኤፍሬም በዚያች ሌሊት ከምድር እስከ ሰማይ የሚደርስ የብርሃን ምሰሶ ተተክሎ አየ ከዚህ ራእይም የተነሣ አደነቀ ይገልጽለትም ዘንድ ወደ ጌታ ጸለየ ይህ የቂሣርያ ሊቀ ጳጳሳት ብፁዕ ባስልዮስ ነው የሚል ቃል ከሰማይ ወደርሱ መጣ።
❖ ቅዱስ ኤፍሬምም ያየው ዘንድ ወድዶ ወደ ቂሣርያ ሀገር ተጓዘ በደረሰም ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ በማእዘኑ በኩል ቆመ ቅዱስ ባስልዮስንም ወንጌልን ሊያነብ በወጣ ጊዜ ዋጋው ብዙ የሆነ ከወርቅ የተሠራ ልብሰ ተክህኖ ለብሶ አየው፤ ሦስት ምልክቶችንም እሰኪያይ ድረስ ተጠራጠረ ምልክቶችም እኒህ ናቸው ነጭ ርግብ መጥታ በራሱ ላይ አረፈች ሁለተኛም በልብሱ ላይ የሚያርፉ ተዋሐስያን ይቃጠሉና ይረግፉ ነበር። ሦስተኛም ከአፉ የእሳት ነበልባል ወጥቶ በምእመናን ላይ ያድር ነበር።
❖ ከዚህም በኋላ ቅዱስ ባስልዮስ ቅዱስ ኤፍሬምን በስሙ ጠራውና እርስ በርሳቸው ሰላምታ ተለዋወጡ፤ በአስተርጓሚ ይነጋገሩ ጀመሩ፤ የየራሳቸውንም ቋንቋ ይገልጽላቸው ዘንድ ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልይ ቅዱስ ኤፍሬም ቅዱስ ባስልዮስን ለመነው፤ በጸለየ ጊዜም ተገልጾላቸው ያለ አስተርጓሚ ተነጋገሩ።
❖ ከዚህ በኋላም ቅዱስ ኤፍሬምን ዲቁና ሾመው ከጥቂት ወራትም በኋላ ቅስና ሾመው ከእርሱም ብዙ ትሩፋቶች ተገለጡ በመንፈሳዊ ተጋድሎ ሁሉ ተጋደለ፤ አንዲት በወገን የከበረች ባለ ጸጋ ሴት ነበረች ራስዋንም ለካህን ለማስመርመር ታፍር ነበር ከታናሽነቷ ጀምራ የሠራችውን ኃጢአቷን ሁሉ ጽፋ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ አመጣች፤ አባቴ ሆይ በዚህ ክርታስ ውስጥ ያሉት ኃጢአቶቼ ይደመሰሱ ዘንድ ተናገር ብላ ለመነችው እርሱም እንዳልሺው ይሁንልሽ አላት፤ እርሷም ክርታሱን በገለጠች ጊዜ ከአንዲት ኃጢአትዋ በቀር ኃጢአቷ ሁሉ ተደምስሶ አገኘች ያችም ኃጢአት አስጨናቂና ታላቅ ኃጢአት ነበረች።
❖ ባገኘቻትም ጊዜ ያቺን የቀረች ኃጢአቷን ያጠፋላት ዘንድ አልቅሳ ለመነችው እርሱም ወደ ቅዱስ ኤፍሬም ሒጂ እርሱ ይህችን የቀረች ኃጢአትሽን ያስተሠርይልሻል አላት፤ ወዲያውም ወደ ቅዱስ ኤፍሬም ሔዳ ከርሷ የሆነውን ሁሉ ነገረችው፤ እርሱም እንዲህ አላት ፈጥነሽ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ሒጂ ግን ሙቶ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዱት ታገኝዋለሽ ሳትጠራጠሪም ይህችን ክርታስ በላዩ ጣይ ይደመሰስልሻል።
❖ ያቺም ሴት ወደ ቅዱስ ባስልዮስ ተመለሰች ሙቶ ተሸክመው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዱትም አገኘችው፤ ያንንም ክርታስ በአስክሬኑ ላይ ጣለችው ወዲያውኑም ተደመሰሰላት፤ ይህም ቅዱስ ኤፍሬም ብዙ ተአምራቶችን አድርጓል በዘመኑም ዲዳን የሚባል አንድ ከሀዲ ተነሣ ይህም አባት ኤፍሬም ተከራክሮ ረታው።
❖ እጅግም ብዙ የሆኑ ዐሥራ አራት ሽህ ድርሳናትንና ተግሣጻትን ደረሰ ከእርሳቸውም ውስጥ አምላክን የወለደች የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ውዳሴዋ ነው፤ አቤቱ የጸጋህን ማዕበል ግታልኝ እስከሚል ድረስ ድርሳናትን ደርሶአል፤ መልካም የሆነ ገድሉንም በፈጸመ ጊዜ ወደ ወደደው ወደ እግዚአብሔር ሔደ።
ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በብፁዕ ኤፍሬም ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
አርኬ
ሰላም ለኤፍሬም ከመ ርግብ ተመሲሎ። መንፈስ ቅዱስ ዘርእየ ለርእሰ ባስልዮስ ዘይጼልሎ። ውኂዘ ድርሳናት ብዙኀ ሶበ ለልቡ ኀየሎ። አኀዝ እምኔየ መዋግደ ጸጋከ ኲሎ። ለእግዚአብሔር አምላክ እንዘ ይብል ሰአሎ።

https://t.me/Orthodoxtewahdoc ጆይን እያላችሁ ተቀላቀሉ
1.5K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 11:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 14:03:12 #ሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ ማን ነው

❖#ወር_በገባ_በ15 የቅዱስ ሚናስ ሰማዕት ወርኀዊ በዓሉ ነው።
የዚህም ቅዱስ አባቱ አናቅዮስ ከሚባል አገር ነው ስሙም አውዶክስዮስ ነው እርሱም አገረ ገዥነት ተሹሞ ሳለ ወንድሙ ቀንቶበት በንጉሥ ዘንድ ነገር ሠራበት ንጉሡም ወደ አፍራቅያ አገር ሰደደውና በዚያም አገረ ገዢ አድርጎ ሾመው የአገር ሰዎችም ሁሉ ደስ አላቸው እርሱ ለሰው የሚራራ እግዚአብሔርንም የሚፈራ ደግ ሰው ነውና።

❖ እናቱም ልጅ አልነበራትም በአንዲት ዕለት ወደ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በበዓልዋ ቀን ገብታ የክርስቲያንን ወገኖች ያማሩ ልብሶችን ለብሰው ከልጆቻቸው ጋር ደስ እያላቸው ሲገቡ አየቻቸው።

❖ በእመቤታችንም በቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት አለቀሰች ልጅን ይሰጣት ዘንድ ወደ ልጅዋ ወደ እግዚአብሔር እንድትለምንላትም ለመነቻት በዚያንም ጊዜ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል አሜን የሚል ቃል ወጣ።

❖ ከዚህም በኋላ ወደ ቤቷ ገብታ ይህን ቃል ለባሏ ነገረችው እርሱም የእግዚአብሔር ፈቃዱ ይሁን አለ፤ ከጥቂት ቀኖችም በኋላ እግዚአብሔር ይህን የተባረከና የከበረ ልጅን ሰጣት የእመቤታችንም ሥዕል ሚናስ ብላ እንደሰየመችው ስሙን ሚናስ ብለው ሰየሙት፤ ጥቂት በአደገ ጊዜም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተማሩት።

❖ ዐሥራ ሁለት ዓመትም ሲሆነው በመልካም ሽምግልና አባቱ አረፈ ከእርሱም በኋላ በሦስተኛ ዓመት እናቱ አረፈች ቅዱስ ሚናስም ብቻውን ቀረ።
❖ መኳንንቱም አባቱን አብዝተው ከመውደዳቸው የተነሣ ሚናስን በአባቱ ፈንታ ምስፍናን ሾሙት እርሱም የክርስቶስን አምልኮት አልተወም።

❖ ዲዮቅልጥያኖስም በካደ ጊዜ ሁሉንም ሰዎች ጣዖታትን እንዲአመልኩ አዘዛቸው ብዙዎችም ክብር ይግባውና በክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ሞቱ።
❖ በዚያንም ጊዜ ሚናስ ሹመቱን ትቶ ወደ ገዳም ገባ ታላቅ ተጋድሎን እየተጋደለ ብዙ ዘመናት ኖረ። በአንዲትም ዕለት ሰማይ ተከፍቶ ሰማዕታትን የብርሃን አክሊሎችን ሲአቀዳጁአቸው አየ ስለ ክርስቶስ ስም በመከራ የደከመ ይህን አክሊል ይቀበላል የሚል ቃልን ሰማ።

❖ በዚያንም ጊዜ ወደ ከተማ ተመለሰና ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም ታመነ ሰዎችም አብዝተው አባበሉት በወገን የከበረ እንደሆነ እነርሱ ያውቁ ነበርና።
❖ መኰንኑም ብዙ ቃል ኪዳን ገባለት ባልሰማውም ጊዜ ጽኑዕ በሆነ ሥቃይ እንዲአሠቃዩት አዘዘ፤ ማሠቃየቱንም በሰለቸ ጊዜ ራሱን በሰይፍ እንዲቆርጡ አዘዘ፤ በመንግሥተ ሰማያትም የሰማዕትነት አክሊልን ተቀበለ ብዙዎችም በእርሱ ምክንያት ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም በሰማዕትነት ሞቱ።

❖ የቅዱስ ሚናስንም ሥጋ ወደ እሳት እንዲጥሉት መኰንኑ አዘዘ እሳትም አልነካውም ምእመናን ሰዎችም የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ወስደው በአማሩ ልብሶች ገነዙት የስደቱ ወራትም እስከሚፈፀም በአማረ ቦታ ውስጥ አኖሩት።
❖ በዚያንም ወራት የመርዩጥ አገር ሰዎች ከአምስቱ አገሮች ሠራዊትን ሊአከማቹ ወደዱ የቅዱስ ሚናስንም ሥጋ ረዳት ይሆናቸው ዘንድ በመንገድም እንዲጠብቃቸው ከእርሳቸው ጋር ወሰዱት።

❖ እነርሱም በባሕር ላይ በመርከብ ውስጥ ሳሉ ፊታቸው እንደ ከይሲ አንገታቸው እንደ ግመል አንገት ያለ አውሬዎች ከባሕር ወጡ ይልሱትም ዘንድ ወደ ቅዱስ ሚናስ ሥጋ አንገታቸውን ዘረጉ ከቅዱስ ሚናስም ሥጋ እሳት ወጥታ እነዚያን አራዊት አቃጠለቻቸው ሰዎችም አይተው አደነቁ ደስታም አደረጉ ፈርተው ነበርና።

❖ ወደ እስክንድርያ አገርም ደርሰው ሥራቸውን ፈጽመው ወደ ሀገራቸው በሚመለሱ ጊዜ የቅዱስ ሚናስን ሥጋ ከእሳቸው ጋር ሊወስዱ ወደው በገመል ላይ በጫኑት ጊዜ ገመሉ ከቦታው የማይነሣ ሆነ።

❖ ሁለተኛም በሌላ ገመል ጫኑት እርሱም መነሣትን እምቢ አለ አብዝተውም ደበደቡት ገመሉም ከቶ አልተንቀሳቀሰም እነርሱም ያ ቦታ እግዚአብሔር የፈቀደለት መሆኑን አወቁ ቦታውንም አዘጋጅተው በዚያ ቀበሩት።

❖ ጌታችንም በበግ እስከገለጠው ድረስ ብዙ ዘመናትን በዚያ ቦታ ኖረ ይህም ቤተ ክርስቲያኑ በከበረችበት በሰኔ ዐሥራ አምስት ቀን ተጽፎአል።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

አርኬ
ሰላም ለከ ሐራዊ መስፍን። ሰማዕተ መድኅን። ዘሰመየተከ ሚናስ ዘፆረተከ ማሕፀን። አመ ጸለየት ጸሎተ እንዘ ይእቲ መካን። እምሥዕለ ማርያም ሰሚዓ ዘይቤ አሜን።
1.3K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 11:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ