Get Mystery Box with random crypto!

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxtewahdoc — "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxtewahdoc — "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
የሰርጥ አድራሻ: @orthodoxtewahdoc
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.88K
የሰርጥ መግለጫ

🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን
/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ።
📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼
❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 77

2023-03-07 17:42:50 የነበሩበትም ቦታ ብርሃን ለበሰ፡፡ አቡነ ፄዋለ ጽድቅም ከድንጋጤና ከፍርሃት የተነሳ በግንባሩ ወደቀ፡፡ ጌታችንም ፍርሃቱን አርቆለት በቅዱሳን እጆቹ አንስቶ ሳመውና ‹‹ወዳጄ ፄዋለ ጽድቅ ሆይ! በጸና እምነትህና በቆራጥ ልቡና ሆነህ
መከራ መስቀሌን አስበህ መራራ ልቅሶን አልቅሰህ በለመንኸኝ ጊዜ አሁን እነሆ ከድካም ወደ እረፍት፣ ከሀሳር ወደ ክብር፣ ከጨለማ ወደ ብርሃን፣ ከሃዘን ወደ ፍጹም ደስታ ዛሬ ልወስድህ መጥቻለሁና ደስ ይበልህ፡፡ ደስታ ይገባሃል፣ ወዳጄ ፄዋለ ጽድቅ፣ አርበኛው ልጄ ፄዋለ ጽድቅ፣ ተጋዳዩ ልጄ ፄዋለ ጽድቅ ሆይ! ደስ ይበልህ፣ እጽፍ ድርብ ደስታ ይገባሃል›› አለው፡፡ ዳግመኛም ‹‹ወደጄ ሆይ! እንዳልክ ይሁንልህ፤ ስምህም በዓለም ሁሉ የተገለጠ ይሁን፤ በአንተም ስም
የተማፀነውን፣ ቤተመቅደስህ በታነጸበት፣ ስምህ በተጠራበት፣ ገድልህ በሚነበብበት እኔ በዚያ እገኛለሁ፡፡ አጽምህ ባረፈበት ቦታ መጥቶ እድናለሁ ብሎ አምኖ አንተን አስቦ ከቤቱ ቢነሳ ስለ አንተ ስለወዳጄ ስለ አገልጋዬ ፄዋለ ጽድቅ ልቡ ያሰበውን ሀሳብ ሁሉ እኔ ገና ከቤቱ ሳይነሳ ከቦታህ ሳይደርስ እዛው እያለ የኅሊናውን ሀሳብ እፈጽምለታለሁ፡፡ ገድልህን የጻፈ ያጻፈ፣ ያነበበ የተረጎመ፣ ቃሉንም የሰማ፣ ገድልህን በቤቱ ያኖረ ከዚህ ዓለም ነፍሱ ከሥጋው ስትለይ እኔ መድኃኔዓለም ቃሌ የማይሻረው በደረቴ አቅፌው ያለምንም ወቀሳና ከሰሳ ዓይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው እጅ ያልታነፀውን ሰማያዊ መንግሥቴን
ኢየሩሳሌምን አወርሰዋለሁ፡፡ መላእክትም ከመጠን በላይ እንዲያስደስቱት አድርገዋለሁ፡፡ መላእክተ ጽልመትም ብዙ ርቀት ፈርተው እንዲርቁ አደርገዋለሁ፡፡ወደ ቤተክርስቲያን መጥቶ ‹‹ኃጢአቴን ይቅር በለኝ›› ብሎ ቢማፀን ወንዱን የ40
ቀን ሴቷን የ80 ቀን ሕፃን አደርጌ ወደ ቤቱ በሰላም እመልሰዋለሁ፡፡ ልጅ አጥቶ መካን ሆኖ ወደ አንተ ቢማፀን እቤቱም ሆኖ የፄዋለ ጽድቅ አምላክ ልጅ ስጠኝ ብሎ በስምህ ቢለምነኝ ስለአንተ ስል በቃኝ እስከሚል ድረስ ልጅ እሰጠዋለሁ፡፡ቤተክርስቲያንን ያገለገለ፣ ገድልህን ፈጽመህ ባረፍክበት ቦታ የአንተን አምላክ እኔን አምኖ የሚኖረውን አንተ ከገባህበት አስገባዋለሁ፡፡ እሱም አባቴ ይልሃል፣አንተም ልጄ ትለዋለህ፡፡ እኔም እጥፍ ድርብ ዋጋ እሰጠዋለሁ፡፡ እስከ ሰባት ትውልድም እምረዋለሁ›› አለው፡፡ መድኃኔዓለም ክርሰቶስ ይህን ቃልከዳን ለአቡነ ፄዋለ ጽድቅ ሰጥቶት ነፍሱን ተቀብሏት ስምንተኛው ሺህ ሳይገባ ህዳር 29 ቀን ከቅዱሳን ባለሟሎቹ ጋር በይባቤ በክብር በምስጋና ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡
ጸሎቱ ወበረከቱ የሀሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡የቤተ ክርስቲያኑ አድራሻ፡- ሰሜን ሸዋ ከአዲስ አበባ በሸኖ በኩል እነዋሪ ከተማን አለፍ እንዳሉ ደነባ ከመድረስዎ በፊት አልባሳ ላይ ወርደው ያገኙታል፤
ወይም ከአዲስ አበባ በፍቼ በኩል ደነባ አልፈው እነዋሪ ሳይደርሱ አልባሳ ይወርዳሉ፡፡ በድጋሚ የአቡነ ፄዋ ለጽድቅ አምላክ ልዑል እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን!!!
የአቡነ ፄዋ ለጽድቅ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!!!
የድባ አቡነ ሙሴ ገዳም
325 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 17:42:50 #አቡነ ጼዋ ለ ጽድቅ
# ወር በገባ በ29 ታስበው ከሚውሉት ውስጥ አቡነ ፄዋ ጽድቅ
ይኸውም ጻድቅ በክርስቶስ አምኖ ንስሓ ገብቶ ለጽድቅ የበቃ በቀድሞ ሕይወቱ የአየር ጋኔን የነበረ ነው።
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ እዌጥን መጸሐፈ ገድሉ ለአቡነ ፄዋ ለጽድቅ በስመ እግዚአብሔር አብ ወበስመ እግዚአብሔር ወልድ ወበስመ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ኃይለ አምላኩ ይርድአነ ያፈጽመ በደህና ወበሰላም አሜን፡፡
ገድለ ዘአቡነ ፄዋለ ጽድቅ፡ ጸሎቱ ወበረከቱ የኀሉ ምስለ ኩልነ ሕዝበ ክርስቲያን ለዓለመ ዓለም አሜን፡፡የአባታችን የቅዱስ ፄዋ ለጽድቅ አባት ‹‹ፈረጎ›› ይባላል፡፡ ይኸውም የቀትር ጋኔን
በመሆን የሚመለክ ነበር፡፡ እናቱም ‹‹ሰዓሪተ ሰንበት›› ትባላለች፡፡ ይህችም ዘማዊና ሰንበትን የምትሽር ነበረች፡፡ በእንደዚህ ዓይነት ግብር እያለች ከነበረችበት ቦታ ከእንደለቃቃ በተጉለት ውስጥ ክፉ ጠንቋይ ቃልቻ ስለነበር
ወደ እርሱ ሲሄዱ በመንገድ ላይ አርፋ እንዳለች እንቅልፍ ሸለብ እንዳደረጋቸው ‹‹ፈረጎ›› የሚባለው የቀትር ጋኔን በዚህ ሰዓት በግብረ ሥጋ ተገናኛት፡፡ በዚህን ጊዜ ‹‹መጥቆራ›› የሚባል ሁለት ክንፍ ያለው ኃይለኛ ጋኔን ተፀነሰ፡፡ ከዚያም
ከጠንቋዩ ተመልሳ ወደ ባዕቷ ገብታ ስትኖር ተፀንሶ የነበረው ‹‹መጥቆራ›› ተወለደ፡፡ ከተወለደም በኋላ የግብር አባቱ ዲያብሎስ እንዳስተማረው በአየር እየበረረ ክፉ ሥራውን ያኪያሂድ ነበር፡፡ በዚህ ዘመን የነበሩ ቅዱሳኖች አቡነ
ተክለሃይማኖትና አቡነ ዜና ማርቆስ የኢትዮጵያን ምድር በኪደተ እግራቸው እየተመላለሱ እየዞሩ፣ አጋንንትን እያወጡ፣ ድውያንን እየፈወሱ፣ ያላመነውን እያሳመኑ እያጠመቁ የኢትዮጵያን ምድር ይቀድሷት ነበር፡፡ ነገር ግን ከዚህች ከዘማዊ ሴት የተወለደው ‹‹መጥቆራ›› የሚባለው ሁለት ክንፍ ያለው ኃይለኛ ጋኔን ሥራቸውን ገድላቸውን በየጊዜው እጅግ ይፈትናቸው ነበር፡፡ እነርሱም ከኃይለኛነቱና ከአስቸጋሪነቱ የተነሣ ወደ ፈጣሪያቸው ጸለዩ፡፡ ፈጣሪያቸውም
እነዚህን ቅዱሳን ሲፈትናቸው በተመለከተ ጊዜ ስመ እግዚአብሔር ጠርተው በመስቀል ቢያማትቡበት ከእጃቸው እንሚወድቅ ነገራቸው፡፡ እነርሱም እንደነገራቸው አደረጉ፡፡ በመንቀጥቀጥ በመርበድበድ ወርዶ ከፊታቸው ቆሞ
ተንበርክኮ ሰገደላቸው፡፡ ከዚህ በኋላ አባታችን ዜና ማርቆስ ወደ ገዳማቸው (ደብረ ብስራት) ይዘውት ሄደው አብረው ይኖሩ ነበር፡፡ እርሱም እየታዘዘና ብዙ የሰው ልጆች መሥራት የማይችሉትን ሥራ ይሠራ ነበር፡፡ ይሠራው ከነበረው
ሥራው አንደኛው ከዕለታት በአንድ ቀን ሰላሌ ከሚባለው ሀገር ሄዶ እንጨት እንዲያመጣ አባታችን ዜና ማርቆስ አዘዙት፡፡ እርሱም እንደታዘዘው ሄዶ በ3 ሰዓት ውስጥ ለ300 ሰዎች የማይቻለውን እንጨት ተሸክሞ ወደ ገዳሙ ደብረ ብስራት አድርሷል፡፡ በዚህም ሥራው አባታችን ዜና ማርቆስና ልጆቻቸው እጅግ ይደነቁ ነበር፡፡ ያም እንጨት ለገዳማዊና ከሀገሩ ሕዝብ ለብዙ ጊዜ ሲያገለግል ቆይቷል፡፡እንጨቱ ዛሬም ድረስ በአቡነ ዜና ማርቆስ በገዳማቸው በደብረ ብስራት በዋሻ ቁርጥራጩና የተፈረፈረው ዛሬም ይገኛል፡፡ ከዚህ በኋላ አቡነ ተክለሃይማኖትና አቡነ ዜና ማርቆስ በመዓልትም በሌሊትም ሁልጊዜ ፈጣሪያቸውን በጸሎት
ይጠይቁ ነበር፡፡ ጥያቄያቸውም ‹‹መጥቆራ›› የተባለውን ይህንን ኃይለኛ ጋኔን በጸሎታቸው በመስቀላቸው ኃይል ወድቆ የሰገደላቸውን ከአርአያ አጋንንት ወደ ሰው አርአያ እንዲመለስ በሥላሴ ስም አምኖ እንዲጠመቅ ነበር፡፡
አምላካቸውም ልመናቸውን ሰምቶ አርአያው 140 የነበረው ቁመቱ በሰው አርአያ ቀርጾላቸዋል፡፡ እምነቱንም በእርሱ በአምላኩ አድርጎላቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ መክረው አስተምረው አሳምነው አጥምቀውታል፡፡ ስመ ጥምቱም ፄዋለ ጽድቅ
ተብሏል፡፡ ከዚህ በኋላ ከአቡነ ዜና ማርቆስ እግር ስር ወድቆ ተንበርክኮ ‹‹አባቴ ሆይ ጸሎትህ አማላጅነትህ ይርዳኝ›› እያለ ይማፀናቸው ነበር፡፡የእሳቸውም አርድዕት ሆኖ እያገለገላቸው እነርሱም በጸሎታቸው በምክራቸው እየረዱት እያፅናኑት ቅዱሳን አበው ለተቀበሉትና ለበቁበት የምንኩስና ቅድስና በቅቶ በአቡነ ዜና ማርቆስ እጅ መንኩሶ በጾም በጸሎት፣ በገድልና በትሩፋት በሥራም ሁሉ እያገለገለ ሰባት ዓመት በዚሁ በአቡነ ዜና ማርቆስ ገዳም ተጋድሏል፡፡ይህንንም አገልግሎት ሲያገለግልና ሲጋደል አቡነ ዜና ማርቆስ ገድሉን፣
ትሩፋቱን፣ ጾሙን፣ ጸሎቱን፣ ትዕግስቱን፣ ጽናቱን እያዩ በጣም ያደንቁና አፈጣሪያቸውን ያመሰግኑ ነበር፡፡ ፄዋለ ጽድቅም በትሩፋት ላይ ትሩፋትን እየጨመረ እንደ መላእክት እንደ ነቢያትና እንደ ሐዋርያት በመዓልትም በሌሊትም ‹‹ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ›› እያለ ፈጣሪውን ያመሰግነው ነበር፡፡ከዚህ በኋላ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ገድሉንና ጽናቱን አይቶ በቃሉ አነጋገረው፡፡ ‹‹በዚህ ቦታ እስከ አሁን የተጋደልኸው ይበቃሃል ከእንግዲህ የአንተ ቦታ ይህ አይደለምና ተነስ እኔ ወደምመራህና ወደምወስድህ ቦታ ሂድ፣ ይህም ቦታ በእናቴ በቅድስት ድንግል ማርያም ያነጽኩት ነው፡፡ ፍቃዴና ስምረቴ በሆነው በዚያ በቅዱስ ቦታ አገልግለኝ›› አለው፡፡ ፄዋለ ጽድቅም እሺ በማለት
ወደታዘዘበት ገዳም ሄደ፡፡ ሲሄድም ገና በመንገድ ላይ ሳለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስርቶለትና አዘጋጅቶለት ስለነበር 300 ሊቃውንት፣ 28 ሰሞንኛ በስብሐተ እግዚአብሔር እያገለገሉ አቡነ ፄዋለ ጽድቅ ከዚያ ደረሱ፡፡
እነርሱም ደስ ብሏቸው በምስጋና በደስታ ተቀበሉት፡፡ እርሱ ግን ራሱን ዝቅ አድርጎ ፈጣሪው የተቀበለውን መከራ በማሰብ ለእነዚያ ሊቃውንቶችና ሰሞነኞች እያገለገለ ሕዝብና አሕዛብን እያስተማረ በትሩፋት ላይ ትሩፋትን እየጨመረ
ቀደም ሲል በደብረ ብስራት ያደርገው የነበረውን ትሩፋትና ገድል ጨመረ፡፡ይኸውም ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ለአምላኩ እንደ ማለ ሁሉ ይህም ቅዱስ አባት እንደ እርሱ ‹‹የያዕቆብ ፈጣሪ የሚሆን የእግዚአብሔርን ማደሪያ
እስከማገኝ ድረስ ለዓይኖቼ እንቅልፍን ለቅንድቦቼ መንጎላጀትን ለጎኔ እረፍትን አልሰጥም፣ መኝታዬ አመድ ልብሴም ማቅ ይሁን›› በማለት ሌሊትና ቀን ሳያርፍ
እንደ ዓምድ ተተክሎ የመድኃኔዓለምን መከራውን፣ መገረፉን፣ መሰደብ መደብደቡን፣ መጎተት መደብደቡን፣ መሰቀሉን፣ መራራ ሞቱን፣ በ3 ቀን መነሳቱን፣ ማረጉንና ዳግመኛም ለፍርድ መምጣቱን ሁሉ እያሰበ ሌሊትና ቀን
ፊቱን በድንጋይ እየመታ፣ ሰውነቱን በሰንሰለት እየገረፈ ፈጣሪውን ‹‹አምላኬ ሆይ! አንተ ለእኔ ይህንን ሁሉ መከራ ተቀበልክ…›› እያለ ሰውነቱን ‹‹ጽኚ በርቺ አልቅሺ፣በዚህ ካላለቀስሽ በፈጣሪሽ ፊት ራቁትሽን ትቆሚያለሽ….›› እያለ ላቡ እንደ ቦይ ውኃ እስከሚወርድ ድረስ እየሰገደ ያለቅስ ነበር፡፡ በእንደዚህ ያለ ገድልና ትሩፋት ላይ እንዳለ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክረስቶስ በቅዱሳን መላእክት ታጅቦ
እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምን፣ ነቢያትን፣ ሐዋርያትን፣ ጻድቃንን፣ ሰማዕታትን፣ ዠደናግል መነኮሳትን፣ ወዳጆቹን ሁሉ አስከትሎ በምስጋና በዝማሬ በይባቤ ወደ ወዳጁ አቡነ ፄዋለ ጽድቅ ወረደ፡፡ በወረደም ጊዜ ምድር ተንቀጠቀጠች፣
328 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 17:42:42 እንደዚህ እያደረጉ እየሰሩ እንዲበሉ አስተምራ: አስጠምቃ
ከ6 የሚበልጡ አብያተ ክርስቲያናትን አስተክላላቸዋለች፡፡
+ከዚያም የተወሰኑ አገልጋዮችን አስቀምጣላቸው ወደ
ኢየሩሳሌም በመሄድ ለ7 ዓመታት በአየሩሳሌም ከኖረች
በኋላ የእመቤታችን በዓል ለማክበር ወደ ግብፅ በመሄድ
ላይ ሳለች በመንገድ አንድ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ገብታ
ስትፀልይ እመቤታችን በስዕሏ ላይ ተገልጣ: ቦታዋ
በኢትዮጵያ መሆኑን ነግራ: እጇን ዘርግታ "ወደ ኢትዮ

ጵያ
ሂጂ" ብላ ነገረቻት::

+በኋላ በብርሃን አምድና በቅዱስ ሚካኤል እየተመራች
አሁን ወደ ምትታወቅበትና የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ ወደ
ተገለፀበት እመ ምዑዝ ኪዳነ ምህረት ቅድስት ፍቅርተ
ክርስቶስ አንድነት ገዳም ደርሳለች፡፡
+በቦታው ስትደርስ የቦታው ልምላሜ የሚያስደስት ነበርና
"ይህች ቦታ ምን ታምር!" ብላለች፡፡ ቦታውም እስከ አሁን
ድረስ ምንታምር በመባል ይጠራል፡፡

+ምንታምር ላይ ከአገልጋዮቿ ጋር በመሆን አርፋ ሳለ
ከኢየሩሳሌም መርቶ ያመጣት የብርሃን አምድ በዚያ ቦታ
ላይ በስፋት ረቦ (ከምድር እስከ ሰማ ተተክሎ) ብታየው:
መልአኩም "ቦታሽ ይሄ ነው" ብሎ ቢነግራት በዚያው
ተቀምጣለች፡፡

+የቦታው ባለ አባት "ይህን ቦታ ልቀቂ" ቢሎ ቢጠይቃት
"እግዚአብሔር የሰጠኝ ቦታዬ ነው" ብላዋለች፡፡ እርሱም
ለክስ ወደ ጎንደር በመሄድ አፄ ሱስንዮስ አርፈው አፄ
ፋሲል ነግሰው ነበርና እሳቸውን ፍርድ ቢጠይቃቸው በዝና
ያውቋት ነበርና "ቤተ ክርስቲያን ካልተሰራ ትልቀቅልህ:
ከተሠራ ግን ሌላ ቦታ ይሰጥሃል" የሚል ፍርድ አስፈርዶ
ነበር::

+ሲመለስ ቅዱስ ሚካኤል ቀድሞ "ቶሎ ቤተ ክርስቲያን
ስሪ እንዲህ የሚል ፍርድ ተፈርዷል ብሎ ነግሯት ‹‹ታህሳስ
14 ቀን ከነግህ ፀሎት በኋላ በሰንሰልና በስሚዛ
ግድግዳዋን: በአይጥ ሀረግ ማገር አድርጋ: የግድግዳ
ቤተ መቅደስ በዕለተ አርብ: በአንድ ቀን ሰርታ ታህሳስ 16
ቀን እሁድ ታቦተ ኪዳነ ምህረትን አስገብታ ቅዳሴ
አስቀድሳለች::››

+ቅዳሴውም ከተፈፀመ በኋላ ጌታችን ከቅዱስ መንበሩ
ላይ እንዳለ ሆኖ ከእናቱ ከእመቤታችን ጋራ ታያቸው፡፡
ከመንበሩ ወርዶም ይህን ቦታ በባረከው ጊዜ የስሚዛው
ቤተ መቅደስ በአራቱም አቅጣጫ ለፈጣሪው ሰገደ፡፡

+የመሬት መናወጥም ሆነ:: ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም
"ልታጠፋን መጣህን? ቤተ ክርሰቲያኔንስ ልታፈርሳት
ነው?" ብላ ብትጠይቀው "ይህ የሰንሰል ቤተ መቅደስሽ
ዳግም እስከምመጣ ድረስ ሳይፈርስ: ሳይታደስ ፀንቶ
ይኖራል፣ በውስጡም እስከ ዓለም ፍፃሜ ድረስ
የክሀድያንና ፣ መናፍቃን እግር አይገባበትም፣ በውስጧ
ቁርባንን የተቀበሉ ሁለ ኃጢያታቸው ይሰረይላቸዋል፣
ዘወትር ምህረቴ በረከቴ ከእነርሱ ጋር ይኖራል" በማለት
ተናግሮ ተሰወራቸው፡፡

+ከዚያም በኋላ መነኮሳትና መነኮሳይያት የቅድስት ፍቅርተ
ክርስቶስን የትሩፋት ዜናዋን ሰምተው ከየአቅጣጫው
ተሰበሰቡ፡፡ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም በአምላክ ሀይል
ተጋድሎአቸውን ይፈፅሙ ዘንድ ታስተምራቸው ፣
ትመክራቸው፣ በተግባርም እያሳየቻቸው ለብዙ ዘመናት
ከኖሩ በኋላ በገዳሙ ላይ የአጋንንት ፆር እንዳይነሳ
ወንዶቹን ለብቻ ሴቶቹን ለብቻ አደረገች፡፡

+ዘወትርም እንዳይተያዩ የእግዚአብሔር መልዐክ
በቅድስተ ፍቅርተ ክርሰቶስ ፀሎት ይጠብቃቸው ነበር፡፡
ከዚህ በኋላ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ከዚህ
ኃላፊ ዓለም መለየቷ በቀረበ ጊዜ ሁለት መላዕክት ወደ
እርሷ መጥተው በብርሃን ሰረገላ ጭነው ወደ ደብረ ነባት
(ወደ ብሔረ- ህያዋን) ወስደው በዚያ ቅዱስ ቁርባንን
አቀብለው ወደ ቦታዎ መለሷት፡፡

+መልዐኩም "ከጻማ: ከድካም: ከመታረዝ: ከረሐብ
ከጥም: ከመትጋት: ከእንባ: ከዚህ ዓለም የምትለይበት
ጊዜ እነሆ ደረሰ" አላት፡፡ የካቲት 27 ቀንም ወደ ምስራቅ
እጇን ዘርግታ ቆማ ስትጸልይ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ
ከደስታ ብርሀን ጋር ያማረ ሽታ መላ::

+ጌታችን ከአዕላፋት መላዕክትና ቅዱሳን ጋር ወደ እርሷ
መጣ፡፡ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም ሰገደች፡
ተንበረከከች: እጅግም አለቀሰች፡፡ ከወደቀችበት ቦታ
አንስቶ ‹‹ላጠፋሽ አልመጣሁም ወዳጄ ላከብርሽ ነው
እንጂ›› አላት፡፡

+"የዘለአለም መንግስት አዘጋጅቼልሻለሁና ደስ ይበልሽ"፡፡
ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስም ቃል ኪዳን እንዲገባላት
ተማጸነችው:: ጌታችንም ‹‹ሁሉም እንደ ቃልሽ ይሁንልሽ::
በስምሽ ስሜ ተጨምሯልና ለቤተ ክርስቲያንሽ መባ
የሰጠ፣ የተላከ ፣የተቀበረ፣ ቤተ መቅደስሽ መጥቶ
የተሳለመ ፣ እስከ 12 ትውልድ የምህረት ቃል ኪዳን
ሰጠሁሽ::

+በረከቴም በቤቱና በልጆቹ በገንዘቡም ላይ ይደር::
የገድልሽ መጽሐፍ ባለበት አጋንንት (ሰይጣናት)
አይቀርቡም:: በአዝመራ ስምሽን በጠሩት ጊዜ የለመለመ
ይሁን:: በጸሎትሽ የተማጸነ ሁሉ ባለጤና ይሁን::

+ስምሽን በእውነት የሚጠራ የከበረ ነው፡፡ ያለመጠራጠር
በቀናች ሐይማኖት የገድልሽን መጽሐፍ የጻፈ: ያጻፈ:
ያነበበ: የተረጎመ በሐይማኖት የሰማ: እስከ ቀዝቃዛ ውሃ
ድረስ የሰጠ ኃጢያቱ ይሰረይለታል::
ስለ ድካምሽ ስለ ትሩፋትሽ 7 አክሊሎችን እና ይህን ሁሉ
ቃል ኪዳን ሰጠሁሽ፡፡ ላልምረው ቦታሽን
አላስረግጠውም›› ብሏት ወደ ሰማይ አረገ፡፡

+በማግስቱ ትንሽ ህመም ታመመች ደናግል መነኮሳትን
ጠርታ የእረፍት ቀኗ መድረሱን ነገረቻቸው:: ከመካከላቸው
አንዷን ለገዳሙ አስተዳዳሪነት መርጣ በፍቅር ስም
ተሰናበተቻቸው፡፡ የዳዊት መዝሙርንም ስትጸልይ የካቲት
29 ቀን እሁድ አጥቢያ ጠዋት በጌታ በዓል አንቀላፋች
(ነፍሷ ከስጋዋ ተለየች)፡፡

+ጌታችንም ከእናቱ: ከቅዱሳኑ ጋር መጥቶ ነፍሷን
ተቀብሎ ወደ ዘለዓለም ገነት ወሰዳት፡፡ ቅዱሳንም
ከመላእክት ጋር እልል እያሉ እያመሰገኑ ወደ ዘለዓለም
ቦታ ገነት አስገቧት፡፡ ከቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ መቃብር
ላይ 40 ቀናት ብርሃን ሲበራበት ታይቷል፡፡

+በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት: በመቂት ወረዳ ጥባ
ማርያም ቀበሌ ውስጥ ምን ታምር በመትባል ቦታ ላይ
በ16ኛው መቶ ክ/ዘመን በኢትዮጵያዊቷ ሰማዕትና ጻድቅ
ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ የተመሰረተቸው እመ ምዑዝ
ኪዳነ ምህት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድት ገዳምም
በዓላቶቿ የሚከበሩት ታህሳስ 16 የቅዳሴ ቤቷ እንዲሁም
የካቲት 29 ቀን በዓለ እረፍቷ ይከበራል፡፡

††† ከቅድስት እናታችን በረከት አምላክ አይለየን::

††† የካቲት 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
2.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ (ጻድቅና ሰማዕት)
3.ቅዱሱ ሕፃን (የፍቅርተ ክርስቶስ ልጅ)
4.ቅዱስ ቢላካርዮስ ዘሃገረ አርሞኒ (አረጋዊ: ደራሲ: ጻድቅና ሰማዕት)

††† ወርኀዊ በዓላት
1.የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
2.ቅድስት አርሴማ ድንግል
3.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
4.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ

††† "መልካም ያደረጉ ብዙ ሴቶች አሉ:: አንቺ ግን ከሁሉ ትበልጫለሽ::
ውበት ሐሰት ነው:: ደም ግባትም ከንቱ ነው::
እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች:: ከእጇ ፍሬ ስጧት:: ሥራዎቿም በሸንጐ ያመስግኗት::" †††
(ምሳሌ. 31:29)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
347 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 17:42:42 † † እንኳን ለኢትዮዽያዊቷ እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። † †

† † በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! † †

† † እመ ምዑዝ (እም ምዑዝ) † †

††† ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ሐዋርያዊት: ጻድቅትና ሰማዕት ናት::
ይህስ እንደምን ነው ቢሉ:-
=>ወር በገባ በ29 በቤተክርስቲያናችን ታስበው
ከሚውሉት እግዚአብሔር አምላክ ቃል ኪዳን ከገባላቸው
(ከሰጣቸው) እናቶች ኢትዮጵያዊቷ ሰማዕትና ጻድቅት
ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ (እመ ምዑዝ) ትገኛለች::
ፍቅርተ ክርስቶስ (እመ ምዑዝ) ማን ናት? ምን ቃል ኪዳን
ተሰጣት? ያደረገችውን ተጋድሎ በጥቂቱ እንመልከት:-
✞✞ ጻድቅን በጻድቅ ስም የሚቀበል የጻድቁን ዋጋ
ይወስዳል፡፡ (ማቴ. 10፡40) ✞✞

=>በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት በመቂት ወረዳ ጥባ
ማርያም ቀበሌ ውስጥ ምን ታምር በመትባል ቦታ ላይ
በ16ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኢትዮጵያዊቷ ሰማዕትና
ጻድቅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ የተመሰረተቸው እመ
ምዑዝ ኪዳነ ምህት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንድት
ገዳም ትገኛለች፡፡

+ይህች ገዳም ከአዲስ አበባ በደሴ ወደ ጎንደር
በሚወስደው መንገድ 665 ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኋላ
ገራገር (ፍላቂት) ከምትባለው ከተማ በመውረድ በእግር
2፡30 እንደተጓዙ ከ370 ዓመት ባለይ ያስቆጠረችውን
እመ ምዑዝ ኪዳነምህት ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ በአንድ
ቀን የሠራቻትና ለጌታ በአራቱም አቅጣጫ የሰገደችውን
ታላቅና ድንቅ ቤተመቅደስ ያገኛሉ፡፡

+የዚህች ታላቅ ገዳም መስራች ኢትጵያዊት ሰማዕትና
ጻድቅ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ በደቡብ ጎንደር ደራ ፎገራ
አንበሳሜ ወረዳ ልዩ ስሙ አቡነ ሐራ ገዳም አዋሳኝ ከተታ
ማርያም ተብሎ በሚጠራ ቦታ በሚያዚያ 4 ቀን ተፀንሳ
ታህሳስ 29 በጌታ ልደት ቀን ተወለደች፡፡

+አባቷ ላባ እናትዋ ወንጌላዊት የተባሉ እግዚዘብሔርን
የሚወዱ ትዕዛዙን የሚከብሩ ደጋግ ሰዎች ነበሩ፡፡
መሀን ሆነው ልጅ ባመውለዳቸው እያዘኑ ተግተው ወደ
እግዚአብሔር በመፀለያቸው ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስን
የመሰለች ልጅ: በፀሎትዋ ለሀገር ለወገን የምትበቃ
ሰጥቷቸዋል፡፡

+ከዚያም 80 ሲሆናት ለልጅነት ጥምቀት ወደ ቤተ
መቅደስ በወሰዷት ጊዜ ከጥምቀት በኋላ ስጋ አምላክ
ስትቀበል (ስትቆርብ) "ሕይወት የሆነውን ቅዱስ ስጋህን
ክቡር ደምህን የሰጠኸኝ አምላኬ ክብር ምስጋና ይግባህ"
ብላ አመስግናለች፡፡ ስመ ክርስትናዋ ማርያም ፀዳለ
ሲሆን የአለም ስሟ 'ሙዚት' ነው፡፡ ፍቅርተ ክርስቶስ
የምንኩስና (የቆብ) ስሟ ነው፡፡

+እናታችን ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አባ ዳንኤል ከሚባል
አባት መፅሐፍን እየተማረች ካደገች በኋላ ለአቅመ ሄዋን
ስትደርስ እናትና አባቷ ሊድሯት በመፈለጋቸው ዘርዓ
ክርስቶስ ለሚባል ከደጋግ ሰዎች ወገን ለሆነ ሰው
አጋቧት፡፡

+ማታ እንደ ሙሽሮች ደምብ ወደ ጫጉላ ቤት ሲገቡ
ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ዘርዓ ክርስቶስን "ወንድሜ ሆይ!
እኔ የእናት አባቴን ፍቃድ ለመፈፀም ነው እንጂ ስጋዊ
ሙሽራ መሆን አልፈልግም ፡፡ ፍላጎቴ የእግዚአብሔር
ሙሽራ መሆን ነው" በማለት ብታማክረው ቅዱስ ዘርዓ
ክርስቶስም ፀጋ እግዚአብሔር የበዛለት ሰው ነበርና "እኔም
እናት አባቴን ላክበር ፈቃዳቸውን ለመፈፀም ነው እንጂ
የስጋ ፈቃድ የለኝም በማለት ተነጋገሩ::

+በኋላ በአንድ ቤት ውስጥ ለቤተሰቦቻቸው: ለአገሬው
እንደ ባልና ሚስት ግን በንፅህና ለ40 ዓመት ሁለቱም
በድንግልና ኖረዋል፡፡

+ከዚያም በኋላ በእግዚአብሔር ፈቃድ ቅዱስ ሚካኤል
መጥቶ ወንድ ልጅ እንደሚወልዱ ቢግራቸውም ሁለቱም
"ይህስ አይሆንም" ብለው ለ40 ቀን በጾም: ፀሎት:
በትጋት ጸልየዋል፡፡ መልአኩ ተገልጦ "ይህ የእግዚአብሔር
ፈቃድ ነው ሁለታችሁም ድንግልናችሁ አይፈርስም ብሎ
ነግሮአቸዋል፡፡

+ከዚያም ወንድ ልጅ ወልደዋል:: ህፃኑ በተወለደ በ7
ዓመቱ በቅዱስ ሚካኤል እቅፍ ገነትን ለ7 ቀናት ከጎበኛት
በኋላ ወደ ምድር ሲመልሰው "በእናት አባቴ አምላክ
ይዤሃለሁ ወደዚች ወደ ከፋች ዓለም አትመልሰኝ" ብሎ
ቢለምነው ቅዱስ ሚካኤልም ከአምላክ ጠይቆ በብሔረ
ህያዋን የህፃናት አለቃ ተብሎ እንዲቀመጥ አድርጎታል፡፡
ስሙም ዳግማዊ ቂርቆስ ተብሏል፡፡

+ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶና ቅዱስ ዘርዓ ክርስቶስም ልጅ
ከወለዱ በኋላ እንደ ቀደሞው በቅድስና: በንፀህና ፀንተው
ኑረዋል፡፡ በዘመናቸው በኢትዮጵያ ነግሶ የነበረው አፄ
ሱስንዮስ ሃይማኖቱን ለውጦ 'ሁለት ባህርይ የሚሉ
ካቶሊኮችን በመቀበሉ ክርስቲያኖችን እየገደለ ነው' የሚል
ወሬ ሰምተው ወደ ንጉሱ በመሄድ ሳይፈሩ ስለ ተዋህዶ
ሃማኖታቸው በንጉሱ ፊት መስክረዋል፡፡

+ንጉሱም በጣም የበዛ መከራን አድርሶባቸዋል፡፡ መከራ
በበዛ ቁጥር እነርሱም እየፀኑ ተከታዮቻቸውንና የንጉሱን
ሠራዎቶች ሳይቀር አሳመኑ:: 60,000 ክርስቲያኖችም
ሰማዕትነትን ተቀብለዋል፡፡

+ንጉሱም በጣም የበዛ መከራ አድርሶባቸዋል፡፡ መከራ
በበዛ ቁጥር እነርሱም እየጸኑ ተከታዮቻቸውንና የንጉሱን
ሰራዊቶች እያሳመኑ ቢያስቸግሩ በሰማዕትነት አንገታቸውን
አስቆርቷቸዋል፡፡ አንገታቸውም ሲቆረጥ ከሁለቱም ደም
ውሃ ወተት ፈሷዋል፡፡

+በዚያን ዘመን ከእነ ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ጋር
ሰማዕትነት ከተቀበሉት ውስጥ የማህበረ ስላሴው ጻድቁ
አምደ ስላሴ: የጎረጉር ማርያም አባ መርአዊ: የመሲ
ኪዳነ ምህረት እመ ወተት እና ከ60 ሺ በላይ ክርስቲያኖች
ሰማዕትነት ተቀብለዋል፡፡

+ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ አንገቷ ከተቆረጠና ሰማእትነት
ከተቀበለች በኋላ ወደ ምድር መልሶ አንገቷን ከቀሪው
የሰውነቷ ክፍል ጋር አዋህዶ ከአንቅልፍ አንደሚነቃ ሰው
ቀስቅሶ አስነስቷቷል፡፡
ከዚያም ከአቡነ ማርቆስ ስርዓተ ምንኩስናን በመቀበል
ዋልድባ ገዳም ለ4 ዓመት አገልግላለች፡፡

+ከዚህም ከ500 የሚበልጡ ተከታዮችዋን መነኮሳትን
አስከትላ በሰሜን ወሎ ቆቦ ወረዳ ወደምትገኘውና በፃድቁ
በአባ ጉባ ተመስርታ ጠፍታ ወደ ነበረችው ራማ ኪደና
ምህረት አንድነት ገዳም በመሄድ ገዳሟን አቅንታ: የወንድ
የሴት ብላ ስርዓት ሰርታ: ገዳሟን አስተካክላ: 500
የሚሆኑ አገልጋች መነኮሳትን አኑራ ወደ ኢየሩሳሌም ጉዞ
ጀምራለች፡፡

+በመንገዷም ላይ ሰውን የሚበሉ ወደ ሚኖሩበት አካባቢ
በመድረስ እነርሱም እርሷንና 60 የሚሆኑ አገልጋዮችዋን
ዓይኖቻቸውን በጉጠት በማውጣት ለ4 ወራት በጨለማ
ቤት ውስጥ ዘግተውባቸዋል፡፡ ከአራት ወር በኋላም በዓል
አድገው ለመብላት ከቤት ቢያወጧቸው መልካቸው እንደ
ፀሐይ የሚያበራ ቢሆንባቸው "አንቺ ሴት ምንድን ናችሁ?"
ብለው ጠይቀዋታል፡፡

+እርሷም ክርሰቲያን መሆናቸውንና እነሱ የስላሴ ሕንፃ
የሆነውን የሰውን ልጅ መብላት እንደሌለባቸው
ብትመክራቸው "ምን አንብላ?" ብለዋታል፡፡ እርሷም
ከራማ ኪዳነ ምህረት ስትነሳ የእህል ዘርን በአገልጋዮቿ
አሲዛ ነበርና ስንዴውን በአንድ ቀን ዘርታ: በቅሎ: ታጭዶ:
ደርቆ: ተፈጭቶ ለምግብነት በቅቷል፡፡

+እርሷ ቀምሳ ብታቀምሳቸው እንደማር እንደ ወተት
የሚጣፍጥ ሆኖላቸው በደስታ ተመግበውታል፡፡ ከዚያም
559 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 17:42:38
570 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 14:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-07 15:02:01 ☞"ተስፋ የሕይወት ዘመናችን ብቸኛው ወዳጅ ነው የሚበልጠው ተስፋችን ደግሞ እግዚአብሔር ብቻ ነው።

☞በተስፋ ዋሉ መልካም ቀን።
985 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 12:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ