Get Mystery Box with random crypto!

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxtewahdoc — "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxtewahdoc — "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
የሰርጥ አድራሻ: @orthodoxtewahdoc
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.88K
የሰርጥ መግለጫ

🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን
/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ።
📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼
❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-07-21 14:01:18 ††† እንኳን ለታላቁ ሊቅና አፈ በረከት ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ †††

††† እንደ ቤተ ክርስቲያናችን ትውፊት ቅዱስ ኤፍሬም የተወለደው ንጽቢን በምትባል የሶርያ ግዛት ውስጥ በ298 / 306 ዓ/ም ነው:: ወላጆቹ በክርስቶስ የማያምኑ አላውያን ነበሩ:: (ምንም አንዳንድ ምንጮች ክርስቲያኖች ነበሩ ቢሉም)

ቅዱሱ ተወልዶ ባደገባት ንጽቢን ጵጵስናን የተሾመ ቅዱስ ያዕቆብ የሚባል ታላቅ ሰው ነበር:: የሰማዕትነት: የሐዋርያነት: የጻድቅነትና የሊቅነት ግብር ያለው አባት ነው:: ታዲያ ቅዱስ ኤፍሬም ይሔ አባት ሁሌ ሲያስተምር ይሰማው ነበርና በስብከቱ ተማርኮ ደቀ መዝሙሩ ለመሆን በቃ::

ቅዱስ ኤፍሬም በቅዱስ ያዕቆብ እጅ ከተጠመቀ በኋላ ሙሉ የወጣትነት ጊዜውን ያሳለፈው በትምሕርት ነው:: የሚገርመው መምሕሩ ቅዱስ ያዕቆብ ዘንጽቢን እመቤታችን ድንግል ማርያምን በፍጹም ልቡ የሚወድና ጠርቷት የማይጠግብ አባት ነውና ለልጁ ለቅዱስ ኤፍሬም ይሕንኑ አጥብቆ አስተምሮታል::

ቅዱስ ኤፍሬም ክርስትናን ሲመረምር የእመቤታችን ፍቅር ይበዛለት ጀመር:: ምክንያቱም እመ ብርሃንን ሳይወዱ ክርስትና የለምና:: እንደ እርሱ የሚወዳት የለም እስኪባል ድረስ ያገለግላት: ይገዛላትም ገባ::

እንዲህ እንደ ዛሬ የድንግል ማርያም ምስጋና በአንደበት እንጂ በመጽሐፍ አይገኝም ነበር:: እርሱ ግን ከወንጌለ ሉቃስ በስድስተኛው ወርን (ይዌድስዋን) እና ጸሎተ ማርያምን(ታዐብዮን) አውጥቶ በየዕለቱ በዕድሜዋ ልክ ስልሳ አራት ስልሳ አራት ጊዜ ያመሰግናት ነበር::

በእንዲህ ያለ ግብር እያለ አርዮስ በመካዱ እርሱን ለማውገዝና ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ለማጽናት በ317 (325) ዓ.ም ሦስት መቶ አሥራ ስምንቱ ሊቃውንት በኒቅያ ሲሰበሰቡ አንዱ መምሕረ ኤፍሬም ቅዱስ ያዕቆብ ነበር:: በዚህ ምክንያት ቅዱስ ኤፍሬም ከሊቃውንቱ ትምሕርትና በረከትን አግኝቷል::

ከጉባዔ መልስ መንገድ ላይ በራዕይ የብርሃን ምሰሶ አይቶ "ጌታ ሆይ! ምንድን ነው?" ብሎ ቢጠይቅ "ይሕማ ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ ነው::" አለው:: እርሱም መምሕሩን ቅዱስ ያዕቆብን ተሰናብቶ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ (ቂሣርያ) ወረደ:: ተገናኝተውም በአንድ ሌሊት ቋንቋ ተገልጦላቸው ሲጨዋወቱ አድረዋል::

በቦታው ብዙ ተአምራት ተደርጓል:: ቅዱስ ኤፍሬም ከታላቁ ባስልዮስ ከተማረ በኋላ ሃገረ ስብከት ተሰጥቶት ያስተምር ጀመር:: ሁል ጊዜ ታዲያ ጸሎቱ ይሔው ነበር:: "እመቤቴ ሆይ! ምስጋናሽ እንደ ሰማይ ከዋክብት: እንደ ባሕር አሽዋ በዝቶልኝ: እንደ እንጀራ ተመግቤው: እንደ ውኃ ጠጥቼው: እንደ ልብስም ተጐናጽፌው" እያለ ይመኝ ነበር::

አፍጣኒተ ረድኤት: ፈጻሚተ ፈቃድ እመ ብርሃንም በገሃድ ተገልጻ የልቡን ፈቃድ ፈጸመችለት:: ዛሬ ጸጋ በረከት የምናገኝበትን ውዳሴ ማርያምን ደረሰላት:: ሲደርስላትም እርሷ አእላፍ መላእክትን: ጻድቃን ሰማዕታትን አስከትላ ወርዳ: በፊቱም ተቀምጣ ሲሆን እርሱ ደግሞ ባጭር ታጥቆ: በፊቷ ቆሞ: በመንፈስ ቅዱስም ተቃኝቶ ነው::

ውዳሴዋን በሰባት ቀናት ከደረሰላት በኋላ በብርሃን መስቀል ባርካው: ሊቀ ሊቃውንትም እንዲሆን ምሥጢር ገልጣለት ዐረገች:: ከዚህ በኋላ በምሥጢር ባሕር ውስጥ ዋኝቶ አሥራ አራት ሺህ ድርሰቶችንም ደርሷል:: ዛሬ ሶርያ ውስጥ የምንሰማውን ዜማም የደረሰው ይህ ቅዱስ ነው::

እንዲያውም አንድ ቀን የምሥጢር ማዕበል ቢያማታው "አሃዝ እግዚኦ መዋግደ ጸጋከ" ብሎ ጸልዩዋል:: (የጸጋህን ማዕበል ያዝልኝ) እንደ ማለት ነው:: ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በመጨረሻ ሕይወቱ ተክሪት በምትባል ሃገር ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ ተሹሟል::

በጣፋጭ ስብከቱ ብዙዎችን ካለማመን መልሷል:: የምዕመናንንም ሕይወት አጣፍጧል:: ለመናፍቃንና ለአርዮሳውያን ግን የማይጋፉት ግድግዳ ሆኖባቸው ኑሯል:: በዘመኑም ብዙ ተጋድሎ አፍርቷል:: ተአምራትንም ሠርቷል:: በተወለደ በስልሳ ሰባት ዓመቱ በ365 (373) ዓ.ም ዐርፎ ተቀብሯል::

††† ቅዱሱ ለሶርያ ብቻ ሳይሆን እመቤታችንን ለምንወድ የዓለም ክርስቲያኖች ሁሉ ሞገሳችን ሆኗል:: ስለዚህም እንዲህ እያልን እንጠራዋለን:-
1.ቅዱስ ኤፍሬም
2.ማሪ ኤፍሬም
3.አፈ በረከት ኤፍሬም
4.ሊቀ ሊቃውንት ኤፍሬም
5.ጥዑመ ልሳን ኤፍሬም
6.አበ ምዕመናን ኤፍሬም
7.ርቱዐ ሃይማኖት ኤፍሬም . . . አባታችን አንተ ነህ::

††† ጽንዕት በድንግልና: ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን ለቅዱስ ኤፍሬም የሰጠሽውን ጸጋውን: ክብሩን: አእምሮውን: ለብዎውን በልቡናችን ሳይብን: አሳድሪብን . . . አሜን::

††† ጴጥሮስ ወጳውሎስ †††

††† ዳግመኛ በዚህ ቀን ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ ይታሠባሉ::

ቅዱሳኑ ሶርያ አካባቢ ውስጥ ወደምትገኝ አንዲት ሃገር ገብተው ሕዝቡን ከንጉሣቸው ጰራግሞስ ጋር አሳምነው አጥምቀዋል:: ነገር ግን እነርሱ ሲወጡ ሰይጣን አስቶት አጥፊ ሰው ወደ መሆን ተመልሶ ንጉሡ ሐዋርያትን አሰቃይቷቸዋል::

ስለ ቅዱሳኑ ግን ፈረሶቹ ሰግደው: በሰው አንደበት ቅድስናቸውን መስክረዋል:: በመጨረሻም ንጉሡን ከነ ሕዝቡና ሠራዊቱ በዓየር ላይ ሰቅለው ንስሐ ሰጥተውታል:: በእነዚህ ተአምራትም ሁሉም አምነው ለከተማዋና ለሕዝቡ ድኅነት ተደርጓል::

††† ከአባቶቻችን አበው ሐዋርያት በረከት ይክፈለን::

††† ሐምሌ 15 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ ማሪ ኤፍሬም ሶርያዊ (አፈ በረከት)
2.ብርሃናተ ዓለም ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ወጳውሎስ
3.አባ ሓርዮንና ደቀ መዛሙርቱ (ሰማዕታት)
4.አባ ፍሬምናጦስ መስተጋድል

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ
2.ቅዱስ ሚናስ (ማር ሚና) ሰማዕት
3.ቅድስት እንባ መሪና
4.ቅድስት ክርስጢና

††† "ለምኑ ይሰጣችሁማል:: ፈልጉ ታገኙማላችሁ:: መዝጊያ አንኳኩ ይከፈትላችሁማል:: የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና:: የሚፈልገውም ያገኛል:: መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል::" †††
(ማቴ. ፯፥፯)

††† "የጻድቅ አፍ ጥበብን ያስተምራል::
አንደበቱም ፍርድን ይናገራል::
የአምላኩ ሕግ በልቡ ውስጥ ነው::
በእርምጃውም አይሰናከልም::" †††
(መዝ. ፴፯፥፴)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://t.me/zikirekdusn
1.7K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 14:01:18
1.7K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 11:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 01:24:15 ወር በገባ በ14 ቅዱሳን አባቶች አቡነ አረጋዊ ሙሽራው ገብረ ክርስቶስ እና አባ መቃርስ ናቸው።

ጥበቃቸው አይለየን
2.3K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 22:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 01:22:49 "አባታችን አቡነ አረጋዊ ሆይ ስራችን በተገለጠ ጊዜ ወደ ምታስፈራ ባህረ እሳት ውስጥ እንዳገባ እኛ ልጆችህን አድነን።

አሜን በእውነት
2.2K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 22:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-21 01:12:51 ☞በዕለተ አርብ ከተፈጸሙ ተአምራት፡

✞በዕለተ ዓርብ ከተፈጸሙት ተአምራት ሁሉ እጅግ አሰደናቂው ተአምር የሰው
ልጅ መዳኑ ነው፡፡✞ከፀሐይ መጨለምና ከጨረቃ ደም መምሰል በላይ የእኛ የጨለመ ማንነታችን
ብሩህ ማድረጉ ነው፡፡
✞ከቤተ መቅደስ መጋረጃ መቀደድ በላይ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል
የነበረው የጥል ግድግዳ መፍረሱ ነው፡፡
✞ከሙታን ከመቃብር መውጣት በላይ የሰው ልጅ ከሲኦል መውጣቱ ነው፡፡
✞የክርስቶስ የደሙ ጠብታ ዓለምን ከኃጢአት ማጠቧ እጅግ አሰደናቂዎቹ
የመስቀል ላይ ተአምራት ናቸው፡፡
✞ጌታቼን በሮማውያን እጅ ዕርቃኑ በተሰቀለበት ዕለቴ ከቀኑ በስድስት ሰዓት ላይ
ታላቋ የእሳት ኳስ ብርሃናዊቷ ፀሐይ ድንገት ጨለመች፤ ጨረቃም ደም
መሰለች፤ ከዋክብትም ረገፋ(ጨለሙ)፡፡
✞በነቢዩ ሚልክያስ"ስሜን ለምቴፈሩ ለእናንተ የጽቅ ፀሐይ ትወጣለችኃለች
ፈውሴም በከንፎችዋ ውስጥ ይሆናል" ተብሎ በትንቢት የተነገረለት እውነተኛው
ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ በሐስቀል እጆቹን እንደ ክንፍ በዘረጋ ጊዜ በእውነተኛ
ፀሐይ ፊት ማብራት ያልቻላት ፀሐይ በድንገት ጨለመች፡፡
✞በመዞር ምክንያት የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ የሌለበት ለሁሉ የሚያበራው
እውነተኛው ብርሃን ክርሰቶስ በመስቀል ላይ እንደተሰቀለ ባየች ጊዜ ታናሽዋ
ፀሐይ ብርሃን ከለከለች፡፡
✞ማንነቱን ያልተረዱት አይሁድ ዕርቃኑን ስቅለው እያዩ ሊዘባብቱበት ሲቆሙ
ፍጥረታቱ ግን አምላካቸው ተሰቅሎ አይተው መቋቋም ተሳናቸው፡፡
✞ስለ ጌታችን ሥቃይ ምድርን በኅዘን አጨለሟት፤ ስለ ጌታችን ደም መፍሰስ
ጨረቃ ደም መሰለች፤ ሰዎች በፈጣሪ ፊት ሰላሳዩት ድፍረት የሰዎች መገኛ
የሆነችው ምድር ተንቀጠቀጠች፡፡
✞ሰውነቱ በግርፋት መሰንጠቁን አይተው ዓለታትም ተሰነጣጠቁ፡፡ "ፍጥረታት
ሁሉ በሥቃዩ አብረውት ተሠቃዩ፤ ሲሰቀል እንዳታየው ፀሐይ ሸሸገች፡፡ ከእርሱ
ጋር አብራ ልትሞት ብርሃንዋን አጠፋች ለሦስት ሰዓታት ከሆነ በኃላ ግን መልሳ
አበራቸሰ፤ ይህም በሦርተኛው ቀን እንደሚነሣ ስትመሰክር ነው ይላል ቅዱስ
ኤፍሬም
✞የሰማይ ብርሃናት የመጨለማቸው ምክንያት የጌታችንን ዕርቃኑን እነርሱ
በብርሃናቸው አይተዎ ለሌላ ላለማሳየት ነው፡፡
✞ጻድቁ ኖኅ የወይን ጠጅን ጠጥቶ በሰከረና ዕርቃኑን በሆነበት ዕለት ልጁ ካም
ዕርቃኑን እያየ ሲዘብትበት ሴምና ያፌት የተባሉ ልጆቹ ግን የአባታቸውን ዕርቃን
ሸፍነው ነበር
✞እንደ ኖኅ በጠጅ ሳይሆን በሰው ልጅ ፍቅር ሰክሮ ዕርቃኑን በመስቀል ላይ
የተሰቀለውን መድኃኔ ዓለምን ክርስቶስንም አይሁድ እንደ ካም ሲዘብቱበ፤ ፀሐይ
ጨረቃና ከዋክብት ግን እንደ ሴምና ያፌት ዕርቃኑን ሸፈኑለት፡፡
☞(በዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ ከተጻፈው "ሕማማት" መጻሐፍ የተወሰደ፡፡
☞ሲራክ ተክላጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞14-11-2015

በቅንነት ቴሌግራምተአምራት፡፡
https://t.me/Orthodoxtewahdoc
2.0K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 22:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-20 22:59:57 ከዋሸህ አትማል አንዱ ኃጢአት ይበቃል

✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" ምሳ 1፥33
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ስንክሳር ዘወርኃ ሐምሌ ፲፬/14/

https://t.me/Orthodoxtewahdoc
የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን
2.1K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , edited  19:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-13 01:41:22 አርሴማ ማለት በወርቅ ልብሶች የተጎናጸፈችና የተሸለመች መልከመ ልካምና ውብ ማለት ነው።

የሰማዕቷ ጥበቃ አይለየን
67 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 22:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ