2023-06-12 19:13:26
ወር በገባ በ1እና በ6 ቅዱስ ኤልያስ ነው
መልከአ ቅዱስ ኤልያስ እነሆኝ #ኦ ኤልያስ
1.ተአምራትን ላደረገ ለደቀ መዝሙርህ ለኤልሳዕ ከመጠምጠሚያ ጋር መንፈስን በእጥፍ የሰጠኸው ኤልያስ ሆይ የመልክህን ሰላም እናገር ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እንደወለዳቸው በየሀገሩ ቋንቋም እንደተናገሩ እንደ ሀዋርያት በተቀደሰች ረድኤትህ ከጌታህ ጸጋን ስጠኝ።
*ሰላም ለትርጓሜ ስምከ*
2. ዘይት ለተባለ ለስምህ ትርጓሜ ሰላምታ ይገባል።መቆረጥን ላልተቆረጠ ጸጉርህም ሰላምታ ይገባል ።ስምህን በመጥራት ኤልሳዕ የዮርዳኖስ ውሃ ከፈለ ፤ክፋትን ሳልሰራ ክፉ ስምን አትስጠኝ።
*ሰላም ለርዕስከ ወለ ገጽከ*
3,ለራስህ መልኩ እንደ ጽጌረዳ ለሚያበራው ወደ ብሔረ ሕያዋን በገባ ጊዜ እስክንድር ለተመለከተው ፊትህም ሰላምታ ይገባል።ኤልያስ ሆይ የኩነኔ እና የጭቀትን ወንዝ እሻገርበትም ዘንድ የአንተን መጠምጠሚያህን ስጠኝ።
*ሰላም ለቀራንብትከ ወለአይንትከ*
4 //ለቅንድቦችህ በታቦር ደም ግባቱ ያማረ የክርስቶስን ምስጋና ለተመለከቱ አይኖችህ ሰላምታ ይገባል።
ከታላቅነቱ የተነሳ የሙሴ ጓደኛ የሐዋርያት አለቃቸው ኤልያስ ሆይ ይቅርታን እንዳደረገው እንደ አብድዪ ይቅርታህን አሳየኝ። እንደ ኢዩብም የኃይል መንፈስን አሳድርብኝ።
*ሰላም ለአእዛኒከ*
5. መጀመሪያ በኮሬብ ብኃላም በታቦር ከእግዚአብሔር ዘንድ ነገርን ለሰሙ ጆሮችህ ሰላምታ ይገባል።ኤልያስ ሆይ ምቾትን ሁሉ ትፈጽምልኝ ዘንድ ከድንግል ማርያም ጋር በአንድነት ና።
*ሰላም ለመላትሒከ*
6.ቀጭን እንደሆነ የፉጨት ድምፅ ያለ የአብን ቃል በሰማ ግዜ በመጠምጠሚያው ለተሸፈነው ፊትህ ሠላምታ ይገባል።ይዘኑትን ፊት ብሩህ የምታደርግ ኤልያስ ሆይ በጸሎትህ የመካኗ ደመና ማሕፀን በተፈታ ጊዜ በዚያን ወቅት ኀዘኑ ተረሳ።
*ሰላም ለአዕናፍከ*
7.የጻድቃን ነፍሶች በየጊዜው የሚያሸቱት ሽታው የአሞራ አበባ ለሆነው ለአፍንጫህ ሰላምታ ይገባል።
ከኄኖክና እርሱን ከመሰሉት ጋር በአንድነት የምትኖር ኤልያስ ሆይ ለተወደደው የይቅርታ ደመና አበባው እንዳያልፈኝ አባቴ ለአፍንጫዬ የመዓዛህን በር ክፈት።
8. *ሰላም ለልሳንከ ወለአፍከ*
ለከንፈሮችህ በጽሕም ለተከበበ ከዕርሱም የእሳትና የፍም ነጸብራቅ ለሚወጣበት ለአፍህ ሰላምታ ይገባል።የሁዋላና የፊት ነብይ ኤልያስ ሆይ በሄድሁበት መንገድ ዝናም እንዳይመጣብኝ የቀደመው ተአምርህን ፅንዓት ዛሬ አሳየኝ።
*ሰላም ለስህን ህብስተ*
9 .በመጀመሪያ በሁለተኛ ጊዜም በተቀደሰው መልአክ እጅ የህይወትን ሕብስት ላላመጠው ለጥርስህ ሰላምታ ይገባል። በየለቱ የማትለወጥ ጉዋደኛ ኤልያስ ሆይ በአንድነታቸው ክርክር እንዳይመጣ የዘወትር ፍቅርን ስጣቸው ።
*ሰላም ለልሳንከ*
10. በዕልፍ ሳይሆን በመቶ ወንዶች ዘንድ እንደሚነድድ እሳት ሰይፍ ለሆነው ለአንደበትህ ሰላምታ ይገባል። እስከዘላለሙ የማትተኛ ወፍ ኤልያስ ሆይ በፀሎትህ ዘወትር የሚያሰቃዬኝ የደዌ መንፈስ ከእኔ አስወግድ የአንደበቴ ዛፍ ለስምህ መጠለያ ነውና።
*ሰላም ለቃልከ*
11.በሽንገናላና በበደል ነገር ናቡቴን በገደለው ግዜ አክዓብን ላስደነገጠው ለቃልህ ሰላምታ ይገባል። ኤልያስ ሆይ በአምስቱ ሰነፎች ላይ በሩ በሚዘጋበት ግዜ ከሰማያዊ ሙሽራ ቤት ከብልሆቹ ጋር እገባ ዘንድ በደስታ ወደ አንተ አቅርበኝ።
*ሰላም ለእስትንፋስከ*
*12,,* የሞተ የመበለቷን ልጅ ላስነሣ ለትንፋሽህ የውኃው ምንጭ በጠፋ ጊዜም ለተጠማው ለጉረሮህ ሰላምታ ይገባል ።
ለአርባ ቀን ያህል የጾምህ ኤልያስ ሆይ ዛሬ ግን ረኅብና ጽምን አታሳየኝ ።አሞራ ሆነህ መግበኝ እንጂ።
*ሰላም ለክሳድከ*
*13,,* የቅድስና አስኬማን ለለበሰ ለአንገትህ ሰላምታ ይገባል። ልብሷ የፍየል ሌጦ ለሆነው ለትከሻህ ሰላምታ ይገባል። በምሳሌና በዜና ከታላላቆች ይልቅ ታላቅ የሆንህ ኤልያስ ሆይ ሕይወትህ የመላእክት ነው ። የሀገርህ ጠልም መና ነው አስኬማህም ነውር የለባትም ።
*ሰላም ለዘባንከ*
*14,,* ለጀርባህ የጉልማሳነትህ ጽሕም ንጉስ ለተጠጋበት በፊትህ ለሚገኘው ለደረትህም ሰላምታ ይገባል ። ሕማም በሌለበት ሀገር የምትኖር ኤልያስ ሆይ ነፋስ በነፈሰ ዝናብም በዘነመ ጊዜ በእቅፍህ አድርገህ ከበጋና ከክረምት መብረቅ ሰውረኝ ።
*ሰላም ለአዕዳዊከ*
*15,,* በመስቀል ላይ በቀራኒዮ እንደ ተሰቀለ እንደ ኢየሱስ ክርስቶስ ለጸሎት ለተዘረጉ እጆችህ ሰላምታ ይገባል ። ኤልያስ ሆይ ለለመነህ ምግቡን ስጠው። በፊትህ ቢበድልም በደሉን ይቅር በለው። ለሚቀና መገዛቱ ይቀርለት ዘንድ ተወስኗልና።
*ሰላም ለመዝራዕትከ*
16, በወይን ግድ እዳለ ቅርንጫፍ የአንጓዎችህ ቦታ ለሆኑ ክንዶችህ ሰላምታ ይገባል። በአለም ፍጻሜ ግዜ የትንሳኤን ተስፋ የምትናገር ኤልያስ ሆይ መጠኑ የአምላክ ትንሳኤ የሆነለት ትንሳኤህን በምናምን በእኛ ላይ በረከትህን ላክ።
*ሰላም ለእመትከ*
17,ለክድህ የሚሰጥ ስጋን ለመቀበል ከቁራ አፍ ይልቅ ለሚሰፋው ለመሃል እጅህ ሰላምታ ይገባል። ኤልያስ ሆይ የሳራ ሁለተኛ ከሆነች ከጥበበኛዋ እናትህ ሁለንተናህ በሳት ተከብቦ የተወለድኸው የእዮብ መታሰቢያ በሆነች በመስከረም አንድ ነው።
*ሰላም ለአጻቢእከ*
18// አምስት በወዲያ አምስት በወዲህ ሆነው በጥፍር ልብሶች ለተሸለሙ ጣቶችህ ሰላምታ ይገባል። ኤልያስ ሆይ በምድር ነገስታት እና በእየሱስ ክርስቶስ ፊት የነፍስና የስጋ ሞገስን ስጠኝ። አባት ሆይ አንተ የሞገስ ነብይ ነህ።
*ሰላም ለገቦከ*
19. ማረፊያን፣አልጋን፣ምንጣፍን ላልፈለገው ጎንህ ሰላምታ ይገባል፤የማትተኛ ዘወትርም የማታንቀላፋ ኤልያስ ሆይ ያለጊዜው ከመሞት ወጥመድ ማለፊያ ሁነኝ። ዘወትርም የምገረፍ አልሁን።
*ሰላም ለከርስከ*
20. መብል መጠጥ፣የካህኑ የአሮን ልብስም ለማያስጨንቀው ለሆድህ ሰላምታ ይገባል። ከዕዝራና ከሄኖክ ጋር አንድ የምትሆን ብፁዕ ኤልያስ ሆይ መጽሐፍህ ምስክር እንደሆነ ሀገርህ የተድላና የደስታ ሀገር አይደለችምን?
*ሰላም ለልብከ*
21. በመሬት እየኖረ እንደብፁዓን ፃድቃን የላዩን ለሚያስብ ልቦናህ ሰላምታ ይገባል። እንደ አምላክ በቃልህ ሁሉን የቻልህ ኤልያስ ሆይ ሰባ ሁለቱም የአክዓብ ልጆች ሁሉ በቃልህ ታምመው የጠፋ አይደለምን?
*ሰላም እብል ለኩልያትከ*
22. በሕይወት የምትኖር የሕያዋን አለቃ ኤልያስ ሆይ መንታ ለሆነው ኩላሊትህ ሰላምታ ይገባል ፤ አባት ሆይ ከሩቁ ሰማይ እሳትን በጠራህ ጊዜ፥ መሥዋዕትህን ፤ከድጋዩ ጋርም እንጨቱን በላ ። ከውኃው ጋርም መሬቱን ላሰ።
*እኤምሀ በህሊናዬ*
23 በሕሊናዬ የተቀደሰ ሕሊናህን ሰላም እልሀለሁ።ለውስጣዊ አካልህም ሁሉ ምስጋናን አቀርባለሁ።አሮጌውን የለበስህ አዲሱንም የተጎናጸፍህ ኤልያስ ሆይ ባለሟልነትን ባገኘህ ጊዜ የዝናምን ኃይል አቆምህ ለሶስት ጊዜ ያህልም የሰማይ እሳትን አወረድህ።
*ሰላም ለእንብርትከ*
24 ሞት ያልሰረቅህ መቃብርም ያላጠፋህ መዝገብ ኤልያስ ሆይ ለእንብርትህ ሰላምታ ይገባል።የአንደበቴን ሰላም ዕጠብቅ ዘንድ በደልን የሚያስተሰርይ አድርግልኝ በአዲስ ሕዝቦች መካከል እግዚአብሔርን ሽቶ እንደቀባች አንደ ጥበበኛዋ ማርያምም አድርገኝ።
*ሰላም በኅቊኤከ*
25//መታጠቂያ ቁርበት ለሆነ ለወገብህ ሰላምታ ይገባል። የመለኮት ቃል ምሳርህም አካዝያስ ዛፍን የቆረጠው ነው።ሰውነትህ ጸጉር ነው።ኑሮህም በገዳም ነው።በምግባርም በስም አንድ የምትሆኑ ኤልያስ እና ዮሐንስ ሆይ ዛሬ በበዓላችሁ ቀን ባርኩን።
*ሰላም እብል ለዘዚአከ*
616 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 16:13