2023-05-03 16:28:37
#ኢትዮጵያዊው ፃድቅ አቡነ ሀብተ ማርያም
•••ወር በገባ በ26 የምናስባቸው አምስቱን መቅሰፍቶች የማስወገድ ስልጣን የተሰጠቸው ፃዲቁ አባታችን አቡነ ሀብተማርያም የነበሩበት ዘመን 1486 ዓ.ም ንጉስ እስክንድር በነገሰበት ጊዜ ነው። አባቱ ፍሬ ቡሩክ እናቱ ዮስቴና ይባላሉ። ፍሬ ቡሩክና ዮስቴና በህገ እግዚአብሔር በሃይማኖት በትሩፋት በምግባር ፀንተው የሚኖሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ነበሩ፡፡ አቡነ ሀብተማርያም ከተሰጣቸው ቃል ኪዳኖች ውስጥ አምስት መቅሰፍቶች የማስወገድ ስልጣን ተሰጧቸዋል፡፡ እነሱም፡-
1/ መብረቅ፣
2/ ቸነፈር፣
3/ ረሃብ፣
4/ ወረርሽኝ፣
5/ የእሳት ቃጠሎ ናቸው፡፡
ከብዙ ተጋድሎ በኃላ ፃዲቁ አቡነ ሀብተማርያም በፀሎት ላይ ሳለ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ የቆምክባትን ቦታ ምስራቁን፣ ምዕራቡን፣ ሰሜኑን፣ ደቡቡን ባርክ አለው፡፡ ሲባርክም ሶስት አጋንንት በፀሎቱ ስልጣን ታስረው በፊቱ ታዩት።
እነዚህም አጋንንት ከኖህ ጀምሮ ሰውን በማሳት ከኖርን በኋላ ከአንተ ጋር ምን ፀብ አለን አሉ አባታችንም አቡነ ሀብተማርያም በትዕምርተ መስቀል ሲያማትብ ሁለቱን አጋንንት ምድር ተከፍታ ዋጠቻቸው አንዱ ጊዜዬ ስላልደረሰ አታጥፋኝ አለው፡፡ ያን ጊዜ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አቡነ ሀብተማርያምን ይህንን ተወው ጊዜው አልደረሰም አለው።
የጌታ ቃል እንዲህ ብሎ በተናገረ ጊዜ ሰይጣን ከአባታችን ተለይቶ ጠፋ፡፡ ማር 9፡23 ከዚህም በኋላ ዕለተ ሞቱ በደረሰ ጊዜ ለሞቱ ምክንያት የሚሆን ቸነፈር ያዘው፡፡ ጌታችንም በምስጋና ወደ እርሱ መጥቶ ወዳጄ ሀብተማርያም ሆይ ዛሬ ወደአንተ የመጣሁት ከድካም ወደ እረፍት እወስድህ ዘንድ ነው ሰባት የጽድቅ አክሊሎችን አዘጋጅልሃለሁ አለው።
1/ ስለ ንፁህ ድንግልናህ፣
2/ አለምንና በውስጡ ያለውን ንቀህ በመኖርህ፣
3/ ስለ ፍፁም ምንኩስናህ፣
4/ ዘወትር አራቱን ወንጌላትን በማንበብህና በመፀለይህ፣
5/ ስለ እኔ ብለህ ስለተራብከው፣
6/ በጾም ስለተጋደልክ፣
7/ ቂምና ጥላቻን፣ ትዕቢትን፣ ትምክህትን፣ በልብህ ውስጥ ባለማስቀመጥህ ስለ ንፁህ ተልዕኮ ክህነትህ፣ ስለ ንፁህ መስዋዕትህ ነው ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው፡፡
በተጨማሪም እኔ የሰጠሁህን ቃል ኪዳን ተስፋ አድርጎ መጽሐፈ ገድልህን ለሚጽፈው ስሙን በመንግስተ ሰማያት በእውነት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ፣ ለቤተክርስቲያንህ ዘይትን፣ ወይንን፣ ዕጣንን፣ ህብስትን እስከ ቀዝቃዛ ውሃ ድረስ በአንተ ስም መብዓ የሰጠውን የወደደውን ሁሉ አደርግለታለሁ፡፡ በመንግስተ ሰማያትም ከወዳጆቼ ከቅዱሳን ጋር በደስታ አኖረዋለሁ፡፡
የአቡነ ሀብተማርያም ፈጣሪ ኃጢአቴን ይቅር በለኝ ብሎ ያንተን ስም ጠርቶ ቢለምነኝ ኃጢአቱን አስተሰርይለታለሁ ብሎ ቃልኪዳን ገባለት ይህንንም ካለው በኋላ ጌታችን ሶስት ጊዜ ሳመው፡፡ ያን ጊዜም ከመድኃኒዓለም ጣዕም ፍቅር የተነሳ ነፍሱ ከስጋው ተለየች። #መዝ [115*6] በሰማያዊ መልአክት በምድራውያን ስውራን ቅዱሳን ዘንድ ታላቅ ደስታ ሆነ #ህዳር 26 ቀን አረፈ፡፡ ካህናት በመልካም ልብስ ገንዘው በዝማሬ በማህሌት ከቅዱስ አባታችን ከአቡነ ተክለሃይማኖት አጽም ጋር በፃዲቁ መቃብር ቀበሩት፡፡
አሜን የአባታችን የአቡነ ሀብተ ማርያም በረከተ ረድኤት ምልጃቸው ከሁላችን ጋር ይሁን።
☞ወር በገባ በ26 የጻድቁ አባታችን የአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ወርሐዊ
መታሰቢያቸው ነው፡፡
☞በ245 አመተ ምህረት በቅድስት ሀገር እየሩሳሌም ኅዳር 26 ቀን ተወለዱ፡፡
☞ሲወለዱም ታላቅ ብርሀን ከሰማይ ወርዶ ለ7ቀናት አብርቷል፡፡
☞በተወለድም ጊዜ አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወለድ ቅዱስ አሀዱ ውእቱ
መንፈስ ቅዱስ ብለው ፈጣሪያቸውን በአንድነት በሦሰትነት አመስግነዋል፡፡
☞አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሀን በሌላኛው ሰማቸው ፍሬምናጦስ እየተባሉ
ይጠራሉ፡:
☞በ257 አመተ ምህረት ከእየሩሳሊም ወደ ኢትዮጵያ መጡ፡፡
☞አባታችን በአክሱም በታላቅ ተጋድሎና በትጋት ኖሩ፡፡
☞ቅዳሜ እና እሁድ የዛፍ ቅጠሎችን ከመመገብ በቀር ሌላ ምግብ
አይቀምሱም ነበር፡፡
☞በየቀኑም አምስት ሺህ ስግደትን ይሰግዱ ነበር፡፡
☞ፍሬምናጦስ ወደ እስክንድሪያ ለመሄድ አስበው ሳለ እንደተኙ ድንግል
ማርያም ተገልጣላቸው (ድቅናና ቅስናን መቀበል ይገባሀል ለጵጵስና ተዘጋጅ
እግዚአብሄር ይችን ከፍ ያለች ማዕረግ ሰቶሃል የልጄ ወዳጅ ሆይ በጸሎትና
በልመናህ በስብከትህም የኢትዮጵያ ሰዎች ሁለ ይድናሉ፡፡በእጄህ ስጋዎ ደሙን
ይቀበላሉ አለቻቸው፡፡)
☞አባታችን በእመቤታች በአለ ረፍት ቀን ጥር 21 ቀን በአክሱም ፅዮን በውስጧ
ለመጀመሪያ ጊዜ ሲቀድሱ ቅዱስ ሚካኤል እና ቅዱስ ገብርኤል በግራ እና በቀኝ
እየራዷቸው እሳቸው ከምድር ሦስት ክንድ ከፍ ብለው ሥርአተ ቅዳሴውን
ፈጽመው ለነገስታቱም ለሕዝብም አቁርበዋል፡፡
☞አባታችንም በድፍን ኢትዮጵያ በአራቱም አቅጣጫ እየዞሩ፤ እያጠመቁ አብያተ
ክርስቲያናትን እያሰሩና አገልጋይ የሚሆን ቀሳውስት እየሾሙ በሀገራችን ላይ
ብርሃንን የፈነጠቁ ለኢትያጵያ መግለጽ ከሚቻለው በላይ እጅግ ታላቅ
ባለውለታዋ ናቸው፡፡
☞ከአባ ሰላማ በፊት አኛ ኢትዮጵያውያን ክርስቶስን ከማመን በቀር ጥምቀትና
ሥጋ ወደሙ የመቀበል ልማድ አልነበረንም፡፡ በድንኳን ካለችው ታቦተ ጽዮን
በቀርም ታቦታትና አብያተ ክርስቲያናት አልነበሩም፡፡
☞አባታችን አብነ ሰላማ ከመጡ በኃላ ነው አብያተ ክርስቲያናት የታነጽት
ገዳማት የተገደሙት፡፡
☞አባታችን በተንቤ ምድር በምነና በጽሙና ሲቀመጡ ቆጥኝ ፈልፍለው በሠሩት
ቤተክርስቲያን ላይ የብርሃን መሰላል ተተክሎላቸው በእርሱም ወደ ሰማይ
ወጥተው ከሃያ አራቱ ካህናት ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር አጥነዋል፡፡
☞የተንቢን ምድር ቡሩካን በሆኑ እጃቸው አንስተው አስባርከዋል፡፡
☞መድሀኒአለም እንዲህ አላቸው (በክብር የሚመስልህ የለም እኔ ፈጣሪህ
የእሳት ፈረሶች የሚሆኑ መላዕክት በኪሩቤል ላይ እንደምቀመጥ አንተም ከእነርሱ
በላይ ትሆናለህ፡፡
☞ሰለ ትምህርት ሰለ ስብከትህ ኢቴዮጵያን በሃይማኖት ስለ አበራሀቴ ከፍ ያለ
ክብራትና ማዕረጋትን ፈጽሜ ሰጠሀሁ አንተም ከበቅዱሳን በላይ ብርሀን
አደረግሁ፡፡ከእናቴ ከድንግል ማርያም በታች ትቀመጣለህ አላቸው፡፡
☞አባታችን አባ ሰላማ ሐምሌ 26 ቀን ሲያርፍ ነፍሳቸውን መላዕክት አይደሉም
ራሱ መድሀኒአለም በክብር ተቀብሎ ከእርሱ ጋር አሳስጓታል፡፡
☞ቅዱሳን ነገስታት አብርሀ ወ አጽበሀም ጻድቁ ከዐረፍ በኃላ ወደ ደብረ
መድሀኒት መጥተው ለመካነ መቃብራቸው ሲሰግዱ አባ ሰላማ
ተገልጠውላቸው ከእነሰራዊታቸው ባርከዋቸዋል፡፡
☞የጻድቁ አባታችን በረከት ረዲኤታቸው እንዲሁም አማላጅነታቸው አይለያችሁ፡፡
☞የጽሁፍ ምንጭ መዝገበ ቅዱሳን
የአባቶቻችን በረከት አይለየን አሜን
417 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 13:28