Get Mystery Box with random crypto!

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxtewahdoc — "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxtewahdoc — "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
የሰርጥ አድራሻ: @orthodoxtewahdoc
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.82K
የሰርጥ መግለጫ

🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን
/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ።
📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼
❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-05-02 20:06:10
ስለ ፃድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፀበለ ፃድቅ ቅመሱ
1.9K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , edited  17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 16:28:00 #ቅዱስ መርቆሬዎስ

•••ወር በገባ በ25 ታላቁ ሰማእት ቅዱስ መርቆርዮስ መታሰቢያ በዓል እንኳን አደረሳችሁ አደረሰን ቅዱስ መርቆርዮስ የቀድሞ ስሙ ፒሎፓደር ሲሆን ትርጉሙም #የአብ ወዳጅ የወልድ አገልጋይ ማለት ነዉ፡፡ በወጣትነቱ ከሃዲው ንጉስ ኡልያኖስ ላቆመው ጣኦት አልሰግድም ብሎ የሰው ልጅ ሊሸከመው የማይችለውን መከራ ተቀበለ፤በመጨረሻም ህዳር 25 ቀን አንገቱን ቆርጠው ገደሉት ደም ውኃና ወተት ከአንገቱ ፈሰሰ። ንጉሱ በዚያዉ ዘመን ክርስቲያኖችን በጣም ያሰቃይ ነበር፡፡ቅዱስ ባስልዮስም ይገስጸዉ ነበር በዚህም ምክንያት ንጉሱ ቅዱስ ባስልዮስን አሰረዉ፡፡ጳጳሱ በታሰረበት እስር ቤት የቅዱስ መርቆርዮስ ሥዕል ነበር፡፡ቅዱስ ባስልዮስም ከሥዕሉ ስር በመሆን ጸለየ ሥዕሉም ከቦታዉ ታጣ ያ ሥዕል ወደ ዑልያኖስ ቤት ሄዶ በጦር ወግቶ ገደለዉ፡፡በስዕሉ ላይ ያለዉ ጦር ጫፉ ደም ይንጠባጠብ ነበር፡፡ ቅዱስ ባስልዮስም ከሀዲ ዑልያኖስን ቅዱስ መርቆርዮስ በሥዕሉ አማካኝነት እንደገደለዉ አዉቆ እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡ ይህ ሰማዕት በአገራችን በስሙ በርካታ ገዳማትና አብያተክርስቲያናት አሉት በተለይም ቅዱስ ላሊበላ ካነጻቸው 11 ውቅር አብያተክርስቲያናት አንዱን ቤተ መርቆሪዎስ ብሎ ሰይሞለታል፤ በዚህ በሰሜን ሸዋ ደግሞ የሚገርም ገዳም አለው፤ ካህናት በማህሌት ወረብ ሲያቀርቡ ስዕሉ ያሸበሽባል ይዘላል፤ ይህንንም አይቶ ማረጋገጥ ይቻላል፤ በመዲናችን አዲስ አበባ ቅዱስ ኡራኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ታቦቱ አለ:: መርቆሪዎስ ከሞተ በኃላ ፈረሱ ለሰባት ዓመት ወንጌልን አስተምሯል፤ በኃላም አንገቱን ቆርጠው ገድለውታል እንዴት ብሎ የሚገረም የበልአምን አህያ ይጠይቃት፤ እኛስ እስመ አልቦ ነገር ዘይሳኣኖ ለእግዚያብሔር ብለን እንመልሳለን፤ ዘኁልቁ 22፤28 ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አለ ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነብዩን እብድነት አገደ ይላል 2ጴጥ 2፤16። ከሰማዕቱ በረከት ያሳትፈን።
<ወስብሐት ለእግዚአብሔር>
አሜን አሜን አሜን+++

https://t.me/Orthodoxtewahdoc
2.1K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 16:27:54 #አቡነ_አቢብ_ማለት

#ወር በገባ በ25 " አቡነ አቢብ (አባ ቡላ) መታሰቢያው ነው
ይህን ታላቅ ቅዱስ በምን እንመስለዋለን ¤እኛ ኃጥአን ጣዕመ ዜናውን ነገረ ሕይወቱን ሰምተን ደስ ተሰኝተናል! ¤ቅዱሱ አባታችን:- "ቡላ የእግዚአብሔር አገልጋይ" ብለን እንጠራሃለን::¤ዳግመኛም "አቢብ - የብዙኃን አባት" ብለን እንጠራሃለን::
¤እርሱ ቅሉ አባትነትህ አንተን ለመሰሉ ቅዱሳን ቢሆንም እኛን ኃጥአንን ቸል እንደማትለንም እናውቃለን::
¤አባ! ማነው እንዳንተ የክርስቶስን ሕማማት የተሳተፈ!

¤ማን ነው እንዳንተ በፈጣሪው ፍቅር ብዙ መከራዎችን የተቀበለ!

¤ማንስ ነው እንዳንተ በአንዲት ጉርሻ አማልዶ ርስትን የሚያወርስ!

¤የፍጡራንን እንተወውና በፈጣሪ አንደበት ተመስግነሃልና ቅዱሱ አባታችን ላንተ ክብር: ምስጋናና ስግደት በጸጋ ይገባሃል እንላለን::

+"+ ልደት +"+

=>አባታችን አቡነ አቢብ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን መጨረሻ አካባቢ ሲሆን ሃገረ ሙላዱ ሮሜ ናት:: ወላጆቹ ቅዱስ አብርሃምና ቅድስት ሐሪክ እጅግ ጽኑ ክርስቲያኖች ነበሩ:: ልጅ ግን አልነበራቸውም:: ዘመነ ሰማዕታት ደርሶ ስደት በሆነ ጊዜ እነርሱም በርሃ ገቡ::

+በዚያም ሳሉ በቅዱስ መልአክ ብሥራት ሐሪክ ጸንሳ ብሩሕ የሆነ ልጅ ወለደች:: ቅዱሱ ሕጻን ሲጸነስ ማንም ሳይተክለው የበቀለው ዛፍ ላይ መልአኩ እንዲህ የሚል የብርሃን ጽሑፍ ጽፎበት ወላጆቹ ዐይተዋል::
"ቡላ ገብሩ ለእግዚአብሔር: ወቅዱሱ ለአምላከ ያዕቆብ: ዘየኀድር ውስተ ጽዮን"

+"+ ጥምቀት +"+

=>ቅዱሱ ሕጻን ከተወለደ በሁዋላ ሳይጠመቅ ለ 1 ዓመት ቆየ::
ምክንያቱም ዘመኑ የጭንቅ ነውና ካህናትን እንኩዋን በዱር በከተማም ማግኘት አይቻልም ነበር:: እመቤታችን ግን ወደ ሮሙ ሊቀ ዻዻሳት አባ ሰለባስትርዮስ ሒዳ "አጥምቀው" አለችው::

+ወደ በርሐ ወርዶ ሊያጠምቀው ሲል ሕጻኑ ተነስቶ: እጆቹንም ዘርግቶ:- "አሐዱ አብ ቅዱስ: አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውዕቱ መንፈስ ቅዱስ" ብሎ አመስግኖ ተጠመቀ:: ከሰማይም ሕብስትና ጽዋዕ ወርዶላቸው ሊቀ ዻዻሳቱ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው:: የሕጻኑ ወላጆች "ለልጃችን ስም አውጣልን" ቢሉት "ቡላ" ብሎ ሰየመው:: እነርሱም ምሥጢሩን ያውቁ ነበርና አደነቁ::

+"+ ሰማዕትነት +"+

=>የቅዱሱ ቡላ ወላጆች ለ10 ዓመታት አሳድገውት ድንገት ሕዳር 7 ቀን ተከታትለው ዐረፉ:: ሕጻኑን የማሳደግ ኃላፊነትን የአካባቢው ሰዎች ሆነ:: ሕጻኑ ቡላ ምንም የ10 ዓመት ሕጻን ቢሆንም ያለ ማቁዋረጥ ሲጾም: ሲጸልይ ክፉ መኮንን "ለጣዖት ስገዱ" እያለ መጣ::

+በዚህ ጊዜ በሕጻን አንደበቱ አምልኮተ ክርስቶስን ሰበከ:: በዚህ የተበሳጨ መኮንኑ ስቃያትን አዘዘበት:: በጅራፍ ገረፉት: በዘንግ ደበደቡት: ቆዳውን ገፈፉት: በመጋዝ ቆራርጠውም ጣሉት:: ነገር ግን ኃይለ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበርና 2 ጊዜ ከሞት ተነሳ:: በመጨረሻ ግን ሚያዝያ 18 ቀን ተከልሎ ሰማዕት ሆኗል::

+"+ ገዳማዊ ሕይወት +"+

=>ቅዱስ ቡላ ሰማዕትነቱን ከፈጸመ በሁዋላ ቅዱስ ሚካኤል በአክሊላት አክብሮ ወስዶ በገነት አኖረው:: ከሰማዕታትም ጋር ደመረው:: በዚያም ቡላ ቅዱስ ጊዮርጊስን ተመልክቶ ተደነቀ:: መንፈሳዊ ቅንዐትን ቀንቷልና "እባክህን ወደ ዓለም መልሰኝና ስለ ፍቅርህ እንደ ገና ልጋደል" ሲል ጌታን ለመነ::

+ጌታችን ግን "ወዳጄ ቡላ! እንግዲህስ ሰማዕትነቱ ይበቃሃል::
ሱታፌ ጻድቃንን ታገኝ ዘንድ ግን ፈቃዴ ነውና ሒድ" አለው:: ቅዱስ ሚካኤልም የቅዱስ ቡላን ነፍስ ከሥጋው ጋር አዋሕዶ: ልብሰ መነኮሳትንም አልብሶ ግብጽ በርሃ ውስጥ አኖረው::

+"+ ተጋድሎ +"+

=>አባ ቡላ ወደ በርሃ ከገባ ጀምሮ ዐርብ ዐርብ የጌታን ሕማማት እያሰበ ራሱን ያሰቃይ ገባ:: ራሱን ይገርፋል: ፊቱን በጥፊ ይመታል: ሥጋውን እየቆረጠ ለአራዊት ይሰጣል: ከትልቅ ዛፍ ላይ ተሰቅሎ ወደ ታች ይወረወራል::

+በጭንቅላቱ ተተክሎ ለብዙ ጊዜ ጸልዮ ጭንቅላቱ ይፈሳል:: ሌላም ብዙ መከራዎችን የጌታን ሕማማት እያሰበ ይቀበላል:: ስለ ጌታ ፍቅርም ምንም ነገር ሳይቀምስ ለ42 ዓመታት ጹሟል:: ጌታችንም ስለ ክብሩ ዘወትር ይገለጥለት ነበር::

+የሚታየውም እንደ ተወለደ: እንደ ተጠመቀ: እንደ ተሰቀለ: እንደ ተነሳ: እንዳረገ እየሆነ ነበር:: አንድ ቀንም ጌታችን መጥቶ "ወዳጄ ቡላ! እንዳንተ ስለ እኔ ስም መከራ የተቀበለ ሰው የለም:: አንተም የብዙዎች አባት ነሕና ስምህ አቢብ (ሃቢብ) ይሁን" አለው::

"እስከ ይቤሎ አምላክ ቃለ አኮቴት ማሕዘኔ:
ረሰይከኑ ለባሕቲትከ ኩነኔ:
ዘመጠነዝ ታጻሙ ነፍስከ በቅኔ" እንዲል::

+" ዕረፍት "+

=>አቡነ አቢብ ታላቁ ዕብሎን ጨምሮ በርካታ ደቀ መዛሙርትን አፈራ:: ከእመቤታችን ጋርም ዕለት ዕለት እየተጨዋወተ ዘለቀ:: በተጋድሎ ሕይወቱም ከ10 ጊዜ በላይ ሙቶ ተነስቷል:: በዚህች ቀን ሲያርፍ ገዳሙ በመላእክት ተሞላ::

+ጌታም ከድንግል እናቱ ጋር መጥቶ "ወዳጄ ቡላ! ስምህን የጠራውን: መታሰቢያህን ያደረገውን እምርልሃለሁ:: አቅም ቢያጣ "አምላከ አቢብ ማረኝ" ብሎ 3 ጊዜ በዕለተ ዕረፍትህ የሚለምነኝን: በስምሕ እንኩዋ ቁራሽ የሚበላውን ሁሉ እምርልሃለሁ" ብሎት ነፍሱን በክብር አሳረገ: በሰማይም ዕልልታ ተደረገ::

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
1.4K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 00:54:25 "ዑራኤል ማለት እግዚአብሔር ብርሃኔ ነው አንድም የእግዚአብሔር ብርሃን ማለት ነው"።

"አማላጅነቱ አይለየን።
290 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 21:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 21:32:28 ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" ምሳ 1፥33
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ስንክሳር ዘወርኃ ሚያዝያ 22

https://t.me/Orthodoxtewahdoc
የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን
899 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , edited  18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 21:31:07
900 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 18:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 20:08:33 "ምሮን እንጅ መርምሮን ቢሆን ማን በፊቱ ይቆም ነበር።!

"ተመስገን"
1.1K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ