Get Mystery Box with random crypto!

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxtewahdoc — "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxtewahdoc — "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
የሰርጥ አድራሻ: @orthodoxtewahdoc
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.88K
የሰርጥ መግለጫ

🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን
/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ።
📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼
❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-05-03 16:28:05 #ቅዱስ_ዮሴፍ

•••ወር በገባ በ 26 እመቤታችን በስደቷ ወቅት እንኳን ያልተለያት የእመቤታችን ጠባቂ የአባታችን አረጋዊ ዮሴፍን ወርሐዊ መታሰቢያቸው ፡፡
☞በዕብራይስጥ ቋንቋ ድኅነት ለሚባለው ለስምህ አጠራር ሰላምታ ይገባል ☞መከራንና ጭንቅን የታገሠ የድንግል ሕፃን አምላክ በሥራው ከፍ ከፍ ያደረገው ለስምህ አጠራር ሰላምታ ይገባል፡፡
☞ሕፃኑንና እናቱን በመያዝ ወደ ግብጽ ምድር በወረድህ ጊዜ እንባ ማኅተሙ
ለሆነለት ፊትህ ሰላምታ ይገባል፡፡ የክብራን አለቃቸው የሆንክ ከክቡራን ሁሉ
የምትቀድም ዮሴፍ ሆይ በግብጽ ምድር ደማቸው ለፈሰሰና ለተዋጁ
መጀመሪያቸውና መሪያቸው አንተ ነህ፡
☞መልኩ የከፋ የመከራ ፊት ስደትን በአንድነት ለሚያዩ ዐይኖችህ ሰላምታ
ይገባል፡፡
☞በድንግል እቅፍ የተቀመጠውን የሰማያዊ አምላክ ቃል ዘወትር ለሚሰሙ
ጆሮችህ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞ከድካም የተነሣ የመነጨውን የድንግል ፊት ደም ግባት ወዝ በላያቸው
ለተሣሉባቸው ጉንጮችህ ሰላምታ ይገባል፡፡ በበረሀ የምትኖር የግብጽ ምድር
አንበሳ ዮሴፍ ሆይ የአብ አካላዊ ቃል ወልድን በአፋ ይሰሙ ዘንድ ከአባቶች
ዕድልን ያገኘ እንደ አንተ ያለ ማን ነው፡፡
☞ዮሴፍ ሆይ ከስደት ቅርጫፍ የተገኘ የልቡና ኅዘን አበባን ባለ መረጋጋት
ለአሸተቱ አፍንጫዎችህ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞ልጆችህን የተውህ የግብጽ ምድር ባሕታዊ ዮሴፍ ሆይ ከማርያም ከልጇ ጋር
እውነትን እየተነጋገሩ ፈጽመው ዝም ለማይሉ ከንፈሮችህ ሰላምታ ይገባል፡፡
አረጋዊ ዮሴፋ ሆይ በዚች ምድር ደግ ሰው አልቋልና ፈጽመህ አድነን፡፡
☞ሰሎሜ በምታዝለው በልጇና በድንግል ፊት በሥርዐት ሊሚናገር አፍህ
ሰላምታ ይገባል፡፡ዮሴፍ ሆይ ከቸርነትህና ከሃይማኖት የተነሣ ድህነት
እንድታመጣለኝ መጀመሪያና መጨረሻ የሌለው አምላክ የተቀበለውን
የአማላጅነትህ ፀጋህን አገኝ ዘንድ ዕድሜ ይሰጠን፡፡
☞ፍጻሜ የሌለብህ የአብ ልጅ ፈመን የሆንክ ዮሴፍ ሰሎሜን የምታዝለው
የድንግል ልጅ አምላክ በመጀመሪያ ለመሣመው አፈህ ሰላምታ ይገባል፡፡
☞ዓለምን የሚቃጥል የሚያስፈራ የእሳት ነበልባል ጌታ በመጠኑ ለዳሰሱ
እጆችህ ሰላምታ ይገባል፡፡ ኑሮህ ገዳም የሆነ የናዝሬቱ ባሕታዊ ዮሴፍ ሆይ
በሥጋና በደም በኩል እኅትህ ከሆነች ሰሎሜ ጋር ከወልድና ከእናቱ ዘንድ ስለ
ኢትያጵያና ሕዝቦቿ ለምንልን፡፡(መልክአ ዮሴፍ)
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ

https://t.me/Orthodoxtewahdoc
230 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 13:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 16:27:45 እንኳን አደረሳችሁ
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ
አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

❖ ሚያዝያ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+"+ ሰማዕቱ ቅዱስ ዮሐንስ +"+

+ቅዱስ ዮሐንስ በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የነበረ ቅዱስ ሰው
ነው:: ወላጅ አባቱ ጣኦት ጠራቢና አምላኪ: የጣኦቱ
አጣኝም
ነበረ:: እናቱ ግን በድብቅ ክርስቶስን ታመልክ ነበር::

+ልጇን ክርስትና ብታስተምረው አባቱ ጨካኝ በመሆኑ
ይገድለዋልና ዘወትር ጧት ማታ ወደ ፈጣሪዋ በዕንባ
ትለምን ነበር::
ጧት ጧት አባቱ ጣኦት መጥረብና ማምለክን ያስተምረው
ነበር:: አንድ ቀን እግዚአብሔር ለሕጻኑ ዮሐንስ በራዕዩ
ተገለጠለት::
ምስሥጢራትንም አስተማረው::

+ለተወሰነ ጊዜ በሚደነቅ የክርስትና ሕይወት ከኖረ በኋላ
ምንም ገና እድሜው 12 ዓመት ቢሆንም አባቱን
ጦኦትህን ተው ሲል
መከረው:: አባት ግን ጨካኝ ነውና ትልቅ መጥረቢያ
አንስቶ አንገቱን መታው:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ መሬት ላይ
ስትወድቅ
አካሉ ግን ለ1 ሰዓት ቆሞ በደሙ ተጠመቀ:: ይሕ ሁሉ
ሲሆን የተባረከች እናቱ ቆማ ታይ ነበር::

+መንፈሳዊት እናት ናትና አላዘነችም:: ይልቁኑ ከልጇ ደም
ለበረከት ተቀባች:: አለችም:- "ጌታ ሆይ! የምሰጥህ
ምንም
የለኝም:: ይህንን ንጹሕ መስዋዕት ግን ተቀበለኝ::"

+ቅዱስ ዮሐንስ በሰማዕትነት ካለፈ በኋላ አባቱን ርኩሳን
መናፍስት አሳበዱት:: እናት ግን አረማዊ ባለቤቷን ወደ
ቅዱስ
ዮሐንስ መቃብር ወስዳ ጸለየች:- "ልጄ ሆይ! አባትህን
ይቅር ብለህ ከፈጣሪ ዘንድ አማልድ::"

+ይሕንን ብላ ባሏን ከመቃብሩ አፈር ወስዳ ቀባችው::
አባትም በቅጽበት ድኖ ወደ ልቡ ተመለሰ:: ስለ ሰራው
ሁሉ ተጸጽቶ
አለቀሰ:: በእውነተኛ አምላክ በክርስቶስ አምኖ: ተጠምቆ:
በመልካም ክርስትና ኑሮ ኑሮ: ከተባረከች ባለቤቱ ጋር
ለገነት
በቅቷል::

+"+ ቅዱስ ሱስንዮስ +"+

+ዳግመኛ በዚህ ቀን ቅዱስ ሱስንዮስ ተሰይፏል:: ቅዱሱ
በዘመነ ሰማዕታት ቤተ ክርስቲያንን በገድላቸው ካስጌጧት
ታላላቅ
ሰማዕታት አንዱ ነው::

❖እግዚአብሔር አምላክ ከሰማዕታቱ ጽናትን: ጸጋ በረከትን
ይክፈለን::

❖ሚያዝያ 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሐንስ ሰማዕት (ወልደ ፀራቢ)
2.ቅዱስ ሱስንዮስ ሰማዕት (ሶርያዊ)
3.ሰማዕታት (የቅዱስ ሱስንዮስ ማሕበር)
4.አባ ሠርጋ
5.ቅዱስ ይድራስ

❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ አቡነ ሐብተ ማርያም
2፡ አቡነ ኢየሱስ ሞዐ
3፡ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን
4፡ ቅዱስ ቶማስ
5፡ ሰማዕታተ ናግራን

++"+ ሰውን ከአባቱ: ሴት ልጅንም ከእናቷ: ምራትንም
ከአማቷ እለያይ ዘንድ መጥቻለሁና:: ለሰውም ቤተሰዎቹ
ጠላቶች
ይሆኑበታል:: ከእኔ ይልቅ አባቱን ወይም እናቱን የሚወድ
ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: ከእኔ ይልቅም ወንድ ልጁን
ወይም ሴት
ልጁን የሚወድ ለእኔ ሊሆን አይገባውም:: መስቀሉን
የማይዝ በኋላየም የማይከተለኝ ለእኔ ሊሆን
አይገባውም:: +"+ (ማቴ.
10:35-39)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>

https://t.me/zikirekdusn
"መንግሥተ ሰማያት ቀርባለችና ንስሐ ግቡ::" /ማቴ ፫:፫/
ዝክረ ቅዱሳንን ተማሩ ብለን እንለምናችኋለን!!

ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://t.me/zikirekdusn
270 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 13:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-03 13:54:29 "መርቆሪዎስ ማለት የአብ ወዳጅ የወልድ አገልጋይ ማለት ነዉ።
"ቅዱስ መርቆሪዎስ ሆይ እግረ ልቦናዬ በፊትህ በቆመ ጊዜ በነጋ በነጋ ጎብኘኝ ሰላምንም ስጠኝ።

አሜን በእውነት
882 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 23:07:46 ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" ምሳ 1፥33
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ስንክሳር ዘወርኃ ሚያዝያ ፳፭/25

https://t.me/Orthodoxtewahdoc
የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን
1.8K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , edited  20:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 23:07:07
1.7K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 20:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-02 22:36:19 "የቀንን ውበት አይቶ ለማድነቅ የግድ ጨለማን መጠበቅ ያስፈልጋል።"
ተመስገን ጌታ ሆይ ቸር አሳድረን።

የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን
1.6K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , edited  19:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ