2023-05-12 01:10:38
☞አርብ የፍቅር ቀን
☞በዕለተ ዐርብ የሚፀለይ ጸሎት
☞ንስሓ የገባ ኃጢአተኛ ሰው እንኳን ቢሆን ይህችን የአቡነ እስትንፋ ክርስቶስ
ጸሎት በጸለየ ጊዜ ሺህ ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ጌታችን በማይታበል ቃሉ
ለአባታችን ነግራቸዋል፡፡ ይቺ ፀሎት በአምላክ ልቡና ያለች ጸሎት ነፍሳትን
ከሲኦል አታወጣም ብሎ የሚጠራጠር ቢኖር መንግሰተ ሰማያት አያያትም
የተባለላት የተመረጠች ጸሎት እንሆ በዐለተ ዐርብ ፀልየን በረከት እንጋኝ፡፡
☞ጸሎትና ልመና ወደ እግዚአብሔር ምልጃ ለነፍስና ለሥጋ የሚጠቅም ነው፡፡
በሕይወተ ሥጋ ያሉ ሰዎች ይህንን ጸሎት በሚጸልዩበት ጊዜ አባቶቻቸውን
እናቶቻቸው ዘመዶቻቸውንና ወዳጆቻቸውን በአንዲት ጊዜ ከሲኦል ያወጡበታል፡፡
የሾህ አክሊል ጎንጉነው ያቀዳጁሽ የጌታችን የመድሀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ
ራስ ሆይ ለአንቺ ሠላምታ ይገባሻል፡፡ሥጋችን ለማንጻትና ነፍሳችንን ለመቀደስ
አስከመመታት ደረሰሽ ንጽህ ደምን አፈሰሰሽ፡፡እገሌና ኤገሌን ማርልኝ እያለ ስም
ይጥራ(አባታችን ሆይ በል)
☞ሰይጣን የተፋውን የኃጢአት ምራቅ ከእኛ ለማስወገደ ስለ እኛ አይሁድ ርኩስ
ምራቃቸውን የተፋብሽ የዓለም ቤዛ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የከበርሽ
ፊት ሆይ ሠላምታ ላንቺ ይገባሻል፡፡ ዛሬ የእኔን ኃጢአት አሰወግጅ፡፡(አባታችን ሆይ
በል)
☞አላዋቂ በሆኑ በሰቃልያን አይሁዱ እጅ በጥፊ የተመታችሁ የዓለም ቤዛ
የመድኃኒታችን የኢየሱስ ጉንጮች ሆይ ለእናተ ሰላምታ ይገባችኀል በእናተ
ምክንያት የተዘጋ ገነት ተከፈተ እንዲሁ የልቦና በር ፈጽሞ ይከፈትልኝ፡፡(አባታችን
ሆይ በል)
☞የነፍሳችን የሥጋችን መድኃኒት ትሰጭን ዘንድ የመረረ ሐሞትና ከርቤን
ትጠጪ ዘንድ የወደድሽ የዓለም ቤዛ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የከበርሽ
አፍ ሆይ ለአንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡ እንደዚሁ ለእኔ የሕይወት መጠጥ አጠጪኝ
፡፡ (አባታችን ሆይ በል)
☞ሰለ እኛ በአደባባይ የሞት መስቀል የተሸከምሽ የዓለም ቤዛ የመድኃኒታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ የከበርሽ ከፍ ከፍ ያልሽ ክንድ ሆይ ለአንቺ ሰላምታ ይገባሻል
ሁላችን የእጅ ፍጥረቶች ነንና የኃጢአታችንን ሸክም ተሸክሚል የበደላችንን ሸክም
አቅይልን፡፡(አባታችን ሆይ በል)
☞ሰለ እኛ ሰለፍጥረቶችሽ የመስቀል ግንድ የተላካብሽ የዓለም ቤዛ
የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልዮ የሆንሽ ጀረባ ሆይ ለአንቺ ሰላምታ
ይገባሻል ዛሬም የኃጢአታችንን ግንድ ላኪልን፡፡ (አባታችን ሆይ በል)
☞የተረገሙ አይሁድ በችንካር ይቸነክሩሽ ዘንድ የወደድሽ የመድሀኃኒታችን
የኢየሱስ ክረርስቶሰ ቀኝ እጅ ሆይ ለአንቺ ሰላምታ ይገባሻል፡፡እንደዚሁ
በስንፍናችን የሠራነው በደላችንን አጥፊልን፡፡ (አባታችን ሆይ ይበል)
☞አስቀድመሽ ሰለበደላችን ከሐዲያን አይሁድ ይቸነክሩሽ ዘንድ የወደድሽ
ያለመለወጥ ፍፁም እግዚአብሔር ፍፁም ሰው የሚሆን የመድኃኒታችን
የፈጣሪያችን የኢየሱስ ክርስቶስ የከበርሽ ግራ እጅ ሆይ ለአንቺ ሠላምታ
ይገባሻል፡፡ እንደዚሁ የእኛን በደል ችንክሪ የሞት ችንካር ከሚሆን ከዲያብሎስ
አድኝን፡፡(አባታችን ሆይ በል)
☞ሰለ ኃጢአታችን ክፋዎች አይሁድ ይቸነክሩሽ ዘንድ ፈጽመው ያስሩሽ
የፈጣሪያችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የከበርሽ ቀኝ እግር ሆይ ለአንቺ
ሰላምታ ይገባሻል እንደዚሁ ኃጢአታችንን አስተሰርይልን፡፡(አባታችን ሆይ በል)
☞በእውነት የታመነ እውነተኛ ቅን ንጉሥ የሚሆን የዓለም ቤዛ የመድኃኒታችን
የኢየሱስ ክርስቶስ የከበርሽ ግራ እግር ሆይ ለአንቺ ሰላምታ ይገባሻል ያለ በደል
በቅዱስ መስቀል ላይ የተቸነከርሽ እንደዚሁ ኃጢአታችንን ቸንክሪልን፡፡
የበደላችንን መጽሐፍ ደምስሽልን፡፡(አባታችን ሆይ በል)
☞ኃጢአታችንን የምንታጠብበትና የምናስተሠርይበት ውኃ ደምን(ከጎንሽ
እሰከምታፈሽ ድረስ)በመስቀል ላይ ሳለሽ ጎንሽ የተወጋሽ የጌታችን የአምላካችን
የኢየሱስ ክርስቶስ ልዩ እና የከበርሽ ጎን ሆይ ለአንቺ ሰላምታ ይገባሻል ተዘግቶ
የነበረው የሰማይ ምሥጢር በአንቺ ምክንያት ተገለጠ ተከፈተ እንደዚሁም ሁሉ
የልባችንን በር ይከፈትልን፡፡(አባታችን ሆይ ይበል)
☞በመስቀል ላይ መከራን ለተቀበሉ ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ
ክርስቶስ አካላት ሁሉ ሰላምታ ይገባቸዋል የጌቶች ጌታ የንጉሦች ንጉስ ጌታዬ
ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለአንተ ክብር ምስጋና ይገባሃል በታላላቅ ችንንከሩህ ዘንድ
ለእኛ ስትል የወደድክ ዛሬም በፍቅር ትቸነክረን ዘንድ እለምንሃለን ከእኛ ጋር
መከራን ሰለተቀበልክ እኛም ከአንተ ጋር መከራን እንቀበላለን በመስቀል ላይ
የተቀበልከውን የመከራህ ተሣታፊዎች አድርገኸናልና በመከራ ሰለመስልንስ
እንዲዚሁ በጌትነትህ በምትመጣበት ጊዜ በዕለተ ምጽዐአት ከአገልጋዮችህ
ከቅዱሳን ጋር ክብርን አድለን፡፡[(አባታችን ሆይ በል
☞ታዖስ ወዖ አልፋ ቤጣ የምትባል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የባሕርይ
አባትህ አብ መጠጊያ ኃይል ይሁነን እግዚአብሔር ዕድል ፈንታቸው ጽዋ ተርታችን
ነው እንደ ቸርነትህ ጎዳናችንን አሰተካክልን አንተ ለወደድከው መራራውን ከማር
ይልቅ ጣፋጭ ይሆናል፡፡ እኛም ይህንን እንወዳለን እግዚአብሔረ ሆይ አንተ
መውደድን ሰጠን ፈጣሪያችን አሰመልክተን አሰተዋይ ልቡና ሰጠን ፈጣሪያችን
ጥበበኛ አድርገን፤ ፈጣሪያችን አድነን፤ በውስጥና በውጭ ያለውን የሚታየውንና
የማይታየውን አበሳ የምታውቅ አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ አውግዮን፤አውሎግሶን
ልቦናችንን አና ሰማያዊውን ቤት ክፈትልን ዓይነ ልቡናችንንምአብራልን
ኃጢአታችንንም ይቅር በለን፡፡(አባታችን ሆይ በል)
☞መሐሪ የሆንክ አምላክ ሆይ ይቅር ባይ አምላክ ሆይ ቸር አምላክ ሆይ የእኛን
የበደለኞቹን ኃጢአት ይቅር በል፡፡ (አባታችን ሆይ በል)
☞ዓለም ሳይፈጠር አሰቀድመህ የነበርክ ዛሬም ያለህ ዓለምን አሳልፈህ
የምትኖር የወልድ የመንፈስ ቅዱስ ልባቸው አብ ሆይ ለአንተ ሰላምታ ይገባሐል
ዓለም ሳይፈጠር አስቀድመህ የነበርክ ዛሬም ያለህ ዓለምን አሳልፈህ የምትኖር
የአብ የመንፈስ ቅዱስ ቃላቸው ወልድ ሆይ ለአንተ ሰላምታ ይገባሃል፡፡(ሦስት
ጊዜበል) አቤቱ ፈጣሪያችን ሥጋችንንና ነፍሣችንን ባርክ አቤቱ ፈጣሪያችን
ሕይወታችንና ሞታችንን ባርክ አቤቱ ፈጣሪያችን ጸሎት ልመናችንን ባርክ፡፡
( አባታችን ሆይ በል፡፡
☞ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የሚያስጨንቅ ለአንተ ቀላል ነው የራቀ ለአንተ
ቅርብ ነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ይቅርታህ ከእኛ አታዘግይብን
(አታርቅብን የሚያደንቁህ ከፍ አድርጋቸው ለአንተ ቀላል ነውና ኃጢአታችንን
አስተስርይልን አንተ መከራ በደላችንን ይቅር በለን፡፡(አባታችን ሆይ በል)
☞እግዚአብሔር ፈጣሪያችን ሆይ በሦስትነትህ ተማፀነህ በትክክል ሥልጣን
ተማፀንህ በአንድነትህ ተማፀነህ በመለኮትህ ተማፀነህ አንተን በወለችህ
በድንግል ማርያም እናትህ ተማፀነህ በቅዱስ መስቀልህ ተማወነህ
በምትወደው በወዳጅህ በቅዱስ ዮሐንስ ተማፀነህ አንተን ባጠመቀህ በቅዱስ
ዮሐንስ መጥምቅ ተማፀንህ መልአከ ምክርህ በሆነ በቅዱስ ሚካኤል ተማፀነህ
የአንተን መወለድ ለድንግል ማርያም የደስታ ብሥራትን በነገራት በቅዱስ
ገብርኤል ተማፀነህ እኛም ኃጠአተኛ ባሮችሁ በወዳጅህ በእስትንፋሰ ክርስቶስ
ተማፀነህ የእኛንም የሕዝብ ኃጢአት ይቅር በል አሜን፡፡(አባታችን ሆይ በል)
☞ይቺ በአምላክ ልቡና ያለች ግሩም ጸሎት ነፍሳትን ከሲኦል አታወጣም ብሎ
የሚጠራጠር ቢኖር መንግስተ ሰማያትን አያያትም፡፡ብሎ ጌታችን ለአባታችን
ለአብነ እስትንፋሰ ክርስቶስ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡
☞(ገድለ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ)
☞ሲራክ ተክላጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞19-12-2014
1.7K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 22:10