Get Mystery Box with random crypto!

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxtewahdoc — "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxtewahdoc — "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
የሰርጥ አድራሻ: @orthodoxtewahdoc
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.88K
የሰርጥ መግለጫ

🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን
/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ።
📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼
❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-05-16 00:18:09
80 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 21:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 19:54:20 ታላቁ_አባ_ሲኖዳ +"+

=>የባሕታውን ሁሉ አለቃቸው ታላቁ ቅዱስ ሲኖዳ:-
¤በ4ኛው መቶ ክ/ዘመን የተወለደ
¤በእናቱ ማሕጸን ሳለ መላእክት በሰይፈ እሳት ይጠብቁት የነበረ
¤የታላቅነት ትንቢት የተነገረለት
¤ገና ሳይወለድ ሥውራን አበው የሰገዱለት
¤በሕጻን ሰውነቱ ጾምና ጸሎትን የጀመረ
¤የልጅነት ቁርስና ምሳውን ለነዳያን ያካፍል የነበረ
¤በ9 ዓመቱ ወደ በርሃ የመነነ
¤የአባ አብጐል ደቀ መዝሙር የሆነ አባት ነው::

+ሲመነኩስም በእግዚአብሔር ትእዛዝ #የሠለስቱ_ደቂቅ
አስኬማ: #የኤልያስ ቆብዕ እና የመጥምቁ #ዮሐንስ ቅናትን
(መታጠቂያ) ከያሉበት መላእክት አምጥተውለት የመነኮሰ
¤ዓለምን በሙሉ በጸሎቱ ይጠብቅ የነበረ
¤የግብፅን በርሃ በብርሃን የሞላ
¤በርካታ ድርሰቶችን የደረሰ
¤ያለ ማቇረጥ በየቀኑ ከ100 ዓመታት በላይ ከጌታችን ክርስቶስ
ጋር የተነጋገረ
¤ደመናትን ተጭኖ ይሔድ የነበረና
¤ያለ ዕረፍት ለ111 ዓመታት ከ2 ወራት ፈጣሪውን ያገለገለ
አባት ነው::

+በዚህም ምክንያት አንድ ቀን ገዳማውያን ሁሉ እየሰሙ
እንዲህ የሚል ቃል ከሰማይ መጣ:: "ሲኖዳ ተሠይመ
#አርሲመትሪዳ " (ሲኖዳ አርሲመትሪዳ ሆኗል:: ማለትም
ለባሕታውያን ሁሉ አለቃ ሁኖ ተመርጧል ማለት ነው:: )

+ቅዱሱ የጌታችንን እግር እያጠበም ይጠጣ ነበር::
ግንቦት7በዚህች ዕለት የቅዱሱ ጽንሰት  ይታሰባል። 

#ሲኖዳ ማለት "ደግ ሰው" ማለት ነው::
<<ከበረከታቸው ይክፈለን።>>
" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::  አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
https://t.me/zikirekdusn
932 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 16:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 15:57:24 #የ️አቡነ ኪሮስ ታሪክ ባጭሩ

️ •••በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አሞላክ አሜን እንኻን አደረሳቹ ለአቡነ ኪሮስ ወር በገባ በ8 አቡነ ኪሮስ ናቸው አባ ኪሮስ አባቱ ንጉስ ዮናስ እናቱ አንስራ ይባላሉ፡፡ ሀገሩ ሮም ነው፡፡ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ነበሩና አቡነ ኪሮስ በታህሳስ 8 ወለዱ፡፡ አቡነ ኪሮስ የመጀመሪያ ስሙ ዲላሶር ይባል ነበር፡፡ በኋላ አባቱ ከሞተ በኋላ ሀብቱን ከወንድሙ ተካፍሎ ለድሆች መጽውቶ ዓለምን ንቆ መንኖ ሄደ፡፡ ከአባ በቡነዳ ገዳም ገባ፡፡
በ17 ዓመቱ ሥርዓተ ምነኩስናን ተማረ፡፡ በአባ በቡነዳ እጅ መነኮሰ፡፡ ከዚህ በኋላ በጾም በጸሎት ተወስኖ ኖረ፡፡ስለ ዓለም መከራ ለ40 ዘመን ተኝተው ሲጸልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ መላእክት መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡር ቃል ሰምቶ ወድቀዋል ጌታዬ ድምጹን ያሰማኝ አላቸው በኋላ ኪሩቤል አንስቶ ወስዶ ገነት አሳይተውት ጌታችንም ቃል ኪዳን ሰቷቸዋል።

ቃል ኪዳናቸውም ፡- መካኖች ልጀ የሌላቸው ገድሉን አቅፈው ቢያለቅሱ ጸበሉን ቢጠጡ ስምህን ቢጠሩ፤ የመካኒቱን ማህጸን እከፍታለሁ፡፡ የሚሞትባቸውን እንዳይሞተባቸው አደርጋለሁ፡ በንጹ ገንዘቡ ቂምና በቀል ሳይዝ በህግ በስጋውና በደሙ የጸና ሰው በስምህም በተሠራው ቤተክርስቲያን ጧፍ ዘይት ያበራ መገበሪያ ያመጣውን ልጅ አሰጠዋለሁ፡፡ ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ከዚም በኋላ በተወለዱ 270 ዓመታቸው  ሐምሌ 8 አርፈዋል።
ረድኤት በረከታቸው አማላጅነታቸው ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን
ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን


ጆይን እያላችሁ https://t.me/Orthodoxtewahdoc
1.3K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 12:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 15:56:48 ወር በገባ በ8 የቅዱስ  አባ (ብሶይ) ብሾይ  ወርኀዊ መታሰቢያያ በዓላቸው ነው።

#የገዳም ኮከብ ቅዱስ አባ ብሶይ በግብጽ ሼስና በተባለች ቦታ የተወለደ ሲኾን ሰባት ወንድሞች ነበሩት፤ ከዕለታት ባንዳቸው ለእናቱ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልሟ ተገልጾ “ጌታ ከልጆችሽ መኻከል አንዱን እንዲያገለግለኝ ስጪኝ ይልሻል አላት” ርሷም፤ “ጌታ የወደደውን ይውሰድ” ብላ መለሰችለት፤ መልአኩም ቀጭን የነበረውን ሰውነቱም ደካማ የነበረውን የብሶይን እጁን ይዞ “ዝንቱ ውእቱ ወልድ ለእግዚአብሔር ገባሬ ሠናይ” (ለእግዚአብሔር መልካም ሥራ የሚሠራ ይኽ ልጅ ነው” አለ፤ ያን ጊዜ እናቱ “የእኔ ጌታዬን እንዲያገለግለው ጠንካራውን ይውሰድ” በማለት ስትመልስ፤ መልአኩም “ጌታስ የመረጠው ይኽነን ነው” ብሎ መልሶላታል፡፡

ከዚያም በ340 ዓ.ም. ቅዱስ አባ ብሶይ ወደ ሲሐት በረሓ በመኼድ ቅዱስ ዮሐንስ.ሐጺርን ባመነኮሱት በአባ ባውማ እጅ ምንኲስናን ተቀበለ፡፡ አባ ባውማ ባረፈ ጊዜ ቅዱስ ዮሐንስ ሐጺርና አባ ብሶይ በጸለዩ ጊዜ መልአኩ ለአባ ብሶይ ተገልጾለት ወደ ገዳም መርቶ አድርሶታል፤ በዚያም ወደ ርሱ ለተሰበሰቡ ለብዙዎች መነኮሳት አባት ኾኗቸዋል፤ በቅድስና እጅግ የከበረ፤ በፍቅር፣ በደግነት፣ በርኅራኄ የሚታወቁ በተጋድሎም የበረታ ነበረና ዜናው በመታወቁ ቅዱስ ኤፍሬም ወደ አባ ብሶይ መጥቶ አይቶታል፡፡

ጌታችንን በእጅጉ ከመውደዱ የተነሣ ቅዱሳት መጻሕፍትን አዘውትሮ በማንበብ በመጻሕፍት ቃል ነፍሱን እያረካ፤ እጅግ ጽኑ የኾነ ተጋድሎን በማድረግ በጾም፣ በጸሎት ይጋደል ነበር፤ ሁሌም ርሱን ለማመስገን ከመሻቱም የተነሣ በምሽት ጸሎት ጊዜ እንቅልፍ እንዳይወስደው ጸጒሩን በገመድ በማሰር ይጸልይ ነበር፤ ዛሬ ድረስ ይኽ ማሰሪያ በዚያው ገዳም አለ፤ በዚኽም ንጽሐ ልቡና መኣርግ ላይ በመድረሱ ጌታችን ደጋግሞ ይገለጽለት ነበር፤ ከዕለታት ባንዳቸውም ጌታ በአምሳለ ነዳይ በእንግድነት ወደ በዓቱ በመጣ ጊዜ በእንግዳ ልማድ ውሃ አቅርቦ ለማጠብ ሲዠምር በምስማር የተወጉ እግሮቹን ዳስሶ በማየቱ ጌታችን እንደኾነ ዐውቋል፡፡ ርሱም በደስታ በመኾን ጌታን ያጠበበትን ውሃ ጠጥቶታል፡፡

ይኽነን ብቃቱን አይተው መነኰሳቱ ጌታችን እንዲገለጽላቸው ይለምንላቸው ዘንድ እጅጉን በዘበዘቡት ጊዜ ወደ ጌታችን አመለከተ፤ ጌታም በተራራው ላይ እንደሚገለጽ ነግሮት ለመነኰሳቱ ኹሉ ነገራቸው፤ እነርሱም በማለዳ ወደ ተራራው ጫፍ ሲገሰግሱ ከተራራው ሥር ጌታን በአምሳለ አረጋዊ ኾኖ በመገለጥ ይዘውት እንዲወጡ ቢጠይቃቸው አንዳቸውም በእንቢተኝነት ጸንተው ወደ ተራራው ይሮጡ ጀመር፡፡ በመጨረሻም አረጋዊዉ አባ ብሶይ ወደ ተራራው ሊወጣ ሲል በአምሳለ አረጋዊ የተገለጸው ጌታችን ዐዝሎት እንዲወጣ ጠየቀው፤ አባ ብሶይም በትሕትና በመኾን ታዝዞ ዐዝሎት ሲወጣ በእጅጉ ከበደው ቀስ እያለ ግን ቀለል ቀለል እያለው መምጣቱን ዐውቆ ጌታችን መኾኑን ተረድቶ ቀና ብሎ ቢያይ ዠርባው ላይ በፍቅር የታዘለው ርሱ ነው፤ ጌታም ስለ ትሕትናው ለርሱ እንደተገጠለት ነግሮት አባ ብሶይን ባርኮታል፤ በመኾኑም የባሕርይ አምላክ ክርስቶስን ያዘለበት የአባ ብሶይ ሰውነት ዛሬ ድረስ ሳይፈርስ ሳይበሰብስ ብዙ ተአምራትን እያደረገ በገዳሙ አለ፡፡

ቅዱስ አባ ብሶይ የመንፈስ ቅዱስን ህልውና ክዶ የነበረውን በበረሓ የነበረውን ሰው ስለ ነገረ መንፈስ ቅዱስ ከብሉይ ከሐዲስ በምሳሌ ጭምር በስፋት አስተምሮ እንዲመለስ አድርጓል፤ ቅዱስ አባ ብሶይም ብዙዎች ተጋድሎዎችን ካደረገ በኋላ ሐምሌ 8 በ417 ዓ.ም. በመዐዛ ገነት፣ በይባቤ መላእክት ነፍሱን ለእግዚአብሔር ሰጥቷል፡፡

የቅዱሳኑ በረከት ከእኛ ጋር ትሁን፡፡

#መጋቤ_ሐዲስ_ሮዳስ_ታደሰ

https://t.me/Orthodoxtewahdoc
935 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 15:56:22 #ቅዱስ_ሙሴ_የነብያት_አለቃ

❖ ዳግመኛም ወር በገባ በ8 በዚችም ቀን ደግሞ የእግዚአብሔር ሰው የሆነ ደርሶ የዋህ ቅን ጻድቅ የነብያት አለቃ የሙሴ ወርኃዊ መታሰቢያው ነው። ዛሬ መስከረም 8 አመታዊውም ናው።
❖ ይህ ነቢይ ነፍሱን ስለእሳቸው አሳልፎ እስከ መስጠት ከእግዚአብሔር ወገኖች ጋር የደከመ ነው እርሱም በግብጽ አገር በኤርትራ ባሕርም ድንቆች ተአምራትን ያደረገ ነው።

❖ ይህም ስለ ፈርዖን ትእዛዝ ወላጆቹ በግብጽ ወንዝ ውስጥ በጣሉት ጊዜ አውጥታ ላሳደገችው ለፈርዖን ልጅ ለተርሙት ልጅዋ መባልን አልወደደም።

❖ እርሱ ፈርዖን የዕብራውያንን ወንዶች ልጆች ይገድሏቸው ዘንድ አዝዞ ነበርና፤ በአገኘችውም ጊዜ ለርሷ ልጅ ሊሆናት ወስዳ በመልካም አስተዳደግ አሳደገችው።

❖ አርባ ዓመትም በሆነው ጊዜ አንዱን ዕብራዊ የግብጽ ሰው የሆነ ሲያጠቃው አየ ለዕብራዊውም ተበቅሎ ግብጻዊውን ገደለው፤ በማግሥቱ ደግሞ ሁለት ዕብራውያን እርስ በርሳቸው ሲጣሉ አያቸው ሊአስታርቃቸውና በመካከላቸው ሰላምን ሊአደርግ ወደደ፤ አንዱ ዐመፀኛም ትላንት ግብጻዊውን እንደገደልከው ልትገድለኝ ትሻለህን አለው።

❖ ስለዚህም ነገር ሙሴ ፈርቶ ወደ ምድያም አገር ሸሸ በዚያም ሚስት አግብቶ ሁለት ልጆችን ወለደ በዚያም አርባ ዓመት ኖረ በጳጦስ ቍጥቋጦ ውስጥም እሳት እየነደደ ራእይን አየ።

❖ አይቶ ሊረዳ በቀረብ ጊዜ ጳጦስ በተባለ ቊጥቋጦ ውስጥ እግዚአብሔር ተናገረው፤ ወደ ግብጽ አገርም ሒዶ የእስራኤልን ልጆች ከዚያ እንዲአወጣቸው አዘዘው።

❖ ከዚህን በኋላ እግዚአብሔር በሙሴ እጅ በግብጻውያን ላይ ዐሥር መቅሠፍቶችን አመጣ፤ መጀመሪያው የወንዙን ውኃ ደም ማድረግ የመጨረሻው የግብጻውያንን የበኵር ልጅ መግደል ነው።

❖ ከዚህም በኋላ ሕዝቡን ከግብጽ አገር አወጣቸው የኤርትራንም ባሕር ከፍሎ በውስጡ አሳለፋቸው የባሕሩንም ውኃ በጠላቶቻቸው በፈርዖንና በሠራዊት ላይ ገልብጦ አሠጠማቸው።

❖ ከዚህም በኋላ በምድረ በዳ ውስጥ አርባ ዓመት ሙሉ መና አወረደላቸው ውኃንም ከአለት አፈለቀላቸው ይህን ሁሉ በጎ ሥራ በዚህ በደግ ነቢይ ሙሴ እጅ እግዚአብሔር አደረገላቸው እነርሱ ግን ይዘልፉት ነበር ብዙ ጊዜም በድንጊያ ሊወግሩት ሽተው ነበር።

❖ እርሱ ግን በእነርሱ ላይ ልቡን አስፍቶ በመታገሥ ስለርሳቸው ወደ እግዚአብሔር ይማልዳል፤ እነርሱንም አብዝቶ ከመውደዱ የተነሣ እግዚአብሔርን አቤቱ የዚህን ሕዝብ በደሉን ይቅር ካላልክ ከሕይወት መጽሐፍህ ሰርዘኝ አለው።

❖ ሰው ከወዳጁ ጋር እንደሚነጋገር አምስት መቶ ሰብዓ ቃላትን ከእግዚአብሔር ጋር እንደተነጋገረ መጽሐፍ ምስክር ሆነ፤ የእስራኤል ልጆችም በሚያዩት ጊዜ እንዳይሞቱ ፊቱን እስከ ሸፈነ ድረስ በእግዚአብሔር በጌትነቱ ብርሀን ፊቱ በራ።

❖ መቶ ሃያ ዓመት የሆነ ዕድሜውም በተፈጸመለት ጊዜ ለአገልጋዩ ለነዌ ልጅ ለኢያሱ ሕዝቡን እርሱ እንደጠበቃቸው እንዲጠብቃቸው በእጁ ውስጥ እንዲአስረክበው እግዚአብሔር ሙሴን ለኢያሱ አስረክብ ብሎ አዘዘው።

❖ ሙሴም ኢያሱን ጠርቶ የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አዘዘው ሕጉንም እንዲጠብቅ ሕዝቡንም ለኢያሱ በእጁ አስረከባቸው ወደ ምድረ ርስትም እርሱ እንደ ሚአስገባቸው አረጋገጠለት።

❖ ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው በምስክሩ ድንኳን ውስጥ የሚሠራውን ሁሉ ሠርቶ ከአዘጋጀ በኋላ በተራራ ውስጥ አረፈ በዚያም በመላእክት እጅ በሥውር ተቀበረ፤ የእስራኤል ልጆች ወስደው እንዳያመልኩት እግዚአብሔር የሙሴን ሥጋ ሠወረ።

❖ በእስራኤል ልጆች ውስጥ እንደ ሙሴ ያለ ደግ የዋህ ቅን የሆነ ነቢይ እንደማይነሣ መጽሐፍ ምስክር ሆነ፤ ሰይጣንም የሙሴን ሥጋ ለእስራኤል ሊገልጥላችው በወደደ ጊዜ ሐዋርያው ይሁዳ በጻፈው መጽሐፉ እንደመሰከረ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ገሠጸው ከዚህም ሥራ ከለከለው የእስራኤል ልጆችም አርባ ቀን አለቀሱለት።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በጸሎቱ ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

                    አርኬ
ሰላም እብለ ለዘሰገደ ወአስተብረከ፡፡ መልዕልተ ዕፅ ነጺሮ በነደ እሳት መልአከ፡፡ መፈውሰ ቍስል ሙሴ ዘእምደዌ ምድር ተነስከ፡፡ ወእስከ ተሠየመ በላዕለ ፈርዖን አምላከ፡፡ ስብሐተ ቅዱሳን አድምዐ ወዝክረ ብሩከ፡፡  https://t.me/Orthodoxtewahdoc
668 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ