2023-03-07 17:42:55
#ቅዱስ አባታችን አባ አፍፄ ማለት
☞ወር በገባ በ 29 የአባ አፍጼ ወርሐዊ መቲሰቢያው ነው፡✞ አባ አፍጼ ከተሰዐቱ ቅደሳን አንዱ ናቸው፡፡
☞አባቱ አቡድራስ እናቱ አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ በሕፃንነቱ ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንን ተምሮ በ15 ዓመቱ ዲቁና ከተቀበለ በኃላ ወደ ግብጽ በመኼዶ ገዳመ አስቄጠስ ገብቶ ሥርዐተ ምንኩስናን ተቀብሏል፡፡
☞ከሌሎች 8 ቅዱሳን ጎደኞቹ በመኾን ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል፡፡
☞በአክሱም ተቀምጦ በቤተ ቀጢን የሀገሪቱን ባሕል እና ቋንቋ አጥንቷል፡፡
☞ገዳማዊ ኑሮን ለመመሥረት በእየራሳቸው ሲበታተኑ ከአክሱም 8 ኪሎ ሜትር
ራቅ ብሎ ወደ ሚገኝ የሐ ወደ፡ተባለው ጥንታዊ ከተማ በመኺድ ጣዖት
አምላኪውን ሕዝብ አስተምሮ ወደ ክርስትና መልሷል፡፡
☞ቀጥሎም ሳባውያን ከደቡብ ዐረብ በመፍለስ ቀይ ባሕር ተሻግረው የሐ
ውስጥ እንደ ሰፈሩ የሠሩትን የጣዖት ማምለኬያ መቅደስ ባርኮ ወደ ቤተ
ክርስቲያን በመለወጥ ለክርስቲያኖች መገልገያ አድርጎታል፡፡
☞ንዑድ ክቡር የዓለም ብርሃን የፀሐይ ጮራ የሆነ ተአምራትና ድንቆችን
የሚያደርግ የማር አቡነ አፍጼ ተአምር ይህ ነው ጸሎቱ በረከቱ ከህዝበ
ክርስቲያኑ ጋር ይሁን፡፡
☞ልጅ የሌለው ልጅ በማጣቱም ምክንያት ሲያዝን የሚኖር አንድ ሰው ከሩቅ
ሀገር ንዑድ ክቡር የዓለም ብርሃን ወደ ሆነ ተአምራትና ድንቆችን ወደ ሚያደርግ
ማር አቡነ አፍጼ ቤተ ክርስቲያን መጣ በአቡነ አፍጼም በዓል ቀን አባቴ ሆይ
በእግዚአብሔር ዘንድ በከበረች በምትስማም ጸሎትህ የተሰገነ እግዚአብሔር
ደስ የሚያሠኝ ፈጽሞ የተባረከ ትእዛዙ መንፈሳዊት የሰውንም ፍጠረት ሁሉ
የሚያረጋጋ ፈቃድን የሚፈጽም ልጅ ትሰጠኝ እማፀናለሁ ብሎ ለመነ፡፡
☞በበዓሉ ቀን ማምሻ ንዑድ ክብር የዓለም ብርሃን የፀሐይ ጮራ የሆነ
ተአምራትና ድንቆችን የሚያደረግ የማር አቡነ አፍጼ በግልጥ ታየው ሰውየውንም
ወዳጄ ሆይ ልጅ በማጣት ምክንያት አትዘን እንሆ ሚስትህ እግዚአብሔር ደስ
የሚያሠኝ ትእዛዙንም አብዝቶ የሚፈጽም በጎና የተባረከ ልጅ ትወልዳለች አለው፤
ይህንንም ብሎ ንዑድ ክቡር የዓለም ብርሃን የፀሐይ ጮራ የሆነ ተአምራትን
ድንቆችን የሚያደርግ ማር አቡነ አፍጼ ከእሱ ተሠወረ፡፡
☞ሰውየውም ይህንን ነገር ሰምቶ ፈጽሞ ደስ አለው፤ንዑድ ክቡር የዓለም ብርሃን
ከሆነ ከማር አቡነ አፍጼ ግርማ ሞገስና ከጸዳሉ የተነሣ ይህን ሁሉ ቸርነት
ያደረገለትን ፈጽሞ እግዚአብሔር አመሰገነ፡፡
☞ከዚያ በኃላ ወደ ሀገሩ ተመለሰ ወደቤቱም ገብቶ ይህን ሁሉ ነገር
ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ድረስ ንዑድ ክቡር የዓለም ብርሃን የፀሐይ
ጮራ የሆነ ማር አቡነ አፍጼ እንደተገለጠለትም ለሚስቱ ነገራት፡፡የአቡነ አፍጼ
የገድሉና መጽሐፍ የተነበበትን የአባታችንን ጠበል ረጫት አጠጣትም፡፡
☞ከዚያ በኃላ ሚስቱን በግብር ዐወቃት ያንጊዜም ፀነሰች፡፡ የፅንሱ ጊዜ
ሲፈጸምም መልከ መልካም ልጅ ወለደችለት፡፡ አሦስት ዓመት ፍጻሜ በኃላ ይህ
ሰው ለዓለም ብርሃን አቡነ አፍጼ ቤተ ክርስቲያን እጅ መንሻ ይሰጥ ዘንድ ቡዙ
ገንዘብ ይዞ ሄደ፡፡
☞ያንም ገንዘብ ለካህናት ሰጣቸው በረከትም ተቀበለ፡፡
☞የንዑድ ክቡር የዓለም ብርሃን የፀሐይ ጮራ ተአምራትንና ድንቆችን
የሚያደርግ የማር አቡነ አፍጼን ደግነቱን ትሩፋቱን ተአምሮቹንና ድንቆችን
እየመሰከረ ወደ ሀገሩ ተመለሰ፡፡
☞ጸሎቱና በረከቱ የክርስቲያን ወገኖች ከምንሆን ከእኛ ከሁላችን ከሀገራችን
ከኢትዮጵያ ጋር ትሁን ለዘለዓለሙ ይሁን፡፡
☞(ገድለ አፍጼ)
☞አባታችነ አቡነ አፍጼ የእኛንም ጎዶሏችንም ይሙሉልን፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ ልጅ
☞28-5-2014
425 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 14:42