Get Mystery Box with random crypto!

"ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxtewahdoc — "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
የቴሌግራም ቻናል አርማ orthodoxtewahdoc — "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒
የሰርጥ አድራሻ: @orthodoxtewahdoc
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 22.88K
የሰርጥ መግለጫ

🌹«ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን
/አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ።♥ https://t.me/Orthodoxtewahdoc

ሐምሌ 3 በ2014 ዓ°ም ተከፈተ።
📌እግዚአብሔር ቢፈቅድ የቅዱሳኑን ታሪክ እንመማርበታለን ብለን ከፈትነው ቅዱስ እግዚአብሔር ይፍቀድልን አሜን‼
❤የእመ ብርሃን ልጅ🤗

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-05-15 15:56:00 ✞#አርባዕቱ_እንስሳ ማለት

ወር በገባ በ8 ስምንት በዚች ቀን ሥጋ የሌላቸው #የአርባዕቱ_እንስሳ በዓላቸው ነው፣
እሊህም መንበሩን የሚሸከሙ የእግዚአብሔር ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ ዙፋን ፊት በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት እንስሶች አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው።

የፊተኛው አንበሳ ይመስላል ሁለተኛውም ላም ይመስላል ሦስተኛውም የሰው መልክ ይመስላል አራተኛውም የሚበር አሞራ ይመስላል።

የእሊህም የአራቱ እንሰሶች እያንዳንዱ ክንፋቸው ስድስት ስድስት ነው ሁለንተናቸውም ዐይኖችን የተመሉ ናቸው። የነበረ የሚኖር የአማልክት አምላክ እግዚአብሔር ጽኑዕ ክቡር ልዩ ነው እያሉ በመዓልትና በሌሊት ዕረፍት የላቸውም።

ሁለተኛውም ስለእርሳቸው ኢሳይያስ እንዲህ አለ ከዚህም በኋላ ንጉሡ ኦዝያን በሞተ ጊዜ አሸናፊ እግዚአብሔርን ሰፊ በሆነና ከፍ ከፍ ባለ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ብርሃኑም ቤቱን መልቶ ሱራፌልም በዙሪያው ቁመው አየሁት።

የአንዱም የአንዱም ክንፋቸው ስድስት ነው በሁለቱ ክንፋቸው ፊታቸውን በሁለቱ ክንፋቸው እግሮቻቸውን ይሸፍናሉ በሁለቱ ክንፎቻቸው ከጽንፍ እስከ ጽንፍ ይበራሉ። አንዱም አንዱም ከአንዱ ጋራ ፍጹም አሸናፊ የሆንክ እግዚአብሔር ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለህ የምትመሰገነው ምስጋናህ በምድርና በሰማይ የመላ ነው እያሉ ያመሰግናሉ።

ነቢይ ዳዊትም በኪሩቤል ላይ ተቀምጦ በረረ አለ ሁለተኛም በኪሩቤል ላይ የተቀመጠ እርሱ ምድርን አናወጻት አለ። ሕዝቅኤልም እንዲህ አለ ከወደ ሰሜን እነሆ ጥቅል ነፋስ ሲመጣ አየሁ ታላቅ ደመና አለ በዙሪያውም ብርሃን አለ ከእሱም እሳት ቦግ ብሎ ይወጣል።

በደመናውም መካከል ባለ በእሳቱ ውስጥ እንደ አራት ራስ አሞራ መልክ የሚመስል አለ በመካከሉም እንደ አራቱ ኪሩቤል መልክ ያለ አለ። መልካቸውም እንዲህ ነው በውስጣቸው የሰው መልክ አላቸው የአንዱም የአንዱ ፊቱ አራት ነው ክንፉም አራት ነው።

እግራቸውም የቀና ነው ከእግራቸውም ክንፍ አላቸው ሰኮናቸው ግን እንደ ላም ሰኮና ነው ከሱም እሳት ቦግ ይላል እንደጋለ ብረት ፍንጣሪም ይበራል።

ወንጌላዊ ዮሐንስም ዳግመኛ እንዲህ አለ በዚያው ዙፋን ዙሪያ የብዙ መላእክትን ድምፅ የእንስሶቹንም የእነዚያ አለቆችንም ቃል ሰማሁ ቁጥራቸውም እልፍ አለቆች ያሉአቸው ብዙ የብዙ ብዙ ነው።

ለዚያ ለተገደለው በግ ኃይልን፣ ባለጸግነትን፣ ጥበብን፣ ጽናትን፣ መንግሥትን፣ ክብርን፣ ጌትነትን፣ ምስጋናን ገንዘብ ሊያደርግ ይገባዋል ብለው በታላቅ ቃል ተናገሩ።

በሰማይና በምድር ከምድር በታች በባሕር ውስጥ በእነዚያም ውስጥ የተፈጠረው ፍጥረት ሁሉ ጌትነት ክብር ኃይል በረከት በዙፋኑ ለተቀመጠው ለሱ ለበጉም ለዘላለሙ ይገባዋል አሉ። በእውነት ይገባዋል። እሊህም አራቱ እንስሶች አሜን ይላሉ። እሊያም አለቆች ይሰግዳሉ።

ስለ ልዕልናቸውና ስለ ክብራቸው ለእሊህ አርባዕቱ እንሰሳ ከብሉይና ከሐዲስ ብዙ መጻሕፍት መስክረዋል መሐሪና ይቅር ባይ እግዚአብሔርም ስለ ሁሉ የሰው ፍጥረት ይለምኑት ዘንድ ቀራቢዎቹ አደረጋቸው። ዳግመኛም እንዲህ ተባለ ገጸ ሰብእ ስለ ሰው ፍጥረት ይለምናል። ገጸ አንበሳ ስለ አራዊት ይለምናል ገጽ ላሕም ስለ እንስሳ ይለምናል ገጸ ንስርም ስለ አዕዋፍ ይለምናል ከሰማይ ሠራዊት ሁሉ እነርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ በባለሟልነት እጅግ የቀረቡ ናቸውና።

ስለዚህም በዓለሙ ሁሉ በስማቸው አብያተ ክርስቲያን እንዲታነፁ በዚችም ቀን መታሰቢያቸው እንዲደረግ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዘዙ እነርሱ ስለ ሰው ወገን በእግዚአብሔር ዘንድ ይማልዳሉና።  https://t.me/Orthodoxtewahdoc
662 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 12:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 15:55:26 ††† እንኳን ለጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጥንተ በዓለ ዕርገት እና ለጻድቁ አባ ዳንኤል ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ዕርገተ እግዚእ †††

††† ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በዓለ ዕርገትን 2 ጊዜ ታከብራለች:: አንዱ "ጥንተ በዓል" : ሁለተኛው ደግሞ "የቀመር በዓል" ይሠኛል:: ጥንተ በዓል ማለት ጌታችን በትክክል ያረገበትን ቀን ያመለክታል::

የክብር ባለቤት መድኃኔ ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ በኪነ ጥበቡ (በሕማሙ : በሞቱ) ዓለምን አድኖ: 40 ቀን ለሐዋርያቱ መጽሐፈ ኪዳንን: ትምሕርተ ኅቡዓትን አስተምሯቸዋል::

በ40ኛው ቀን 120ውን ቤተሰብ ይዟቸው ወደ ቢታንያ ወጣ:: በዚያም እስከ ሊቀ ዽዽስና ድረስ ሾሟቸው : ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡም አዟቸው የመንፈስ ቅዱስን ተስፋ ጠብቁ ብሏቸዋል:: እየባረካቸው በተዋሐደው ሥጋ ወደ ሰማያዊ ዙፋኑ አርጓል::

ሰማያት: ምድር: ደመናት: ነፋሳት: መባርቅትና መላእክት: ፍጥረት በሙሉ አመስግኗል:: አይሁድ መናፍቃን ዕርገቱን ምትሐት ነው እንዳይሉ: ጌታችን ትንሳኤውን አማናዊ እንደሆነ ለማስረዳት በ40ኛው ቀን ዐረገ::

አንድም ራስ ባለበት ሌሎች የሰውነት ክፍሎች ሊኖሩ ይገባልና ጌታችን ዕርገቱን በገሃድ አደረገው:: "ዐርገ እግዚእ ከመ ያለቡ ዕርገተ ጻድቃን ንጹሐን" እንዲል::

††† ዐርገ እግዚአብሔር በይባቤ::
ወእግዚእነ በቃለ ቀርን::
ዘምሩ ለአምላክነ ዘምሩ:: †††
(መዝ. 46:6)

††† ታላቁ አባ ዳንኤል †††

††† ይህ ቅዱስ አባት ስም አጠራሩ ክቡር ነው:: በሁሉ ነገሩ የተቀደሰ የገዳማውያን መብራትም ነው:: ከተረፈ ንጹሕ ሕይወቱ ጣዕመ መንግስተ ሰማያትን አይቷልና:: አባ ዳንኤል በትውልድ ግብጻዊ ሲሆን ዓለምን ንቆ (መንኖ) ገዳም የገባው ገና በወጣትነቱ ነው::

ጊዜውም ዘመነ ጻድቃን (በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን) ነበር:: በገዳመ አስቄጥስ እና በደብረ ሲሐት ይታወቃል:: ታላቋ መካነ ቅዱሳን ገዳመ ሲሐት ዛሬም ድረስ በስሙ የምትጠራ ሲሆን ለዚህም ምክንያቱ እጅግ ለብዙ ዘመናት በውስጧ ተጋድሎ ፍሬ ስላፈራባት : ደቀ መዛሙርትን በቅድስና ስለ ወለደባት ነው::

ስለዚህም ዛሬም ድረስ "አባ ዳንኤል ዘደብረ ሲሐት" ተብሎ ሲጠራ ይኖራል:: ሌላኛው ስሙ ደግሞ "ዘገዳመ አስቄጥስ" ይሰኛል:: ገዳመ አስቄጥስ የታላቁ ቅዱስ መቃርስ ርስት ሲሆን በዓለም በስፋትም : ብዙ ቅዱሳንን በማፍራትም አንደኛ የሆነ ገዳም ነው::

በዚህ ገዳም ላይ አበ ምኔት ሆኖ የሚሾሙ አበው ሁሌም የብቃት መዓርግ ላይ የደረሱ ሲሆኑ ክብራቸው ከፓትርያርክ በላይ ነው:: አባ ዳንኤልም ከብዙ የቅድስና ዓመታት በኋላ በአስቄጥስ ገዳም አበ ምኔት ሆኖ ተሹሞ እልፍ አእላፍ መነኮሳትን በጽድቅ መንገድ መርቷል::

ቅዱሱ ከትጋቱ የተነሳ ለምግብና ለእንቅልፍ ጊዜ አልነበረውም:: ቀን ቀን መነኮሳቱን ሲናዝዝ : ድውያንን ሲፈውስ : ሥርዓተ ገዳምን ሲቆጣጠር ይውላል:: ልክ ሲመሽ ጭው ወዳለውና ስውራን ወደ ሚገኙበት በርሃ ይወጣል::

+በዚያም ሙሉውን ሌሊት የተሰወሩ አባቶችን ሲፈልግ ያድር ነበር:: በዚህም ምክንያት የብዙ ስውራንን ገድል የጻፈ ሲሆን ባረፉ ጊዜም ገንዞ በመቅበር በረከታቸውን ተሳትፏል:: ታላቅ ሙያንም ፈጽሟል::

እርሱ ገንዞ ቀብሮ : ዜናቸውን ከጻፈላቸው ሥውራን ቅዱሳንም እንደ አብነት እሥራኤላዊቷን ቅድስት ዓመተ ክርስቶስን (ለ38 ዓመት ራቁቷን በሥውር የኖረች) እና ቅድስት በጥሪቃ ንግሥትን (መንግስቷን ትታ በሥውር የኖረች ናት) መጥቀስ እንችላለን::

ከዚህ ባለፈም አባ ዳንኤል በሰው ዘንድ የተናቁትንም ማክበርን ያውቅበታል:: ለምሳሌ በሴቶች ገዳም እብድ ናት ተብላ በበር የተጣለችውን ቅድስት አናሲማን : በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ዻዻሳቱ ሳይቀር "እብድ ነው" ብለው የናቁትን ቅዱስ ምሕርካን: እብድ ሳይሆኑ ራሳቸውን የሠወሩ ቅዱሳን መሆናቸውን ገልጧል::

አባ ዳንኤል ሐዋርያዊም ነበር:: በጊዜው ጦማረ ልዮን የሚባል የኑፋቄ ደብዳቤ ይላክ ነበርና ለዚህ ኬልቄዶናዊ ኑፋቄ በትጋት ምላሽ ይሰጥ ነበር:: አንድ ቀንም በንጉሥ ትዕዛዝ ኑፋቄው በእርሱ ገዳም ሊነበብ ሲል ቅዱሱ ከወታደሩ ቀምቶ ስለ ቀደደው ለሞት እስኪደርስ ደብድበውታል::

ጻድቁ አባ ዳንኤል አንዴ አውሎጊስ የሚባልድሃ ድንጋይ ጠርቦ እንግዳ ሲቀበል ተመልክቶ "ጌታ ሆይ! ይህንን ደግ ሰው ለምን ድሃ አደረከው?" ሲል በፈጣሪ ሥራ ገባ::

ጌታም እንደ ወትሮው በገሃድ ተገልጦ "በነፍስህ ትዋሰዋለህ?" አለው:: "አዎ ጌታየ" ስላለው ጌታችን ለአውሎጊስ ሃብትን ሰጠው:: ግን ወዲያው የጦር አለቃና ጨካኝ ሰው ሆነ::

ጻድቁ ወሬውን ሰምቶ ሊጠይቅ ቢሔድ የአውሎጊስ ወታደሮች ደበደቡት:: ጌታችንም አባ ዳንኤልን ወደ ፍርድ ዙፋኑ አቅርቦ "ወዳጄን መልስልኝ" አለው:: እመ ብርሃን ግን ቀርባ የልጇን እግር ሳመች::

"ልጄ ሆይ ማር!" አለችው:: ጌታም "እሺ" ብሎ ጻድቁን ወደ በአቱ: አውሎጊስን ወደ ቀደመ ግብሩ መለሳቸው:: የአባ ዳንኤል ድንቁ ብዙ ነው::

ሌላው ቢቀር ሽፍታ አባ ዳንኤልን መስሎ ወደ ደናግል ገዳም ሊዘርፍ : በማታለል ገባ:: ደናግሉም ጻድቁ መስሏቸው እግሩን አጥበው ዐይነ ስውሯን ቢቀቧት ዐይኗ በርቷል:: ሽፍታውም ደንግጦ ንስሃ ገብቷል:: አባ ዳንኤል ግን ተጋድሎውን ፈጽሞ በዚህች ቀን ዐርፏል::

††† በተረፈው ግን ከቅድስና ሕይወቱ ባሻገር:-
1.በገዳመ አስቄጥስ (ግብጽ) አበ ምኔት ሆኖ ተሹሞ ባሳየው ትጋት::
2.በሃይማኖት ጠበቃነቱ በደረሰበት ድብደባና ስደት::
3.ብዙ የበርሃ ቅዱሳንን በየበአታቸው እየዞረ በመቅበሩ::
4.የብዙ ስውራን ቅዱሳንን ዜና ሕይወት በመሰብሰቡ::
5.በየጊዜው በእግዚአብሔር ኃይል ይፈጽማቸው በነበሩ ተአምራት:: እና
6.ለድንግል እመቤታችን ማርያም በነበረው ልዩ ፍቅር ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ታከብረዋለች::

††† ቸር አምላክ ክርስቶስ ከዕርገቱና ከጻድቁ በረከት አይለየን::

††† ግንቦት 8 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን የጌታ ቤተሰብ (120ው)
2.ቅዱስ አባ ዳንኤል ጻድቅ
3.ቅዱስ ዮሐንስ ሰማዕት
4.ቅዱስ መክሲሞስ መስተጋድል
5.አቡነ ዮሐኒ ዘደብረ ዳሞ (አቡነ ተክለ ሃይማኖትንና አቡነ ኢየሱስ ሞዐን ለምንኩስና ያበቁ)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
2.ኪሩቤል (አርባዕቱ እንስሳ)
3.አባ ብሶይ (ቢሾይ)
4.አቡነ ኪሮስ
5.አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
6.ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ (ከ12ቱ ሐዋርያት)

††† "እስከ ቢታንያም አወጣቸው:: እጆቹንም አንስቶ ባረካቸው:: ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ:: ወደ ሰማይም ዐረገ:: እነርሱም ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ:: ዘወትርም እግዚአብሔርን እያመሰገኑና እየባረኩ በመቅደስ ኖሩ::" †††
(ሉቃ. 24:50-53)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††

https://t.me/zikirekdusn
997 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 12:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 01:06:53 ✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
"የሚሰማኝ ግን በእርጋታ ይቀመጣል ከመከራም ሥጋት ያርፋል" ምሳ 1፥33
        
✥•••••●◉ ✞ ◉●•••••✥
ስንክሳር ዘወርኃ ግንቦት 5

https://t.me/Orthodoxtewahdoc
የያዕቆብ ሌሊት ይሁንልን
219 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , edited  22:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 01:06:38
217 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 22:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 16:07:49 ️ #የአባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታሪክ ባጭሩ

አባታችን አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሐገራቸው ንሂሳ ግብጽ ነው፡፡ አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ልጅ አጥተው 30 ዘመን ሲያዝኑ ኖረዋል፡፡ አንድ ቀን አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከሥዕለ ሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን ክብሩ ከሰማይ ከፍታ የሚበጥ ልጅ እንኪ ተቀበይ የሚል ድምጽ ሰማች፡፡

በዚህ መሠረት ቅዱስ አባታችን ጻድቁ አቡዬ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መጋቢት 29 ተፀንሰው ታኀሣስ 29 ተወለዱ፡፡

አባታችን ዓይን በገለጹ ጊዜ ከሚታይ ነገር ላይ እንዲያርፍ እርሳቸውም በተወለዱ ጊዜ አፈፍ ተነስተው «ስብሐት ለአብ ስብሐት ለወልድ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ዘዓውፃእከኒ እምጽልመት ውስተ ብረሃን» ብለው አመስግነዋል።

በኋላም ምድራዊ መብል መጠጥ ሳይመገቡ ሳይጠጡ ለምስጋና ተግተው በመኖራቸው መላዕክትን ይመስላሉ፡፡
አባታችን ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
በኢትዮጵያ 262 ኖረው በ562 ዓመታቸው በተስፋቸው ያመነውን በኪዳናቸው የተማጸነ ጌታ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ሊምርላቸው ተስፋቸውን ተቀብለው በዕለተ እሁድ ዐርፈዋል፡፡
መላእክት በአክናፈ እሳት ኢየሩሳሌም ወስደው በየማነ ምስዋዕ ቀብረዋቸዋል፡፡

ለፅንሰትከ ፤ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ በብሥራተ መልአክ ለተፀነስነከው መፀነስና በወርኃ ታኀሣሥ ለተወለድከው ልደትህ ሰላም እላለሁ።

ክቡሩ አባት ሆይ ስለ ዓለሙ መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ ጌትነቱ ልደት ተርሴስ ግብር እንደገበረ፤እኔም ፍጹም ልባዊ የእጅ መንሻ ወርቅ አቀርብልሃለሁ።

ለተኃፅኖትከ፥ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሆይ የቤተ ክርስቲያን መብራት የምትሆን የተመረጠች የክብርት እናትህን ጡት ባለመጥባት በመንፈስ ቅዱስ እንክብካቤ ስለ አደግኸው አስተዳደግህ ሰላም እላለሁ።


የአባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከትታቸው አይለየን አሜን

ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን

https://t.me/Orthodoxtewahdoc
1.4K views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 13:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 16:00:18 #ተአምረ አቡነ ፊልጶስ

•••ወር በገባ በ 5 ታሰበው የሚውሉ የአባታችን የአቡነ ፊልጶስ (ዘ ደብረ ቢዘን) በየወሩ የሚነበብ ገድላቸው ይህ ነው፡፡ወደ ሰማዕቱ አቡነ ፊልጶስ ምስክርነትና ተጋድሎ ወደ ነገሩ ትሩፋት እንመለስ፡፡

☞ሰለ አንደበቴ ድካምና ስለ ልቡናየ ጉድለት እየተንቀጠቀጥኩና እየፈራለሁ
የምነግራችሁ ትንሸ ስሙኝ፡፡
☞ነገር ግን ደስታን የተመላ መንፈሳዊ ቃልን ትሰሙ ዘንድ ገድሉን እናገራለን
መንፈስ ቅዱሳን እንደገለጠልኝ እናገራለሁ፡፡
☞መልካም ሥራን ለመስራት ይፈጥናል በንግግሩ ፀጥ ያለ ነው በሐሳቡም
ዝም ያለ ነው፡፡
☞በነፍሱም ንጽሕ ነው በሥጋውም የፀና ነው ከሰው ሁሉ ጋር ሰላማዊ ነው፡፡
በሥራውም እውነተኛ ነው፡፡ እንግዳ ምጽዋትን ወዳጅ ነው፡
☞ኑሮውም በጾምና በጸሎት ነው፡፡በጸሎትም ጊዜ እንደ ምሰሶ ይቆማል እንደ
መንኮራኩር ይሰግዳል፡፡
☞እንደ በደለኛ ሥጋውን እየገረፈ እንደ ምንጭ ውኃ ዕንባውን ያፈሳል፡፡
☞እንደ ልብስ ማቅን ይለብስ ነበር እንደ መታጠቂያም የብረት እሾህ
ይታጠቃል፡፡ ጥጋቡ ረኃብ ነው፡፡ መተጡም መጠማት ነው፡፡ ደስታውም ጾምና
ጸሎት ነው፡፡
☞መራቆት ነው፡፡ ሙቀቱም ውርጭ ነው የጉኑ ምኝታም እሾህ አሜካላ ነው፡፡ ስለ
ደስታ ምኝታም ከመሬትና ከአመድ ላይ ይተኛል፡፡
☞ዕረፍቱ ሥጋውን የሚያቀዘቅዙ ምንጣፎች ናቸው፡፡ ዕረፍቱም ሰውነቱን
ከሚቆርጥ ከተሳለ ድንጋይ ላይ መተኛት ነው፡፡ ጫማዎቹ የወንጌል ቃላት ናቸው፡፡
☞መመላለሱ ወደ ሃይማኖት ጎዳና ነው፡፡ የእጁ ምርኩዝ ድንቁርናን ጠላትን
የሚያሽንፍ መስቀል ነው፡፡ ዜማው በለሆሳስ ነው፡፡ ትሕትናው ራስን ማዋረድ
ነው፡፡
☞ኑሮው ፀጥታ ነው፡፡ ሰለ አቡነ ፊልጶስ ሁለተኛ በዋልድባ ገዳም የሚ
ገዳማውያን አባቶች ተናገሩ፡፡ ከፀሐይ ይልቅ የሚያበራ ሰውን አየን እንደ
መብረቅም ያበራል በሰማይ ላይም ይበራል በላዩ ላይም የሚያበራ ድባብ አለ
ብለው መስክረው ተናግረዋል፡፡
☞(ገድለ አበው ቅዱሳን ዘደብረ ቢዘን)
☞የጻድቁ አባታችን የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነሐሴ 5ቀን እድሜ እና ጤና ሰቶየዛ ሰው  ይበሉን፡፡
☞የጻድቁ አባታችን የአቡነ ፊልጶስ የጸሎታቸው በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን፡፡
☞ሲራክ ተክለጻዲቅ የተዋህዶ 

https://t.me/Orthodoxtewahdoc
በዚህ ጆይን እያላችሁ አንብቡ እናንብብ ከቅዱሳን በረከት ይክፈለን
952 views "ወለተ ሥላሴ" "አነ ዘክርስቶስ" , 13:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ