Get Mystery Box with random crypto!

፨ወር በገባ በ15 ቅድስት እንባ መሪና ወራኀዊ በዐሏ ነው፨ 'ቤተክርስቲያን እንቁዎቼ ብላ ከምት | "ቤተ ማርያም መንፈሳዊ ሚዲያ💒

፨ወር በገባ በ15 ቅድስት እንባ መሪና ወራኀዊ በዐሏ ነው፨

"ቤተክርስቲያን እንቁዎቼ ብላ ከምትጠራቸው የሴት ጻድቃኖች አንዳ ቅድስት እንባ መሪና ናት።ጣዕመ ዜናዋ ሙሉ ሕይወቷ አስገራሚም አስተማሪም ነው። ቅድስቲቷ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን በምድረ ግብፅ ተወልዳ ያደገቾ ሰማዕት ናት ። ወላጆቿ ከእሷ ሌላ ልጅ የሌላቸው ሲሆን በአኗኗራቸው ደግ እና ቅን ነበሩ።

ቅድስት እንባ መሪና ትክክለኛ ስሟ መሪና ነው።ምክንያቱም እንባ መሪና የወንድ ስም ነውና።ነገር ግን በወንድ የተጠራችበት የራሱ የሆነ ምክንያት አለው።የዛሬ ሴት ሳይጠይቋት ሰላሳውን ትቀባጥራለች ይህች እናት ግን ሴትነቷን ደብቃ ወንድ ነኝ ብላ የአባቷ ደቀ መዝሙር በመሆን ለብዙ አመታት የተጋደለች ናት በታላቁ ፈተናዋ ውስጥ ከፍተኛ ፈተና አጋጠማት ይህም አንዲት ሴት መነኩሴ ይህ ወንድ መነኩሴ አስረግዞኛል በማለት ክስ ለገዳሙ አባቶች አቀረበች ይህች እናትም እሺ አዎን አድርጌዋለሁ በማለት ልጁን ተቀበለች ከገዳሙ እረኞች ለልጁ ወተት እያመጡለት በዚያ እንዲህ እያለች እየተጋደላችሁ ቆየች ልጁንም ኤፍሬም አለችው። መነኮሳቱና አበምኔቱ አናግረው ወደ ገዳሙ መለሷት ከዚያም ባረፈችበት ቀን መነኮሳቱ ሲያዩ ሴት ሆና አገኟት አዘኑ አበምኔቱም በጣም አዘኑ አለቀሱ በጣም ተስቃይታ ስለነበር ማለት ነው።

በመጨረሻም አላስቀብርም ቢሉ ከሙታን ተነስታ እግዚአብሔር ሁላችንም ይቅር ይበለን ብላ ተመልሳ አርፋለች።እረድኤት በረከቷን ከሁላችን ጋር ይኑር አሜን።

----------------------------///////////////------------------------
https://t.me/Orthodoxtewahdoc