Get Mystery Box with random crypto!

Muslim Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ muslimstudentsgroup — Muslim Students M
የቴሌግራም ቻናል አርማ muslimstudentsgroup — Muslim Students
የሰርጥ አድራሻ: @muslimstudentsgroup
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.82K
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን በደና መጡ!....አስተማሪ ታሪኮች፣ ለትምህርት ጥንካሬ ሊያግዙ የሚችሉ አስተምህሮቶችና መልዕክቶች የሚለቀቁበት ነው።ሀሳብ ወይም አስታየት እንዲሁም እዚህ ቻናል ላይ ምርታቹን መስታወዋቅ ለምትፈልጉ @Remdan333

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-05-11 11:22:20 ዛሬ የደስታ ቀን ነው!!

በየእድሜያቹ እየገባቹ ተደሰቱማ!

እድሜ መዋሸት ያስቀጣል
525 views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 08:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 23:01:16
Addot furniture
Use for order
@busin333
286 viewsBus, 20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 08:04:58 የፍቅረኛችሁን ሰው ስም የመጀመርያ ፊደል በመጫን የምታገኙትን የፍቅር ቻናል ተጋበዙልኝ ︎


ዳይ ለሁላችሁም ነው እንዳያመልጥዎ!!
518 views✬ ּ ִ ۫ ثبت قلبي على دينك ✬ ּ ֗, 05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-10 07:20:30
Addot furniture
Use for order
@busin333
572 viewsBus, 04:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 21:53:47 ➧ *የማስወረድ ፍርድ*

አንቺ ሙስሊም እህቴ ሆይ! አሏህ በማህፀንሽ ውስጥ በፈጠረው ፅንስ በሸሪዓው እምነት ጥሎብሻል፤ እንዳትደብቂው። አሏህ እንዲህ ይላል፦

﴿ وَلَا يَحِلُّ لَهُنَّ أَن يَكْتُمْنَ مَا خَلَقَ اللَّهُ فِي أَرْحَامِهِنَّ إِن كُنَّ يُؤْمِنَّ بِاللَّهِ وَالْيَوْمِ الْآخِرِ ۚ ﴾ [ سورة البقرة: 228]

~“በአሏህና በመጨረሻውም ቀን የሚያምኑ ቢኾኑ አላህ በማሕፀኖቻቸው ውስጥ የፈጠረውን ሊደብቁ ለነርሱ አይፈቀድላቸውም።” (አል-በቀራህ፡ 228)

~በየትኛውም መንገድ እሱን ለማውረድ እና ከሱ ለመላቀቅ ዘዴን አትፈልጊ።
ከጎደሎ ሁሉ የጠራው አሏህ እርጉዝ በሆንሽበት ስዓት እንኳን የረመዷን ፆም በአንቺ ወይም በፅንስሽ ላይ ችግር የሚያስከትል ከሆነ ማፍጠርን አግርቶልሻል።

~በዚህ ዘመን ተሰራጭቶ ያለው የውርጃ ስራ ሐራም የሆነ ተግባር ነው። የተረገዘው እሩህ ተነፍቶበት ከሆነ እና የሞተው በውርጃው ምክንያት ከሆነ ይህ ተግባር አሏህ ያለ ሀቅ እንዳትገደል ከጠበቃት ነፍስን እንደማጥፋት ይቆጠራል። እናም በወንጀል መጠየቅን እና እንደየ መጠኑ በዝርዝር ጉማ (የደም ካሳ) ማስከፈልን ያስከትላል።

~በማካካሻም(ከፋራህ) በኩል አንዳንድ ዑለሞች ሙእሚን የሆነችን ባሪያ ነፃ ማውጣት ሲሆን ይህን ካላገኘ ሁለት ወር በተከታታይ መፆም ነው ይላሉ። አንዳንድ ዑለሞች ይህቺን ተግባር ትንሿ ከእነ ህይዎት መቅበር ይሏታል።

~ሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ኢብራሂም መጅሙዑል-ፈታዋ ኪታባቸው 11ኛው ጥራዝ ገፅ 151 ላይ እንዲህ ይላሉ፦

~ “ፅንሱ በማህፀን ውስጥ መሞቱ እስካልተረጋገጠ ድረስ ፅንሱ ለማስወረድ እንቅስቃሴ ማድረግ አይፈቀድም፤ ማህፀን ውስጥ መሞቱ ከተረጋገጠ ማስወረዱ ይፈቀዳል።”
በ1407/6/20 ዓ.ሂ ላይ የታላላቅ ዑለማዎች ኮሚቴ የሚከተለውን የጋራ መግለጫ በ140ኛው ቁጥር ላይ አውጥቷል፦

❶) “በጣም ጠባብ በሆነ ገደብ እና በሸሪዓዊ ምክንያት እንጂ በየትኛውም የእድገት ደረጃ ላይ ያለን ፅንስ ማስወረድ አይቻልም።

❷) ፅንሱ በመጀመሪያው የእድገት ደረጃ ማለትም በመጀመሪያው 40 ቀን ከሆነ እና በማስወረዱ ሸሪዓዊ ጥቅም የሚኖረው ከሆነ ወይም ችግር ለማስወገድ ማስወረዱ ይቻላል። ነገር ግን በዚህ የእድገት ደረጃ ላይ እያለ ማውረድ ያስፈለገው ልጆዎችን ለማሳደግ ችግርን በመፍራት ወይም የኑሮ ወጫቸውን እና ማስተማሪያቸውን በመፍራት ወይም ለወደፊት ህይወታቸው ብሎ ወይም ሁለት ባል እና ሚስት ያላቸው ልጆች በቂ ስለሆኑ እና ልጅ ስለማያስፈልጋቸው ከሆነ ማስወረድ አይቻልም።

❸) ታማኝ የሆኑ የህክምና ኮሚቴዎች ፅንሱ መቀጠሉ በእናትዮዋ ጤንነት ላይ አደጋ ያመጣል ብለው እስካላረጋገጡ ድረስ ፅንሱ የረጋ ደም ወይም የተላመጠ ስጋ እድገት ደረጃ ላይ ከደረሰ በኋላ ማስወረድ አይፈቀድም። የፅንሱ መቀጠል ለእናትዮዋ መጥፋት ምክንያት ይሆናል ተብሎ ከተፈራ ፅንሱ ማስወረድ ይቻላል፤ ይህም የሚሆነው ሀኪሞቹ ፅንሱን ለማትረፍ ሁሉንም አማራጮች ተጠቅመው ሲያቅታቸው ነው።

➍) እርግዝናው አራት ወር ከሞላው እና ከሶስተኛው የእድገት ደረጃ ከደረሰ በኋላ ሁሉም ታማኝ የሆኑ እስፔሻሊስቶች የፅንሱ ከማህፀን ውስጥ መቆየት ለእናቲቱ መሞት ምክንያት ይሆናል ብለው እስካላረጋገጡ ድረስ ፅንስን ማስወረድ አይቻልም። ይህም ማስወረድ የሚከናወነው የፅንሱን ህይወት ለማትረፍ ሁሉንም አማራጮች ከተጠቀሙ በኋላ ነው።

~ከላይ በተጠቀሱት መስፈርቶች መሰረት ማስወረድ የተፈቀደው ከሁለቱ ችግሮች ትልቁን ችግር ለማስወገድ እና ከሁለቱ ጥቅሞች ትልቁን ጥቅም ለማግኘት ሲባል ነው።

~ኮሚቴው ከላይ ያለፈውን መግለጫ ሲሰጥ አሏህን በመፍራት እና ነገሩን በማረጋገጥ ላይ አደራ ይላል። መልካሙን ገጣሚው አሏህ ነው፤ የአሏህ ሶላት እና ሰላም በነብዩና በባልደረቦቻቸው ላይ ይውረድ።” ንግግሩ አበቃ።

~በሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አልዑሰይሚን “ሪሳለቱ አዲማኢ አጥጦቢዒያህ ሊንኒሳእ” በተሰኘው ኪታባቸው ላይ ሲናገሩ፦

~“ እርጉዝ ሴቶች በሚያስወርዱበት ሰአት የተፈለገው ፅንሱን ማስወገድ እና “ሩህ” ከተነፋበት በኋላ ከሆነ ይህ ተግባር ያለጥርጥር ክልክል ነው። ምክንያቱም ይህ ያለ ሀቅ ነፍስን ማጥፋት ነው። የተከበረች ነፍስ ያለ አግባብ መግደል ደግሞ በቁርአን፣ በሐዲስ እና በኢጅማዕ ክልክል ነው።” (ከላይ በተጠቀሰው ኪታብ ገፅ 60 ላይ ይመልከቱ)

~ኢማም ኢብኑል ጀውዚ “አሕካሙ አንኒሳእ” በሚባል ኪታባቸው ገፅ108-109 ላይ እንዲህ ይላሉ፦

~ “የኒካህ ዋና አላማው ልጅን ማግኘት ነው፤ ሁሉም ውሃ(የዘር ፍሬ) ልጅ አይሆንም ይህ ከተሳካ በእውነት የተፈለገው ተገኘ፤ ሲታወቀው ለማስወረድ መሞከር የተፈለገበትን አላማ እና ጥበብ የሚፃረር ነው። ይህም በመጀመሪያው የእድገት ደረጃ “ሩህ” ከመነፋቱ በፊት ከሆነ ትልቅ ወንጀል ነው። ምክንያቱም በማደግ እና በመዳበር ላይ ያለ ስለሆነ ነው። ነገር ግን ሩህ ከተነፋበት አንፃር ሲታይ ወንጀሉ ዝቅ ያለ ነው።

~ አንዲት ሴት “ሩህ” በውስጡ ያለውን ፅንስ ለማስወረድ ሲታወቃት ብታደርገው ሙእሚን ሰው እንደመግደል ይቆጠራል። አሏህ እንዲህ ይላል፦

-{ وَإِذَا الْمَوْؤُدَةُ سُئِلَتْ (8) بِأَيِّ ذَنْبٍ قتلت (9) }. [التكوير الآيات 8-9]

“በሕይወቷ የተቀበረችውም ሴት ልጅ በተጠየቀች ጊዜ፤በምን ወንጀል እንደተገደለች።” (አተክዊር 8-9)

➤ሙስሊም እህቴ ሆይ!አሏህን ፍሪ! ይህን አስከፊ ወንጀል ለየትኛውም አላማ ብለሽ አትዳፈሪ። አጥማሚ የሆኑ መካሪዎችንም በመስማት አትሸንገይ።እምነት እና ህሊናን መሰረት ያላደረገች ብልሹ ባህልን አትከተይ።
799 viewsumu abdul basit ደግ ልቦች ከውብ ፊቶች ይበልጣሉ ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 18:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 21:51:45
አብዛኛውን ጊዜ ዱዓዎች
ስኬታማ የሚሆኑት በሚስጥር
ወደ አላህ ሲደርሱ ነው ።

إِذْ نَادَىٰ رَبَّهُ نِدَاءً خَفِيًّا

ጌታውን የምስጢርን ጥሪ በተጣራ ጊዜ (አስታውስ)፡፡
*መርየም* 3

๏ ከሰው ልጅ ጆሮ እና አይን
የምትደብቃቸው የህመሞችህ
ሹክሹክታዎች የምድር እና የሰማያት
ጌታ ይሰማልሃል ። ጌታህን በዱዓህ
አናግረው ፣ ቅሬታህን ንገረው ፣
ልመናህን አሰማው ።
ከእርሱ የሚያስደስትህንም ተጠባበቅ ።
755 viewsumu abdul basit ደግ ልቦች ከውብ ፊቶች ይበልጣሉ ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 10:16:53
አንድ ሸይኽ ሴቶችን ወደ ሂጃብና መገላለጥን እንዲተዉ
እየጠራቸው ነበር ። ከመካከላቸው አንዷ " ለምን ወንዶች
አይናቸውን አይሰብሩም?" በማለት ቅሬታዋን አቀረበች ።
- ሸይኹም : " እስቲ አንድ ነገር አስቢ ፣ አንድ ማር ያለው እቃ አጠገብሽ ሆኖ ዝንቦች ቢሰባሰቡበት እንዴት ዝንቦቹን ከማሩ ላይ ታባሪያለሽ?" ብሎ ጠየቃት ።
- እሷም : " እቃውን እሸፍናለሁ " በማለት መለሰችለት ።
- ሸይኹም : " ልክ እንደዛውም ሴት ልጅ መልካም ነገሮቿን
ብትሸፍን የሰው ዝንቦች ይሄዱለታል " ብሎ መለሰላት
1.4K viewsumu abdul basit ደግ ልቦች ከውብ ፊቶች ይበልጣሉ ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 07:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 10:14:20 አያተል ኩርሲይ

﴿اللَّهُ لا إِلهَ إِلّا هُوَ الحَيُّ القَيّومُ لا تَأخُذُهُ سِنَةٌ وَلا نَومٌ لَهُ ما فِي السَّماواتِ وَما فِي الأَرضِ مَن ذَا الَّذي يَشفَعُ عِندَهُ إِلّا بِإِذنِهِ يَعلَمُ ما بَينَ أَيديهِم وَما خَلفَهُم وَلا يُحيطونَ بِشَيءٍ مِن عِلمِهِ إِلّا بِما شاءَ وَسِعَ كُرسِيُّهُ السَّماواتِ وَالأَرضَ وَلا يَئودُهُ حِفظُهُما وَهُوَ العَلِيُّ العَظيمُ﴾

ሱረቱል በቀረህ [255]

አየተል ኩርስይ ሳትቀራ እንዳትተኛ!!

ሸኽ አብዱል አዚዝ ኢብኑ ባዝ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል።

ከመተኛት በፊት አያተል ኩርስይ መቅራት፦ ከሲህርና ከሸይጣን ተንኮል ለመከላከል ከአይነተኛ ሰበቦች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ነው።

نور على الدرب ٢٩٥/٣
1.2K viewsumu abdul basit ደግ ልቦች ከውብ ፊቶች ይበልጣሉ ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 07:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-27 22:45:18 1- ክርስቲያን ጎረቤት ቢታመም መጠየቅ ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ነብያችን ﷺ የታመመን የሁዲ ጠይቀዋል። [ቡኻሪ፡ 1356]
2- የክርስቲያንን የግብዣ ጥሪ መቀበል ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ነብዩን ﷺ አንድ የሁዲ ጠርቷቸው ሄደዋል። [አሕመድ፡ 13201]
3- ክርስቲያን የሆነ ሰው ቤተሰብ ቢሞትበት ለተዕዚያ ወይም ለማፅናናት መሄድ ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ከላይ የተጠቀሱት መረጃዎች ለዚህ ድጋፍ መሆን ይችላሉ።
4- ለክርስቲያን ደሃ ሶደቃ መስጠት ይቻላል?
አዎ ይቻላል። [ቡኻሪና ሙስሊም]
5- በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ለክርስቲያን መልካም መዋል ይቻላል?
አዎ ይቻላል። [አልሙምተሒናህ፡ 8-9]
6- ለገና በዓል "እንኳን አደረሳችሁ" ማለት ይቻላል?
በፍፁም!
ከላይ የተዘረዘሩት የሚፈቀዱ ከሆነ  ይሄኛው የሚከለክልበት ምክንያት ምንድነው?
የመጀመሪያዎቹ ነገሮች የተፈቀዱት እምነታዊ ሳይሆን ዱንያዊ ጉዳዮች ስለሆኑ ነው። ሃይማኖታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ግን ይሄ የሚፈቀድ አይደለም። በቃልም በተግባርም ማጀብ አይቻልም፡፡ የአላህ ነብይ ዒሳን ጌታ አድርጎ ሲገልፅ፣ ከዚያም "ጌታ ተወለደልኝ" ብሎ ሲደሰት "እንኳን ጌታ ተወለደልህ!" ትላለህ? የእምነታችን አንዱ መሰረትኮ "አላህ አልወለደም፣ አልተወለደም" ነው። በሌሎች ሃይማኖታዊ በአላትም ወይም ድግሶችም ላይ እንዲሁ ነው። እና ወንድሜ! የእምነትህን ህግ ለመጠበቅ ፈፅሞ ወኔ አይጠርህ። ጓደኝነት፣ ትውውቅ ሸብቦህ፣ አጉል እፍረት አስሮህ ከጌታህ ጋር አትጣላ። በነገራችን ላይ ይሄ "የጌታ መውሊድ" ብለው የሚያከብሩት የገና በአል መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የማይገኝ በቅድመ-ክርስትና ከነበረው የጣኦታውያን እምነት የተኮረጀ ነው። በዚያ ላይ ዛሬ የጎርጎሮሳዊውን አቆጣጠር የሚከተሉት የሚያከብሩበት December 25ም ሆነ "የኢትዮጵያውን" አቆጣጠር የሚከተሉት የሚያከብሩበት ታህሳስ 29
1.9K viewsumu abdul basit ደግ ልቦች ከውብ ፊቶች ይበልጣሉ ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 19:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-24 07:39:45 ከዝንግዎች ላለመሆን…

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿من قرأ عشرَ آياتٍ في ليلةٍ لم يُكتَبْ من الغافلينَ.﴾


“በሌሊት (በምሽት) አስር የቁርዓን አንቀፆችን ያነበበ ከዝንግዎች ተደርጎ አይመዘገብም።”

ሲልሲለቱ አሶሂሃ: 2/242
752 viewsumu abdul basit ደግ ልቦች ከውብ ፊቶች ይበልጣሉ ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 04:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ