Get Mystery Box with random crypto!

1- ክርስቲያን ጎረቤት ቢታመም መጠየቅ ይቻላል? አዎ ይቻላል። ነብያችን ﷺ የታመመን የሁዲ ጠይቀዋ | Muslim Students

1- ክርስቲያን ጎረቤት ቢታመም መጠየቅ ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ነብያችን ﷺ የታመመን የሁዲ ጠይቀዋል። [ቡኻሪ፡ 1356]
2- የክርስቲያንን የግብዣ ጥሪ መቀበል ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ነብዩን ﷺ አንድ የሁዲ ጠርቷቸው ሄደዋል። [አሕመድ፡ 13201]
3- ክርስቲያን የሆነ ሰው ቤተሰብ ቢሞትበት ለተዕዚያ ወይም ለማፅናናት መሄድ ይቻላል?
አዎ ይቻላል። ከላይ የተጠቀሱት መረጃዎች ለዚህ ድጋፍ መሆን ይችላሉ።
4- ለክርስቲያን ደሃ ሶደቃ መስጠት ይቻላል?
አዎ ይቻላል። [ቡኻሪና ሙስሊም]
5- በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ለክርስቲያን መልካም መዋል ይቻላል?
አዎ ይቻላል። [አልሙምተሒናህ፡ 8-9]
6- ለገና በዓል "እንኳን አደረሳችሁ" ማለት ይቻላል?
በፍፁም!
ከላይ የተዘረዘሩት የሚፈቀዱ ከሆነ  ይሄኛው የሚከለክልበት ምክንያት ምንድነው?
የመጀመሪያዎቹ ነገሮች የተፈቀዱት እምነታዊ ሳይሆን ዱንያዊ ጉዳዮች ስለሆኑ ነው። ሃይማኖታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ግን ይሄ የሚፈቀድ አይደለም። በቃልም በተግባርም ማጀብ አይቻልም፡፡ የአላህ ነብይ ዒሳን ጌታ አድርጎ ሲገልፅ፣ ከዚያም "ጌታ ተወለደልኝ" ብሎ ሲደሰት "እንኳን ጌታ ተወለደልህ!" ትላለህ? የእምነታችን አንዱ መሰረትኮ "አላህ አልወለደም፣ አልተወለደም" ነው። በሌሎች ሃይማኖታዊ በአላትም ወይም ድግሶችም ላይ እንዲሁ ነው። እና ወንድሜ! የእምነትህን ህግ ለመጠበቅ ፈፅሞ ወኔ አይጠርህ። ጓደኝነት፣ ትውውቅ ሸብቦህ፣ አጉል እፍረት አስሮህ ከጌታህ ጋር አትጣላ። በነገራችን ላይ ይሄ "የጌታ መውሊድ" ብለው የሚያከብሩት የገና በአል መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የማይገኝ በቅድመ-ክርስትና ከነበረው የጣኦታውያን እምነት የተኮረጀ ነው። በዚያ ላይ ዛሬ የጎርጎሮሳዊውን አቆጣጠር የሚከተሉት የሚያከብሩበት December 25ም ሆነ "የኢትዮጵያውን" አቆጣጠር የሚከተሉት የሚያከብሩበት ታህሳስ 29