Get Mystery Box with random crypto!

Muslim Students

የቴሌግራም ቻናል አርማ muslimstudentsgroup — Muslim Students M
የቴሌግራም ቻናል አርማ muslimstudentsgroup — Muslim Students
የሰርጥ አድራሻ: @muslimstudentsgroup
ምድቦች: ትምህርት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.82K
የሰርጥ መግለጫ

እንኳን በደና መጡ!....አስተማሪ ታሪኮች፣ ለትምህርት ጥንካሬ ሊያግዙ የሚችሉ አስተምህሮቶችና መልዕክቶች የሚለቀቁበት ነው።ሀሳብ ወይም አስታየት እንዲሁም እዚህ ቻናል ላይ ምርታቹን መስታወዋቅ ለምትፈልጉ @Remdan333

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 44

2022-07-13 11:02:25
☞ትክክለኛ "ተወኩል" በአሏህ ላይ ካደረክ በከባባድ ፈተናዎች ውስጥ እያለህ ቢሆንም የደስታ ስሜት እንጅ
☞ሀዘን ልብህን አይጎዳውም!

♡...መመኪያም በአሏህ በቃ!
1.7K views 𝙯𝚞𝚣𝚞 𝓫𝓲𝓷𝓽 𝙮𝙪𝙨𝙪𝙛 ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 08:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 08:38:13 *እንኳን ለ1443 አ,ሂ*
*ኢደል አድሃ በሰላም አብሮ አደረስን*

*تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال*
*وكل عام وأتم بألف خير*


@Muslimstudentsgroup
2.9K views 𝙯𝚞𝚣𝚞 𝓫𝓲𝓷𝓽 𝙮𝙪𝙨𝙪𝙛 ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 05:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 21:58:22 ምርጥ የዐረፋ ቀን ዱዓ
——————
በዛሬው የአረፋ ቀን በብዛት መባል ያለበት ዱዓ /ዚክር

لاَ إِلَـهَ إِلاَّ اللهُ وَحْدَهُ لاَ شَرِيْكَ لَهُ، لَهُ الْمُلْكُ وَلَهُ الْحَمْدُ، وَهُوَ عَلَى كُلِّ شَيْءٍ قَدِيْرٌ

‹ላኢላሀ ኢልለሏሁ ወህደሁ ላ ሸሪከለሁ፣ ለሁል ሙልኩ፣ ወለሁል ሐምዱ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር ።

› «ከአላህ ውጭ በእዉነት የሚገዙት አምላክ የለም፡፡ እርሱ አንድ ነው ፡፡ ለርሱ አጋር የለውም ፡፡ ንግሥና የርሱ ብቻ ነው፡፡ ምስጋናም ተገቢነቱ ለረርሱ ብቻ ነው ፡፡ እርሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው››

@Muslimstudentsgroup
3.0K views 𝙯𝚞𝚣𝚞 𝓫𝓲𝓷𝓽 𝙮𝙪𝙨𝙪𝙛 ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 18:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 07:59:07 ተክቢራ እናብዛ

አላሁ አክበር
አላሁ አክበር


@Muslimstudentsgroup
3.0K views 𝙯𝚞𝚣𝚞 𝓫𝓲𝓷𝓽 𝙮𝙪𝙨𝙪𝙛 ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , edited  04:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 07:58:31 * የውሙ ዐረፋ ዒባዳ*

የውሙ ዐረፋን (9ኛውን ቀን ) መፆም የ2 ዓመት ወንጀል እንደሚያሰርዝ ነቢዩ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ተናግረዋል።

የዐረፋን ቀን ፆም ሙሉ አጅር ለማግነት፣
1/ ስምንተኛው ቀን ምሽት ላይ ጾምን ነይቶ ማደር፣
2/ በዕለቱ ከዐረፋ ፆም ውጪ ሌላ (የቀዳና ወዘተ) ፆም አዳብሎ አለመነየት ይገባናል።

ማስታወሻዎች፥
ቀዳ ያለበትም ሰው ቢሆን የዐረፋን ቀን ጾም መጾም ይችላል።
ማንኛውም ከነጋ በኋላ ምግብና መጠጥ ያልቀመሰ ሰው ከነጋ በኋላም ቢሆን ነይቶ ጾም መጀመር ይችላል።
ነገር ግን ምንዳው የሚጀምረው ከነየተበት ሰዓት ጀምሮ ነው።
ከ9ኛው ቀን በፊት ምንም ላልጾመ ሰውም ቢሆን 9ኛው ቀን ብቻ መፆም ይቻላል/ችግር የለውም።
በዐረፋ (9ኛው ቀን) ላይ ይበልጥ የሚወደዱ 3 ዒባዳዎች፣
1/ ቀኑን መጾም
2/ ዚክር ማብዛት በተለይም ተክቢር
3/ ዱዓእ ማብዛት
ለዐረፋ ቀን ራሱን የቻለ ዱዓእ የለውም ሁሉም የቻለውንና የሚፈልገውን ዱዓእ ማድረግ ይችላል።

ነገን (ጁሙዓ ሰኔ 30/2014) በልባችን የዐረፋን ፆም በማሰብ(በመነየት) እንጾም!
ለወዳጅና ዘመድም እናስታውስ
ለራሳችን፣ለቤተሰባችን፣ ለሀገርና ለኡመታችን ዱዓእም እናብዛ

ሀሙስ / ዙል-ሒጃህ 8)1443 ዓ.ሂ

አላህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ይላል:-
وَتَزَوَّدُوا فَإِنَّ خَيْرَ الزَّادِ التَّقْوَىٰ ۚ وَاتَّقُونِ يَا أُولِي الْأَلْبَابِ
"ስንቅ ያዙ፤ ከስንቆች ሁሉ በላጩ አላህን መፍራት ነው፤ የአእምሮ/ የልብ ባለቤቶች ሆይ ፍሩኝ" ሱረቱል በቀራ /197
2.8K views 𝙯𝚞𝚣𝚞 𝓫𝓲𝓷𝓽 𝙮𝙪𝙨𝙪𝙛 ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-08 07:58:03

@Muslimstudentsgroup
2.3K views 𝙯𝚞𝚣𝚞 𝓫𝓲𝓷𝓽 𝙮𝙪𝙨𝙪𝙛 ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 04:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 22:21:47
3.0K views 𝙯𝚞𝚣𝚞 𝓫𝓲𝓷𝓽 𝙮𝙪𝙨𝙪𝙛 ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , 19:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 16:20:54
ሰው ሰራሽ የአይን ሽፋሽፍት (ርሙሽ) መቀጠል


ለሸኽ ፈውዛን የቀረበ ጥያቄ

ጥያቄ፦ የተለያዩ በሰርግና የደስታ ፕሮግራሞችና በተለያዩ አጋጣሚዎች ላይ ለመዋብና ለማጌጥ ስል ሰው ሰራሽ ሽፋሽፍት እጠቀማለሁ። ይህ እንዴት ይታያል

መልስ፦ ከዚህ ነገር በአላህ እንጠበቃለን። ይህ ተግባር ሀራም (የተከለከለ) ነው። ይህን መጠቀም አይቻልም። ይህ ተግባር "الوصل" (ፀጉርን በሌላ ፀጉር መቀጠል) የሚለው ውስጥ ይገባል። የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሌላን ፀጉር "ዊግ" የምታስቀጥለውም የምትቀጥለውም ረግመዋል።

@Muslimstudentsgroup
3.5K views 𝙯𝚞𝚣𝚞 𝓫𝓲𝓷𝓽 𝙮𝙪𝙨𝙪𝙛 ቁጥብ ሁኚ ውድ ትሆኛለሽ , edited  13:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-05 10:11:30 ጨዋና ጥብቅ የሆንሽው ውድ እህቴ ሆይ! እስቲ የተወሰኑ ነገሮችን ልምከርሽ ጆሮ ስጪኝ፡፡ ከጆሮሽ በፊት ወደ ቀልብሽ እንዲደርስ የምፈልገው መልዕክት አለኝ፡፡
:
እህቴ … በሸሪዓው የማይኖሩ፤ አላህ (ሱብሃኑታአላ) ያዘዛቸውን የማይሰሙና የማይቀበሉ ሴቶች በዝተዋልና መብዛታቸውን አይተሽ አትታለዪ፡፡ በሒጃብ ጉዳይ ችላ የሚሉ ሴቶች በርክተዋልና ከነርሱ አትሁኚ፡፡ ወንድ ጓደኛ የሚይዙ፣ በፍቅር ሥም አላስፈላጊና ሐራም ግንኙነት የመሰረቱትን አይተሽ አትሞኚ፡፡ ዓላማቸውና ወሬያቸው ሁሉ ፊልምና ቲያትር ብቻ በሆኑት እህቶች አትሳቢ፡፡
:
ይበልጥ በግልጽ እንምከርሽ … በርግጥ ፈተናዎች በዝተዋል፣ መከራዎች በግራ በቀኝ አይለዋል፡፡ እይታን የሚፈትኑ፣ መስሚያን የሚፈትኑ፣ …አንዳንዶቹ ዝሙት ምንም አይመስላቸውም፣ ሌሎች የገንዘባቸው ምንጭ ምንነት የማያሳስባቸውም፡፡ ተቆጣጣሪ እንደሌለው ሆነው እንደፈለጉትና እንደሻቸው ይኖራሉ፡፡
:
ይህ ዘመን በርግጥ ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያሉት ዘመን ሳይሆን አይቀርም፡፡ ምን አሉ መሰለሽ … ‹ከኋላችሁ ትዕግስትን የሚጠይቅ ዘመን አለ፡፡ በዚያን ዘመን ውስጥ መታገስ ፍምን እንደመጨበጥ ነው፡፡ የናንተን ዓይነት ተመሳሳይ የሆነ መልካም ሥራ የሚሰራ ሰው የሃምሳ ሰው ምንዳ ያገኛል፡፡ …› ሐዲሡን ቲርሚዚ፣ አልሓኪምና ሌሎችም ዘግበውታል፡፡
:
አዎን … በመጨረሻው ዘመን የመልካም ሰሪ ሰው ምንዳው ብዙ ነው፡፡ ለምን ከተባለ በመልካም መንገድ ላይ ብዙ አጋዦች አይኖሩትምና ነው፡፡ በአመጸኞች መካከል የሚኖር ባይተዋር ብቻ ሆናል፡፡ አዎን ብቸኛ… እነርሱ ሙዚቃ ያዳመጣሉ እሷ አታዳምጥም፣ ሐራም ነገር ያያሉ እሷ አታይም፣ ቦይ ፍሬንድ ይይዛሉ እሷ አትይዝም … ሌላው ቀርቶ በድግምት እና በሺርክ ጭምር ውስጥ ይገባሉ፤ እሷ ግን ከሁሉም የራቀች ነፃ ናት፡፡
:
ሙስሊም በዘገቡት ሐዲሥ የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ‹ እስልምና ባይተዋር ሆኖ ተጀመረ ባይተዋር እንግዳ ሆኖ ይመጣል፡፡ ባይተዋር ሆኑት ምንኛ ታደሉ!.. › ብለዋል፡፡ አዎን ዕድለኞች ናቸው፡፡ እነዚያ ወንጀሎች በበዙበት ዘመን ጽድቅ የሚሰሩ፣ ሰዎች ሲያጠፉ የሚያስተካክሉ፣ ሌሎች ሲያምጹ የሚታዘዙ …
:
በቡኻሪ ዘገባ ደግሞ የአላህ መልዕክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ‹ጌታችሁን እስከምትገናኙበት ቀን ድረስ አንድ ቀን መጥቶ ሌላ አይተካም ክፋቱ የባሰ ቀን የተተካ ቢሆን እንጂ፡፡› ብለዋል፡፡
:
አልበዛር በዘገቡት ሐዲሥ ደግሞ ሀያሉና ተከበረው አላህ ‹በሀያልነቴ እምላለሁ በባሪያዬ ላይ ሁለት ጊዜ ስጋትን አላደርግበትም፡፡ ሁለት ደህንነትንም አላደርግለትም፡፡ በምድር ላይ እያለ ከኔ ያልተጠነቀቀ እንደሆነ በመጨረሻው ዓለም ስጋት ውስጥ ነው፡፡ በምድር ላይ እያለ እኔን ከፈራና ከተጠነቀቀ ደግሞ የትንሳኤ ቀን ደህንነትን እሰጠዋለሁ፡፡› ብሏል፡፡
:
አዎን … በምድር ላይ እያለ አላህን ሲፈራና ሲያልቀው የኖረ ሰው የትንሳኤ ቀን የደህንነት ዋስትና አለው፡፡ ስጋትም ሆነ ፍራቻ የለበትም፡፡ ከአላህ ጋር በመገናኘቱ ይደሰታል፡፡ ጀነት በገባ ጊዜ እንዲህ በማለት ከባልደረቦቹ ጋር ይጠያየቃል፡፡ አላህ (ሱብሃኑታአላ)
:
‹የሚጠያየቁ ሆነውም ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ይዞራል፡፡ ‹እኛ ፊት ቤተሰቦቻችን ውስጥ (የአላህን ቅጣት) ፈሪዎች ነበርን፡፡ አላህም በኛ ላይ ለገሰ፡፡ የመርዛም ቅጣት እሳት ቅጣትንም ጠበቀን፡፡ እኛ ከዚህ በፊት እንለምነው ነበር፡፡ እነሆ እርሱ በጎ ዋይ አዛኝ ነውና፡፡›ይላሉ፡፡›› (አጥ-ጡር ፡ 25-28) ካላቸውም መካከል ይሆናል፡፡
:
የወንጀል ባለቤት የሆነና በአላህ ሲያምጽ የኖረ፣ ሙሉ ሀሳቡንና ትኩረቱን ሆድና ወሲብ ላይ ያደረገ፣ የአላህን ቅጣት ያልፈራ፣ ለማስጠንቀቂያው ቁብ ያልሰጠ ሰው ደግሞ … በመጨረሻው ዓለም በፍራቻ ውስጥ ይኖራል፤ ድንጋጤም ይወርሰዋል፡፡

تَرَى الظَّالِمِينَ مُشْفِقِينَ مِمَّا كَسَبُوا وَهُوَ وَاقِعٌ بِهِم
‹በዳዮች ከሰሩት ሥራ የፈሩ ሆነው ታያቸዋለህ፡፡ እርሱም በነርሱ ላይ ወዳቂ ነው …› (አሽ-ሹራ ፡ 22)
:
ውድ እህቴ… ግልጽ በሆነው እውነት ላይ ነሽና በጌታሽ አላህ (ሱብሃነሁ ወተአላ) እውነተኛ መመካትን ተመኪ፡፡ በዲን ላይ ጽኑዎች ትንግርት ቢሆኑም ከነርሱ ለመሆን ጣሪ፡፡ አጥፊዎች የተበራከቱ ቢሆንም ብዛታቸውን አይተሽ አትታለዪ፡፡
:
አላህ በጥበቃው ይጠብቅሽ፡፡ በእዝነቱ ያካብብሽ፡፡ እሱን ከሚፈሩ አማኞችም ያድርግሽ፡፡ ወደሱ ጎዳና መንገድ ከሚጣሩትና ያወቁትን ከሚተገብሩትም ያድርግሽ፡፡
:
ውድ እህታችን … ምክራችንን የማትቀበዪ ብትሆኚ እንኳን ሁሌም እህታችን ነሽ፡፡ መልካም ነገር እንመኝልሻለን፡፡ በሌሊትም ሆነ በቀን አላህን ዱዓእ እናደርግልሻለን፡፡ ዘወትር አንችን ከመምከርና ከመጠበቅ ወደኋላ አንልም፡፡ ጥረታችን ውጤት እንደሚኖረው በአላህ ላይ ተስፋ አለን፡፡ ስኬት ከርሱ ዘንድ ነው፡፡
:
የአላህ ሰላም እዝነትና በረከት በናንተ ላይ ይሁን፡፡

https://t.me/Al_Islam_Media_Et

https://t.me/Al_Islam_Media_Et
2.8K viewsAbu Umar Ibnu Sadik, 07:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ