Get Mystery Box with random crypto!

ሰው ሰራሽ የአይን ሽፋሽፍት (ርሙሽ) መቀጠል ለሸኽ ፈውዛን የቀረበ ጥያቄ | Muslim Students

ሰው ሰራሽ የአይን ሽፋሽፍት (ርሙሽ) መቀጠል


ለሸኽ ፈውዛን የቀረበ ጥያቄ

ጥያቄ፦ የተለያዩ በሰርግና የደስታ ፕሮግራሞችና በተለያዩ አጋጣሚዎች ላይ ለመዋብና ለማጌጥ ስል ሰው ሰራሽ ሽፋሽፍት እጠቀማለሁ። ይህ እንዴት ይታያል

መልስ፦ ከዚህ ነገር በአላህ እንጠበቃለን። ይህ ተግባር ሀራም (የተከለከለ) ነው። ይህን መጠቀም አይቻልም። ይህ ተግባር "الوصل" (ፀጉርን በሌላ ፀጉር መቀጠል) የሚለው ውስጥ ይገባል። የአላህ መልእክተኛ صلى الله عليه وسلم የሌላን ፀጉር "ዊግ" የምታስቀጥለውም የምትቀጥለውም ረግመዋል።

@Muslimstudentsgroup